Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

Description
ዜና ከምንጩ
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 5 days ago

Last updated 2 weeks, 5 days ago

1 week, 5 days ago

**የአዲስ ማለዳ የሳምንቱ አንኳር ዜናዎች

እሁድ ሚያዝያ 27 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ)**

  1. በምዕራብ እና በሰሜን ትግራይ እንዲሁም ጸለምቲ የሚገኘው ሕገ ወጥ አስተዳደር እስከ ሰኔ 30 ድረስ ይፈርሳል" ሲል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ገለጸ። ሙሉ ዘገባውን https://t.me/addismaleda/19126

  2. በአማራ ክልል ዋና ከተማው ላሊበላ የሆነው የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው የጤና ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሚሊዮን አፈወርቅ ማክሰኞ ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ተገድለዋል። የገዳዮች ማንነት አልታወቀም አልያም ሀላፊነት የወሰደ አካል የለም።

  3. "ምርጫ ቦርድ በፓርቲው ላይ ዛቻ የተቀላቀለ ማስፈራሪያ ማውጣቱ ከአንድ ዴሞክራሲያዊ ተቋም የማይጠበቅ ነው” ሲል ሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ ገለጸ። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ፓርቲው ስሜን እያጠፋ ነው ብሏል። ዝርዝሩን https://t.me/addismaleda/19142

  4. የሠራተኞች ቀን በዓል ላይ ታዳሚ የሆኑ ሠራተኞች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመላው አገሪቱ በየደረጃው የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ጋር በመገናኘት ስላሉ ችግሮች ሲወያዩና መፍትሔ ሲፈልጉ የሚታይ ቢሆንም ከሠራተኛው ክፍል ጋር ውይይት አለማድረጋቸው እንዳሳሰባቸው ገለጹ። ሙሉ ፅሁፉ https://t.me/addismaleda/19124

  5. በአዲስ አበባ ከተማ በዚህ ሳምንት አስቸጋሪ የጎርፍ መጥለቅለቅ በተለያዩ ቦታዎች ያጋጠመ ሲሆን ሰኞ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል። ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ የሚወስደው መንገድ ተደጋጋሚ ጎርፍ አጋጥሟል።

  6. በኢትዮጵያ ጾታዊ ጥቃቶችን ለመቆጣጠር እስከ ሞት ድረስ ያሉ ከባድ ቅጣቶች እንደሚያስፈልጉ የሕግ ባለሞያዎች ገለጹ። አዲስ ማለዳ ተጎጂዎችና የሕግ ባለሞያዎችን እንዲሁም ምልከታዎች የተካተቱበት ዝርዝር ዘገባ https://addismaleda.com/archives/37941 ያንብቡ

  7. የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና (ማትሪክ) ከሐምሌ 3 እስከ 11 ቀን 2016 ይሰጣል። ዝርዝሩን https://t.me/addismaleda/19100

  8. ኢትዮጵያ አሁን ከመፍረስና ከመዳን የትኛው እድሏ የሰፋ ነው ቢባል "የመፍረስ እድሏ ነው፤ 20/30 ፐርሰንት (በመቶ) የመዳን እድል የለንም" ያሉት ልደቱ አያሌው፤ "ምክንያቱም ሁላችንም ወደጥፋቱ አቅጣጫ ነው እየገፋን ያለነው። ከጥፋቱ ወደሚያወጣን አቅጣጫ የሚገፋ ኃይል የለም" ብለዋል። https://t.me/addismaleda/19113

  9. የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የኢትዮጵያ ቢሮ እንዳስታወቀው በአማራ ክልል ከ4.1 ሚልየን በላይ ተማሪዎች በግጭት ሳቢያ ትምህርት አቋርጠዋል።

  10. የአውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያውያን የሚሰጠው ቪዛ አሰራር ላይ ገደብ መጣሉን በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። ገደቦቹ የኢትዮጵያ መንግስት ህጋዊ ያልሆኑ ዜጎቹን ከአውሮፓ ለማስወጣት ቸልተኛ በመሆኑ እንደተጣሉ ቢገለጽም የኢትዮጵያ መንግስት አስተባብሏል፤ ሙሉ ዘገባውን https://t.me/addismaleda/19139

  11. እናት ፓርቲ በመንግሥት እየተከናወኑ የሚገኙ "አይን ያወጡ ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶችን ስንመለከት የሥርዓቱ የመጨረሻ ግብ መሠረታዊ እሴቶችን አጥፍቶ የመውረስ ክፉ ደዌ መሆኑን" ለመገንዘብ አያዳግትም ብሏል። የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ማሳደድ ይቁም ብሏል፤ ሙሉ ፅሁፉ https://t.me/addismaleda/19146

  12. የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም የቀድሞ ኃላፊ ጣሂር መሀመድ በግምገማ ከስልጣን ተነስተው እንጂ በፈቃዳቸው አይደለም በማለት የቢሮው ምክትል ኃላፊ ገልጸዋል። https://t.me/addismaleda/19151

  13. የ ‘ገበታ ለሀገር’ ፕሮጀክቶች ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለክልል መንግስታት የተላለፉ ሲሆን ሎጆችን የማስተዳደር ኃላፊነት ለስካላይት ኢትዮጵያ ሆቴል ተሰጥቷል።

  14. የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በአዲስ አበባ ከተማ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በሕይወት የመኖር እና የአካል ደህንነት መብቶች አደጋ ውስጥ መሆናቸውን አሳሰቧል፤ ተጨማሪ መረጃ https://t.me/addismaleda/19118

  15. ኢትዮጵያ የትምባሆ አምራቾችን ጫና ተቋቁማ የሲጋራ አጫሾችን ቁጥር መቀነሷን ጥናት አመላከተ https://addismaleda.com/archives/37948

Telegram

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

#ወቅታዊ #developing "በምዕራብ እና በሰሜን ትግራይ እንዲሁም ጸለምቲ የሚገኘው ሕገ ወጥ አስተዳደር እስከ ሰኔ 30 ድረስ ይፈርሳል"- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሐሙስ ሚያዝያ 24 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) "በምዕራብ ትግራይ" የሚገኘውን "ሕገ ወጥ" አስተዳደር የመበተን ስራ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 እንደሚያልቅ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ታደሰ ወረደ ገለጹ። …

1 week, 5 days ago
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
1 week, 6 days ago
**ፋሲካ (በዓለ ትንሣኤ)**

ፋሲካ (በዓለ ትንሣኤ)

ሚያዝያ 27 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የትንሳኤን ትርጉም በአምስት እንደሚከፈል የሃይማኖት አባቶች ይገልጻሉ።

የመጀመርያው ትንሣኤ ሕሊና ነው፤ ይህም ማለት ተዘክሮተ እግዚአብሔር (እግዚአብሔርን ማሰብ) ነው፡፡ ሁለተኛውም ትንሣኤ ልቡና ነው፤ የዚህም ምሥጢሩ ቃለ እግዘብሔርን መስማትና በንስሐ እየታደሱ በሕይወት መኖር ነው፡፡ ሦስተኛው ትንሣኤ ለጊዜው (በተአምራት) የሙታን በሥጋ መነሣት ነው፡፡ ነገር ግን በድጋሜ ሌላ ሞት ይከተለዋል፡፡ አራተኛው ትንሣኤ ክርስቶስ በሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱን ያመላክታል፡፡ ዝርዝሩን https://addismaleda.com/archives/37952 ያንብቡ
———
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየት እና የሚዲያ ሽፋን ጥቆማ ለማድረስ
የአዲስ ማለዳ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይቀላቀሉ፤ ለሌሎችም ያጋሩ!
Telegram | Facebook | YouTube | X | www.addismaleda.com | 0961414141

2 weeks, 5 days ago

የአዲስ ማለዳ የሳምንቱ አንኳር ዜናዎች

እሁድ ሚያዝያ 20 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ)

  1. አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ  "እብደት በሕብረት" የተሰኘ የአንድ ሰው ቴአትሩን ለማሳየት ወደ እስራኤል አገር ሊጓዝ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች መያዙ ተገለጸ፡፡

2.የህወሓት እና የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ባደረጉት ውይይት "ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነው" ሲል ድርጅቱ ባሰራጨው መግለጫ ማስተባበሉን እንዲሁም (ህወሓት) ከብልጽግና ፓርቲ ጋር "ለመቀላልቀል" ውይይት አላደረግኩም ማለቱን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

3.በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ከሚገኙት አላማጣ እና ሌሎችም ግጭት የተከሰተባቸው አካባቢዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ወረዳ አጎራባች እና በዋግ ኽምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ መሸሻቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።የተፈናቃዮች ቁጥር ከአንድ ሳምንት በፊት ሚያዝያ 8 ቀን ከተመዘገበውም “በሶስት እጥፍ ጨምሯል” ሲል የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ገልጿል።

4.ዲላ ዩኒቨርሲቲ እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በቅጥር ግቢያቸው ውስጥ ለተማሪዎች በተለጠፈ ማስታወቂያ “እንደአገር ባጋጠመን የምግብ በጀት እጥረት” እና “የምግብ ጥሬ ዕቃ ዋጋ በየቀኑ መጨመር” ሳቢያ የምግብ ዓይነቶች እንደሚቀየሩ በማስታወቂያ መግለጻቸውን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡ ዝርዝሩን https://addismaleda.com/archives/36490

5.የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትጥቅና ሰላማዊ ባልሆነ መንገድ የሚታገሉ አካላት ጉዳት ሳይደርስባቸው በምክክር ሂደቱ እንዲሳተፉ እንደሚደረግ አስታወቀ፡፡

6.ከየመን የባህር ዳርቻ ልዩ ስሙ 'አራ' የተባለ ስፍራ 77 ኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ ጅቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ በመገለብጧ 23 ኢትዮጵያዉያን መሞታቸውን እና 23 ሰዎች የገቡበት አለመታወቁ ተገለጻል።

7.አሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጃፓን እና ጣሊያን፣ የትግራይ እና አማራ ክልሎች በሚወዛገቡባቸው አካባቢዎች ሰሞኑን የተፈጠረው ውጥረት እንዳሳሰባቸው ሰሞኑን በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

8.የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ለኮሪደር ልማት ሲል ያፈረሳቸውን ሠፈሮች ጨምሮ በ250 በላይ ቦታዎች ላይ የሊዝ ጨረታ ማውጣቱን ዋዜማ ዘግባለች።

9.አብን በሚያዚያ 14 ምሽት ባወጣው መግለጫ ሕወሃት በአማራ ሕዝብ ላይ ሌላ ዙር የጦርነት ጉሰማ ሲጀምር መንግሥት የሚያሳየው የሃላፊነትና የግልጽነት ጉድለት አገሪቱ ወደባሰ ችግር ውስጥ እንድትገባ ግንባር ቀደም አስተዋጽዖ አድርጓል በማለት ከሷል።

10.የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሰሞኑን መነጋገሪያ የሆነውን ተንቀሳቃሽ ምስል አመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ በቤተ ክርስቲያን በዓል ላይ የተቋሙን ደንብ ልብስ የለበሰ አባል ሲዘምር እና በህዝብ ፊት ሲተኩስ በመታየቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል።

11.ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከተመካከረ በኋላ ባወጣው መግለጫ “በስምምነቱ መሠረት የህሐት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው” ብሎ “የማንነት እና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች ጉዳይ እልባት ለመስጠት እንዲቻል የተቀመጠው አቅጣጫ ተግባራዊ መደረግ አለበት” ሲል አስታውቋል።ዝርዝሩን https://addismaleda.com/archives/36504

12.ኢትዮጵያ ውስጥ የትጥቅ ትግል እያደረገ የሚገኘው እና በአገሪቱ ፓርላማ “አሸባሪ” ተብሎ የተፈረጀው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሠ) በሚያዚያ 16 ይፋዊ የኤክስ ገጽ የብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት ለአገሪቱ ስብራት ያስቀመጣቸው መፍትሔዎች በሙሉ በገዢው ፓርቲ ነው ሲል አስታውቋል።

13.ምርጫ ቦርድ ስድስተኛው ዙር አገር ዓቀፍ ምርጫ ባልተካሄደባቸውና ድጋሚ ምርጫ በሚካሄድባቸው በአፋር፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ሶማሌና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ሰኔ 9 ለሚያካሄደው ምርጫ የጊዜ ሰሌዳዎችን አውጥቷል።

14.የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ የመንገድ ኮሪደር ልማት ሳቢያ ከሠፈራቸው ለተነሱ ከ4 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ካሳ እንደተከፈላቸው በሚያዚያ 18 ለከተማዋ ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት ተናግረዋል።እስካሁን 5 ሺህ 135 ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው እንደተነሱና ወደ ሌላ ቦታ እንደተዛወሩ ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል።

15.በኢትዮጵያ የተጠለሉ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር ከ1 ሚሊዮን 59 ሺ በላይ መሻገሩን የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ገልጻል፡፡ባለፈው አንድ ወር ብቻ ከ100 ሺህ በላይ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡና የሱዳናዊያን ስደተኞች ብዛት ብቻ ከ52 ሺህ 600 በላይ መድረሱን ኮሚሽኑ ጠቁሟል፡፡

16.በደቡብ ኢትዮጵያን በዎላይታ ዞን የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ መዘግየት እና ያለመከፈል የተመለከቱ  አቤቱታዎችን በማጣራት ሰራተኞቹ ችግር ላይ መሆናቸውን አረጋግጫለው ሲል የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

17.የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔ ለ2016 ዓመት የሚውል 21 ነጥብ 74 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አስትድቋል። ከጸደቀው ተጨማሪ በጀት ውስጥ 909 ሚሊዮን ብር ለመደበኛ እንዲሁም 20 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ለካፒታል በጀት የሚውል መሆኑ ተገልጿል።

18.ሚንስትሮች ምክር ቤት በሚያዚያ 17 ባካሄደው ስብሰባ በወጪ ንግድ ላይ የቀረጥ ማበረታቻ ሥርዓት የሚደነግግ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ አጽድቋል።

19.ሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ)“ቦርዱ የፓርቲው ውስጠ-ጉዳይ ላይ ጠልቃ በመግባት” እንዲሁም ከፓርቲው ከተሰናበቱት የቀድሞ አባላት ጋር በማበር የሀገሪቱ ህግና የኢፌዴሪ ህገመንግስት በተፃረረ መልኩ የተለያዩ “ህገወጥና አደገኛ ውሳኔ” በማስተላለፋቸው በማለት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በፓርቲው የቀድሞ አባላት ላይ ክስ መስርቷል፡፡ዝርዝሩን https://addismaleda.com/archives/36508

20.የትግራዩ ተቃዋሚ ሳልሳዊ ወያነ በኢትዮጵያ የሚገኙ የሰባት አገራት ኢምባሲዎች የትግራይን ግዛቶች "አወዛጋቢ ቦታዎች" በሚል ቃል መግለጣቸውን ኮንኗል። ፓርቲው "አወዛጋቢ" የተባሉት አካባቢዎች "በኃይል የተያዙ የትግራይ ግዛቶች እንጅ ውዝግብ የተነሳባቸው አይደሉም" ብሏል።

2 weeks, 5 days ago
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
2 weeks, 6 days ago
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
2 months, 3 weeks ago
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
2 months, 3 weeks ago
**ከአዲስ አበባ - ደሴ የሚገኘው መንገድ …

**ከአዲስ አበባ - ደሴ የሚገኘው መንገድ “ላልተወሰነ ጊዜ” ተዘገቷል

ቅዳሜ የካቲት 16 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ)** ከአዲስ አበባ - ደሴ በሚገኘው አውራ ጎዳና ከዛሬ የካቲት 16 ቀን 2016 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሰውና የንብረት እንቅስቃሴ እገዳ እንደተጣለ አዲስ ማለዳ ከማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም ከደሴ - ሸዋሮቢት_ ደብረ ብርሃን እንዲሁም ከደብረ ብርሃን -ሸዋሮቢት - ደሴ የሚደረግ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ለጊዜው እንዲቆም ተወስኗል።

በተመሳሳይ አዲስ ማለዳ ከአዲስ አበባ ወደ ወሎ እንዲሁም ወደ ደሴ የሚጓዙ ሰዎች መንገድ ላይ በታጣቂዎች ጥቃት እየተፈጸመባቸው መሆኑን የደረሷት ጥቆማዎች ያመላክታሉ።

ጠንካራ የህግ ማስከበር ኦፕሬሽን ስራ እየተሰራ...https://addismaleda.com/archives/36217
———
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየት እና የሚዲያ ሽፋን ጥቆማ ለማድረስ
የአዲስ ማለዳ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይቀላቀሉ፤ ለሌሎችም ያጋሩ!
Telegram | Facebook | YouTube | X | www.addismaleda.com | 0961414141

2 months, 3 weeks ago

https://www.youtube.com/watch?v=C5Ph2CUeaoE

YouTube

ኦሮሚያ ክልል“የጦር ወንጀል”ተፈጽሟል? | #ethiopia #ethiopian #ethiopianews #addisababa #ዜና #ኢትዮጵያ

#ethiopia #ethiopian #ethiopianews #addisababa #ዜና #ኢትዮጵያ አዲስ ማለዳ ወቅታዊ የኢትዮጵያን ጉዳዮች በስፋትና በጥልቀት የምትተነትን፣ እንዲሁም የተረጋገጡና የትም ያልተሰሙ ዜናዎች የሚቀርቡባት የብዙኃን መገናኛ ናት። በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሚዲያ ባለስልጣን በመዝገብ ቁጥር 241/2010 ተመዝግባለች። የአዲስ ማለዳን መረጃዎችን በየዕለቱ ለመከታተል…

4 months, 4 weeks ago
[#ማስታወቂያ](?q=%23%E1%88%9B%E1%88%B5%E1%89%B3%E1%8B%88%E1%89%82%E1%8B%AB)

#ማስታወቂያ
#Advertisement

Caption: 6ኛው የኢቲ ሪል እስቴት እና የቤት ዕቃ አቅራቢዎች ኤግዚብሽን 10 ቀናት ብቻ ቀሩት፤ በታህሳስ 20 እና 21፣ 2016 በስካይ ላይት ሆቴል በተዘጋጀው ኤግዚብሽን ላይ በቦታው ላይ በመገኘት ልዩ ቅናሾችን በመጠቀም የቤት ባለቤት የመሆን እድሎን ይጠቀሙ:: የሁሉንም ፍላጎት የሚያሟላ ዝግጅቱን አሰናድቶ የሚጠብቀው እርስዎን ነው። ይምጡና ይጎብኙን፡፡ እንዳያመልጥዎ! ለበለጠ መረጃ በ ስልክ ቁጥር +251938036993 ይደውሉ ወይም ✉️ በ etrealestate@251communications.com ይፃፉልን::

#Ethiopia #AddisAbaba #realestate #realestatetips #realestateagency #realestateinvesting #realestateinvestment #homeexpert #homeexpo #homefurniture #furniture #furnituredesign #HomeImprovement #villas #apartments #luxuryapartmentliving #construction #constructioncompany #homeaccessories #banks #mortgage #diaspora #expats #expatsinaddis #expo #exhibition #Remittance

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 5 days ago

Last updated 2 weeks, 5 days ago