Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

TIKVAH-ETHIOPIA

Description
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 6 days, 17 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 week, 3 days ago

Last updated 1 week, 3 days ago

1 week ago
[#CAR](?q=%23CAR)

#CAR

የ77 ዓመቱ የቀድሞው የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፍራንሷ ቦዚዜ ላይ የእስር ማዘዣ ትዕዛዝ ወጣ።

ማዘዣው የወጣው ሠራዊታቸው ከእአአ 2009 እስከ 2013 ባለው ጊዜ ውስጥ በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል ፈጽሟል በሚል ነው።

ማዘዣውን ያወጣው በባንጊ ላይ የተሰየመውና ከሃገር ውጪ ካሉ ፍርድ ቤቶች ጋራ የሚሠራው ልዩ የወንጀል ችሎት ነው።

ይህ ችሎት በእ.አ.አ 2015 በተመድ እገዛ የተቋቋመ እንደሆነ ተገልጿል።

የቀድሞ የሀገሪቱ መሪ ቦዚዜ ፦
- ግድያ፣
- አስገድዶ መሰወር፣
- ሰቆቃ፣
- መድፈር እና ሌሎች ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን ፈፅመዋል በሚል ተከሰዋል።

ቦዚዜ በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጡት በእ.አ.አ 2003 ሲሆን ከአስር (10) ዓመታት በኋላ ከወንበራቸው ተወግደዋል።

ቦዚዜ ካለፈው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ #በስደት ጊኒ ቢሳዉ የሚገኙ ሲሆን፣ ከዛ ሆነው ዋናኛ የሚባል አማጺ ቡድን በመምራት ላይ ይገኛሉ።

ጊኒ ቢሳዉ ተጠርጣሪውን ቦዚዜ #ይዛ እንድታስረክብ ተጠይቋል። #VOA

@tikvahethiopia

1 week ago
“ ማን እንደገደላቸው መረጃ የለኝም ፤ …

“ ማን እንደገደላቸው መረጃ የለኝም ፤  በተተኮሰባቸው ጠይት ተገድለዋል ዞሮ ዞሮ ” - ስሜ አይገለጽ ያሉ ባለስልጣን

በአማራ ክልል፣ ሰሜን ወሎ የላስታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው ጤና ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ ትላንት በጥይት  መገደላቸውን ዞኑ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋገጧል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ አንድ የሰሜን ወሎ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ባለስልጣን በሰጡት ቃል፤ “ ትላንት ከዞን ግምገማ ቆይተው ሲመለሱ ነው ግድያው የተፈጸመው። የሞቱት የወረዳው አስተዳዳሪ የወረዳው ጤና ኃላፊ ናቸው ” ብለዋል።

“ ኩል መስክ የሚባል ቦታ ነው ግድያው የተፈጸመው ” ሲሉ ተናግረዋል።

ሌላ የተጎዳ ሰው አለ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፣ “ ሌላ እዛው ኩል መስክ የቀበሌ ሊቀመንበር የተጎዳ አለ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ አርብና ቅዳሜ ግምገማ ነበረ፤ እዚያ ተመልሰው ኩል መስክ ቆይተዋል ለሁለት ቀናት ” ሲሉም አክለዋል።

ግድያውን የፈጸመው ማነው ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ “ እስካሁን መረጃው የለኝም፤ በተተኮሰባቸው ጠይት ተገድለዋል ዞሮ ዞሮ ” ብለው፣ የገዳዮቹን ማንነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

“ ዞሮ ዞሮ በግድያ የሚመለስ አንድም ጥያቄ የለም። እነዚህ (ሟቾቹ) የሕዝብ አስተዳዳሪዎች ናቸው። ሕዝብም ጥበቃ ሊያደርግላቸው ይገባል እንጂ መሞት አለባቸው ብዬ አላስብም ” ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

1 week ago
TIKVAH-ETHIOPIA
2 weeks, 2 days ago

በአዲስ አበባ ከተማ የ2ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክ/ ከተማ (ፒያሳ) በዓድዋ ድል መታሰቢያ አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ ፦
- በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣
- በኮልፌ ቀራንዮ፣
- በአራዳ፣
- በአቃቂ ቃሊቲ፣
- በየካ፣
- በቦሌ፣
- በአዲስ ከተማ፣
- በቂርቆስ፣
- በጉለሌ
- በልደታ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

(ዝርዝር የጨረታው መረጃ በPDF ተያይዟል - ይመልከቱ)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ የጨረታ መረጃ ባለቤት አዲስ ልሳን መሆኑን ያሳውቃል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia

