እየኖሩ መሞት🤍🦋

Description
ℎ𝑒𝑦 ʷᵉˡᶜᵒᵐᵉ ᵗᵒ ᵐʸ ᵒᶠᶠⁱᶜⁱᵃˡ ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ 📖😊
#አንብበን ከወደድናቸው መሀል ወይም ካሳለፍናት ህይወት የተማርነውን share እንደራረጋለን ! ֶָׁ֪𓆩♡𓆪

# መድረሻህን ሳታልም ጉዞ አትጀምር ፤ መኖርህን ሳታውቅ አትሙት። 𝆬 ׁ ֶָ֪ 𓆩♡𓆪 ህይወት ዛሬ ናት !
✍ ✨ @Mapoem2 𝆬 ׁ ֶָ֪ 𓆩♡✨

👇✨🖤👇
@Mapoem2
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago

2 months ago

[በዓል አንወድም
       ፡
       ፡
ቢጫ መሬት
ህይወት ግን እንደሬት

አበባ ሙሉ ሜዳ
ህይወት ግን እንግዳ

ኩበት እና ውበት
ህይወት ሀዘን ሽበት

"እንኳን አደረሰን" ተባብለን
የሆነ የሚከፋን ነገር አለን

ከውስጣችን እንደታመቀ
አልቅሰነው እንዳላለቀ
ወልደነው እንዳልተመረቀ

            ብቻ
በዓል አልወድም የሚስብለን
       አንድ ነገር አለን::

መሬቱን ቢጫ ወርሶት
እኛ ደሞ ትንሽ ብሶት

አናለቅሰው ነገር ተድላ
ጠማን አንል ነገር ጠላ ተደላድላ

ራበን አንል ምን ተብሎ
መሶቡ አልከደን ብሎ

ምን እንደቸገረን ባናውቅም
በዓል  ግን አንወድም፡፡

ከጠላ የቀረረ
ከመውረድ የቀረ

ዕንባችንን ዋጥ አድርገነው
ሲጨፍሩ ለይመሰል ትከሻችንን ነቅንቀነው

ሲስቁ የምንስቀው
ሲቀርቡ የምንቀርበው
(ይምሰል ነው
ቢጤ ለመሆን ነው)

እዛና እዚህ ሚያስረግጠን
                 እዚያና እዚህ ሚረግጠን
                               ፡
                               ፡
                      ከትናንት - እውርርርርር
                      ከትናንት - ስብርርርርር
                      ከትናንት - ሽንክልልልል
     ትንሽ መከፋት አለን የልጅ 'ዲምፕልን' የሚያክል ፡፡

ኤልያስ ሽታኹን](http://t.me/Mapoem2)

2 months ago

Selam selam🖐🖐

እነሆ የምርጥ ምርጥ channal ተከፈተ👍
👉የዚህ channel አላማው

👉 የ ስዕሎች ልምድ መለዋወጥ 👨‍👧‍👦🌇
👉ስዕሎችን መገምገም🌉
👉የ ስዕሎች ውድድር 🏞🏞🏞
👉የ ስዕል ቀለማት...🎇🎇🎇

እና ሌሎችም ይዘቶች ያሉት ምርጥ channel ነው። 🙏🙏🙏

@hb_art_27👈
@hb_art_27👈
@hb_art_27👈

ለበለጠ መረጃ @huuuund ያናግሩኝ

ጥበብ የምታደንቁ ከሆነ
#share #share #share

2 months, 2 weeks ago
4 months, 1 week ago

#መናገርም መፃፍም ከምችለዉ በላይ የቃላቶች ጋጋታ ከሚገልፁት በላይ ነው የናፈከኝ?, ግን ላይህ አልመጣሁም ያዉ ሰው ማየት አስጠላኝ እና አልመጣሁም መጥላት ስልህ ያው መራቅ መርጬ  እንጂ ሌላ ነገር አስቤ አደለም? በማይሆን ሰአት  መጣህ በዝምታ አትመጣም ብዬ መኖርን ቀጥዬበት ነበር በጠላሁክ እላለው ግን እኔንጃ  እድሉንም ባገኝ ማደርገው ግን አይመስለኝም ያው ታውቅ የለ ሰው መጥላት አልችልም አንተን ደሞ መጥላት እና መጉዳት ማይታሰብ ነው ❤️‍? የወደድኩህ መስፈርት አውጥቼ አልነበረም እንዲ አርግና ሁን ብይህ አላቅም አደል ላንተ ያለኝን ስሜት አንተ ብቻ ሳትሆን እኔም አይገባኝም? ተመፃደኩብህ እንዴ በርግጥ ፊትህ ቆሜ እንዲህ እንደማልልህ እና አቅሙም እንደሌለኝ ታውቃለህ ያው በፁሁፍ  ስለሆነ ቀሎኝ እንጂ? እሱ እየጠራሁት አይሰማኝም እየነገርኩትም ቢሆን አይረዳኝም ለዛም ነው ከሰው ጋር መኖር  አሁን ላይ ሚከብደኝ ሁሉም እንዳንተ ነው ሚመስለኝ,,
?እሚመጣ እንጂ እማይቆይ?

4 months, 2 weeks ago

ሰፈራችን ቢራ ቤት አለ ሸምገል ያሉ ጃኬት ሹራብ ያደረጉ ጠና ያሉ ሰዎች በረንዳ ላይ እየጠጡ ቁጭ ብለው ያወጋሉ ...
እኛ ከትምህርት መልስ ኳስ እንጫወታለን !
ሰፈራችን ቤርጎ አለ ጥንዶች  ተቃቅፈው  ተረጋግተው እያወጉ እየተሳሳሙ እየተሽኮራመሙ ፣ አልጋቤት ገብተው ይወጣሉ እኛ እርግጫ ላይ ስለምንሆን ወይ ሲገቡ ወይ ሲወጡ እናያቸዋለን ፦

እቤት ስንገባ ታላላቆቻችን ዜና ጓጉተው ያያሉ ይወያያሉ ዜናውን እያዩ ትክዝ ግርም ይላቸዋል ፦

"ዜና አሁን ምኑ ይታያል ?"
ይላል ልጅነታችን

እኛ ድራማ ፣ፊልም፣ Wrestling ፣ታላቅ ፊልም፣ኳስ፣ ህብረት ትርኢት ለማየት እንጠብቃለን እንቅልፍ አሸንፎ ካልጣለን ፦
ማታ ያየነውን ከጓደኞቻችን ጋ እንቀዳለን
"እከሌ እከሌን ወደደ ፣ እከሌ እከሌን ካደችው፣ ካዳት ፣አስረገዛት  ፣እከሌና እከሌ  ተጋቡ፣ ወለዱ" ብለው ያወራሉ እንሰማለን ብዙ ትርጉም አይሰጠንም ።

እኛ ትርጉም የሚሰጠን  ኳስ ፣ እርግጫ ፣ብይ፣ቆርኪ ፣ ሌባ እና ፖሊስ ፣ቃጤ ቃጤ ፣ በረዶ ፣ጠጠር ፣  ሱዚ.... ነበር

ስጋታችን እዛ ሰፈር የተጣላነው ትንሽ ልጅ ፣ በቴስታ የሚማታው ጓደኛችን ፣እምትቧጨረው ጓደኛችን ፣ እዚ ጋ አትጫወቱ የሚሉት ሴትዮ ፣ "ሲጫወቱ አጥሬን መቱብኝ "ብሎ ለቤተሰብ የሚከሰን  ሰውዬ ... ጨዋታ አትጫወቱም አጥኑ የሚል  የቤተሰብ ክልከላእና ጡጫ ፣ ለበዓል የሚገዛልን ልብስ ....
እምንፈራው በተረት የሰማነው አያ ጅቦ ..ስጋታችን በጨለማ  ለሽንት ስንወጣ የምንሰማው ኮቴ ነበር
ማደግ  ያጓጓንም ነበር ።

አደግን ፦

መጠጥን ቀመስነው ...
ቤርጎውን አየነው ...
ዜናውን ተራቆትንበት ...
ተካካድን ....

የማናቀው ነገ አስፋራን ፣ ማደጋችን አስደነገጠን ፣ ትልቅ ሰውዬ ነው ያልነው ሰው እድሜ የኛ ሆነ።
ልጅ ሆነን የምናዉቀው አለም ተቀየረ !!

# ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! ??

4 months, 2 weeks ago

* ? ጓደኛ ማለት ረጅም ጊዜ ያወቅከዉ ሰው ሳይሆን ወደ ህይወትህ መጥቶ በደስታህ ተደስቶ በሐዘንህ ‹ከጎንህ ነኝ› ብሎህ የደገፈህ ማለት ነዉ፡፡
ያው መጠቃቀም ስለሆነ ሁሉም ግኑኝነት
?*?‍♀

◈ በልብ ለልብ መገናኘት እንጂ በጊዜ ብዛት የሚመጣ አይደለም።

? # ማንኛዉንም ሰው አለመጠን አትደገፍ ፤ በጣም ከተደገፍክ ብዙ ትጠብቃለህ ብዙ መጠበቅህ ደግሞ ጥልና ሀዘን ውስጥ ይከትሃል፡፡**@Mapoem2@Mapoem2@Mapoem2@Mapoem2@Mapoem2

4 months, 2 weeks ago

? ብዙ ጊዜ ከምንወዳቸው ሰዎች የተሰጡን ትንንሽ ነገሮች ከነበሩን ውድ ነገሮች በላይ ዋጋ ያላቸው ይሆናሉ።
# ምክንያቱም እኛ ዋጋ የምንሰጠው ለስጦታዎቹ ሳይሆን ለስጦታዎቹ ባለቤቶች ስለሆነ ነው!!!!
በዋጋ ሲተመን ትንሽ ዋጋ ያለው ስጦታ
በዋጋ የማይተመን ስሜትን ያንፀባርቃል!!!?
@Mapoem2@Mapoem2@Mapoem2@Mapoem2@Mapoem2

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago