ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 Monate, 3 Wochen her
Last updated 2 Monate, 2 Wochen her
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 Monat, 2 Wochen her
ዛሬ በእነ ዲያቆን ዶክተር ብንያም ቤት ደስታ ሆነ
#Ethiopia | ዲያቆን ዶክተር ብንያም ኢሳይያስ
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በህክምና ዘርፍ ተመርቋል።
አባት አቶ ኢሳይያስ
እናቱ ወ/ሮ ለተየሱስ
ከደብረ ብርሀን ዩኒቨርስቲ በኮምፒዩተር ሳይንስ የተመረቅቀከው ታናሽ ወንዱሙ
“ አቤሴሎም ኢሳይያስ”
እንዲሁም መላው ቤተሰቦቹ እንኳን ደስ አላችሁ።
ልክ የዛሬ ሦስት ዓመት ነበር።፣ የቀድሞ የአምስተኛ ዓመት የህክምና ተማሪ፣ የአሁኑ ዶክተር ብንያም ኢሳይያስ አምስት ዓመታትን ፈታኙን የህክምና ትምህርት ሲከታተል ቆይቶ....
ድንገታዊ በሆነ መልኩ፣
አንተ ትምህርት መማር አትችልም።፣ ትምህርቱን አቋርጥ ተብሎ የተነገረው።
ምክንያቱ ደግሞ፣ የግራ እጁ ከክንድ በታች ከወሊድ ጀምሮ ስላልነበረ ብቻ ነበር።
ይህ ውሳኔ ሀሳቡን ላመጣው፣ ውሳኔውን ላሳለፈው ግለሰብ ቀላል ሊመስል ይችላል።
ይሁንና ለባለቤቱ፣ ለእናትና አባት፣ ከፍ ሲል ደሞ ለአካል ጉዳተኛው ማህበረሰብ ምን ያህል ከባድ እንደሚሆን አልተገነዘቡትም ነበር።
ከዚህ ጋር ተያይዞ አንዲት ሁለት እግሯ ከጉልበት በታች ሳይኖሯት የተወለደች ህፃን ልጅና እናቷን ሁሌ አስታውሳለሁ።
የሚኖሩት ገጠራማ የሀገራችን ክፍል ውስጥ ሲሆን፣ እናት እግር ሳይኖራት የተወለደችውን ልጅ በማሰብ በማየት ሰማይ ምድሩ ጨልሞባታል። የምታደርገውም ግራ ገብቷታል። ሌላው ይቅርና ሰው እንዳያይባት የፀሀይ ብርሀን እንኳን ለማሞቅ ወደ ውጭ አታወጣትም። ብቻ አንድ ቀን ክእኔ ጋር ተገናኘን።
ቀላል ነው እግር እንሰራላታለን ቆማ ትሄዳለች። አሁን " ዳዴ " ወይም " የምትድህበት " እግር እንሰራላታለን ብለን ሰርተን ሸኘናት።
ያኔ ታድያ ይእናቲቱ ደስታ ልነግራችሁ አልችልም። በዚህ ፅሁፍ እንኳን ለመግለፅ ይከብዳል ቃላትም፣ፊደልም፣ አላገኝለትም።
አሁን ለፍታ ጥራ ታሳድጋታለች። እኛም እግሯን እየሰራን እናሳድጋታለን።
እንዲህ አድርገን አሳድገን ትምህርት ልትማር ስትል፣ ወይም ተምራ ስራ ልትይዝ ስትል፣ አይ አንቺ እግር ስለሌለሽ፣ አካል ጉዳተኛ ስለሆንሽ መማር አትችይም፣ስራ መስራትም አትችይም ተብላ ብትመለስ ለወላጅም ለእኛም የሚሰማንን ስሜት አስቡት?።
የዲያቆን ዶክተር ብንያም ሁኔታ እንዲህ ነበር። ከልጅነቱ ጀምሮ አይዞህ እጅህ ስትወለድ ጀምሮ ባይኖርህም ምንም ችግር የለውም እንድያውም ጎበዝ ተማሪ ሆነህ " ሀኪም፣ዶክተር " ትሆናለህ ተብሎ ተምሮ አድጎ ለህክምና ትምህር የሚያስፈልገውን ውጤት አምጥቶ፣ ለዛውም በሀገሪቱ አንጋፋና እውቅ አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ዩኒቨርስቲ ገብቶ አምስት ዓመታት ያህል ተምሮ፣
የለም የለም አንተ በቃ እጅ ስለሌለህ ይህንን ትምህርት መማር አትችልም፣ እና አቋርጥ። ሲባል የሚደርስበትን የህሊና ህሙም አስቡት።
የሆነው ሆኖ ጠንካራ እናትና አባት፣ እንዲሁም ተቆርቋሪ ማህበረሰብ ስላለው ትምህርቱን ቀጥሎ አሁን ላይ ትምህርቱን በስኬት አጠናቆ ለመመረቅ በቅቷል።
ዛሬ በነ ዲያቆን ዶክተር ብንያም ቤት ደስታው እጥፍ ድርብ ነው።
ታናሽ ወንድሙ
ከደብረ ብርሀን ዩኒቨርስቲ ተመርቆ ደስታውን ከቤተሰብ ጋር ሆነው እያጣጣሙት ነው።
ዲያቆን በንያም እንዴት ያለ ባለ ስነምግባር ባለ ጥሩ ትህትና ባለቤት መሰላትሁ።
እናም እኛም የደስታው ተካፋይ ሆንን እላችኋለሁ
" ምክረ ሀሳብ ለሁሉም "
ልንገራችሁ
" ማንም ሰው ድንገት አካል ጉዳተኛ ላለመሆኑ ምንም ዋስትና የለውም።" ( አራት ነጥብ)
በመሆኑም ለአካል ጉዳትና ለአካል ጉዳተኞች ልዩ ክብካቤ ማድረግ ዋጋ ያሰጣል እንጂ አያሳንም።
ስለዚህ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ካሏችሁ፣ የስራ ባልደረባ ካሏችሁ ልዩ ክብካብ አድርጉላቸው። ታተርፉበታላችሁ።
ዲያቆን ዶክተር ብንያምና
ከመላው ቤተሰባችሁ ጋር እንኳን ደስ አላችሁ።
ሰሎሞን አማረ
የካቲት 23/ 2017ዓም
Feeling overwhelmed by research? 😩 We're here to help! 🤝 Our research center offers comprehensive support for all your academic needs, specializing in law but covering social fields too. We can assist with:
Proposals: Crafting compelling research proposals. 📝
Full Research Projects: Conducting in-depth research. 🧐
Detailed Research: Providing thorough and comprehensive analysis. 📚
Term Papers & Assignments: Completing high-quality academic papers. ✍️
Exam Prep (Law Focus): Specialized preparation for law exams. ⚖️
Quizzes (All Subjects): Assistance with quizzes across various disciplines. ❓
Consultations: Personalized guidance and support. 🗣
Advisor Feedback Incorporation: Refining your work based on advisor comments. 🔄
PowerPoint Presentations: Creating engaging and informative presentations. 📊
Our Guarantees:
AI & Plagiarism Free: All work is 100% original and plagiarism-free. ✅
Low Cost: Affordable services to fit your budget. 💰
Support & Improvement: We're dedicated to helping you s쳮d. 👍
Special Offer: Refer 50+ people and get a FREE full research sponsorship! 🎉
Contact us today! Let us ease your academic stress and help you achieve your goals. 😊 join as via https://t.me/allresearchcenter
✟"ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጠመቁ ምክንያት ከብሉይ ወደ ሐዲስ፥ ከኦሪት ወደ ወንጌል አሻገረን፤ የመንግሥተ ሰማያትን ደጅ ከፈተልን፤ ወደ ሀገራችን (ወደ ሰማይ) ይጠራን ዘንድ ብቻ ሳይኾን ሊነገር በማይችል ክብር ያከብረን ዘንድም ቅዱስ መንፈሱን ላከልን፡፡"
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
መልካም በዓል!!!
በአካታች ማህበረሰብ ውስጥ ሁሉም አሸናፊ ነው።
የጠፋ id
Abeba Frew
0049/17
ያገኛችሁ ካላችሁ 0945801335 ደውላችሁ አሳውቁኝ ወረታውን እከፍላለሁ
በተቋማት የምልክት ቋንቋ የሚችል አስተርጓሚ አለመኖሩ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ክፍተት መፍጠሩ ተገለጸ
ታሕሳስ 18/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የምልክት ቋንቋ የሚችል አስተርጓሚ አለመኖሩ በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ ክፍተት እየፈጠረ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
መስማት የተሳናቸው ዜጎች ጉዳታቸው አለመታየቱ ለተጨማሪ ጉዳት እየተዳረጉ እንደሚገኙና በተቋማት ላይ የምልክት ቋንቋ የሚችል አስተርጓሚ የማያገኙበት ሁኔታ ስለመኖሩ በኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሄራዊ ማህበር ፕሬዝዳንት ዩሀንስ ተክላይ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንዲሁም ለማብቃት፤ በጤና፣ በትምህርት እና በማንኛውም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ የምልክት ቋንቋን የሚችል አስተርጓሚ እንዲኖሩ አስቻይ ሁኔታን መፍጠር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ማህበረሰብ ማብቃት ማህበር መስራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ትዕግስት አለማየሁ በበኩላቸው፤ ተቋማት መስማት ለተሳናቸው ዜጎች ምቹ አለመሆን፤ የምልክት ቋንቋን የሚችል አስተርጓሚ በተቋማት ላይ አለመኖር፣ በበቂ ሁኔታ የምልክት ቋንቋ ማሰልጠኛ እጥረት እንዲሁም በማበረሰቡ ዘንድ ለመስማት የተሳናቸው ዜጎች ያለው የተሳሳተ ግንዛቤ በዋናነት ለችግሮቹ ተጠቃሽ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
አክለውም ከመስማት መሳን በተጨማሪ ማንበብ እና መጸፍ የማይችሉ ተደራራቢ ጉዳት ያለባቸው ዜጎች ስለመኖቸው ገልጸዋል፡፡
በጤና ተቋማት እና በትምህርት ቤቶች፣ በትራንስፖርት እና በሥራ ቅጥር፣ በሥራ ፈጠራ እንዲሁም በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰጡ አግልግሎቶች መስማት የተሳናቸውን ያካተቱ ሊሆኑ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
ማህበሩ በ2014 ዓም የተመሰረተ መሆኑን ገልጸው፤ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማህበረሰቦችን ማብቃት ላይ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ለአብነትም መስማት የተሳናቸው ሕጻናት ወላጆች የምልክት ቋንቋን መናገር አለመቻላቸው ከፍተኛ አሉታዊ አስተዋጾ በማሳደሩ በተለይም ማህበሩ መስማት በተሳናቸው ሕጻናት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ወላጆች ከልጆቻው ጋር መግባባት እንዲችሉ ለማስቻል ለሕጻናት እና ለወላጆች የምልክት ትምህርት ለማሰልጠን እየሰራበት እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
በአዲስ አበባ 12ተኛ ክፍል ተፈትነው ያለፉ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ሽልማት ተበረከተ
የሴቶችና ሕጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ 2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለተፈተኑ 39 አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት መስጠቱን ገለጸ።
ከተሸለሙ ተማሪዎች ውስጥም 9ኙ ቀጥታ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የተዘዋወሩ ሲሆን የተቀሩት 30 ተማሪዎች በሪሚድያል ውጤታቸውን አሻሽለው ወደ ዩንቨርስቲ እንደሚቀላቀሉ ተናግረዋል።
የአዲስአበባ የሴቶች ሕጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወሮ ገነት ቅጣው " የአሁኑ አመት ካባለፈው አመት የተማሪዎች ውጤት መሻሻል እንደታየና ተማሪዎቹም ያለባቸውን ጉዳት ተቋቁመው ይህን ውጤት በማስመዝገባቸው ሊበረታቱ ይገባል
እንዲሁም ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ የሽልማት መርሐግብራችንንም አካሂደናል" ብለዋል።
በዕለቱም አካል ጉዳተኛ የሆኑ የዮንቪርሲቲ ተማሪ የነበሩ ሰዎች በመገኘት ለተማሪዎቹ ግንዛቤ ማስጨበጥና ከህይወት ልምዳቸውም በማካፈል አካልጉዳተኝነታቸው ከምንም እንደማያግዳቸው መግለጻቸውን አሳውቀዋል ።
በ2016 በአካል ጉዳተኞችና በአይነስውራን የተሰሙ አበይት ክስተቶች
የሰው ልጅ በተለያዩ የህይወት ውጣውረድ ሲያልፍ ኑሮው አሰልቺ እንዳይሆንበት ጊዜን በሴኮንድ፣ በደቂቃ፣ በሰኣት፣ በእለታት፣ በሳምንት፣ በወራትና በአመታት እየከፋፈለ በጊዜ ምሕዋር ይጓዛል።
ባበጀው ጊዜና በወቅቶች ፍርርቆሽ ላይ በመመርኮዝ ግላዊና የወል በአላትን ይዘክራል፡ ያከብራል። እንዲያ እንዲህ እያለ ነባሩን ጊዜ “አሮጌ” ብሎ ሲሸኝ መጪውን ደግሞ በአዲስ መንፈስ ራሱን አድሶ ይቀበላል።
“አዲሱ አመት” ብለን የተቀበልነው 2016 አመት በተራው ደግሞ “አሮጌ” ተብሎ ላዲሱ 2017 አመት ተራውን ካስረከበ 16 ቀናት ተቆጠሩ። እነሆ ዛሬ መስከረም 16 2017 ነውና እንኳን ለመስቀል ደመራ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!!
በ2016 በአካል ጉዳተኞችና በአይነስውራን ዙሪያ የተከሰቱ ሁነቶችን በወፍበረር እንደሚከተለው እንዳስስ።
የአዲስ አበባ የአካል ጉዳተኞች ማህበር ከወረዳ አንስቶ እስከማእከል ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ አዳዲስ አመራሮችን ሾሟል.
ከሞላጎደል “ሰላማዊ ነው!” በተባለው ምርጫ በትምህርት ደረጃቸው የተሻሉና በድምጽ ብልጫ ያሸነፉ አዳዲስ አባላት ተመርጠዋል።
አዳዲስ የአይነስውራን ት/ቤቶች ተገነቡ.
በአዲስ አበባ በአቃቂቃሊቲ ክፍለከተማ በቀዳማዊ እመቤት ጽ/ቤት አስተባባሪነት “ብርሀን የአይነስውራን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት” የተሰኘው ት/ቤቱ በግንቦት ተመርቆ 312 ተማሪዎችን ለመቀበል ክፍት ሆኗል።
በተጨማሪም በቢሾፍቱ/ደብረዘይት ከተማ “ድጋፍና እንክብካቤ” ማእከል ልዩ የአይነስውራን አዳሪ ት/ቤት ገንብቶ በሚያዝያ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል።
የኢትዮጵያ አይነስውራን ብሄራዊ ማህበር የስነጽሁፍ ምሽት አዘጋጀ.
ከቅርብ አመታት ወዲህ “የመጀመሪያው ነው!” በተባለው የስነጽሑፍ ምሽት የማህበሩ አባላትና ተጋባዥ እንግዶች የራሳቸውንና የሌሎች ደራሲያን ስራዎችን አቅርበዋል።
በማህበሩ ጽ/ቤት አዳራሽ በተካኼደው የስነጽሁፍ ምሽት የበርካታ ሙያዎች ባለቤት የሆነው ደበበ ሰይፉ ተዘክሯል።
የእለቱ የክብር እንግዳ የነበረችውና የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ስራአስኪያጅ የሆነችው የዝና ወርቁ የስነጽሁፍ ልምዷን ለታዳሚያን አካፍላለች።
"ከለቻ" መጽሐፍ ተመርቋል።
በአይነስውሩ ጋዜጠኛ ሐብታሙ ባንታየሁ "ከለቻ" በሚል ርዕስ የተጻፈ መጽሐፍ በጳጉሜ 3 2016 በብሔራዊ ቤተመዛግብት እና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር ) ብላቴን ጌታ ህሩይ ወ/ሥላሴ አዳራሽ ውስጥ ተመርቋል።
"ከለቻ" መጽሐፍ በዘውግ በኩል ረጅም ልቦለድ ሲሆን በ5 ምዕራፎች ተከፍሎ፣ በ96 ገፆች ተቀንብቦ በ200 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።
በዚህ መጽሐፍ የምርቃት ሥነሥርዓት ላይ ፀሐፌተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ ደራሲ ጌታቸው በለጠ እና ሌሎችም ሀሳቦቻቸውን አጋርተዋል።
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን “አ.ሚ.ኮ” የሚሰራው ጋዜጠኛ ሐብታሙ ባንታየሁ በ2012 “እየሞኸረሩ መሀይም” የተሰኘ መጽሐፉን አሳትሞ ነበር።
በስፖርቱ ዘርፍ ያለውን ጉዳይ ስንዳስስ በፓሪስ ፓራል ኦለምፒክ ትእግስት ገዛኸኝ በ1500 ሜትር ከፊል/ጭላንጭል አይነስውራን ውድድር ወርቅ አግኝታለች። በፈረንጆቹ አቆጣጠር በቶክዮ 2021 በተካኼደው የፓራል ኦለምፒክ በተመሳሳይ ርቀት አሸንፋለች።
ኢትዮጵያ በታሪኳ በ1500 ሜትር ከፊል/ጭላንጭል አይነስውራን ያገኘችው ወርቅ ሜዳሊያ ሁለት ሲሆን ሁለቱንም ወርቆች ያመጣችው ትእግስት ገዛኸኝ ናት።
በፓሪስ 2024 የፓራል ኦለምፒክ ያየሽ ጌቴ በ1500 ሜትር ሙሉበሙሉ አይነስውር “T11” በተደረገው ውድድር አራት ደቂቃ 27 ሴኮንድ 68 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት ውድድሩን አሸንፋለች።
ያየሽ ጌቴ በጃፓን ኮቤ 2024 የአለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ውድድር በራሷ ተይዞ የነበረውን “አራት ደቂቃ 31 ሴኮንድ” የአለም ሪከርድ በአራት ሴኮንድ በማሻሻል የበላይ ሆናለች።
በሌላ በኩል በስድስት ኪሎ ጥር 18 2016 ከማርቆስ ቤተክርስትያን ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ሲሻገሩ ሶስት ሴት የአዲሳባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በደረሰባቸው የትራፊክ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሶስቱም ተማሪዎች አዲስ ገቢዎች ነበሩ። የአንደኛዋ ተማሪ ህይወት ወዲያውኑ አልፏል።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 Monate, 3 Wochen her
Last updated 2 Monate, 2 Wochen her
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 Monat, 2 Wochen her