Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

Sheger ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

Description
ሸገር 102.1 መስከረም 23፣2000 ዓ.ም ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡

ጣቢያችን ለማንም ባለመወገን ለሁሉም በታማኝነትና በመልካም ሥነ ምግባር መልካም አገልግሎት በመስጠት የሚያምንና ለእነዚህም እሴቶች ትልቅ ክብር የሚሰጥ ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡

ሸገር የእናንተ ነው!

https://bit.ly/33KMCqz
Advertising
We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 day, 15 hours ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month, 2 weeks ago

1 week ago

የጨዋታ እንግዳ፦ ተወዳጁ ተዋናይ ፣አዘጋጅ እና የተውኔት ደራሲ ተክሌ ደስታ ጨዋታ ከመዓዛ ብሩ ጋር 2ኛ ሳምንት ክፍል 2 - ግንቦት 3፣2016

https://youtu.be/YJIawdN9al0

#YechewataEngida #TekleDesta #MeazaBirru #kidameChewata #Chewata #የቅዳሜ_ጨዋታ #የጨዋታ_እንግዳ #ተክሌ_ደስታ #Ethiopia

YouTube

Yechewata Engid -Tekle Desta With Meaza Birru ተወዳጁ ተዋናይ ፣አዘጋጅ እና የተውኔት ደራሲ ተክሌ ደስታ ጨዋታ 2ኛ ሳምንት ክፍል 2

#yechewataengida #TekleDesta #kidameChewata shegerfm,sheger fm news,sheger maleda,sheger,sheger sport,shegernews,shegercafe,shegerradio,shegershelf,shegerfm...

1 week ago

ትዝታ ዘ አራዳ - ባለቅኔው መንግስቱ ለማ በተፈሪ ዓለሙ ክፍል 12 ግንቦት 3፣2016

https://youtu.be/SuNGG-fTQY0

#Ethiopia #ShegerFM #TizitaZeArada #Mengistulemma #TeferiAlemu

YouTube

Sheger Tizita Ze Arada -ባለቅኔው መንግስቱ ለማ Mengistu Lemma - በተፈሪ ዓለሙ Teferi Alemu@ShegerFM1021Radio

#MengistuLemma #TeferiAlemu #Tizita\_Ze\_AradaSheger Tizita Ze Arada - ባለቅኔው መንግስቱ ለማ Mengistu Lemma - በተፈሪ ዓለሙ Teferi Alemu @ShegerFM1021Radio shegerfm,sh...

1 week, 1 day ago

ግንቦት 2፣2016

ስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት ያግዛለ በሚል መመሪያ የወጣለት ስታርት አፕ(Start UP) ተግባር ላይ ለማዋል ብዙ መስራት ይጠይቃል ተባለ፡፡

በተለያዩ መስኮች የሚመነጩ የፈጠራ ሀሳቦችን ወደ ተግባር ለማውረድ መንገድ ያቃናል በሚል እየተወራ ያለ ጉዳይ ነው ሰታርት አፕ፡፡

በተለይ በአሁን ወቀት ለሀገር አስፈላጊ እንደሆነ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ በተለያዩ የዘርፉ አካላት ተደጋግሞ እየተነገረለትም ነው፡፡

የስታርት አፕ ሀሳብ ሲፍታታ፤ ለስራ ፈጣሪዎች የተመች ከባቢን መፍጠር፣ ችግር ፈቺ መስኮች ላይ አተኩሮ መስራት፣ ለዘርፉ የተስማሙ ፖሊሲዎችን አፅድቆ ድጋፍ ማድረግና ተያያዥ ጉዳዮችን ያጠቃልላል፡፡

ይህ ሀሳብ ለዓመታት በተለያዩ አካላት እየተነሳ ቢቆይም ትኩረት ተሰጥቶት ባለመሰራቱ በወጣቶች የመነጩ የስራ ሀሳቦች መሬት ላይ ወርደው ጠቃሚ መሆን ሳይችሉ ቀርተዋል ተብሏል፡፡

ዘርፉ የሚመራበት ህግም በሀገሪቷ አለመኖር ዋነኛው ችግር ሆኖ መቆየቱ ተነግሯል፡፡

መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሀሳቡ ጠቃሚነት ተረደቻለሁ ብሎ፤ በሚመለከታቸው አካላት የቀረቡለትን፤ ዘርፉን እና ተያያዥ መስኮችን የሚደግፉ 11 መመሪያዎችን አስተዋውቋል፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህ ይፋ የተደረጉ መመሪያዎች ወደ ተግባር ለማውረድ ገና ብዙ መስራት እንደሚጠይቅ ተነግሯል፡፡

