Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

Description
ዜና ከምንጩ
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

5 days, 12 hours ago

የአዲስ ማለዳ የሳምንቱ አንኳር ዜናዎች

እሁድ ሚያዝያ 20 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ)

  1. አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ  "እብደት በሕብረት" የተሰኘ የአንድ ሰው ቴአትሩን ለማሳየት ወደ እስራኤል አገር ሊጓዝ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች መያዙ ተገለጸ፡፡

2.የህወሓት እና የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ባደረጉት ውይይት "ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነው" ሲል ድርጅቱ ባሰራጨው መግለጫ ማስተባበሉን እንዲሁም (ህወሓት) ከብልጽግና ፓርቲ ጋር "ለመቀላልቀል" ውይይት አላደረግኩም ማለቱን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

3.በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ከሚገኙት አላማጣ እና ሌሎችም ግጭት የተከሰተባቸው አካባቢዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ወረዳ አጎራባች እና በዋግ ኽምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ መሸሻቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።የተፈናቃዮች ቁጥር ከአንድ ሳምንት በፊት ሚያዝያ 8 ቀን ከተመዘገበውም “በሶስት እጥፍ ጨምሯል” ሲል የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ገልጿል።

4.ዲላ ዩኒቨርሲቲ እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በቅጥር ግቢያቸው ውስጥ ለተማሪዎች በተለጠፈ ማስታወቂያ “እንደአገር ባጋጠመን የምግብ በጀት እጥረት” እና “የምግብ ጥሬ ዕቃ ዋጋ በየቀኑ መጨመር” ሳቢያ የምግብ ዓይነቶች እንደሚቀየሩ በማስታወቂያ መግለጻቸውን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል፡፡ ዝርዝሩን https://addismaleda.com/archives/36490

5.የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትጥቅና ሰላማዊ ባልሆነ መንገድ የሚታገሉ አካላት ጉዳት ሳይደርስባቸው በምክክር ሂደቱ እንዲሳተፉ እንደሚደረግ አስታወቀ፡፡

6.ከየመን የባህር ዳርቻ ልዩ ስሙ 'አራ' የተባለ ስፍራ 77 ኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ ጅቡቲ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ በመገለብጧ 23 ኢትዮጵያዉያን መሞታቸውን እና 23 ሰዎች የገቡበት አለመታወቁ ተገለጻል።

7.አሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጃፓን እና ጣሊያን፣ የትግራይ እና አማራ ክልሎች በሚወዛገቡባቸው አካባቢዎች ሰሞኑን የተፈጠረው ውጥረት እንዳሳሰባቸው ሰሞኑን በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

8.የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ለኮሪደር ልማት ሲል ያፈረሳቸውን ሠፈሮች ጨምሮ በ250 በላይ ቦታዎች ላይ የሊዝ ጨረታ ማውጣቱን ዋዜማ ዘግባለች።

9.አብን በሚያዚያ 14 ምሽት ባወጣው መግለጫ ሕወሃት በአማራ ሕዝብ ላይ ሌላ ዙር የጦርነት ጉሰማ ሲጀምር መንግሥት የሚያሳየው የሃላፊነትና የግልጽነት ጉድለት አገሪቱ ወደባሰ ችግር ውስጥ እንድትገባ ግንባር ቀደም አስተዋጽዖ አድርጓል በማለት ከሷል።

10.የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሰሞኑን መነጋገሪያ የሆነውን ተንቀሳቃሽ ምስል አመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ በቤተ ክርስቲያን በዓል ላይ የተቋሙን ደንብ ልብስ የለበሰ አባል ሲዘምር እና በህዝብ ፊት ሲተኩስ በመታየቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቋል።

11.ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከተመካከረ በኋላ ባወጣው መግለጫ “በስምምነቱ መሠረት የህሐት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት አለባቸው” ብሎ “የማንነት እና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች ጉዳይ እልባት ለመስጠት እንዲቻል የተቀመጠው አቅጣጫ ተግባራዊ መደረግ አለበት” ሲል አስታውቋል።ዝርዝሩን https://addismaleda.com/archives/36504

12.ኢትዮጵያ ውስጥ የትጥቅ ትግል እያደረገ የሚገኘው እና በአገሪቱ ፓርላማ “አሸባሪ” ተብሎ የተፈረጀው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሠ) በሚያዚያ 16 ይፋዊ የኤክስ ገጽ የብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት ለአገሪቱ ስብራት ያስቀመጣቸው መፍትሔዎች በሙሉ በገዢው ፓርቲ ነው ሲል አስታውቋል።

