"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 1 month ago
The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 month, 2 weeks ago
እንኳን ደህና መጡ‼
✔ማስታወቂያ ለማሰራት እና ጥቆማ ለመስጠት በዚህ ይጠቀሙ ☞https://t.me/WasuMohammed
✔ ቻናሉን ለመቀላቀል Join ☞http://t.me/Wasulife
ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏
Last updated 2 weeks, 6 days ago
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 29 ጀምሮ ይሰጣል‼️
በትግራይ ክልል ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ የቆየው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፊታችን መስከረም 29 ቀን ጀምሮ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡
አገልግሎቱ የፈተና አሰጣጡን አስመልክቶ ከፌደራል ፖሊስ ሃላፊዎችና ከክልሉ የፈተና አስፈጻሚዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በክልሉ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ የቆየውን የ12ኛ ክፍል ፈተና ለማስቀጠል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ይልቃል ወንድሜነህ ተናግረዋል፡፡
ፈተናውን በሶስት ዙር ለመስጠት መታቀዱን ጠቁመው÷የመጀመሪያው ዙር ፈተና (የ2012 ዓ.ም) ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡
የተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 8 እስከ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት እንደሚከናወን መገለጹንም የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
የመዲናዋ የህንጻ አዋጅ መስፈርቶችን በማይከተሉ የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው‼️
የአዲስ አበባ የህንጻ አዋጅ መስፈርቶችን በማይከተሉ የግንባታ ፕሮጀክቶች በሚሳተፉ አልሚ፣ ተቋራጭና አማካሪው ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ዴሲሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት÷ በመዲናዋ ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ የህንጻ ግንባታዎች እንዲከናወኑ እስከ ወረዳ ድረስ የተቀናጀ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት ተከናውኗል።
በዚህም የህንጻ አዋጅ መስፈርቶችን በማያሟሉ ፕሮጀክቶች ላይ በሚደረግ ቁጥጥር የሚወሰደው እርምጃ በአልሚው ላይ ብቻ ሳይሆን በተቋራጩና አማካሪው ላይ ጭምር መሆኑን ገልጸዋል።
በ2015 ዓ.ም የህንጻ አዋጁን የተላለፉ በተለይም በከተማዋ በተለያዩ ቦታዎች በግንባታ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የተወሰኑ አካላት የግንባታ ሰራተኞችን እንዲሁም ማህበረሰቡን ለጉዳትና ለአደጋ በሚያጋልጥ ሁኔታ ግንባታ ማከናወናቸውን ተከትሎ በርካታ አልሚዎች ላይ ቅጣት መጣሉን አስታውሰዋል።
ከተጣለው ቅጣት ውስጥ 67 ሚሊየን ብር የሚጠጋ የገንዘብ ቅጣት የተጣለባቸው ወደ 20 የሚጠጉ ፕሮጀክቶች እንደነበሩም ተናግረዋል።
ከእነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ የአያት ሪል እስቴት 8 ሚሊየን ብር የገንዘብ ቅጣት ተጥሎበት እንደነበር ጠቅሰው፥ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው አልሚዎች የህንጻ ግንባታ ፍቃዳቸው እንዲታገድ መደረጉንም አንስተዋል።
በተያዘው 2016 ዓ.ም ተቋሙ የነበረውን የሰው ኃይል ክፍተት በመቅረፍ እስከ ወረዳ ድረስ በተዋረድና በተቀናጀ መልኩ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የህንጻ አዋጁን የተለያዩ መስፈርቶችን በማያሟሉ አልሚ፣ ተቋራጭና አማካሪዎች ላይ አስተማሪ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።
በጅምር የህንጻ ግንባታ ስራ ላይ የሚሰማሩ አካላት የሰራተኞቻቸውን የደህንነት ግብዓቶች እና ሌሎች መስፈርቶች እንዲያሟሉ አስቀድመው የግንዛቤ ስራ እንደሚሰሩም ነው የገለጹት።
ማህበረሰቡም መንገድ በመዝጋት ጥንቃቄ የጎደላቸው ግንባታዎችን በሚያከናውኑ አካላት ላይ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጠይቀዋል።
በመዲናዋ የዘመን መለወጫ በዓል ያለምንም አደጋ መከበሩ ተገለጸ‼️
የ2016 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል ያለምንም አደጋ በሰላም ተከብሮ ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።
የ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በዋዜማውም ሆነ በበዓሉ ዕለት እሳትና መሰል አደጋዎች ሳያጋጥሙ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽኑ በዓሉ ከመድረሱ በፊት በተለያዩ አማራጮች ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
በዚህም ህብረተሰቡ ከኮሚሽኑ የተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረጉ በዓሉ ያለ ምንም አደጋ ክስተት በሰላም መከበሩን አመልክተዋል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ህብረተሰቡና የሚዲያ ተቋማት አደጋን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ ላደረጉት አስተዋጽዖ ምስጋናውን በማቅረብ በቀጣይ በሚኖሩ በዓላትና በመደበኛ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ተመሳሳይ ጥንቃቄዎች እንዲደረጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
M-PESA፣ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ፋይናንሺያል አገልግሎት ጀመረ‼️
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ፋይናንሺያል አገልግሎት የሚሰጠው M-PESA ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ካገኘ ከሶስት ወራት በኋላ አገልግሎት መጀመሩን ዛሬ አስታውቋል።
ሁሉም የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደንበኞች M-PESA አገልግሎትን ለመጠቀም *733# መደወል ወይም በተዘጋጀው የሞባይል መተግበሪያ መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፥ አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት በቂ ሙከራ ማድረጉንና ከተለያዩ ባንኮች ጋር የአጋርነት ስምምነት ማድረጉን እንዲሁም ወኪሎችንም መልምሎ ማሰልጠኑን በመግለጫው ጠቅሷል።
አገልግሎቱ አሁን ላይ በአንድሮይድ መተግበሪያ በአምስት ቋንቋዎች የቀረበ ሲሆን ለአይ ኦ ኤስ ተጠቃሚዎች በቅርብ ሳምንታት ውስጥ አገልግሎት ይጀምራል ተብሏል።
"ግብረሰዶም ከተፈጥሮ ሕግ ያፈነገጠ ኢትዮጵያን የማይመጥን ወንጀል ነው"‼️
🗣ኡስታዝ አቡበከር
የወንጀሉ ፈጻሚዎች ላይ ለሌሎች መቀጣጫ የሚሆን ርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል
የግብረሰዶም ተግባር ከተፈጥሮ ማንነትና ህግ ያፈነገጠ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን የማይመጥን ወንጀል ነው ሲሉ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አማካሪ የሆኑት ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ገለጹ፡፡
ወንጀሉን በሚፈጽሙ አካላት ላይም ለሌሎች መቀጣጫ ሊሆን የሚችል ርምጃ መወሰድ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ኡስታዝ አቡበከር ለኢፕድ እንደተናገሩት፤ የግብረሰዶም ወንጀል ከሰዋዊ የተፈጥሮ ባህሪያት ውጪ የሆነ በእስልምና እምነትም በሸሪዓ ህግ እስከ ሞት ድረስ የሚያስቀጣ ሲሆን፤ ከተፈጥሮ ማንነትና ህግ ያፈነገጠ ኢትዮጵያን የማይመጥን ተግባር ነው፡፡
እንደ ኡስታዝ አቡበከር ገለጻ፤ ወንጀሉ ከባህል እምነትና ማንነት አንፃር ተቀባይነት የሌለው ተፈጥሮን የሚፃረር አደገኛና የከፋ ማንነትን የሚያናጋ የተጠላ ተግባር ነው፡፡
የግብረሰዶም ወንጀልን በሚመለከት የእምነት አባቶች፣ መንግሥትና የህግ አካላት በርካታ የቤት ስራዎች እንደሚጠበቅባቸው የገለጹት ኡስታዝ አቡበከር፤ ከግልም ባለፈ ሁሉም እምነቶች የጋራ መግባባት በመፍጠር በጉዳዩ ላይ አቋማቸውን ማሳየት እንደሚጠበቅባቸውም ነው የገለጹት፡፡
ወንጀሉ ካደግንበት ኢትዮጵያዊ መንፈሳዊና ባህላዊ ማንነት ከማፈንገጡም ውጪ ተራ ከሆነ ስሜትን የማርኪያ መንገድነቱ ያፈነገጠ ሲሆን፤ ለበሽታ አጋላጭ በመሆኑ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በጉዳዩ ላይ ያለውን የማውገዝ አቋም ሊያሳይ እንደሚገባው አመላክተዋል፡፡
የሃይማኖት አባቶች ጉዳዩን በማውገዝ ትውልድን የመታደግ ሥራ በመስራት ትውልድን ሊያበላሽ የመጣውን ተግባር ሊያስቆሙ ይገባቸዋል ሲሉም አክለው ተናግረዋል፡፡
ነገ በዱራሜ ሊደረግ የነበረው ሰልፍ እንዲሰረዝ መደረጉን የዱራሜ ከተማ አስተዳደር ገለፀ‼️
ከነባሩ ክልል / ስያሜውን " የማዕከላዊ ኢትዮጵያ " በሚል እየተደራጀ ከሚገኘው ክልል የተቋማት መቀመጫ እና ድልድል ጋር በተያያዘ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ቅሬታዎች እንዳሉ ይታወቃል።
ነዋሪም ቅሬታውን በተለያየ መንገድ እየገለፀ ሲሆን የዱራሜ ከተማ ምክር ቤትም የቢሮ ክፍፍሉ ፍትሃዊ አይደለም በሚል በሙሉ ድምፅ ተቃውሞ በማድረግ ማስተካከያ እንዲደረግ ጠይቋል።
ከዚሁ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ካለው ቅሬታ ጋር በተያያዘ ነገ በዱራሜ ከተማ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነበር።
ሰልፉን ለማድረግ ሲያስተባብሩ የነበሩ አካላት " በከምባታ ጠምባሮ ዞን ላይ የሚፈፀምን ኢፍትሃዊ ድርጊትና የልማት ተጠቃሚነትን የሚጎትት ውሳኔ የዓለም ህዝብ እንዲያውቀው ለማድረግ ሰላማዊ ሰልፉ እንደተዘጋጀ " ገልጸው የነበረ ሲሆን በከተማው አስተዳደርም እውቅና አግኝቶ ነበር።
በከተማው አስተዳደር የተፈደቀው ሰልፍ ነገ ከጥዋት 3 እስከ 5 ሰዓት ድረስ ለማካሄድ እቅድ ተይዞ ነበር።
ነገር ግን በዛሬው ዕለት በከተማው ከንቲባ በተፃፈ ደብዳቤ " ሰልፉ መሰረዙ " ተገልጿል።
የከተማው አስተዳደር የሰልፉ መሰረዝ " በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች ያለዉን ግጭት ምክንያት በማድረግ ሰላማዊ ሰልፉን ወደ ብጥብጥ በመቀየር የሰዉ ህይወት እንዲያልፍና ንብረት እንድወድም ለማድረግ የተዘጋጁ ሀይሎች አንዳሉ የክልሉ ፀጥታ ቢሮ በጥልቀት የገመገመ በመሆኑ ነው " ብሏል።
ከዚህ ባለፈ ፤ የቢሮዎች ድልድል ፍትሃዊነትን በተመለከተ የክልሉ መንግስት ከዞን አመራር ጋር በመቀናጀት ምላሽ እንደሚሰጥ ከስምምነት ላይ የተደረሰ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉ ተሰርዟል ሲል አሳውቋል።
በሌላ በኩል ፤ " በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " የክላስተር ማዕከላት ከተሞች የቢሮዎች ድልድል ሒደት ለከምባታ ጠምባሮ ዞን የተደለደለው የቢሮ ቁጥር አነስተኛ መሆኑን በተመለከተ የዞኑ አመራር ባቀረበው ጥያቄ መነሻነት የከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴ አካላት ከደቡብ ክልል አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ጋር ነሐሴ 6 ቀን 2015 ዓ/ም በአካል ባደረጉት ውይይት ቢሮዎች እንዲጨመሩ ከስምምነት ደርሰዋል ሲል ዞኑ ገልጿል።
ለዱራሜ ከተማ እንዲጨመሩ የተወሰኑት ቢሮዎች የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስፈፃሚ መ/ቤቶችን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በሚወጣው አዋጅ ተካትተው ከሌሎች የክላስተር ማዕከላት እኩል ሥራ እንዲጀምሩ እንደሚደረግም ዞኑ ገልጿል።
በዚህ መነሻነት የሀገሪቱ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ በተለይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተካተቱ ክልከላዎችንና የአስቸኳይ ጊዜው አዋጁን የተፈፃሚነት ወሰን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዱራሜ ከተማ የሚካሔድ ሰልፍ እንደማይኖር ሊታወቅ ይገባል ብሏል።
የሰልፉ ዓላማ ከቢሮ ቁጥር ማነስ ጋር የሚያያዝ ቢሆንም የዞኑ አስተባባሪ ኮሚቴ ከክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ባደረገው ውይይት አፋጣኝ ምላሽ በማግኘቱ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ወደ ልማት ሥራዎች ፊቱን እንዲያዞርና ጊዜውን በአግባቡ እንዲጠቀም የዞኑ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል።
ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ‼️
የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ያከናወናቸውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ተግባራት ገምግሟል፡፡ የዕዙ የመጀመሪያ ምዕራፍ ዕቅድ በባሕር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ በደብረ ብርሃን፣ በላሊበላ፣ በጎንደርና በሸዋ ሮቢት አካባቢ የተሰባሰበውን በዘረፋ እና በጥፋት የተሰማራ ቡድን በመምታትና ከተሞቹን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ መመለስ ነበር። እነዚህ አካባቢዎች የተመረጡት ብዙ ሕዝብ የሚኖርባቸው፣ ከፍተኛ የንግድና የቱሪስት እንቅስቃሴ ያለባቸው፣ የፖለቲካና የኢንዱስትሪ ማዕከላት በመሆናቸው ነው።
በዚህ መሠረት በስድስቱ ከተሞች ዙሪያ የመጣው የጥፋት ቡድን መሣሪያውን እንዲያስረክብና እጁን እንዲሰጥ የተሰጠውን ዕድል ባለመጠቀሙ እርምጃ ተወስዶበታል፣ የሕግ የበላይነትም እንዲከበር ተደርጓል። የክልሉ ሕዝብ በዚህ ዘራፊ ቡድኑ የተማረረ በመሆኑ፣ የህግ አስካባሪ አካላት ተልዕኮዋቸውን በስኬት እንዲወጡ ተገቢውን ድጋፍ አድርጓል። ጠቅላይ መመሪያ እዙም የክልሉ ህዝብ ላደረገለት ትብብር ምስጋናውን ያቀርባል።
በአሁኑ ሰዓት ከተሞቹ ከዘረፊዉ መንጋ ስጋት ነጻ ሆነዋል። የመከላከያ ሠራዊቱ እና የክልሉ ህግ አስከባሪ አካላት በየሥርቻው የተራረፈውን ዘራፊ በማጽዳት ላይ ናቸው። ማኅበረሰቡም መረጃ በመስጠት፣ አቅሙ በፈቀደው ሁሉ ለዚህ ስራ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ሽንፈት የተከናነበው የፅንፈኞች ቡድን በአንዳንድ አካባቢዎች ወደ ቅርስ ቦታዎችና የእምነት ተቋማት በመግባት ለመደበቅ እየሞከረ ነው። የመከላከያ ሠራዊቱ እና የክልሉ ህግ አስከባሪ አካላት ህግ፣ ሥርዓትና ሞራልን ባከበረ መንገድ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ይገኛል። በቀጣይም የመጨረሻውን የማጽዳት እና የመልቀም ተግባር በማከናወን ከተሞቹ በአጭር ጊዜ ወደ ተሟላ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲመለሱ ይደረጋል።
በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የጠቅላይ መምሪያ ዕዙ እስካሁን 14 ተጠርጣሪዎችን በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ሥር ያዋለ ሲሆን ወደፊትም እንደሁኔታው በቁጥጥር ሥር የሚያውላቸውን ግለሰቦች አስመልክቶ አስፈላጊውን መረጃ ለህዝብ ይፋ ያደርጋል።
በመጀመሪያው ምዕራፍ ዕቅድ የተያዘው ከተሞቹን ከዘራፊ የጥፋት ቡድን የማጽዳቱ ተግባር እየተጠናቀቀ በመሆኑ፣
1. ከሐሙስ ነሐሴ 4 ጀምሮ ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች መደበኛ የአውሮፕላን በረራ ይጀመራል፤
2. ከባጃጅና ከሞተር ሳይክል በስተቀር ሁሉም ዓይነት የከተማ የትራንስፖርት አገልግሎቶች ወደ አገልግሎት ይገባሉ፤
3. የመንግሥት፣ የማኅበረሰብ አገልግሎት፣ የንግድ፣ የጤና፣ የፋይናንስ፣ ወዘተ. ተቋማት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል።
በዚሁ አጋጣሚ የክልሉ ሕዝብ ራሱን ከዘራፊውና ከጽንፈኛው መንጋ በመነጠልና በመከላከል፣ ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር በመሰለፍ ላደረገው ተጋድሎ ዕዙ በድጋሚ ምስጋናውን ያቀርባል።
የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ያስተላለፈው ትዕዛዝና ክልከላ ቁጥር 1
የሕዝብን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6 /2015 አንቀጽ 5 መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ የሚከተሉትን ትዕዛዞችና ክልከላዎች ደንግጓል።
1) በባሕርዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ሸዋ ሮቢትና ላሊበላ የሕዝብ የአገልግሎት ሰጪ፣ የመንግሥት፣ የማኅበረሰብና የንግድ ተቋማት ከነሐሴ 4/2015 ጀምሮ ክፍት እንዲሆኑ ታዟል።
2) በባሕርዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ሸዋ ሮቢትና ላሊበላ እስከ ነሐሴ 17፣2015 የሚቆይ የሠዓት እላፊ ገደብ ተጥሏል፡፡ በዚህም መሰረት የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ከሚሰጡ ተሽከርካሪዎች፣ የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ሰጪ ባለሞያዎች እና የፀጥታ አስከባሪ ተቋማት ባልደረቦች ውጪ ለማንኛውም ሰው እና ተሽከርካሪ ከምሽቱ አንድ ሰዐት በኋላ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
3) የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ ፈቃድ ውጪ በአማራ ብሔራዊ ክልል ከተሞች የአደባባይ ስብሰባ፣ ሰልፍ እና መሰል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ፈጽሞ የተከለከለ ነው። እንዲሁም በማንኛውም መልኩ የህዝብ እንቅስቃሴን የሚያስተጓጉል እና የትራንስፖርት አገልግሎትን የሚያሰናክል ድርጊት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
4) በአማራ ብሔራዊ ክልል ውስጥ ለጸጥታ ሥራ ከሚንቀሳቀሱ የህግ አስከባሪ አካላት እና ከነዚህ አካላት ፈቃድ ውጭ የጦር መሣሪያ ይዞ መዘዋወር ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
5) በአማራ ብሔራዊ ክልል ከላይ በተራ ቁጥር አንድ በተገለጹት ከተሞች የባጃጅ እና የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ ከነሐሴ 4 እስከ ነሐሴ 17፣2015 ድረስ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
6) ከባጃጆችና ከሞተር ሳይክሎች በስተቀር ሌሎች የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ከነሐሴ 4 ጀምሮ ወደ ሥራ የመመለስ እና አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለባቸው።
7) በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሽፋን ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ትእዛዝ ውጭ ወቅታዊ ሁኔታን ሰበብ በማድረግ ግለሰቦችን ከመደበኛው ህግ አግባብ ውጪ ማሰር እና ማቆየት፣ የንግድ ቤቶችን ማሸግ እና መሰል እርምጃዎችን መውሰድ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
ከላይ የተዘረዘሩትን ትዕዛዞችና ክልከላዎችን በሚጥሱ ላይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አንቀጽ 7 መሰረት ሃይልን በመጠቀም፣ እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸውን እርምጃዎችን በመውሰድ ትዕዛዝና ክልከላዎችን እንዲያስፈጽሙ ለሁሉም የህግ አስከባሪ አካላት ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷል።
አቶ ደመቀ መኮንን ችግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚገባ ገለፁ‼️
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአማራ ክልል እየተስተዋሉ ያሉ የጸጥታ እግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚገባ ገለፁ፡፡
አቶ ደመቀ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ የፀጥታ ችግሮች አሳሳቢ እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡
ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎች እንዲመለሱ እና ችግሮችን ለመፍታት ጠቃሚው መንገድ ሰላማዊና የውይይት አግባብ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡
"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።
Last updated 1 month ago
The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot
Last updated 1 month, 2 weeks ago
እንኳን ደህና መጡ‼
✔ማስታወቂያ ለማሰራት እና ጥቆማ ለመስጠት በዚህ ይጠቀሙ ☞https://t.me/WasuMohammed
✔ ቻናሉን ለመቀላቀል Join ☞http://t.me/Wasulife
ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏
Last updated 2 weeks, 6 days ago