2 weeks, 2 days ago
TIKVAH-ETHIOPIA
2 weeks, 2 days ago
[#ሊዝ](?q=%23%E1%88%8A%E1%8B%9D) [#አዲስአበባ](?q=%23%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5%E1%8A%A0%E1%89%A0%E1%89%A3)

#ሊዝ #አዲስአበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ መሬትን በሊዝ ለማስተላለፍ 2ኛ ዙር ጨረታ አውጥቷል።

መሬትን በሊዝ የማስተላለፍ ተግባር ለአራት ዓመታት ከተቋረጠ በኋላ ግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል፡፡

2ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታም ረቡዕ ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም መውጣቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቢሮና ከአዲስ ልሳን ጋዜጣ መረጃውን አግኝቷል።

በከተማዋ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ መረጃ መሠረት፣ በ2ኛው ዙር ጨረታ 243 መሬት (ቦታ) የተዘጋጀ ሲሆን፣ እነዚህ ቦታዎችም በአስር ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ናቸው፡፡

በአራዳ ክ/ከተማ (ፒያሳ) በዓድዋ ድል መታሰቢያ አካባቢ በኮሪደር ልማት ምክንያት የፀዱ ቦታዎችን ጨምሮ ፦
- በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣
- በኮልፌ ቀራንዮ፣
- በአራዳ፣
- በአቃቂ ቃሊቲ፣
- በየካ፣
- በቦሌ፣
- በአዲስ ከተማ፣
- በቂርቆስ፣
- በጉለሌ እና በልደታ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ የልማት ቦታዎች በ2ኛው ዙር ጨረታ በሊዝ ሊተላለፉ እንደቀረቡ ታውቋል።

ከዚህ ቀደም አልሚዎች ተጫርተው አሸናፊ ከሆኑ በኋላ በሚተላለፉ የተለያዩ ቦታዎች ላይ “የይገባኛል” ጥያቄዎች ይነሱባቸው እንደነበር ነበር።

አሁን ለመተላለፍ የተዘጋጁ ቦታዎች ግን ከሶስተኛ ወገን ጥያቄ ነፃ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ገልጿል።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለም ሆቴል አካባቢ ኤም.ኤ (MA) ህንፃ ላይ በሚገኘው በከተማዋ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት እንዳለባቸው ተመላክቷል፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡ዐዐ ሰዓት ጀምሮ በ9 ተከታታይ የስራ ቀናት በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዳራሽ የሚከፈት ሆኖ፣ ዝርዝሩ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል ተብሏል፡፡

ተጫራቾች ቦታውን በአካል ቀርበው ለመመልከት ከፈለጉ በ16/8/16 ዓ.ም እና በ18/8/16 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡00 እና ከሰዓት በ8 ሰዓት ለጨረታ የተዘጋጁ ቦታዎች የሚገኙበት ከፍለ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽህፈት ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚህ ስራ በሚመደቡ አስጎብኚዎች አማካኝነት መመልከት እንደሚችሉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮና / ከአዲስ ልሳን ጋዜጣ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ዝርዝር የጨረታውን መረጃ ከታች (በቀጣይ ፖስት) እናያይዛለን።

@tikvahethiopia

2 months, 2 weeks ago
[#BDU](?q=%23BDU)

#BDU

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ እስካሁን ጥሪ ባልተደረገላቸው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉዳይ ላይ ከተቋሙ ተጨማሪ ምላሽ አግኝቷል።

በዚህም ተቋሙ ፤ " ተማሪዎቹን ለመጥራት አስቻይ ሁኔታዎች እየተጠበቀ ነው። " ብሏል።

" አሁን ያለው ሁኔታ ተማሪዎቹን ለመጥራት እየተገመገመ ነው። ተማሪዎቹ በትዕግስት ይጠብቁ። " ሲል አሳውቋል።

ተጨማሪ ዝርዝር የምናጋራችሉ ይሆናል።

@tikvahuniversity @tikvahethiopia

2 months, 2 weeks ago
TIKVAH-ETHIOPIA
2 months, 2 weeks ago
" ዩኒቨርሲቲው የሚጠራም ከሆነ የማይጠራም ከሆነ …