13.ምርጫ ቦርድ ስድስተኛው ዙር አገር ዓቀፍ ምርጫ ባልተካሄደባቸውና ድጋሚ ምርጫ በሚካሄድባቸው በአፋር፤ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ሶማሌና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ሰኔ 9 ለሚያካሄደው ምርጫ የጊዜ ሰሌዳዎችን አውጥቷል።

14.የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ የመንገድ ኮሪደር ልማት ሳቢያ ከሠፈራቸው ለተነሱ ከ4 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ካሳ እንደተከፈላቸው በሚያዚያ 18 ለከተማዋ ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት ተናግረዋል።እስካሁን 5 ሺህ 135 ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው እንደተነሱና ወደ ሌላ ቦታ እንደተዛወሩ ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል።

15.በኢትዮጵያ የተጠለሉ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር ከ1 ሚሊዮን 59 ሺ በላይ መሻገሩን የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ገልጻል፡፡ባለፈው አንድ ወር ብቻ ከ100 ሺህ በላይ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡና የሱዳናዊያን ስደተኞች ብዛት ብቻ ከ52 ሺህ 600 በላይ መድረሱን ኮሚሽኑ ጠቁሟል፡፡

16.በደቡብ ኢትዮጵያን በዎላይታ ዞን የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ መዘግየት እና ያለመከፈል የተመለከቱ  አቤቱታዎችን በማጣራት ሰራተኞቹ ችግር ላይ መሆናቸውን አረጋግጫለው ሲል የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

17.የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔ ለ2016 ዓመት የሚውል 21 ነጥብ 74 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አስትድቋል። ከጸደቀው ተጨማሪ በጀት ውስጥ 909 ሚሊዮን ብር ለመደበኛ እንዲሁም 20 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ለካፒታል በጀት የሚውል መሆኑ ተገልጿል።

18.ሚንስትሮች ምክር ቤት በሚያዚያ 17 ባካሄደው ስብሰባ በወጪ ንግድ ላይ የቀረጥ ማበረታቻ ሥርዓት የሚደነግግ ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ አጽድቋል።

19.ሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ)“ቦርዱ የፓርቲው ውስጠ-ጉዳይ ላይ ጠልቃ በመግባት” እንዲሁም ከፓርቲው ከተሰናበቱት የቀድሞ አባላት ጋር በማበር የሀገሪቱ ህግና የኢፌዴሪ ህገመንግስት በተፃረረ መልኩ የተለያዩ “ህገወጥና አደገኛ ውሳኔ” በማስተላለፋቸው በማለት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በፓርቲው የቀድሞ አባላት ላይ ክስ መስርቷል፡፡ዝርዝሩን https://addismaleda.com/archives/36508

20.የትግራዩ ተቃዋሚ ሳልሳዊ ወያነ በኢትዮጵያ የሚገኙ የሰባት አገራት ኢምባሲዎች የትግራይን ግዛቶች "አወዛጋቢ ቦታዎች" በሚል ቃል መግለጣቸውን ኮንኗል። ፓርቲው "አወዛጋቢ" የተባሉት አካባቢዎች "በኃይል የተያዙ የትግራይ ግዛቶች እንጅ ውዝግብ የተነሳባቸው አይደሉም" ብሏል።

5 days, 12 hours ago
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
6 days, 16 hours ago
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
2 months, 1 week ago
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
2 months, 1 week ago
**ከአዲስ አበባ - ደሴ የሚገኘው መንገድ …

**ከአዲስ አበባ - ደሴ የሚገኘው መንገድ “ላልተወሰነ ጊዜ” ተዘገቷል

ቅዳሜ የካቲት 16 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ)** ከአዲስ አበባ - ደሴ በሚገኘው አውራ ጎዳና ከዛሬ የካቲት 16 ቀን 2016 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሰውና የንብረት እንቅስቃሴ እገዳ እንደተጣለ አዲስ ማለዳ ከማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም ከደሴ - ሸዋሮቢት_ ደብረ ብርሃን እንዲሁም ከደብረ ብርሃን -ሸዋሮቢት - ደሴ የሚደረግ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ለጊዜው እንዲቆም ተወስኗል።

በተመሳሳይ አዲስ ማለዳ ከአዲስ አበባ ወደ ወሎ እንዲሁም ወደ ደሴ የሚጓዙ ሰዎች መንገድ ላይ በታጣቂዎች ጥቃት እየተፈጸመባቸው መሆኑን የደረሷት ጥቆማዎች ያመላክታሉ።