ይህንን የስታርት አፕ ሀሳብን የሚያበረቱ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ሀገሪቱ እንድታደርግ ወትዋች ከነበሩት አካላት መካከል ‘’የኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ወጣቶች ማህበር’’ የሚጠቀስ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የስራ ፈጠራ ስነምህዳር የተመቸ እንዳልሆነ የጠቀሱት የማህበሩ ፕሬዝደንት ሳሚያ አብዱርቃድር፤ በቅርቡ በመንግስት ለዘርፉ የተሰጠው ትኩረት የሚበረታታ ቢሆንም ወደተግባር ለማውረድ ግን አሁንም ብዙ ስራዎች እንደሚቀሩ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

በተለይ በተለያየ ጊዜ የታየው የመንግስትም ሆነ የግል መስሪያ ቤቶች የእርስ በእርስ የመነናበብ ችግር ሊቀረፍ እንደሚገባም ጠቅሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ የስራ ፈጠራ ሀሳብን በገንዘብ ካለመገደፍ(Idea Financing) በተጨማሪ ዘርፉ የሚመራበት ፖሊሲ መንግስት ሳያዘጋጅ መቆየቱ ዘርፉን እንደጎዳው መንግስት ራሱ አምኗል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) የሚሉትም ይህንኑ ነው፡፡

https://tinyurl.com/3wy89vtn

ማንያዘዋል ጌታሁን

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የስራ_ፈጠራ #ስታርት_አፕ #Start_UP #Idea_Financing

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

2 weeks ago

ሚያዝያ  26፣2016

የባንኮች የሳይበር ጥቃት ጉዳይ!

https://youtu.be/vdTpsL9sAHU

#Ethiopia #ShegerWerewoch  #Bank_Cyber_Attack #ባንኮች #የሳይበር_ጥቃት

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:  https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

YouTube

የባንኮች የሳይበር ጥቃት

ሚያዝያ 26፣2016 የባንኮች የሳይበር ጥቃት ጉዳይ! ተህቦ ንጉሴ #Ethiopia #ShegerWerewoch #Bank\_Cyber\_Attack #ባንኮች #የሳይበር\_ጥቃት የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio Website: https://www.shegerfm.com/…

2 weeks, 1 day ago

ሚያዝያ 26፣2016

ለፍትሀዊነቱ፤ ልዩ ችሎት ወይስ ልዩ ፍርድ ቤት?

https://youtu.be/UxdLEcZ1dhA

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የሽግግር_ፍትህ_ፖሊሲ #ልዩ_ችሎት

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

YouTube

ለፍትሀዊነቱ፤ ልዩ ችሎት ወይስ ልዩ ፍርድ ቤት?

ሚያዝያ 26፣2016 ለፍትሀዊነቱ፤ ልዩ ችሎት ወይስ ልዩ ፍርድ ቤት? ትዕግስት ዘሪሁን #Ethiopia #ShegerWerewoch #የሽግግር\_ፍትህ\_ፖሊሲ #ልዩ\_ችሎት የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio Website: https://www.shegerfm.com/…

2 weeks, 1 day ago

ሚያዝያ 26፣2016

እርድ፤ እንዴት ነው መከወን ያለበት?

https://youtu.be/hNQP7ma9tKQ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ቅርጫ #በሬ #እርድ #ፋሲካ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

YouTube

እርድ እንዴት ነው መከወን ያለበት?

ሚያዝያ 26፣2016 እርድ እንዴት ነው መከወን ያለበት? ምንታምር ፀጋው #Ethiopia #ShegerWerewoch #ቅርጫ #በሬ #እርድ #ፋሲካ የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio Website: https://www.shegerfm.com/ Tiktok:…

3 weeks, 4 days ago

ሚያዝያ 16፣2016

ወባ እና ተቅማጥ የመሳሰሉ በአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ የሚደርሱ በሽታዎች ያላቸውን የተጽዕኖ መጠን የሚያስረዳ የዳሰሳ ትንተና ሊሰራ መሆኑ ተሠማ፡፡

https://tinyurl.com/m3x42b8y

ንጋቱ ሙሉ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ወባ #ተቅማጥ #አየር_ንብረት_ለውጥ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: @ShegerFMRadio102_1

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

3 weeks, 4 days ago

ሚያዝያ 16፣2016

በአዲስ አበባ በአፈር እና ግንብ መናድ አደጋ ስድስት ሰዎች ሞቱ፡፡

አደጋው ያጋጠመው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ጠሮ መስጅድ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ሌሊት 11:00 ሰዓት ላይ ነው ተብሏል፡፡

የግለሰብ መኖሪያ ቤት አፈርና ግንብ ተንዶ በደረሰው በዚህ አደጋ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች በመኖሪያ ቤታቸው ተኝተው የነበሩ ናቸው ተብሏል።

በአደጋው ምክንያት በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ የደረሰውን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ወደፊት እናሳውቃለን ሲሉ የአዲስ አበባ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል።

ንጋቱ ረጋሳ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #አደጋ #ጠሮ_መስጅድ #የቤት_መናድ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: @ShegerFMRadio102_1

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

3 weeks, 4 days ago

ሚያዝያ  15፣2016

አዲሱ የካላዛር ህክምና ወደ ምዕራፍ ሁለት የክሊኒካል ሙከራ መሸጋገሩ ተሰማ፡፡

ካላዛር  ከወባ ቀጥሎ በዓለም ላይ በጥገኛ ተህዋሲያን የሚተላለፍ ገዳዩ በሽታ ነው፡፡

በሽታው  ትኩሳት፣ የክብደት መቀነስ፣ ከልክ ያለፈ የጣፊያና የጉበት እድገት ያስከትላል፣  በጊዜው ካልታከመም ለሞት ሊዳርግም ይችላል፡፡

ፈውስ ትኩረት ለተነፈጉ በሽታዎች ኢኒሺዬቲቭ ወይንም ዲ ኤን ዲ የጤና ምርምር የተባለ ተቋም እና አጋሮቹ  ለዚህ በሽታ የሚያደርጉት የመድሃኒት ፍለጋ ምእራፍ ሁለት የክሊኒካል ሙከራ ደረጃ መሸጋገሩን ተናግሯል፡፡

ወደ ምእራፍ ሁለት የክሊኒካል ሙከራ መሸጋገሩ የተነገረው መድሃኒቱ ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ፣ አስተማማኝ፣ ለአጠቃቀም ቀላል እና ለህሙማን ምቹ የሆነ በአፍ የሚወሰድ ነው ተብሏል፡፡

የካላዛር መድሃኒት ለማስገኘት የሚያካሂዱት ምርምር አዲሱ የካላዛር ህክምና በእጅጉ ትኩረት የተነፈገውንና ለማከምም አስቸጋሪ የሆነውን የካላዛር በሽታ ለማዳን በሚደረገው ርብርብ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ያግዛል ተብሎለታል፡፡   

በአፍሪካ አሁን እየተሰጠ የሚገኘው የካላዛር ህክምና በሆስፒታል ውስጥ በየቀኑ ለ17 ቀናት የሚወሰድ ከፍተኛ ህመም የሚፈጥር ክትባት ሲሆን ልብን፣ጉበትን እና ቆሽትን በመጉዳት ለህይወት አስጊ የሆኑ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሊያስከትል ይችላል።

በአንፃሩ በኢትዮጵያ በምርምር ላይ የሚገኘው አዲሱየ“LXE408”በአፍ  የሚወሰድ መድሀኒት አሁን ከሚሰጠው ህክምና የበለጠ ፈዋሽና አስተማማኝ እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል።

“ኢትዮጵያ እንደ አንድ ካላዛር የተንሰራፋበት አገር፣አዳዲሶቹ ኬሚካላዊ ምርምሮች ወደሚካዱበት ምእራፍ ሁለት ክሊኒካዊ ሙከራ መግባቷ ትልቅ እምርታ ነው ሲሉ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የካላዛር በሽታ ጥናትና ህክምና ማዕከል ውስጥ በሚካሄደው በዚህ ክሊኒካል ሙከራ ተባባሪ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር እሌኒ አየለ አስረድተዋል፡፡

“አሁን ላይ በኢትዮጵያ ያሉት የካላዛር ህክምና አማራጮች ከፍተኛ የሆነ ውስንነት ያለባቸው፣ ጎጂ ክትባትን ግዴታ የሚያደርጉ፣ እጅግ ቀዝቃዛ የህክምና ቁሳቁሶች ጥቅም ላይ የሚውሉባቸው እንዲሁም ህሙማን አገልግሎቶቹን ፍለጋ የረጅም ርቀት ጉዞ የሚጠይቁ እና ለረጅም ጊዜም ሆስፒታል ውስጥ ተኝተው የሚታከሙባቸው ናቸው" ሲሉም ተመራማሪዋ ጠቅሰዋል፡፡

በምርምሩ ከሰመረ ላይ ህክምናው ፈዋሽ፣ የጎንዮሽ ጉዳቱ አነስተኛ የሆነና ህሙማን በመኖሪያ ቤታቸው ፣አቅራቢያ በሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ተቋማት ማግኘት ይትላሉ ሲሉ ተመራማሪዋ አስረድተዋል፡፡

ከምንም በላይ በሽታውን እስከወዲያኛው ለማስወገድ የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ ያግዛል ተብሏል፡፡

አዲሱ ህክምና በኢትዮጵያ የመድሃኒትሙከራ መስፈርት መሰረት የሚካሄድ ሲሆን በየቀኑ የሶዲየም ስቲቦግሉኮኔት እና ፓሮሞማይሲን ድብልቅ መርፌዎች ለ17 ቀናት ይሰጣል።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ ከ18 እስከ 44 ዓመት … https://tinyurl.com/yck2pa6y

#Ethiopia #ShegerWerewoch  #የካላዛር_ህክምና #ወባ #የካላዛር_በሽታ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram:  @ShegerFMRadio102_1

Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

2 months, 3 weeks ago

የካቲት 14፣2016

በዘመን ባንክ በኩል ለሚደረጉ አለም አቀፍ ንግዶች የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን(IFC) የ30 ሚሊዮን ዶላር መተማመኛ ለመስጠት ተስማማ።

ስምምነቱም በዛሬው ዕለት በዘመን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ደረጀ ዘበነ እና በአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ቢሮ ሃላፊ ማዳሎ ሚኖፉ ተፈርሟል።

በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ የግብይት ስርዓት መዛባት ሲያገጥም፣ በሽያጭ እና ገዢ መካከል አለመተማመን ሲኖር ባንኮች እምነት እንዲጣልባቸው ጥሬ ገንዘብ በመመደብ ጭምር ድጋፍ ያደርጋሉ ተብሏል።

ይህ ደግሞ በባንኮች ላይ ጫና እንደሚፈጥር ያስረዱት የዘመን ባንክ ስራ አስፈፃሚ ደረጀ ዘበነ ይህ በኢትዮጵያ የፀጥታ ችግር ባጋጠመባቸው ወቅቶች ጎልቶ ታይቷል ብለዋል።

በዚህ ስምምነት መሰረት የአለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የዘመን ባንክን የትሬድ ፋይናንስ (የወጪና ገቢ ንግድ ገንዘብ አቅርቦት) እንቅስቃሴ ለማጠናከርና በኢትዮጵያ ላሉ የወጪ ንግድ ላይ ለሚሰሩ ድርጅቶች አዲስ የንግድ ትስስርን ለመፍጠር የ30 ሚሊዮን ዶላር ዋስትና ያቀርባል ተብሏል።

ፕሮግራሙ ለባንኩ የንግድ ፋይናንስ ድጋፍ በማቅረብ የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ንግድ ለመደገፍ ብሎም አህጉራዊ ንግድን ማበረታታትን አላማው ያደረገ ነው ሲባል ሰምተናል።

ስምምነቱ ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት በሚኖርበት ወቅት በገቢና ወጪ ንግድ ላይ የተሰማሩ የንግድ አጋሮችንም ሆነ የባንኩን ስጋት በእጅጉ እንደሚቀንስ የዘመን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ደረጀ ዘበነ አስረድተዋል፡፡

ይሀ ፕሮግራም የወጪ ንግድ ፋይናንስ እንዳይስፋፋ የሚገድቡ እከሎችን ወይም ለዘርፉ ፈታኝ የሆኑ ስጋቶችን ለመቀነስ የሚረዳ ነው ተብሎለታል።

ለወጪና ገቢ ንግድ ዘርፍ ፋይናንስ የማቅረብ አቅምንም ያሰፋል ሲባልም ሰምተናል።

ዘመን ባንክ ባንክ ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ያገኘው የ30 ሚሊዮን ዶላር የአለም አቀፍ ንግድ ዋስትና፤ ኮርፖሬሽኑ ለአፍሪካ ሀገራት መሰል ስራ ብሎ የያዘው 1 ቢሊዮን ዶላር አካል መሆኑ ተነግሯል።

ከዘመን ባንክ ጋር በአጋርነት ለመስራት የተፈራረመው አለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን፤ የዓለም ባንክ አባል ሲሆን በማደግ ላይ ያለውን የግል ዘርፍ ላይ የተለየ ትኩረት በማድረግ የሚደግፍ የልማት ተቋም መሆኑን ሰምተናል፡፡

ባለፈው ዓመት ብቻ በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች ለሚካሄዱ የግል ኩባንያዎችና የገንዘብ ተቋማት 43.7 ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር አበርክቷል ተብሏል፡፡

#Ethiopia #ShegerWerewoch #ዘመን_ባንክ #IFC

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw

Website: https://www.shegerfm.com/

Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month, 3 weeks ago

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 day, 15 hours ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 1 month, 2 weeks ago