" ዩኒቨርሲቲው የሚጠራም ከሆነ የማይጠራም ከሆነ አቋሙን ያሳወቀን " - ተማሪዎች

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ/ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም ያደረገውን ጥሪ ባላወቁት ምክንያት አራዝሞት እንደነበር፣ ይሁን እንጂ ከዚያ ወዲህም “ ኑም ” ሆነ “ አትምጡ ” ባለማለቱና የትምህርት ጊዜው እያገፋ በመሆኑ ጭንቀት ውስጥ መሆናቸው ውሳኔውን እንዲያሳውቃቸው ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው ይጠየቅልን ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አንድ ተማሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ዩኒቨርሲቲው የሚጠራም ከሆነ የማይጠራ አቋሙን ያሳወቀን” ብሏል።

ተማሪዎቹን ወክሎ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ የሰጠ ሌለኛው ተማሪ ፤ “ እኛ የ2016 ዓ/ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደብን Freshman እና Remedial ተማሪዎች ነን። ነገር ግን አስካሁን ከሌሎች የአማራ ክልል በተለዬ የእኛ ካምፓስ ለተማሪዎቹ ጥሪ አላደረገም ” ሲሉ አማሯል።

ዩኒቨርሲቲው ጥር 21 ቀን 2016 ዓ/ም ጥሪ አድርጎላቸው እንደነበር ያስታወሰው የሁሉንም ተማሪዎች ቅሬታ አቅራቢው፣ “ ባልታወቀ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ እንደተራዘመ ከተነገረን ወር ሊሞላን ነው ” ብሏል።

በመሆኑም፣ መጥራት የሚችሉ ከሆነ ጥሪ እንዲያደርጉ፣ መጥራት የማይችሉ ከሆነ ደግሞ ተማሪዎቹ በመጠበቅ ጊዜያቸውን እንዳያባክኑ እንዲያሳውቁ፣ እንዲሁም በቅርቡ መቅደላአምባ ዩኒቨርሲቲ እንዳደረገው ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካለ ዩኒቨርሲቲው ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመድባቸው ጠይቋል።

“ ከእነዚህ አማራጮች ውጪ ግን ‘ተማሪዎች ጠብቁ’ የሚል መልስ መስጠት እንደማይቻል ይታወቅልን። ምክንያቱም ከዚህ በላይ ትዕግስት ሊኖረን ስለሚይችል። በዕድሜያችንና በሞራላችን እየተቀለደ ነው ያለው ” ሲልም የተማሪዎቹ ተወካይ አሳስቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው አንድ የዩኒቨርሲቲው አካል በሰጡት ቃል፣ “ ዩኒቨርስቲው አሁን አልጠራም ማለትም አይችልም (ምክንያቱም አልጠራም ቢል ከትምህርት ሚኒስቴር ግዳጅ አለበት)። ጠርቶ እንዳያስገባ ደግሞ አካባቢው ላይ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኃይሎች እያደረጉ ያሉትን ነገር በዓይናችን እያዬን ነው ” ሲሉ ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው አሁንም ይታገሱ እንዲላቸው ሳይሆን ቁርጡን እንዲያሳውቃቸው ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

“ ዩኒቨርሲቲው የማይጠራበትን ምክንያት፣ አሁን አካባቢው ላይ ያለው ነገር ጥሩ ስላልሆነ ነው። በጸጥታ ችግር ከጤና እና ከአግሪካልቸር ግቢዎች ለቀው ወደ ፔዳና ፖሊ ካምፓሶች የተደረቡ ተማሪዎች Still ትምህርት አልጀመሩም። አሁን አዲስ ተማሪዎችን ቢጠራ የት ላይ ነው የሚያደርጋቸው? ” ሲሉም ጠይዋል።

“ ማስተባበሪያ ክላስ ራሱ ጠቦን እየተቸገርን ነው። የዶርም እጥረት አለ። ተማሪዎቹ ወደዬ ግቢያቸው እስካልተመለሱ ድረስ” ያሉት እኚሁ አካል ፣ “አሁንም ፔዳ (Main campus) ያለው ሁኔታ አስጊ ነው። ‘እስከ ነገ ሐሙስ ‘ለቃችሁ ውጡ’ የሚል ወሬ ስለመጣ ዩኒቨርሲቲው አዲስ ተማሪዎችን መጥራት አይችልም። የመጡት እየተሰቃዩ ነው። እነዚህም መጥተው ከሚሰቃዩ ቢረጋጉ ነው የሚሻላቸው ” ሲሉ አሳስበዋል።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia

4 months, 3 weeks ago
TIKVAH-ETHIOPIA
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 6 days, 17 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 week, 3 days ago

Last updated 1 week, 3 days ago