ጠንካራ የህግ ማስከበር ኦፕሬሽን ስራ እየተሰራ...https://addismaleda.com/archives/36217
———
ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየት እና የሚዲያ ሽፋን ጥቆማ ለማድረስ
የአዲስ ማለዳ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይቀላቀሉ፤ ለሌሎችም ያጋሩ!
Telegram | Facebook | YouTube | X | www.addismaleda.com | 0961414141

2 months, 1 week ago

https://www.youtube.com/watch?v=C5Ph2CUeaoE

YouTube

ኦሮሚያ ክልል“የጦር ወንጀል”ተፈጽሟል? | #ethiopia #ethiopian #ethiopianews #addisababa #ዜና #ኢትዮጵያ

#ethiopia #ethiopian #ethiopianews #addisababa #ዜና #ኢትዮጵያ አዲስ ማለዳ ወቅታዊ የኢትዮጵያን ጉዳዮች በስፋትና በጥልቀት የምትተነትን፣ እንዲሁም የተረጋገጡና የትም ያልተሰሙ ዜናዎች የሚቀርቡባት የብዙኃን መገናኛ ናት። በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሚዲያ ባለስልጣን በመዝገብ ቁጥር 241/2010 ተመዝግባለች። የአዲስ ማለዳን መረጃዎችን በየዕለቱ ለመከታተል…

4 months, 2 weeks ago
[#ማስታወቂያ](?q=%23%E1%88%9B%E1%88%B5%E1%89%B3%E1%8B%88%E1%89%82%E1%8B%AB)

#ማስታወቂያ
#Advertisement

Caption: 6ኛው የኢቲ ሪል እስቴት እና የቤት ዕቃ አቅራቢዎች ኤግዚብሽን 10 ቀናት ብቻ ቀሩት፤ በታህሳስ 20 እና 21፣ 2016 በስካይ ላይት ሆቴል በተዘጋጀው ኤግዚብሽን ላይ በቦታው ላይ በመገኘት ልዩ ቅናሾችን በመጠቀም የቤት ባለቤት የመሆን እድሎን ይጠቀሙ:: የሁሉንም ፍላጎት የሚያሟላ ዝግጅቱን አሰናድቶ የሚጠብቀው እርስዎን ነው። ይምጡና ይጎብኙን፡፡ እንዳያመልጥዎ! ለበለጠ መረጃ በ ስልክ ቁጥር +251938036993 ይደውሉ ወይም ✉️ በ etrealestate@251communications.com ይፃፉልን::

#Ethiopia #AddisAbaba #realestate #realestatetips #realestateagency #realestateinvesting #realestateinvestment #homeexpert #homeexpo #homefurniture #furniture #furnituredesign #HomeImprovement #villas #apartments #luxuryapartmentliving #construction #constructioncompany #homeaccessories #banks #mortgage #diaspora #expats #expatsinaddis #expo #exhibition #Remittance

4 months, 2 weeks ago
4 months, 2 weeks ago

“ፌሽታ” የተሰኘ የሕፃናትና የወጣቶች ፌስቲቫል በቀጣይ ሳምንት ሊካሄድ ነው
አርብ ታህሳስ 5 ቀን 2016(አዲሰ ማለዳ) የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ፌሽታ የተሰኘ የሕፃናትና ወጣቶች ፌስቲቫል በመጪው ታህሳስ 13 እና 14 ቀን 2016 በኤቫ ሌግዠሪ ሰርፕራይዝ ፕላነር አዘጋጅነት ሊካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

በጊዮን ሆቴል በሚካሄደው በዚህ ፌስቲቫል ላይ ከ5 ሺሕ በላይ ህጻናት ይገኙበታልም ነው የተባለው።

በመርሐግብሩ ላይ የሕፃናት እና ወጣቶች ዕቃ አስመጪና አቅራቢዎች ፣ የስጦታ ዕቃ አስመጪና ሻጮች፣ ምግብና መጠጥ አቅራቢዎች ፣ የመዝናኛ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ተቋማት በዝግጅቱ ላይ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።

በዕለቱ መግቢያው 250 ብር ሲሆን ቲኬቱን ከነገ ታህሳስ 6 2016 ጀምሮ በቴሌብር ላይ እንደሚሸጥ ተገልጿል።
___
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA

Telegram

Addis Maleda - አዲስ ማለዳ

ዜና ከምንጩ

**“ፌሽታ” የተሰኘ የሕፃናትና የወጣቶች ፌስቲቫል በቀጣይ ሳምንት ሊካሄድ ነው**
4 months, 2 weeks ago
Addis Maleda - አዲስ ማለዳ
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas