Prip➠Official3

Description
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago

hace 3 meses, 1 semana

ብቸኝነት ይሰማኛል። ብቻ ድብርታም ነገር ነኝ እና አባ እየጠራኝ ነው በቃ ሰአታችን ደረሰ አንተም ስልክ አላነሳህም ማስታወሻዬን ላንተ ሳላደረስ መሞት አልፈልግም ወይ የምድንበት መንገድ ከተገኘ በጣም ደስስ ይለኛል። ባይሆንም ፈጣሬን አላማረውም" ዕዝራ ሁለተኛውን ገፅም ጨረሰ። እና ከደነው የሲማይን ስእል ሳመው ደጋግሞ ሳመውና ማታወሻውን  ከትራሱ ስር አረገው እና ተኛ። እንቅልፍ ወዲያው ነበር የወሰደው ወዲያውም ቅዠት ጀመረው።

፨ ከሲማይ ጋር በፍቅር ክንፍፍ እያለ የምታምር ልጅ ይዘው ልጅትዋን እያፈራረቁ ሲስሞት ነበር የያየው። በጣም ደስስ ብሎታል የእውነት አለም ውስጥ ያለ መስለው። በእዛ ደስታ መሀል ግን ነጭ ልብስ የለበሰች ሲማይን መሳይ ሴት መጣችና ሲማይን እና ህፃንዋን ይዛቸው ሄደች። ዕዝራ "አይሆንም አትውሰጃቸው ስለፈጠረሽ አምላክ ተያቸው ተያቸው እያልኩሽ ነው ተይ ተይ ተይይይይይይተይይይይይይይይይይይይ
ብንን ብሎ ባነነ። ከባነነ በኋላ "አይይይ
ልትወስጃቸው አትችይም የትኛዋ ነሽሽሽ ወሳጅዋ ወይስ ተወሳጅዋ ለምን አተይኝም ተይኝ አይ አይ በጭራሽ ግን አትተይኝ ሲማይ አታገላችኝ እባክሽን" እያለ ሲጮህ አባቱ ለዶክተሩ ደወሎ "ልጄ አበደ  በለሊት ሲጮህ ይህ ሁለተኛ ቀኑ ነው በቃ ልጄ ለየለት" አሉ። ዶክተሩ የዕዝራ አባትን "በሉ ተረጋጉ መጀመሪያ ምን ተፈጥሮ ነው"አሉት። የዕዝራ አባት ስልካቸውን ወደ ዕዝራ መኝታ ቤት ይዘው ሄደው ዕዝራ የሚለውን አስሙት።
       ፨ ዶክተሩም "ዕዝራ ወደ እራሱ ለመመለስ እየታገለ ነው። አይፍሩ በቃ አሁን ወደ አልገመዎት ሄደው ይተኑ። ዕዝራ የሀይምሮ እክል እንደገጠመው ሁላችንም እናውቃለን አላቸው። "እሺ " ብለው አልጋቸው ላይ ሄደው ጋደም ከማለታቸው። የሆነ መስታወት ፎጭ ብሎ ሲከሰከስ ሰሙ። የዕዝራ አባት ወደ ዕዝራ ለመሄድ ሲሮጡ ደረጃው አንሸራቷቸው ተንከባለው ወደቁ።

ክፍል 12
ይቀጥላል........

hace 3 meses, 1 semana

ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ

ሳልሳዊ
ክፍል። 11

፨ የሲማይን ስእል ሲያቅፈው ሲማይን ያቀፉት ነበር የመሰለው። ውሰጡ በሀሴት ተሞላ የሆነ አይነት ደስታ ሳያስበው ወረሰው። ዕዝራ በድንገት ነው ፍክት ያለው ይህ ህይወት ለዕዝራ ከስር ከስር ደስታ ከስር ከስር ሀዘን መስማቱ ህሌናው ምን ያክል እንደተጎዳ ያስብቃል። ዕዝራ ሲማይ አጠገብ ያለች የመስለውን ስሜት መፋቅ አይፈልግም የሲማይን ስዕል እየዳበሰ አይኑን ጭፋን አረጎ "ሲማይዬ የኔ ልእልት ካላንቺ ሁሉም ነገር ከባድ ነው አንዳንዴ ታቂያለሽ አንቺን የማግኘት ፈላጎቴ ሲንረ እና ሳጣሽ ሁሌም ያመኛል" አለና ዝም አለ እንባው በጨፈናቸው አይኖቹ ፈሰሱ። ለደቂቃዎች ከቆየ በኋላ ተነስቶ ወኔ እና ቅጥልጥል የሆነ ስሜት ውስጥ ሆኖ "ከእዚህ በኋላ ግን አንቺ እንደፈለግሽው ህይወቴን እቀጥላለሁ ያልሽኝን ነው የማረገው አለ።
ተነስቶም ወደ ሳሎን ሄደ። ዶክተር ፣ አስሚ እና አባቱ ሳሎን ቁጭ ብለው እያወሩ ነው። ዕዝራ አብሯቸው ቁጭ አለ። ሶስቱም የዕዝራ ሁኒታ ግራ ተጋበተዋል። ዶክተሩ ግን ግራ ከመጋባቱ በዘለለ የዕዝራ ሁኔታ ወደ ማንነቱ ለመመለስ በሚሞክረበት ጊዜ የተፈጠረ መሆኑ በጥቂቱም የገባው ይመስላል። ዶክተሩ "እእ ዕዝራ ዛሬ ወደ ሲማይ መሄድ ትፈልጋለህ?" አለው። ዕዝራ "አዎ ምን ጥያቄ አለው እሷን ለማየት ሁሌም ዝግጁ ነኝ ከፈላጎት ጋር " አለ። አስሚም "ጥሩ እኔም አብሬያቹ ብሄድ ደስ ይለኛል" አለች። ዶክተሩ "እሺ በቃ የዕዝራ አባት እዝህ መቆየት ይችላሉ እኔ ዕዝራን ወስጄ እመልሰዋለሁ መኪናዬ ውጪ አለች።" ሲል የዕዝራ አባት "ጥሩ በቃ በጊዜ ተመለሱ" አሏቸው።
         ፨አሁን ከእረዥም ጉዟ በኋላ የሲማይ መቃብር ጋር ደረሰዋል። ዕዝራ ሲማይ መቃብር ጋር ተንበረክኮ "ልእልቴ ያስቀመጥሽልኝን ማስታወሻ እያነብኩት ነው። ቆይ አንቺ ለምን የማይመስል ነገር ታወሪያለሽ አለሽ አንቺ ሁሌም አለሽ ውስጤ ምን ያህል ጊዜ በተስፈ ልጠብቅሽ እንደሆነ ልትፈትኚኝ እንደሆነ ይሰማኛል" አለ። ዶክተሩ ወደ አስሚ ጆሮ ጠጋ ብሎ "እሱ እስኪጨረስ ወደ መኪናው እንሂድ የምነግረሽ ነገር አለ" አላት። አስሚ ግራ እየገባት "እሺ" ብላ ተከታትለው ወደ መኪናው ሄዱ።
        ፨ ዶክተሩ ከአስሚ ጋር መኪና ውስጥ ገባና።  "እእእ አስሚ የሆነ ነገር ልጠይቅሽ ነው እኔ ቃላትን ለእራሴ ህይወት ሲሆን አመቻችቼ መናገር አልችልም ኡፍፍፍፍ" አለ። አስሚ ሳቅዋ እየተናነቃት አንገቷን ደፈታ "ምነው የሆንከው ነገር አለ ዶክተር አለችው" ዶክተሩም "ዶክተር ብለሽ አትጥሬኝ በፈጠረሽ" አላት። አስሚ በድጋሜ አንገቷን ደፈታ ሳቅ እየተናነቃት "እሺ ምን ልበልህ ዶክተር?" ስትለው ዶክተሩ "ፈጣሪዬ ኧረ ምን ይሻለኛል እየሳቅሽብኝ ነው አደል እስቲ ቀና በይና እይኝ" አላት። አስሚም ከሳቅዋ መለስ ብላ ቀና አለችና
ዶክተሩን አየችው ዶክተሩም "ቆይ ለምን ዶክተር ትይኛለሽ" አላት። አስሚም "እንዴ ዶክተር ስለሆንክ ነዋ" አለችው። ሳቋ ጮፍ ደረሷል። ዶክተረም "አዎ አቃለሁ ዶክተር ነኝ ኡፍፍፍ እሺ ከእዚህ በኋላ በስሜ ጥሪኝ" ሲላት አስሚ "እንዴ ዶክተር እሺ ስምህ ማነው" አለችው። ዶክተሩ እረረ ብሎ " አኪም " አላት። አስሚ የተቆጣጠረችው ሳቅ ፈንድቶ አመለጣትና እየሳቀች "እና ዶክተር እና አኪም ምንድነው ልዩነቱ" አለችው። ዶክተሩ "አስሚ ስሜ ሀኪም ሳይሆን አኪም ነው" አላት። አስሚ ሳቋን ማቆም አቃታት እንባ በእንባ እየሆነች እና እንባዋን እየጠረገች "እሺ ዋናው ሀሳብህ ምንድነው?" ሰትለው። "ዋናው ሀሳቤማ" ብሎ የስሚን ከንፈረ በንፈስ ፈጥነት ከከንፈሩ ለጠፈው  አስሚ ደነገጠችም ደስም አላት። አይኑዋን በስሱ ጭፍን አረገችው። እና እሷም መልሳ ሳመችው።
           ፨ዶክተሩ በቀስታ ወደ አስሚ ጆሮ ጠጋ ብሎ ከእዚህ የዘለለ ነበር አላት" አስሚ "ማለት?" አለችው። ዶክተሩ አስሚን አቀፈትና "አስሚ አፈቀረኩሽ አንዳፈቀረሽኝ አቃለው ላገባሽ እና አብሬሽ ልኖርም እፈልጋለሁ አስሚ  አፈቅርሻለሁ" አላት። አስሚ "እኔም ካንተ ይምጣ ብዬ እንጂ በጣም አፈቅርሀለው ብላ አጥብቃ አቀፈችው" አስሚ በድንገት ወይኔ "ዕዝራስ ግን" አለች። ከመኪናው ወረደው
ወደ ዕዝራ ሄዱ። ዕዝራ ግን የለም  ደነገጡ መቃብር ቦታዎቹን ሁሉ ዕዝራን እየጠሩ መፈለግ ጀመሩ።
          ፨የመቃብር ቆፋሪዎቹን ሲጠይቁ የዕዝራን ምልክት ሲነግሯቸው አንደኛው "እእ የሆነ ቀይ ቆንጆ ልጅ ወደ ፊት እየሳቀ ቆይ አትሂጂ ጠብቂኝ እንጂ" እያለ  እየሮጠ እንዳየው ነገራቸው። ዶክተሩ እና አስሚ እስከማታ ዕዝራን መቃብሩ ቦታን አስሰው ቢፈልጉትም ሊያገኑት አልቻሉል ዕዝራ ቢሉም አሜት የሚላቸው ሰው አጡ። ቀኑ እየመሸ ሲሄድ የዕዝራ አባት ለአስሚ እና ለዶክተሩ መደወል ጀመሩ ማናቸውም ማንሳት አልቻሉም። እያለ እያለ ሰአቱ ሄደ ከምሽቱ ሶስት ሰአት ሆነ። የሲማይ መቃብር ጋር ቁጭ ብለው ጠበቁ ዕዝራን ሊያገኑት ግን አልቻሉም። አስሚም አሚር በቃ የግድ ለአባቱ ማሳወቅ አብን ያለ በዝያ አማራጭ የለንም ስትል። ዕዝራ "አዎ እኔን ከማመን ውጪ አማራጭ የላችሁም" አለ። አስሚ እና ዶክተር ደንግጠው ዞር ሲሉ ዕዝራ ፊቱ ጭው ብሎ አዩት። አስሚ "ዕዝራ የት ነበረክ ሰትለው እራሱን ስቶ ወደቀ። ተደናግጠው ወዲያው ወደ ሀኪም ቤት ወሰዱት። ከ3ቀናት በኋላ ዕዝራ ተሻለውና ቤት ገባ።
          ፨ከዛን ቀን ጀምሮ ዕዝራ ሰው ፊት ወደ እራሱ የተመለሰ ለመምሰል መታገል ጀመረ ግን አልቻለበትም።  እንደውም ሲማይ ህይወቱ ውስጥ ሳይሆን ልቡ ውስጥ ብቻ እንዳለች ሲያስበው አሳበደው ሲማይ በጣም ስትናፈቀው የፃፈችለትን ገልጦ ባለፈው ካቆመበት ለማንበብ ወዳስቀመጠበት እጁን ሰዶ አወጣው። ገለጠው ሁለተኛው ቀን ላይ የፃፈችው ማስታወሻ ነው ማንበብን ቀጠለ። "ዕዝሬ ስምህን ስፅፈው ከአንደበቴ ሳወጣው ልቤ በደስታ እየጨፈረች እንደሆነ ታቃለህ ዕዝሬ ፍቅሬን ልገልፅልህ አልችልም ሰው ማፈቀር ማለት ደሞ የግዴታ ያፈቀሩት ሰው መሆን ሳይሆን በአፈቀሩት ልብ ውስጥ መኖረም ነው። እኔ አልቆልኛል አንተ ግን ዕዝረዬ ገና ብዙ ነገር ይጠበቅብሀል እየውልህ ዕዝሬ ወደፊት የምታገባት ሴት ካስከፋችህ ግን አለቃትም እየውልህ መቃብር ፈንቅዬም ቢሆን ተነስቼ ልኳን ነው እማሳያት ግን አንተን አግኝታ መላክ የማትሆን ሴት አለች? ዕዝሬ ደግሜ ደጋግሜ ብፈጠረ እና የተፈጠረኩበት አለም ላይ ሁሌም አንተ ብትኖር ሁሌም አንተን ደግሜ ደጋግሜ ባፈቅርህ አይቆጨኝም ፈጣሪ ሁሌም ልክ እንዳንተ ለአንድ ስከንድም ቢሆን አፋቃሪ ቢገኝ ትልቅ ሽልማት ነው። ውይ ዕዝሬ ብታይ ዛሬ በረራ አለኝ ደውዬልህ ስልክም አታነሳም
ለምን ወዴት ልትሄጂ ነው ካልከኝ የተፈጠረውን ለአባቴ ስነግረው እኔ ጋር ነይና የመጨረሻ እድል ሞክሬ አለኝ። ዕዝሬ አንተን ሳላገኝ በፊት ቢሆን ይህንን ዜና የሰማውት ለህይወቴ ምንም ስለማልሳሳ ሞቴን ቁጭ ብዬ እጠብቅ ነበር ምክንያቱም አባ አጠገቤ ስላልሆነ

hace 3 meses, 1 semana

እቀጥልልሀለው ይላል።

፨ ዕዝራ ቀጣዩን ማንበብ ጀመረ። "ዕዝሬ ተመልሻለሁ እሄድበታለሁ ያልኩክ ቦታ እኮ ሄድኩ። ዕዝረዬ ምን ልበልህ ምን አባቴ እንደምልህ ጭንቅ አለኝ እኮ ግን ያው መናገሬ ግድ ነው ይህንን ዜና ስሰማ እኔም ደንግጫለሁ ምን መስለህ ዕዝረዬ
በተደጋጋሚ ሲነስረኝ ለህክምና ስሄድ የምርመራዬ ውጤት ውጪ ተልኮ ደረሷል ተብዬ ሄጄ ነበር። ዕዝረዬ በቃ አልቆልኛል ልሞት ነው" ዕዝራ ፊቱ ቀላ አለቀሰ ደነገጠ ጥረሶቹን በሀይል እያንቀራጨጨ ማንበብን ቀጠለ "ያን ያክል የከፈ ነገር አልመሰለኝም ነበር በዛ ላይ ፍቅር ካንተ ሲይዘኝ ጥሩ ህይወት እንደምኞር ተሰምቶኝ ነበር ግን አልሆነም በቃ እኔ ሳታፈቅሬ አትሙቺ ፍቅረን አይተሽ ሳታጣጥሚው ሙቺ የተባልኩኝ ነኝ። መቀየር የማልችለው ፈተና ውስጥ ገባው። ዕዝሬ እኔ የደም ካንሰር ህመም ይዞኛል ምልክቱ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ስላሳየ ከፈጣሪ በቀረ አዳኝ የለኝም። አንተ ግን ጠንካራ ሁን እሺ ሁሌም እየመጣህ ጠይቀኝ ምክያቱም ዕዝሬ ትናፈቀኛለህ። " የሲማይ እንባ ወረቀቱ ላይ አረፎ ከለሩን አልፎ አልፎ ቀይሮታል አሁን ደሞ የዕዝራ እንባም ወረቀቱ ላይ እየዘነበ ነው።
          ፨ ዕዝራ ማንበቡንም ማልቀሱንም አላቆመም "ዕዝረዬ ምን ማለት እንዳለብኝ እራሱ እኮ ግራ ነው የገባኝ። እኔ ቅድም እንዳልኩክ ፈጣሪ ፍቅርን ሳታይ አትሙቺ ብሎኝ ነው። አንተን ግን ምን አልባት ዳግመኛ ፍቅር እንደሚይዝ  ሊያሳህ ይሆናል በእረግጠኝነት እንደዛ ነው። ህይወትህን ቀጥል እሺ ያለ በለዝያ በጣም እከፋብሀው እንድኩፋ ደሞ አትፈልግም አደል ስለዝህ የወደፊቷን ሚስትህን እስክታገኝ ብቻህን አንዳዴም ከአስሚ እና አባቴ ጋር እየመጣህ እየኝ ውስጤ ከአስሚ ጋር እንደምትቀራረብ ይነግኛል ጥሩ እህት ትሆንሀለች ደሞ አባቴን አደራ ዕዝረዬ" ይላል የመጀመሪያው ገፅ። ዕዝራ ሊላኛውን ገልፆ ለማንበብ ፈራም ፈለገም። ማስታወሻውን ከደነውና ክፍሉ ውስጥ ካለው የልብስ ማስቀሙጫ ቁም ሳጥን ከፈቶ ሲማይን የሳላት ስእል አውጥቶ መሬት ላይ ተንጋሎ  አቅፎ  ማልቀስ ጀመረ።

ክፍል 11
ይቀጥላል...

hace 3 meses, 1 semana

ደራሲ ቤዛዊት ፋንታዬ
ሳልሳዊ
ክፍል 10

፨የዕዝራ አባት ዕዝራን ሲያዩት በጣም እየሳቀ ነበር። "ልጄ ምነው ምን ተፈጥሮ ነው እንዲህ ፊትህ የበራው። አሉት። ዕዝራ "አባባ ሲማይ እዝህ ነበረች። ተኝቼ ነበር ከዛ ውሀ ጠምቶኝ ስነሳ ሲማይ ከጎኔ ተኝታ ነበር።" ዕዝራ ሲናገር ፊቱ ከመብራቱ ባሻገር በደስታ አፉ ተሳስሮም ይንቀገቀጥ ነበር። አባቱ "ልጄ ወደ እራስህ ተመለስ እንጂ ምን ነክቶሀል ሲማይ ሞታለች በቃ እመን እባክህ እመን" አሉት። ዕዝራም "እንዴ አባባ ታዲያ ከሞተች እዝህ ምን ትሰራለች" አለ አባቱን በፈገግታ እያያቻው። የዕዝራ አባትም "ልጄ ምን ነካክ ታዲያ እዝህ ከነበረችስ የታለች በቃ ተኛ ልጄ እባክክ ልለምንህ ወደ እራስህ ተመለስ።" ብለውት ወጡ።
        ፨ ከወራት በኋላ ዕዝራ ጠዋት ከእንቅፉ ተነስቶ ሻውር ወሰደ። ልብሱን በጥሩ ሁኒታ ለብሶ ወደ ሳሎን ሄዶ የምግብ ጠረጴዛው ላይ ተቀምጦል ቤቱ በዕዝራ ሽቶ ታጥኖል። ዕዝራ በእሱ ሾቶ የታወቀ ነው። አባትየው  ደረጃውን እየወረዱ የዕዝራ ሽቶ አፈጫቸውን አወዳቸው። ግራ ተጋብ ደረጃውን ወረደው ሲያዩ አይናቸውን ማመን ተሳናቸው ዕዝራ ዝንጥ ብሏል። ቲሸረቱን መብላቱ ኩስስ ማለቱ እና የሲማይን ስጦታ መያዙ እንዳለ ሆኖ። አባትየው ደስ አላቸው። በአንድ ለሊት እንዲ መለወጡ ሳሎን  የመቀመጡ ብቻ ሁሉም ነገር ገረሞቸው። አጠገቡ ቁጭ ብለው በግረምት እያዩት። "ልጄ ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው" ሲሉት ዕዝራም "አይ አባባ ዛሬ ሲማዬ በህልሜ መጥታ እንደ ድሮህ ሁን ብላኝ ነው ለእሷ ብዬ ነው" አለ። የለበሰውን ቲሸረት ወደ አፉ ለማስገባት እየሰደደ አንገቱን ድፍት አረጎ። አባቱ "እሺ ጥሩ ስለዚህ ዛሬ ቁርስ የምበላው ከልጄ ጋር ነዋ" አሉ። ዕዝራ ከሚበላው ቲሸረቱ አፉን አውጥቶ "አዎ አባባ ከእንግዲህ ሁሌም አብረን ነው የምንበላው" አላቸው። አባቱ ሁለት ስሜት ውስጥ ገቡ። ደስታ እና መደናገረ ውስጥ።
         ፨ቁረስ በልተው እንደጨረሱ ሰራተኛዋ ብና ለማፈላት ጉድ ጉድ ማለት ጀመረች። ዕዝራ አባቱን "አባባ" አለው። "አቤት ልጄ " አሉት። ወደ ሳፋው እየሄዱ። ዕዝራም ተከትሏቸው ወደ ሶፋው ሄደና አባቱ ባለ አንዱ ጋር ሲቀመጡ እሱ ባለ ሶስቱ መቀመጫ ላይ ተቀመጠ። የዕዝራ
አባት "ልጄ ምን ልጠይቀኝ ነበር?" ሲሉት ዕዝራ "እማማ የት ነው ያለችው አትመጣም እንዴ" አላቸው። የዕዝራ አባት ፈገግ ብለው "እናትህ ትመጣለች " ሲሉት። ዕዝራ "ኡፍፍፍፍፍ" አለ። የዕዝራ አባት "ምነው ልጄ?" ሲሉት። "አይ አባባ ይህንን ጥያቄ ስጠይቅህ ልክ እንደ ሲማይ እማማንም ላሳህ ብለህ ይዘከኝ እንዳትሄድ ፈረቼ ነበር። እማማ ወደ እኛ ከመጣች እንደ ሲማይ   .." አለና ዝም አለ። አባቱ "እንደ ሲማይ ምን ልጄ " ሲሉት። ዕዝራ "አይ ምንም አባባ እማማን ጥራልኝ ትምጣ" አላቸው። እንዲህ እያወሩ ቡና መቆላት ሲጀምር  ዶክተር እና አስሚ "እንዴት አረዳቹ" እያሉ ተከታትለው ገብ። ሁለቱም የዕዝራን ሳሎን መገኘት እንደ ታምር ስላዩት ደነገጡ። ደሞም ታምር ነው እንጂ!።
          ፨ብና እየጠጡ በመሀል ዝም እያሉ። አስሚ እና ዶክተሩ እየተያዩ እየተሽኮለመሙ። ዕዝራ ቲሸረቱን እያኘከ በመሀል የሲማይን ስጣታ በስስት እየሳመ እና እጆቹን እያፋተገ ነው። የዕዝራ አባት እና ሰራተኛዋም የዕዝራን ሁሌታ እና የዶክተሩን እና የአሚን ትይንት እያዩ ብናው ተፈልቶ አለቀ።
         ፨ዶክተሩ ከእዝህ መሀል የዕዝራን አባት "ጋሼ አንዴ ውጪ ላዋሮት እችላለሁ" አላቸው።  "እሺ " ብለው ተያይዘው ውጡ። ከወጡ በኋላ የዕዝራ አባት "ዶክተር ምንነው ችግር አለ?" አሉ።
ዶክተሩም "አይ ምንም የተለየ ነገር የለም እኔም እረሶም የሲማይን ማስታወሻ አንብበነዋል በተጨማሪም ከእኔ በተሻሉ ሳይካትሪስቶች እስካሁን ሳስገመግመው ነበር። ዕዝራ ማስታወሻውን ካነበበ ጥሩ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል" አላቸው። የዕዝራ አባትም "ባረገልኝ እና እናቱም ከጎናችን በሆነችልን በነገራችን ላይ ዛሬ እማማ የት ናት ብሎ ጠይቆኝ ነበር ከአጠያየቁ ግን እናቱ ሞተች ተብሎ እንዳይነገረው የፈራ ይመስላል" ሲሉ። ዶክተሩ "ይህ ጥሩ ዜና ነው ይህ ማለት እኮ ዕዝራ በዙሪያው የሊለውን ነገር ማገናዘብ ጀምሯል ማለት ነው ለማንኛውም የሀይምሮ ህመም በጣም ውስብስብ ነው እናቱን ይዘውለት ይምጡ። በተረፈ እኔ ዛሬ የሲማይን ማስታወሻ በሲስተም እንዲያነበው እሰጠዋለሁ ሲማይ ብልህ ሴት ነበረች ማስታወሻዋን በሚገረም የሀይምሮ ግንባታ ላይ ተመረኩዛ ነው የፆፈችው በቃ አሁን እንግባ ያልኮትን ያረጉ።" አላቸውና በበሩ መስታወት በኩል ዶክተሩ አስሚ እና ዕዝራ እያወሩ አያቸውና። "የዕዝራ አባት ኑ ተመልከቱ" አላቸው። ጠጋ ብለው መመልከት ጀመሩ።
         ፨ዕዝራ እያወራ አስሚ ደሞ እያዳመጠችው ነበር። አንገቱን ድፍት አረጎ ባንደኛው እጁ የሲማይን ስጦታ በሊላኛው ደሞ ቲሸረቱን ወደ አፉ አስጠግቶ በወሬው መሀል በእልህ ያኝከዋል ቆየት እያለ የሲማይን ስጣታ አስቀምጦ መዳፎቹን ያፋትጋቸዋል።
ከዛም ደሞ የሲማይን ስጣታ አንስቶ በስስት ይስመዋል። የዕዝራ አባት "ስለ ምን ይሆን የሚነግራት ያው ስለ ሲማይ ነው።  ግን ምን ይሆን" አሉ። ዶክተሩም
"ገብተን እኛም እንስማ" ብሎ እጁን ወደ ሳሎኑ በረ ጠቆማቸው። ተከታትለው ገብ። ዕዝራ ማውራቱን አላቆመም ነበር። የዕዝራ አባት እና ዶክተሩ የዕዝራን ንግግር በደረሱበት በእየ ቦታቸው ተቀምጠው መስማት ጀምረዋል። ዕዝራ
እጆቹን እያፋተገ እያወራ ነው።  "ሲማይ ዛሬ በጣም የሚያምር ነጭ ቀሚስ አረጋ በባዳ እግሯ  በህልሜ መጥታ እንዲህ ጭምት መሆን የለብህም እኔም አባትህም እናትህም ጓደኛዬ አስሚም ሆነ ዶክተሩ ላንተ ደህንነት እንጨነቃለን እኔም ሁሌም ከጎንህ ነኝ በጠዋት ተነስተክ እንደ ድሮህ ለመሆን ሞክር አለችኝ" አለ። እጆቹን በሀይልል እያፋተጋቸው ነው እግሮቹንም እንደዛው።
        ፨ ንግግሩን ሲጨረስ የሲማይን ስጣታ ይዞ ቲሸረቱን ማኘክ ቀጠለ። ዶክተሩም "ዕዝራ ሲማይ እንድታነበው የምትፈልገው አንድ ነገር አለ። ካላነበብከው ትከፈለች"። ብሎ ማስታወሻውን እና ወረቀቱን ሰጠው። ዕዝራም ቲሸረቱን ለቆ በፍጥነት ብድግ ብሎ ማስታወሻውን ምንጨቃ በሚመስል መልኩ ተቀበለው። ዶክተሩ ፈገግ አለ። ዕዝራም በፍጥነት ወደ መኝታ ቤቱ ገባ።
የሲማይን ስጦታ አጠገብ የአልጋው እግረጌ  ጋር አስቀመጠ ሲሸረቱን መብላቱንም አቆመ እና ትይሽዬዋን ወረቀት አላነበባትም በቀጥታ የአልጋው እግረጌ ጋር ተቀምጦ ማስታወሻውን ከፈተው። ዕዝራ ማንበብ ጀመረ። በቃላቶቹ ውስጥ የሲማይን ድምፅ ይሰማቸዋል። ከማስታወሻው ላይ ከተገናኑበት ቀን በነጋታው ያለው ቀን እስከ አመተ ምህረቱ እና ወሩ እንዲሁም ሰአቱ ተጠቅሷል "ዕዝረዬ ትናት ያሳለፋነው ቀን በህይወቴ ዳግመኛ ብፉጠረም የማሳልፈው አይመስለኝም ዕዝረዬ እስቲ ወዬዬዬ በለኝ" ዕዝራ ፈገግ ብሎ "ወዬዬዬ" አለ። "ታቃለህ አደል በጣም እንደምወድህ" ዕዝራ እያለቀሰ "አዎ እኔም በጣም አፈቅረሻለሁ" አለ። እና ማንበብን ቀጠለ "ይህንን ማስታወሻ የፃፈኩልህ ልክ እኔ እና አንተ ተለያይተን ወደየ ቤታችን እንደገባን ነው ምን ላረግ ዕዝረዬ አጠገብህ ስሆን እኮ ቃላቶቼ ሁሉ ይጠፉብኛል። ሰው እንዴት በአንድ ቀን እንዲህ ያለ ፍቅር ይይዘዋል። የኔ ፍቅር እንደማፈቅረህ ልነግረህ እችላለሁ ግን።! ብላ በቃ አሁን መሄድ ያብኝ ቦታ አለ። እሺ ስመለስ

hace 3 meses, 1 semana

?አለሜ ነሽ?

?ክፍል 14

✍️ደራሲ፦ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ

""
""
ምን መሰለሽ "በህይወትጉዞ ውስጥ የምታፈቅሪው ሰው አንድ ብቻ
ነው ፍቅር የፈጣሪ ስጦታ ነው ደስ የሚል ግዴታ ፈጣሪ
የህይወታችንን አጋር እንድናፈቅር ግዴታ አስተላልፎብናል ደስ
የሚል ግዴታ በእዚህ ግዴታ ውስጥ መናፈቅ፣ መጨነቅ ፣ማስብ
፣ማልቀስ፣ ማዘን በጣምም መደስት ፣በጣም ማዘን በፍቅር
ውስጥ የሁሉም ሰው ልብ ስስ ነው ። አንድ ሰው ብዙ ሰው
ይወዳል አንድ ሰው ያፈቅራል የሚወደውን መጥላት ይቻላል።
በመውደድ ውስጥ ሁለት ልቦች ሁለት ናቸው። በማፍቀር ውስጥ
ደሞ ሁለት ልቦች አንድ ናቸው።
ከምናፈቅርው ሰው ጋር የምንጣላውም፦ ለምን አልበላክም፤ ለምን
አልጠጣክም ፤ለምንስ ነው ብርድ ሆኖ ሳለ ጃኬት የማትደርበው
፤እየበላክ ከሆነ ቢያንቅህስ ለምን ውሀ አጠብክ አላስቀመጥክም
፤መንገድ ተጠንቅቀክ ሄድ ፤ ፍቅር ዛሬ እኔ ነኝ ምሳ የምጋብዝክ፤
ራስክን ጠብቅ ፤ሲሆን የሚወድሽ ሰው ደሞ ሲሆን፦ ለምንድን ነው
ይህንን ያልስራክልኝ፤ ለምድነው ምሳ የማትስጠኝ ፤ስበላ
ቢያንቀኝስ ለምድነው እንደ ሌላ ቀኑ የማትንከባከበኝ ነው
የሚለው። ሰው ሰውን ለመውደድ ምክንያት ይፈልጋል ጥቅም
ይፍልጋል ። ፍቅር ግን ከምክንያት የፀዳ ነው የሚወደን ሰው
እንዲወደን ያርገውን ነገር ሲያጣ ይርቀናል ከዛም አልፎ
ይጠላናል። ያፈቀርን ግን ያፈቀርን ያለ ምክንያት ስለሆነ በጭራሽ
አይጠላንም። ሰው ውስጣችን ሲገባ ፍቅር ይሁን መውደድ
የምናቀው እራሳችንን በማዳመጥ ነው።
ይህ ሰው ምኑ ነው የሳበኝ ብለሽ እራስሽን ስትጠይቂ የሳበሽን
ነገሮች መዘርዘር ከቻልሽ እሱ መውደድ ነው። ምክንያቱም ቅድም
ያልኩሽን አስታውሺ ነገር ግን ለእራስሽ ይህ ሰው ምኑ ነው
የሳበኝ? ስትይ መልስ የምታጪ ከሆነ እሱ ፍቅር ነው ጊዲዮን
የመጣ እለት ከሄደ በኋላ ስለ ሄዋን ላንቺ ማውራትን የመርጠው
እኔ ሳልሆን ልቤ ነው ያዘዘኝ። በፍቅር ምርኮኛ ሆኖ በልብ መታዘዝ
እጅክ ያስደስታል " ሲል ዲና በጣም ተመስጣ ከሰማች በኋላ
"ዋውውው በጣም በሚገርም ቃላት እና ማብራሪያ ጋር በሚገባኝ
መልኩ ነው ያስርዳከኝ " ስትል አዳም ምንም አደል አላት ።
"አሁን ሁለት ጥያቄዎች እጠይቅሻለው" አለ ዲናም "እሺ "አለች
ፈጠን ብላ የሆነ ሹል ነገር ላይ ድቡልቡል ነገር ማስቀመጥ
ትችያለሽ? ዲና ፈጠን ብላ" አይ አይ እንዴት ሆኖ"አለች አዳምም
ፈገግ ብሎ "ፍቅር ያልያዘው ልብ እንዲ ነው ያቅበጠብጠዋል።
ያንቺን ልምር፤ አይ አይ ይህቺ ትሻላላለች። እያለ ይቆይና
በስተመጨርሻ ፍቅር ሲይዘው ሹሉ ነገር ተነስቶ ድቡልብሉን ነገር
ማስቀመጥ የሚችል ነገር ሲመጣ ድብልብሉ ነገር እርፍ
እንደሚለው።
ልብም እርፍ ይል እና አፈቀርኳቸው ላላቸው ሰዎች ነበርው ስሜት
መውደድ እንጂ ፍቅር እንዳልነበር ይርዳል" አለና ኡፍፍፍፍፍ አለ
ዲና በአግራሞት ቀና ብላ ፈገግ እያለች በተቆራረጠ ድምጽ "እሺ
ሁለተኛውስ " አለች አዳምም አቀርቅሮ እያያት" ስላንቺ ማወቅ
ከተቻለ ብትነግረኝ ደስ ይለኛል "አለና ያቀርቀር አንገቱን ቀና አደርገ
ዲና "ስለ እኔ ስለእኔ ምን ልንገርክ እንዳንተ መሳጭ ታሪክ
የለኝም" ስትለው አዳም ፍጠን ቀልጠፍ ብሎ "መቼም ማንም
ሰው ያለ ታሪክ አይኖርም አደል" አላት ዲናም እንደመፈገግ እያለች
"እእእ ያው እኔ ተወልጄ ያደኩት ድሬደዋ ሳፕያን በምትባል ስፈር
ነው እድሜ ለትምሕርት ሲደርስ ቤተስቦቼ ሀብታም ስለነበሩ ጥሩ
ትምህርት ቤት ገባው ከዛም እስከ 6ተኛ ክፍል ከተማርኩኝ በኋላ
አቋርጥኩት" ስትል አዳም "ለምን? "አላት። እሷም የሆነ ሀዘን
የረጨው ፊት እያሳየችው "ምክንያቱም አባቴ በነበርበት የስኳር
በሽታ በድንገት ሞተ ከዛም እኔ እና እናቴ ብቻ ቀረን አባቴ ከብዙ
ባንኮች ለስራ ማስኬጃ ብሎ ተበድሮ ነበር ተባለና ተወራ እኔም
ሆንኩኝ እናቴ ግን በጭራሽ አናቅም አባቴ የሞተው በሰው ተገሎ
ነው ይባላል ግን ሞቶ ሲገኝ ምንም አይነት አሻራ ስላልተገኘ እና
በሚሰራበት ቢሮ ወንበር ላይ ተቀምጦ ጠረቤዛ ላይ ተደፍቶ ነበር።
ከዛ ሀዘናችንም ሳይወጣልን አባቴ የተበደርው ብር ስላለበት እና
ጊዜው ስላለፈ በሚል የነበሩን ነገሮች አንድም ሳይቀር ተሸጠ
የቀረው ቤታችን ነበር እሱንም ትንሽ ቆይቶ የተሸጠው እቃ እዳውን
አልከፈለም ብለው ቤታችንን ሽጠው የቤታችንን አንድ አራተኛ ብር
ሰጡን እና ሌላውን ወስዱት እናቴ በብስጭት እና በጭንቀት
አልጋ ላይ ዋለች እኔም ትምርቴን አቋርጬ እናቴን ማስታመም
ጀመርኩኝ ከቤታችን በቀረው ብር አነስተኛ እና በጣም ትንሽ ቤት
ተከራየን ግን ይህ ብር ብዙ አላቆየንም አለቀ። ከዛም እናቴ
መንቀሳቀስም ስላቃታት እኔ ጎረቤቶቻችን አዋጥተው ለስራ ብለው
በስጡኝ ብር መንገድ ላይ ምግብ መሽጥ ጀመርኩኝ ቢሆንም ግን
ለእናቴ መሆን አልቻልኩም እኔ የምስራው ለእለት ምግብ እንጂ
ለእናቴ ህክምና አልሆነም እናቴን የኔን ህይወት በእዚህ መሀል
ነበር ዳግመኛ ላታየኝ ላላያት ያሽለበችው።
እኔ ስልችቻት ነው? ወይስ ተገዳ እንጃ ብቻ የሚወዱትን ማጣት
ምን ያክል እንደሚከብድ አቀዋለው ለእዛም ነው አንተ ስትጎዳ
ማየት ያቃተኝ እና ላፅናናክ የወስንኩት"።
"በህይወታችን ውስጥ ህይወታችን አድርገን የሾምነውን ሰው
ማጣት ውስጥ ያለውን ስቃይ አውቀዋለው ልክ እንዳንተ ልናጣው
ሲመስንም የሚስማንን ጭንቀት እናቴ ሳትሞት በፊት በጣም
ሲያማት ላጣት ነው ብዬ የተስማኝን "
"የሆነ ቀን ቤት ስገባ እናቴ ፍራሽ ላይ ጥቅልል ብላ ተኝታለች
እራታችንን እንደተለመደው አቅርቤ ስቀስቅሳት ግን እንደ ሊላ ቀኑ
አልተነሳችልኝም። በጣም ጮክ ብዬ ብጠራትም አቤት አላለችኝም
አበድኩ ልክ እንደ እብድ አረገኝ እናቴ ከእዚህ በኋላ ከጎኔ
እንደማትሆን ስርዳ ፤ከእዚህ በኋላ ስመርቅ ከትምህርት ቤት
ሽልማት ሳገኝ ፣ስጨነቅ፣ ስደሰት አጠገቤ እንደማትሆን ሳስበው
ውስጤን አመመኝ አልቻልኩም በቃ አልቻልኩም። ጎረቤት
ተሰበሰበ እናቴን ገናዥ ጠርተው አስገነዟት ከዛም በቃ በነጋታው
ተቀበረች እንደ ዋዛ እንደቀልድ እናቴን አጣዋት"።
"ለቅሶ ካለፈ በኋላ ብቻዬን ለ3ወራት ኑሮ በማይባል መልኩ
ኖርኩኝ። ቤተስብ እና ብዙ ነገር አጥቼ። ከዛም ማታ ከስራ
ስመለስ አክስቴ መጥታ ወደ አዲስ አበባ እወስድሻለው ብላኝ
በነጋታው ያለኝን እቃ ሽጠን ወደ እዚህ አመጣችኝ አክስቴ
ስልጧኗን ለእኔ ለማሳየት የተቻላትን አደርገች እኔም ጠንክሬ
መማር ጀመርኩኝ። የማታ ትምህርት አስገባችኝ። ቀን ለእሷ ለባሏ
እና ለልጆቿ መገልገያ ነኝ።
"ማታ ከትምርት ስመለስም እንደዛው። እኔ ግን ከስራዬ ስአት
መቀነስ ባልችልም ከእንቅልፌ ቀንሼ አጠና ነበር። መብራት
ይቆጥራል ለሊት አታብሪ ስለምትለኝ በርንዳ ወጥቼ በባትሪ
እያጠናው ተማርኩኝ።
" ልጆቹ ሲያጠኑ ምንም አትልም ለእኔ ግን በቃ ተወዉ ብቻ
"አለችና እንባዋን ዘርገፈችው አዳምም አለቀሰ ከዛም "አሁን የት
ነው ያለሽው" አላት ዲናም" አሁንማ በቃኝ ብዬ ቤቶን ትቼላት
ከወጣው 6ወር ሆነኝ ጓደኞቼ ናቸው ለቤት ክራይ የከፈሉልኝ
እቃም ያሞሉልኝ ያው ሀብታም ጓደኞች ነው ያሉኝ "ብላ ፈገግ
አለች።
"እኔ ደሞ ለጊዜው ስራ እየፈለኩኝ ነው" አለች።አዳም ፈጠን ብሎ

hace 3 meses, 2 semanas

Like ሳታረጉ ስትቀሩ ማንም የሚያነብ ሰው ያለ ስላልመሰለኝ ሰልችቷቹ ምተውት ነው ሚመስለኝ
ስለዚህ like brr አይደለም አትሰስቱ
አንድ ሁለት ሰው ብቻ ሚከታተለኝ ከሆነ ኑ @Beker33 ሰብስቤ ልክላቿለው

#ግድ_የለም_react ❤️?? #አይቆጥርባቹም

hace 4 meses, 2 semanas

ቆጣ ብላ አንቺስ ስላት ቁጣዋ ወደሳቅ ተቀይሮ ሳቀችና አቀፈችኝ
ሁለቱንም እኮ አደለም የምስጥክ አንዱን ነው ብላ ለቀቅ አድርጋ
አይኔን እያየች እኔ ደሞ ቆይ እሺ አንቺን ኩላሊት ቢያምሽስ ልክ
እንደኔ አልኳት ፀባይክ ካላማረና ካመመኝ ትመልሳክ አለች ፍገግ
ብላ ከዛ እጄን ልቦ ላይ አደርገችው እና ሁሉ ነገሬ ያንተ እና ያንተ
ብቻ ነው አለችኝ እኔ ምን እንደምላት ግራ ገባኝ ያኔም የመኪና
አደጋ ሲደርስብኝ ደም ለግሳኝ ነበር በነገራችን ላይ አንደኛው
ጓደኛዬ ካደጋው ተርፎ አሁን ደቡብ አፍሪካ እና አሜሪካ
እየተመላለስን ንግድ ነው የሚስራው የሄዋን ጥሩነት ከአቅሜ
በላይ ሆነ ከ15 ቀን በኋላ ወደ ውጭ ሀገር ሄደን ንቅለ ተከላውን
አደረግን ትንሽ ሳገግም ደሞ ወደ ዱባይ ሄደን እቴቴ ባወርስችኝ
ቤት ዘና አልን ዲና በጣም ደስ ይላል ከሚያፍቅሩት ጋራ አብሮ
መዋል እና ማደር ስትል አዳም አዎ በጣም ግን ከሄዋን ጋር
አብርን አናድርም እንውላለን እንጂ እስክንጋባ አብርን አንተኛም
አላት ዲና በመገርም እና እስካሁን ምንም አርጋቹ አታቁም አለችው
አዳምም አዎ አናቅም ዲና ግርም አላትና እሺ ሌላው ቀርቶ ስትል
አዳም እሩቅ አትሂጂ ከንፍሯንም ስሚያትም ስማኝም አታቅም
ምክንያቱም ያረከስኳት ነው የሚመስኝ እኔ እሷን የምፈልጋት
ለደቂቃ ስሜት ሳይሆን ለዘላለም ደስታ ነው አላት ዲና በጣም
ተደመመች።
ዲና ከሩቅ አንድ ዶክተር አየች አዳምን ወደሱ እንዲያይ በአይኗ
ምልክት እየስጠችው ተመልከት ይህንን ልክስክስ ዶክተር ከህፃን
ታካሚ እስከ ጉልማሳ አይቀርውም ሲባልግ ነርስ ዶክተር ዘበኛ
አይመርጥም በእሱ ያለተበላሽነው ጥቂቶቻችን ነን ምክንያቱም
እዚህ ሀኪም ቤት ሁሌ አፓረንት ስንወጣ አየዋለው አለችው
አዳም ግራ እደተጋባ ተማሪ ነሽ እንዴ አላት አዎ ነኝ ስትለው
አዳም ግራ በመጋባት ነርስ መስለሽኝ ነበር ለካ ነርስነት
እየተለማመድሽልኝ ነው አላት አይ አይ ያኔ አንተን ለማዋራት
ሰለፈለኩኝ ነበር የቆየውት እና እልካለው ኮማ ውስጥ ሴት ካለች
እሷንም አይምርም ምክንያቱም ገና ሲታይ እንደምታየው ፍቅር
የሚያሲዝ ነው በተለይ አቋምና መልክ ላላቸው ሴቶች እንክብካቤ
ያበዛል ሄዋን ግን ሰውነቷ እንዴት ነው ያምራል? አለችው ጠቀስ
አድርጋው በቀኝ አይኗ ስለ ስውነት አቋሟ ልነግሽ አለችም
ምክንያቱም እሱን አይቼ ስላላፍቅርኮት ልነግርሽ የምችለው አይቼ
ስላፍቀርኩት ልቧ ነው አላት ዲና በአግራሞት ጭንቅላቷን
ነቀነቀች በነገራችን ላይ ያንተ ፍቅር የመጨርሻ ደረጃ ላይ ነው
ስትለው የፍቅርም ደርጃ አለው አላት ዲናም እንዴ አዎ
የሳይካትሪስት ተማሪ አይደለው እሱን ያላወኩኝ ምን ላቅ ነው
አለችው አዳምም እሺ እስቲ ንገሪኝ አላት ዲናም ፈገግ ቀልጠፍ
ብላ የመጀመሪያው love ይባላል ይህ ማለት ደሞሞ
ይህ እጅግ በጣም መውደድ ነው ከዛ ሌላው ደሞ like ነው
በጣም መውደድ ማለት ነው ሳስተኛው Adore ይባላል ይህ
ማለት ደሞ ማፍቀር ነው ስትለው አዳም ፍገግ ብሎ እና እኔ
Adore ላይ ነኝ ሲላት አይ አይ አልጨርስኩም አራተኛው
worship ejik ነው ይህ በጣምምምም ማፍቀር ነው
አለጨርኩም ይቀራል አለች ዲና አዳም ሊያወራ ሲል
አምስተኛውእና የመጨርሻው ፍቅር ደሞ become crazy
ይባላል ይህ ማለት የፍቅር ጥግ ላይ ደርሰካል አብደካል ማለት
ነው አምስተኛው አንተን ይገልፅሀል አለችው አዳም በለው ኧርር
ጓበዝ ጥሩ ማብራሪያ ነው ወደጄዋለው
ሄዋን ነቅታ ይሆን አለና ዶክተሩ እሷ ጋር ብዙ እንዳይመላለሱ
የነገር ትዝ አለው ግን አልቻለም እና ብድግ ብሎ ሄደ ሄዋን
ለጥጥ ብላለች ሄዶ ግንባሯን በቀስታ ስሟት ወጣ እና ወደቦታው
ተመለስ ዲና ጎን ተቀመጠ ያ ልክስክሱ ዶክተር ወደ እነሱ
እየቀርበ መጣ ከዛም በጣም ቀርበ እና ሄዋን የተኛችበትን ክፍል
በር ለመክፍት የበር እጀታውን ያዘው አዳም ሊያብድ ደርስ ወደ
ዶክተሩም ተጠጋ

ይቀጥላል......

hace 4 meses, 2 semanas

?አለሜ ነሽ?

?ክፍል 12

✍️ደራሲ፦ቤዛዊት ፋንታዬ የሽዋ ልጅ

""
""
አዳም ፈገግ ብሎ አስቢው እስቲ ሄዋኔ ስታወራ በጣም
የምትጮህ ካልጮከች የምታወራ የማይመስላት ናት ግን ያኔ
የወሰደችኝ ሰዎች ድምፅቸውን ቀንሰው የሚያወሩበት ሁለት
ሰዎች በብዛት ደሞ ፍቅረኛሞች እየመጡ የሚያወሩበት ማንም
ማንንም መረበሽ ፍፅሞ እንደማይፈቀድ መግቢያው ላይ የተፃፈበት
ነው ከዛ በውስጤ ቢቆይም ከሄዋን ጋር እንደዚህ አይነት ቦታ መምጣት
አግባብ ነው አልኩኝ ና ብላ እጄን ጎትታ የሆነ መቀመጫ ላይ
ተቀመጥን መቀመጫው ያንዠዋዥዋል ልክ እንደ ዥዋዥዊ እና 2
ሰው የሚይዝ ነው ከዛም ከተቀመጥን በኋላ ሄዋን በእግሯ
መሬቱን እየገፋች መንዠዋዠው ጀመርች እኔ ደሞ ጥሎብኝ
ዥዋዥዌም ሆነ ምንም አይነት ተንቀሳቃሽ ነገር ላይ መቀመጥ
አልወድም እንድታቆም ለመንገር ፈራው የሰውነቴ እና የፊቴን
እንቅስቃሴ በማየት እንዳልተመቸኝ አውቃ ነው መሰለኝ
ማንዠዋዠውን አቆመች እና ዝም ብላ ታየኝ ጀመር ያኔ ልቤ
በጣም ደነገጠ መምታት ጀመር ወደኔ ተጠጋች ላብ በላብ ሆንኩኝ
ከዛ ወደ ከንፈሬ አከባቢ ያለውን ጉንጬን ሳመችው እና ግጥሜስ
አለችኝ ጮክ ብላ ሰዉ ዞሮ አፈጠጠባት ከዛም ወደራሳቸው ወሬና
ተመስጦቸው ተመለሱ ። እኔም የያዝኩትን የተጣጠፈ ወረቀት
አወጣው ወረቀቱ ላይ ለሄዋን የገጠምኩት ግጥም ነበር። ሲል
ዲና ምን የሚል እስቲ በልልኝ አለችው አዳምም በደስታ አለና
ጉሮሮውን ጠራርገው የግጥሙ
ርዕስ እኔስ ገረመችኝ ይላል

እኔስ ገረመችኝ ኧረ አስደመመችኝ
ይህቺ ሴት በድንገት መጥታ የሳመችኝ
ኧር እንደውም በጣም አስደነገጠችኝ
ክው ብዬ ቀርው የሳመችኝ እለት
ሳስባት አደርኩኝ ቀን አልቀርኝ ለሊት
ጉንጬን ስትስመኝ ደንገጥገጥ አልኩና
ግንባሪን ስስመኝ ልቤ ተናጋና
ይህቺ ሴት ልቤ ውስጥ ገባች በጠና
ልቤ ታመመላት ተጨናቀላትም
ታቀዉ ይሆን እንዴ የልቤን መታመም
ወይስ ልብ ሳትል ቀርታ ይሆን እንዴ
ግራ ይገባኛል ዘወትር አንዳንዴ
ብዬ ግጥሙን ጨርሼ ቀና ስል ሄዋን ኩስትርትር ብላ ነበር
በጣም ደነገጥኩ ምነው ልልላት ብዬ ፈራው ምን አልባት ግጥሙ
ላይ ለእሷ ያለኝን ስሜት ስለገለፅኩ ተናዳ ይሆን ብዬ አስብኩኝ
ከዛም ሄዋን እየቀለድክብኝ ነው እንዴ አለች ደነገጥኩ
ሰዉ ሁሉ ዞሮ አየን በጥፊ መታችኝ ግራ ገባኝ ለመሳም
ያዘጋጀውትን ጉንጬን ጥፊ አረፈበት ለነገሩ እኔም ይህንን ግጥም
ስፅፍ በግጥሙ አመካኝቼ ፍቅሬን ልገለፅ ነበር አሀ በቃ
ስለማታፈቅርኝ ነው በእዚህ ግጥም የተናደደችው ብዬ አስብኩ
የመታችን ጉንጭ ይዤ ቀረው ደንዝዤ ፍዝዤ በነገራችን ላይ
በሰአቱ እሷ ስለተናደደችብኝ አዘንኩ እንጂ ሰው ፊት ስለመታችኝ
ምንም አለመስለኝም ከዛ ጮክ ብለክ ያነብክለኝ ግጥም በልልኝ አለችው እ አልኳት አዎ በልልኝ አለችኝ ከዛም ጮክ ብዬ አነበብኩት የሰው ሁሉ ትኩርት እኛ ላይ ነበር
ከዛም ሄዋን ጮክ እና ከት ብላ ሳቀችና የእኔ ውድ ቆይ ምን
አይነት ስው ነክ እእ ብላ ጉንጭ እና ግንባሬን ሳመችኝ ከዛ ሁሉም
እንደ ትንግርት እኛን ማየት ጀመረ ፈገግ አሉ ዲና ቆይ ይህ
የሆነው ሀኪም ቤት ገብተክ ፍቅራችውን ከተገላለፃቹ በኋላ ነው
አለችው አዳምም አይ ከዛ በፊት ነው ያኔ እኔና ሄዋን ከመናፈሻው
ስንወጣ እራሱ ሄዋን ግጥሙ እንዳልገባት ሆና ዝም ብላ ሌላ ወሬ ነበር ስታወራ
የነበርው ሄዋን ግቢያችን በተቀላቀለች በነጋታው ብዙ ወዳጅ ነበር
ያፈራችው ወንዶችን በፍቅር ሴቶችን በመውደድ ጠብ አርጋን ነበር እውነት ለመናገር እሷን አለመውደድ በጭራሽ አይቻልም ተጨዋች ያልሆነውን ተጫዋች
ጉልበተኛ የነበርውን ከጉልበተኝነት እንዲላቀቅ ሱሰኛ የነበርውን
ከሱሱ እንዲላቀቅ እረድታለች ሱስ ስልሽ ለአደንዛዥ እፅ
፣የነገር፣የመላከፍን ይጨምራል ለጥናትም እንደዛው ጥናታቸው
ላይ አተኩርው ጭብጥ ብለው የሚማሩትን ፣ በተለያየ ችግር
ጭምት የሆኑትን ፈታ እንዲሉ አድርጋለች ሄዋን ማለት ስለ ሰው
ችግር ሰምተው እና ይሄ ከእኔ ህይወት ጋር ምን አገናኘው የሚሉት
አይነት ስው አደለችም ብዙ ወንዶች ሄዋንን አፈቀርኩሽ ማለት
ሲጀምሩ እንዳውም በእየ ኮሊደር እና ክፍል ውስጥ 12 ሆነን
ሄዋንን ወደው ኛል እሷ ትስቃለች እኛ ተጨንቀናል ብለው ብዙ
ተማሪዎች ፅፈዋል።
ከ 2አመት በፊት ትምህርት ተዘግቶ እረፍት ልንወጣ ስንል በጣም
ያመኝ ጀመር ጎኔን ይጠዘጥዘኛል ብዙ መራመድ ያቅተኛል ምናምን እንደምንም
ትምህርቱን ስጨርስ ህክምና አደርኩ ይህ የምነግርሽ የመኪና
አደጋው ከተፈጠር በኋላ ነው ፊቴ መበላለዝ ሲጀምር የግቢ ልጆች
ሁሉም ጓደኞቼን በማጣቴ ሀዘኑ በርትቶብኝ ነበር የመስላቸው አንድ
ቀን ከሄዋን ጋር እየሄድን መንገድ ላይ ወደኩኝ ከዛም ሄዋን
በመጮህ እና ሰው እንዲረዳት በማድርግ ሀኪም ቤት ወስደችኝ
ያኔ ያመመኝ እንደ ነገ የግቢው ተማሪ በሙሉ ለእርፍት ሊሄድ ነበር
ስመርመር ሁለቱም ኩላሊቶቼ ፌል እንዳደረጉ እና ከተቻለ
በአፋጣኝ ንቅለ ተከላ እንደሚያስፈልግ ዶክተሩ ተናገር ሄዋን
ይህንን ስትስማ እኔ እስጠዋለው አለች ፈጠን ብላ ዶክተሩ ምኑ
ነሽ አላት እና መልሷን መጠባበቅ ጀመረ እኔ በቀስታ ደምፅ ሁሉ
ነገሬ ናት አልኩኝ ዶክተሩ ግራ ገባው ሄዋን ምርመራ አድርገሽ
ለእሱ መስጠት ከቻልሽ ልስጭው ነው ማለቴ እርግጠኛ ነሽ?
አለቻት አዎ ያው ፀባዩ ካላማረ እቀበለዋው አለች እና ፈገግ
አለች ከዛ ዳክተሮቹ እዚህ አልጋ እንድይዝ እና ኩላሊት ከተገኘለኝ
ወደ ውጪ ሀገር ሄጄ እንደምታከም ነገርኝ ዘመድ ካለኝም ጠየቀኝ
የሩቅም ቢሆን ሲለኝ አይ የማደጎ ልጅ ነኝ አልኩት እና የመታከሚያ
ብር አለህ ሲለኝ በሚገባ አልኩት ምክንያቱም ከማደጎ በኋላ እንደ
ልጃቸው ያኖሩኝ ወይዘሮ ብርትካን በጣም ብዙ ሚሊየን ብር
አውርስውኝ ስለሞቱ ። እማማ ብርትካንን እቴቴ ነው የምላት እኔ
ባደኩበት ማደጊያ እርዳታ በመስጠት ይታዉቃሉ ሲመጡ ሁሌም
ሰላም ይሉኛል ከዛ 15 አመት ሊሞላኝ ከድርጅቱ አስወጥተው
እንደ ልጃቸው ተቀብለው አኖሩኝ የአበባ እርሻ እና የአበባ ማሽጊያ ድርጅት እና ደሞ 2 ሀገር ውስጥ 3 ደሞ ውጪ ቤት አላቸው በየ ሀገሩ በበረሩ ቁጥር ማራኪ አበባ
ካለ ይዘው ይመጣሉ ባላቸው ሞቷል መሀን ስለነበሩ አልወለዱም
ባለቤታቸው አቶ አሰፋም ምርጥ ሰው ነበሩ እቴቴን አንቱ እያልኩ
ነው የማናግራት አንቺ ስላት ያረከስኮት ያክል ነው የሚስማኝ
የሆነ ቀን እቴቴ ዱባይ በረው ሲመለሱ አውሮፕላን ውስጥ ነው
በድንገተኛ አደጋ የሞቱት ግን ከመሞታቸው በፊት ሙሉ
ንብርታቸው ለእኔ 18 አመት እንደሞላኝ መታወቂያ አውጥተውልኝ
ያሸጋገሩት ለእዛም ነው ለዶክተሩ ብር አለኝ ያልኩት
በ3 ቀን በኋላ ሄዋን ምርመራውን አድርጋ ለእኔ መለገስ
የምትችልበት ደርጃ ላይ እንደሆነች ተነገራት ሄዋን
እየተፍለቀለቀች መጥታ እንኳን ደስ አለክ የኔ ፍቅር የኔ ሁሉ ነገር
ዛሬ ደስስስ ብሎኛል እንኳን ደስስስ አለክ አለችኝ ዲያሊስስ
ተደርጌ ስጨርስ ምን ተገኘ አልኳት እኔ ላንተ ኩላሊት መለገስ
እንደምችል ተነገርኝ አንተ ብሩን አዘጋጅ እኔ ደሞ ኩላሊቴን ብላ
በሳቅ አለች ከዛ እኔ አይ አይሆንም አልኳት እሷም ለምን አለችኝ

hace 4 meses, 2 semanas

ነው አልኳት ከተቀመጠችበት ተነሳች ወደየት ልትሄድ ነው ብዬ
ቁጭ ካልኩበት ቀና ብዬ ተመለከትኳት ወደ እኔ ቀረበች ግጥም
አድርጋ ጉንጬን ሳመችኝ ይህንን ግጥም እማ አለች እየሳቀች
ይህን ግጥምማ የሆነ እምወደው ቦታ አለ እዛ ነው ምታነብልኝ
አለችኝ ውስጤ ደስ እያለው እሺ ብያት መሄድ ጀመርን መንገድ
ላይ እየተራመድን ስሟን ጠየኳት ሄዋን አለችኝ እኔ ደሞ አዳም
አልኳት ከዛም ኦኦኦኦ አዳምና ሄዋን አለችኝ አዳም እና ሄዋን ምን
አይነት አጋጣሚ ነው ሁለታችንም ስማችን አስገርሞን ነበር ።
ከምንራመድበት ገታ ብለን ያው ይህ ነው ቦታው አለችኝ ቦታውን
በአይኔ በደንብ ቃኘሁት ሄዋኔ እዚህ ባታ ትሄዳለች ይህንን ቦታ
ትወዳለች ብዬ አልጠበኩም ነበር እና ገርመኝ ዲና ስፍ ብላ ምን
አይነት ቦታ አለችው

.....ይቀጥላል.....

hace 7 meses, 2 semanas

‍ ​​?ሴና?

#የመጨረሻው ክፍል!

#ደራሲ: በ ኬቤክ (kebek) እንደተፃፈ✍?✍?✍?

#ክፍል37⃣

◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ ሴና?

. . . አይኔን ስገልጥ ነጭ ኮርኒስ ነው የታየኝ፡፡ አልጋ ላይ እንደተኛው ይሰማኛል፡፡ አንገቴን ወደ ጎን ዞር ሳደርግ አጠገቤ አንድ ነጭ ጋወን የለበሰ ሰው ቆሞ የአይዞሽ አሁን ደና ነሽ" አለኝ ግንባሬን በመዳፉ እየዳበሰ፡፡ የተኛውት የሀኪም ቤት ክፍል ውስጥ እንደሆነ ገባኝ፡፡ ወዲያው የክፍሉ በር ተከፍቶ እነ ሚጣ ተከታትለው ገቡ፡፡ "አሁን እንዴት ነሽ?" እያሉ ጥያቄ ያከታትሉብኝ ጀመር፡፡ "አሁን ደና ስለሆነች ይዛቹሀት መሄድ ትችላላቹ ፡፡ትንሽ ድንጋጤው እንጂ ሌላ ምንም ችግር የለባትም" አለ ባለ ነጭ ጋወኑ ሀኪም፡፡ እነ  ሚጣ ደግፈው ከአልጋ ካወረዱኝ ብሀላ ጫማዬን አድርገውልኝ ከተኛውበት ክፍል ይዘውኝ ወጡ፡፡
              ከክፍሉ ስወጣ ከግቢ ውጪ ያለ ሀኪም ቤት እንደነበርኩ ገባኝ፡፡ አይኔ ያነባል፡፡ እነ ሚጣ አይዞሽ ይሉኛል ፣ ጥያቄ ይጠይቁኛል ፣ማብራሪያ ይሰጡኛል ፣ሊያረጋጉኝ ይሞክራሉ፡፡ እኔ ግን ማልቀሴን አላቆምኩም፡፡ ከሀኪም ቤቱ በር ላይ ስደርስ ያየውት ግራ ገባኝ ፡፡ የወንድሜ መኪና ቆሞአል፡፡ እንዴት እንደሰማ ግራ ገባኝ፡፡ "ቆይ ውስጥ ነው ይመጣል"አለችኝ ሚጣ በቀኝ በኩል ደግፋኝ እንደቆመች፡፡ እንዴት መጣ? ማን ነገረው? ቆይ እኔ እንዴት እዚ መጣው?' ጠየኳት ሚጣን እንባዬ አሁንም እንደወረደ ነው፡፡ ድምፄ ጉንፋን እንደያዘው ሰው ተዘግቶአል፡፡ "ቆይ ሁሉንም እናውራለን፡፡ አሁን ተረጋጊ"አለችኝ ሚጣ ጉንጬ ላይ የወረደውን እንባዬን በሹራቧ ጫፍ እየጠረገች፡፡ በዚ መሀል ወንድሜ መጣ "አይዞሽ ምንም አልሆንሽም"ብሎ አቀፈኝ፡፡ ጥያቄ ሆነብኝ፡፡ ወዲያው የመኪናውን ሁዋላ በር ከከፈተልኝ ብሀላ ወደ ውስጥ ገባው፡፡ ሚጣ ተከትላኝ ገባች፡፡ ሌሎቹ ከተሰናበቱኝ ቡሀላ ሄዱ፡፡
             ወንድሜ ወኪናውን አስነስቶ መሄድ ሲጀምር 'ቆይ ምንድነው ነገሩ ግራ አጋባቹኝ እኮ 'አልኩኝ በደከመ ድምፅ፡፡ ማንም መልስ አልሰጠኝም፡፡ ወንድሜ መኪናውን እየነዳ ከከተማ ወጣ ወዳለ ቦታ ከወሰደን ብሀላ መኪናውን ከአንድ ሜዳማ ስፍራ አቁሞ ሞተሩን ካጠፋ ብሀላ ከመኪናው ወረደ፡፡ሚጣም ተከትላው ወረደች፡፡ ግራ ገባኝ እኔም ተከትያቸው ወረድኩኝ፡፡ ወንድሜ መኪናውን ተደግፎ ቆመ፡፡ ገና ከመኪና ከመውረዴ ሚጣ ማውራትጀመረች፡፡ "የውልሽ ሴና ያኔ ለ እረፍት ወደ ቤት የሄድን ሰአት ነበር ፍሬ በድንገተኛ አደጋ ያረፈው፡፡ እና የዛን እለት ላንቺ ይሄንን ልነግርሽ አስቤ ነገር ግን እንደዚ አይነት ነገር በስልክ ብነግርሽ ያለሽበት ሁኔታ ደሞ ጥሩ ባይሆን ይሄንን ስትሰሚ የሆነ ነገር ቢፈጠር ወይም የሆነ ነገር በራስሽ ላይ ብታደርሺ ብዬ ስለፈራው ለወንድምሽ ደወልኩለት፡፡ የሱን ስልክ ከየት አገኘሽው ካልሽኝ እኛ ግቢ ምትማረው የባልደረባችን ልጅ ያልሽኝ ከሷ ነው የተቀበልኩት፡፡ የሷን ስልክ ደሞ ያገኘውት እነሱ ዶርም የምትኖር ልጅ ጉዋደኛ እሱን ጠይቄ በሱ በኩል አድርጌ አፈላልጌ ነው፡፡ ያ አማራጭ ባይኖረኝ የዛኔ ቀጥታ ሀዋሳ ቤታቹ መጣ ነበር፡፡ ይሄንን አድርጌ ለወንድምሽ ደውዬ ሁሉንም ነገር ነገርኩት፡፡ የዛን እለት ወንድምሽ ሰበብ ፈልጎ ስልክሽን ተቀበለሽ፡፡ ያንን ያደረግነው ደሞ ከሌላ ሰው እንዳትገናኚ እና ከሌላ ሰው እንዳትሰሚው አስበን ነው፡፡"
         ሚጣ ይሄንን ስትነግረኝ ወንድሜን እየተመለከትኩት ማንባቴን ቀጠልኩ፡፡ ሚጣ ቀጠለች፡፡ " . . .ለ ዴቭ ስትደውይለት አጠገቤ ነበር፡፡ ፍሬን እንዳላየው እና ሀዋሳ እንሆነ እንዲነግርሽ የነገርኩት እኔ ነበርኩኝ፡፡ ሰኞ ለምዝገባ መጥተሽ ምዝገባ አርብ ነው ሀሙስ እንመጣለን ያልኩሽ ግዜ እኔ ግቢ ነበርኩኝ፡፡ ሌሎቹም የዶርም ልጆች መጥተው ከተመዘገብን ብሀላ ወንድምሽ ንቺን ግቢ እንዳደረሰሽ በሌላ በር ገብቶ አንቺ መምጣት እንደማትችይ ነግሮ ግቢ ውስጥ በሚያውቀው ሰው አማካይነት እንድትመዘገቢ አደረግን፡፡ ከዛ እኔና የዶርም ልጆች እናንተ ቤት ነበርን፡፡ ምክንያቱም ሀሙስ ነው ምንመጣው ያልንሽ ብቻሽን እንድትሆኚ ነበር፡፡ ብቻሽን እንድትሆኚ ካደረግን ብሀላ ወንድምሽ ኪሩቤልን ላከው፡፡ ኪሩቤል በአጋጣሚ ካፌ ውስጥ የተዋወቅሽው ተማሪ ሳይሆን የስነልቦና ባለሙያ የሆነ የወንድምሽ ጉዋደኛ ነው፡፡ የፍሬ ስልክ ሲሙ የወጣው በዴቭ ስም ነው፡፡ስለዚ ፍሬ ሲያርፍ ዴቭ ሲሙን አውጥቶ ስለነበር በዛ ስልክ ሚደወሉ ጥሪዎችን በሙሉ ለፍሬ የተደወሉ ይሆናሉ ስለሚል አያነሳውም፡፡
            እኔና ወንድምሽ ይሄንን ስናደርግ ሀሳቡ የኪሩቤል ነበር፡፡ እኛ ያሰብነው ፍሬን ቀስ በቀስ እንድትረሺው ነበር፡፡ ለዛ ነው ኪሩቤል ቢዚ ያደረገሽ፡፡ ያው ባልጠበቅነው መንገድ እውነቱን አወቅሽ እነጂ" ፡፡ሚጣ ይሄንን ሁሉ ስታወራ እኔ እያነባው በግርምት አዳምጣት ነበር፡፡ ወንድሜ መኪናውን እንደተደገፈ ቆሞ ያዳምጣት ነበር፡፡ ወደወንድሜ እየተመለከትኩ ላወራ ስል "ሴና ከህፃንነችሽ ጀምሮ ሳደርግ የነበረው ነገር አንቺ እህቴን በጣም ሰለምወድሽ ነበር፡፡ ታላቅ እንደመሆኔ ደሞ አንቺን ከብዙ ነገር ጠብቄ ትልቅ ሰው ማድረግ ነበር እቅዴ ፡፡ እኔ ይህን ሳደርግ ደሙ ሙሉ ቤተሰባችን ስለሚቀበለኝ አንቺ ይሄንን ከጥላቻ ትቆጥሪያለሽ፡፡ በርግጥ እኔም አበዛውት ግን ላንቺው አስቤ የማደርገው ነገር ስለ. . . " አላስጨረስኩትም ወንድሜ ላይ ጥምጥም አልኩበት፡፡ ይሄንን ሁሉ ነገር ያደርግ የነበረው ለኔው ሲል መሆኑን ሳስብ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ፡፡ ወንድሜን ለቅቄ ሚጣን አቀፍኳት፡፡ ተቃቅፈን አለቀስን፡፡
         ወደ ከተማ እየተመለስን በጭንቅላቴ ብዙ ሀሳቦች ተመላለሱ፡፡ ዠእውነት ለካ ቤተሰቦቼ ለኔ ፍቅር አላቸው፡፡ የተከተሉት መንገድ የጎዳኝ ቢመስለኝም ሁሉን ሚያደርጉት ለኔ ብለው ነው፡፡ የዶርሜ ልጆች እውነትም ለካ ከልባቸው ነው ጉዋደኝነታቸው፡፡ ለኔ ሰሜት ምን ያህል እንደሚጨነቁ አሰብኩኝ፡፡ እውነት እኛ ሰዎች ባሰቡልን ልክ እያሰብናቸው ነው?' ብዬ ራሴን ጠየኩት፡፡ ዶርም ስገባ ስለሁሉም ነገር ጉዋደኞቼን አመሰገንኳቸው፡፡ ከኪሩቤል ጋርም ጉወደኝነታችን ቀጠለ፡፡ ወንድሜና ጉዋደኞቼ ባደረጉት ነገር በጣም ብዙ ተማርኩኝ፡፡ ጉዋደኝነት ፣ቤተሰብ እውነተኛ ፍቅርን ከነሱ አገኘው፡፡ የፍሬ ህልፈት እጅጉን የከፋ ሀዘን ቢያደርስብኝም ቤተሰቦቼ እና ጉዋደኞቼ ከጎኔ በመሆናቸው ብርታት ሰጡኝ፡፡
             ይሄ ታሪክ ከተፈጠረ አመት አለፈው፡፡ አሁን እኔ የሁለተኛ አመት ተማሪ ሆኛለው፡፡ ዶርም ስሄድ ቤቴ ቤት ስሄድ ዶርሜ ይናፍቀኝ ጀመር፡፡ በትምህርቴ ውጤታማ እየሆንኩኝ ነው፡፡እስካሁን የፍቀር ጉዋደኛ አልያዝኩም፡፡ ፍሬ ዛሬም በልቤ፥ አለ፡፡ ነገር ግን ቤተሰቦቼና ጉዋደኞቼ አብረውኝ ስላሉ ደስተኛ ነኝ፡፡ ለሁሉም ነገር ደሞ ፈጣሪን አመሰግናለው፡፡ አምላክ የፍቅርን ጉልበት በቤተሰቦቼና በጉዋደኞቼ በኩል አስተምሮኛል፡፡

ይህንን ታሪክ ያነበባቹ በሙሉ ከዚህ እንደምትማሩ ተስፋ አደርጋለው፡፡

. . . . ህይወት ይቀጥላል  . . .

???? ተ  ፈ  ፀ  መ????

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago