ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago
ፍኖት:
🌿🌿🌿
"ጾም ነፍስን ያነጻል አእምሮን ያሳድጋል፣ ሥጋን ለነፍስ ያስገዛል፣ የምኞት ደመናን ይበትናል፣ የፍትወት እሳትን ያጠፋል፣ የንጽሕና እውነተኛ ብርሃን ያበራል።"
/ቅዱስ አውግስጢን/
━━━━━✦📖 ❖ 📖✦━━━━━
ዐቢይ ጾም
☘☘ፀልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን☘☘
“ጾምን አውጁ” (ኢዩ.፪፥፲፭)
እንኳን ለዐቢይ ጾም አደረሰን!
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ከሚታወጁት ሰባት አጽዋማት መካከል ታላቅ ለሆነው ለዐቢይ ጾም ስላደረሰን አምላካችን እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው!
ዐቢይ ጾም ማለት ምን ማለት ነው?
በመጀመሪያ ‹‹ዐቢይ›› የሚለው ቃል ‹‹አበየ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ትርጓሜውም ‹‹ከፍ አለ›› ማለት ነው፡፡ ጾሙም ዐቢይ የተባለበት ሦስት ዓበይት ምክንያቶች አሉት። የመጀመሪያው ጌታቸን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ የጾመው ስለሆነ ነው፡፡ (ማቴ.፬፥፫-፫) በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት ስለ ሚበልጥና የቀኑ ብዛትም ፶፭ ቀንም ነው፡፡ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች እንዲሁም ደግሞ ሦስቱ ርእሰ ኃጢአት (ትዕቢት፣ ስስት ፍቅረ ነዋይ) በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ድል የተመቱበት በመሆኑ ዐቢይ (ታላቅ) ጾም ተብሏል፡፡ (ማቴ.፬፥፫-፲፩)፡፡
የዐቢይ ጾም ስያሜዎች
ዐቢይ ጾም ከቀኑ ርዝማኔ በተጨማሪ የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡
ጾመ ሁዳዴ፡- ሁዳድ ማለት ሰፊ (ትልቅ) የእርሻ ቦታ ማለት ነው፡፡ በሰፊ እርሻ የተመሰለበት ምክንያት የቀኑ ብዛት ከሌሎች አጽዋማት ስለሚበዛ ነው፡፡
የካሣ ጾም፡- አዳምና ሔዋን በዲያቢሎስ ግዞት እያሉ ክርስቶስ ደሙን በመክፈል (በመካስ) ነጻ ስላውጣቸው የካሣ እየተባለ ይጠራል፡፡
የድል ጾም፡- ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ጾም ሰይጣንን ድል ያደረገበት በመሆኑ የድል ጾም ተብሏል፡፡
ጾም አስተምህሮ፡- ዐቢይ ጾም ‹‹ጾም አስተምህሮ›› የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማስተማር የጾመው በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡
የዐቢይ ጾም ሳምንታት
ዐቢይ ጾም በያዘው በ፶፭ ቀኑ ውስጥ ሰባት ቅዳሜና ስምንት እሑዶቸን ይዟል፤ የእነዚህ የስምንቱ እሑዶች የተለያየ ስያሜ አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም የሰጣቸው የቤተ ክርስቲያናችን የዜማው ሊቅ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ ዘወረደ፣ ቅድስት፣ ምኩራብ፣ ደብረዘይት፣ ገብረ ኄር፣ ኒቆዲሞስ ፣ መፃጉዕ፣ ሆሣዕና ናቸው፡፡
፩ኛ. ዘወረደ፡- በመጀመርያው ሳምንት ዘወረደ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማያት መውረዱን፣ ከአመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን እና እኛን ማዳኑን በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሚወሳበትና የሚዘከርበት ወቅት ሲሆን ይህንንም የሚዘክሩ መዝሙሮች ይቀርባሉ፤ ትምህርቶች ይሰጣሉ፤ ይህንንም እያሰብን ጾሙን እንጾማለን፡፡
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ ለሐዋርያት እንዲሁም ለቀደሙ አባቶቻችን በሥርዓቱ ጹመን እንዲንጠቀም እርዳን፤ አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
☘☘ፀልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን☘☘
"ለችግረኛ እና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው።" መዝሙር ፵÷፩
" ምሂረ ነዳያን "
ለነዳያን የተዘጋጀ የትምሀርት እና የዝማሬ መርሐግብር
ታህሳስ 13 ቀን 2017ዓ.ም ከቅዳሴ በኋላ
በሰንበት ት/ቤት አዳራሽ
የትምህርት እና ሥልጠና ክፍል
ዕለተ ውሂብ ታኅሣሥ 20/2017 ዓ.ም
“... ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው ወርቅና ዕጣን፥ ከርቤም፥ እጅ መንሻ አቀረቡለት።” ማቴ ፪፥፲፩
በኮከብ ተመርተው ወደ ቤተ ልሔም ምድረ ኤፍራታ የተጓዙትን የሰብአ ሰገልን ፍኖት በመከተል በፍቅር የሚከወን የወዳጅነት መገለጫ
ዕለተ ውሂብ (የስጦታ ቀን)
እንኳን አደረሳችሁ !!
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago