ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago
#በሀገርና በህዝብ ሀብት የተቋቋመ የሀገርና የህዝብ ተቋምን እንደ ራሳቸው የአባታቸው ውርስ አድርገው በሚያዩ የሀገር መሪዎች ባሉበት ሀገር የተቋም ክብርና ልእልና ተጠብቆ ሊቀጥል ይችላል ብሎ ማሰብ ዘበት የሆነበት ዘመን ላይ ነን!
#የዛሬ የየካቲት 2,2017 ዓም የእሁድ ጠዋት የሪፖርተር ጋዜጣ የፊት ገፅ: –
"የተሰደዱ ፖለቲከኞችን ከመንግስት ጋ እንዲነጋገሩ ለማድረግ ጥረት መጀመሩ ተነገረ ~ የሚል ርዕስ ያለው ወግ ይዞ ወቷል። ለምርጫ ግርግር ~ preseason chirographic theatrical acting ~ እየተጀመረ ይመስላል።
#በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከፈጣሪ የተቀባነን በማለት ያለ ምርጫ ራሳቸውን በህዝብ ላይ የጫኑ መሪዎች ነበሩ የተባሉትን ከስልጣን በማውረድ በዲሞክራሲ፣ በነፃ ምርጫና በህዝብ ይሁንታ ወደ ዘመናዊ ፖለቲካ መረማመድ የሚቻል መሆኑ በተሰበከንና በነገሩን መሰረት የተጀመረው የኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ አብዬት ተስፋ የተጣለበት የምርጫ ፖለቲካ ጉዳይ ዘመናትን ተሻግሮ ይህ ነው የተባለ ስር ነቀል ለውጥ ለማሳየት የተቸገረበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
#በሀገር አስተዳዳሪነትና በመንግስትነት ስልጣን ያለ ምርጫ ራሳቸውን ህዝብ ላይ የጫኑ እና በህዝብ ምርጫ ወደ ስልጣን የመጡ በሚለው ሀሳብ መካከል ያለው አንኳር የሀሳብ ልዩነት ድሮ ድሮ የመንግስትነት ስልጣን የመያዣ መንገድና ሂደትን የሚመለከት ጉዳይ ይመስል ነበር። በእርግጥ በሰለጠነው አለም ለመንግስትበት በሚደረገው ምርጫ ትግል ውስጥ ሂደቱና ዉጤቱ ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዬች ናቸው። በኛ ሀገር ፖለቲካ ግን ሂደቱ ላይ እንጂ ውጤቱ ላይ ብዙም ለውጥ ያለው ጉዳይ አይደለም።
#ምክኑያቱም ያለ ምርጫ ራሳቸውን በህዝብ ላይ ይጭኑ የነበሩ መሪዎች ችግር ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ የሚያቆያቸው መንገድ በመሆኑ ይተቹ የነበሩት ፖለቲካ እንደ እኛና አብዛሀኛው አፍሪካ ሀገራት በህዝብ ምርጫም ወደ ስልጣን መተው ለረጅም ጊዜም ስልጣን ላይ የሚቆዩበት ፖለቲካ ውስጥ የህዝብ ምርጫ የባለስልጣኖቻችንን ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ የመቆየት ችግር የሚቀርፍ ሆኖ አልተገኘም። ልዩነቱ ያለው የስልጣን ምንጩ ትርክት ላይ ብቻ ነበር። ያለ ህዝብ ምርጫ ወደ ስልጣን ይመጡ የነበሩ መሪዎች የስልጣናቸው ምንጭ አንዳንዶች መለኮታዊ ምንጭ ፣ሌሎች ወታደራዊ ጥንካሬያቸው እንደሆነ ሲገልፁ፣ በምርጫ ወደ ስልጣን የመጡበት ደግሞ የስልጣን ምንጫቸው የህዝብ ደምፅ እንደሆነ ሲናገሩ የሚታወቅ ጉዳይ ነው። ነገር ግን የምርጫ አለመኖር ረጅም የስልጣን ዘመን ኮርቻ ላይ እንዳስቀመጣቸው ሲነገር የነበረው ፖለቲካዊ ችግራችን የህዝብ ምርጫ አለ በሚባልበት ዘመንም ምርጫ ረጅም ዘመን ስልጣን ኮርቻ ላይ የመቀመጡን ሂደት ያስቀረ ሆኖ አልተገኘም። የተቀየረው ነገር ውጤቱ ላይ ሳይሆን ሂደቱ ላይ ያለው ትርክት ብቻ መሆኑ መቼም ሁላችንም ምስክሮች ነን።
#ከዚህ አነፃር ካየነው የባለፈው የበላዔ ሰብዕ_አብይ አህመድ ምርጫ ለጭራቁ_አብይ አህመድ ባለፉት አራት አመታት በህዝብ ድምፅ የተመረጥኩ መሪ ነኝ የሚለውን ~ leverage ~ ይዞ ያሻውን የሚፈፀም መሪ ከማድረግ ውጭ ምርጫው ለፖለቲካችን የጠቀመው አንኳር ጉዳይ አልነበረም። ይህ በህዝብ ድምፅ የተመረጥኩ ነኝ የሚለው መሳሪያ በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ ከወገንተኝነትና ከፓርቲ ፖለቲካ ነፃ የሆኑ ተቋማት መኖር አለባቸው የሚባለውን ህግ ሁሉ አፈር ድሜ በማብላት እንደ ፍርድ ቤቶችና መከላካያ ሰራዊት የመሰሉ ተቋሞች ሁሉ የተቋም ክብራቸውን ገፈው የፓርቲ ፖለቲካ መጠቀሚያ የሆኑበትን አራት አመታት አይተናል።
#አሁን ምርጫ የሚባለው ጉዳይ የቀረው አንድ አመት ነው ተብሏል። ባለፉት አራት አመታት አብይ አህመድ:–
#ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ሽባ አድርጓል
#ማሰር የቻለውን ሁሉ የተቃውሞ ድምፅ አስሯል
#ማሳደድና ከሀገር ማስወጣት የቻለውን ሁሉ አሳዶ ከሀገር አስወጥቷል
#በበላዔ ሰብዕ_አብይ አህመድ የስጦታ ስልጣን ወንበርና ስኳር መታለል የቻለውን ከእስርና ስደት መልስ ያለውን የተቃውሞ ድምፅ ሁሉ በወንበር፣ሰልጣንና ስካር ፖለቲካ የብልፅግና ለማዳ አዳሪ አድርጓቸዋል
#ይህ በተቃውሞ ጎራ ያለውን አካል ሽባ ያደረገበት ፖለቲካ ሲሆን ሀገሪቱ ካለባት ዘርፈ ብዙ ችግሮች አንፃር በመርህ ደረጃም ከ ~ priority ~ መርህ በተቃርኖ በመቆም
#የኮሪደር ልማቶችን ሰርቶ
#ሪዞርቶችን ገንብቶ
#የዋና መንገድ ዳር አስፓልቶችን በመብራት አንቆጥቁጦ
#የውሀ ፋውንቴኖችን ትክሎ
#የብልፅግና ፓርቲ ስምና ዝና እንዲሁም ገፅታ ለመገንባት ብዙ ስራዎችን ለመስራት ጥረት ተደርጓል።
Now
#ዛሬ የሪፖርተር ጋዜጣ በዘገባው ባቀረበው ዜና መሰረት፣ ባለፈው በብልፅግና ጠቅላላ ጉዳኤ ጭራቁ_አብይ አህመድ ብዙ ብስራቶች ይኖራሉ ያለውን ንግግር ወስደን ካየነው ከሀገር እንዲሰደዱ የተደረጉት ፖለቲከኞች ወደ ሀገር ተጠርተው፣በሀገር ውስጥም በእስርና በግዞት ላይ ያሉት በምህረት ስም ተለቀው፣ ከብልፅግና ፓርቲ ውጭ ሆነው ነገር ግን በስጦታ ስልጣን የብልፅግና ፓርቲ አገልጋይ ሆነው የከረሙት የተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች ወደ እናት ፓርቲያቸው ተመልሰው የተቃዋሚ ጎራው በባለፈው አራት አመት ምንም አይነት ስራ ሳይሰራ ቆይቶ በቀሪው አንድ አመት ህዝብ አደራጅተው የሚቀጥለው ምርጫ ለሂደቱ ሽር ጉድ ካልሆነ በስተቀር በውጤቱ ላይ ለውጥ ያለው ነገር ይኖራል ብሎ መጠበቅ አስቁኝ ጉዳይ መሆኑ የማይቀር ነው።
#ባለፉት አራት አመታት የተቃዋሚ ጎራውን አስረህ፣ የሚሳደደውን አሳደህ፣ ወንበርና ስልጣን የሚፈልገውን በወንበር በስልጣን በመደለል አማራጭ ሀይሎችን ሽባ አድርገህ በሌላ በኩል የብልፅግና ፓርቲ ምንም እንኳ የህዝብ ኑሮና የኢኮኖሚው ጉዳይ አረንቋ ውስጥ እያስገቡም ነገር ግን በህዝብ አይን ውስጥ ለምስክርነት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን በሙሉ አቅማቸው ሲባዝቡ ኖረው በህዝብ ፍርድ አይን ውስጥ እኔ ይሄን ሰርቻለሁ እናንተ ምን ሰራችሁ ሊባል በሚችል ተጠይቅ ነጥብ ለማስቆጠር በሚያስችሉ ጉዳዬች ውስጥ በከረመ መንግስትና ባዶ እጁን በከረመው የተቃውሞ ጎራ መካከል ፍትሀዊ የምርጫ ፉክክር ይኖራል ተብሎ ማሰብ ኢሞራላዊ ጉዳይ ነው።
#አማራ ለአማራነቱ ነው እየታገለ ያለው በሚለው ሀሳብ ዙሪያ ጥርጣሬም፣ክስም ሆነ ወይም ያ ለምን ሆነ ብሎ ሊጠይቅ የሚችል አካል ቢኖር አማራን ለምን በአማራነትህ ትታገላለህ የሚለውን ጥርጣሬ፣ከስም ሆነ ሌላ ነገር ይዞ አማራን ከመጠየቁ በፊት አማራ ወደዚያ መንገድ ለገፉት በደሎችና መከራዎች በሙሉ ጠያቂው ራሱ ህያው ምስክር ነበር።
#ችግሩ ለአማራ መከራና በደል ግዴለሽነት ይሁን ወይም መታበይ ግልፅ የሆነ ነገር የሌለ በሚመስልበት መንገድ አማራ ለአማራነቴ እየታገልኩ ነው የሚል የትግል መርህ ይዞ የተጥቅ ትግል እያደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ከብዙው በጥቂቱ መናኛ ጣያቄዎች ወይም ጥርጣሬዎች ውስጥ ኢትዮጵያዊነትስ በሚል የሚቀርበው ጥያቄ አንዱ ነው።
I say ~ What about Ethiopian-ism?
#ዛሬ አማራ የህልውና አደጋ ለወደቀበት አማራነቴ እየታገልኩ ነው ብሎ የወደቀበትን አደጋ አንድ ሁለት ብሎ ዘርዝሮ አቅርቦ ግልፅ ያደረገ ቢሆንም ያንን የህልውና አደጋ ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ አማራ መልስ ላላገኘለት ጥያቄ የትጥቅ ትግል ላይ ባለበት ወቅት የአማራ ህዝብን ትግል ለማንቋሸሽ ወይም ጭቃ ለመቀባት ተገቢ ያልሆነ ~ counter questioning argument ~ በተለይ What about Ethiopian-ism የሚል ወንጋራ ሀሳብ ሲቀርብ እስኪ እናንተን ኢትዮጵያዊ አማራን ሌላ ሊያደርገው የሚያስችለው ~ if they have ~ a million reason ~ ወዲህ በሉ ብትላቸው ሊጠቅሱት ከሚችሉት ነገር ውስጥ አማራ በአንዱም አንሶ የሚገኝበት አንዳች ጉዳይ አይኖርም።
#ችግሩ ይሄን አስረግጦ መናገርም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለአማራ ሲሆን ሀጥያት የመሆኑ ጉዳይ ነው።
#ፋኖዎች ሆይ: –
የህልውና ትግላችን ወደ ህልውና ትግል እንድንገባ በገፉን ሰዎች ጥያቄም ሆነ ሙግት ~ justify ~ አይሆንምና ለጉንጭ አልፋ ክርክር ጊዜ ሳትሰጡ ወይማ ለማስረዳት ሳትደክሙ ወደፊት ብቻ ነው።
#የኛም የአማራ ህዝብ ነገር ተመሳሳይ ነው። ወያኔ በጫካ ዘመን በአማራ ህዝብ ላይ የነበራቸው ጥላቻ 1983 ስልጣን ላይ ወተው የፖለቲካ ስልጣን እስከሚጨብጡ ድረስ ምንም ነገር አልፈጠረም ነበር። ስልጣን ላይ ሲወጡ ~ prejudice +power = Racism ( በኛ ሀገር ~ ethnic racism) የሰጣቸውን ሀይል ሀይል ጨምረውበት በ27 የስልጣን ዘመናቸው የፈፀሙት በደል፣በባለፈው ጦርነት ወደ አማራ ክልል ባደረጉት ወረራ ህዝባችን ላይ የፈፀሙት ሰይጣናዊ እብደትና አሁን በዚህ ሰሞን በአብይ አህመድ የሚመራው የማእከላዊ መንግስት አይዞህ ባይነትና ድጋፍ ቀጣይ ወረራ ለመፈፀም ያላቸውን ፍላጎት አካቶ ስልጣን ከመያዝና ስልጣን ከያዘ አካል ጋ በመመሳጠር የተፈፀመ ዘረኝነት ሆኖ ተመዘገበ። የኦነግም ያም ነው።ኦነጎች ድሮ ስልጣን በጨበጠው ወያኔ ተመርተው ፣ዛሬ እነሱን የሚስል የሀገሪቱን ስልጣን በመጨበጠ ሰው ስር ተደብቀው~ with political impunity and with total delibrate directtives የ prejudice + power ሰይጣናዊ ግብር በህዝባችን ላይ እየፈፀሙበት ለመሆኑ ሁሉም ምስከር ነው። ይሄን ግፍ ለማስቆም አማራው ሲሰባሰብ as if we have prejudice + power እጃችን ላይ እንዳለና የአማራው ህዝብ ራሱን ለማዳን መሰባሰቡ የፈጠረው ቀውስ ያለ ይመስል በራሳቸው ልክ በመለካት አማራውን በአማራነቱ መቆሙን ፅንፈኛ ብሄርተኛ በሚል የተያዘው ፍረጃ ከሞራልም ሆነ ከምንም አንፃር በፍፁም ውሀ የማያነሳ ክስ መሆኑን ለማሳየት ከብዙ ታሪኮች ውስጥ ከላይ በዶር ኻሊድ የቀረበው ትንታኔ የኛን ሀገር የፖለቲካ እብደት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ሀቅ ነው።
#በዚያው ቃለ ምልልስ ላይ ከተመልካች ከቀረቡ ጥያቄዎች ውስጥ ጥቁሮች የከለር ፖለቲካ ላይ ብቻ ትኩረታችሁን ከምታደርጉ ለሁሉም ህዝቦች total liberalization በአሁን ሰአት ባረጋገጠችው አሜሪካ ውስጥ እኩልነትን፣ነፃነትና ፍትህን ለማስፈን ለምን አትሰሩም? የጥቁሮች መብት፣የጥቁሮች ምናምን እያላችሁ ዘር ላይ ከተቸከላችሁ reverse racism ን እናንተስ እየጫወታችሁ አይደለም ወይ የሚል ጥያቄ ነበር የቀረበላቸው?
ተመሳሳዩ ጥያቄ በሀገራችንም ፖለቲካ ውስጥ የተለመደ ነው። የብሄር ፖለቲካን መጫወት ወያኔና ኦነግ ወይም ሌሎች የተወቀሱበትን ነገር መድገም ወይም በነሱ የጥላቻ መንገድ መጓዝ አይሆንም ወይ የሚል ጥያቄ በኛም ወገኖች ዘንድ ሲነሳ ይታያል። ይህ ጥያቄ ልክ ሊሆን ይችል የነበረው የብሄር ፖለቲካን እጠየፋለሁ ለሚል ቡድን የብሄር የፖለቲካ ድርጅቶችን በአቅምም ሆነ በመዋቅር challenge ሊያደርግ የሚያስችል የፖለቲካ መታገያ ሜዳና ይሄን የሚያበረታታ የመንግስት ፍላጎትና ቁርጠኝነት ሲኖር ነበር። በኛ ሀገር ወያኔዎችም ሆኑ ኦነጎች ወይም ሌሎች ያሉበትን የብሄር ፖለቲካ አልደግፍም ሆነ ወይም በነሱ መንገድ አልጓዝም ብትል የሚገጥምህ ተከራካሪ የሌለህ ምንም አይነት political leverage የሌለህ አቅመ ቢስ መሆን ነው። ለዚህ የኛ የአማራ ህዝብ የደረሰበት መከራና የዜግነት ፖለቲካ እናራምዳለን የሚሉ ነገር ግን እስከ አሁን ድረስ ምንም አይነት የፖለቲካ ተፅእኖ መፍጠር ያልቻሉት የነ ዶር ብርሀኑ ነጋና፣የነ ልደቱ አያሌው፣የነ ታማኝ በየነ ያለፉት የ34 አመት የፖለቲካና የአክቲቪዝም የህይወት ጉዟቸው ምስክር ነው።
Hearken unto me, my people:–
የማንም ጩኸትና ዘለፋ ሳይረብሸን በአማራነት ብቻ በአንድነት ከመታገል ውጭ አማራጭ የሚሆን መንገድ የለም።
(Prejudices + power = Racism)
(ጭፍን ጥላቻ + ስልጣን = ዘረኝነት)
=========================
#የአማራ ህዝብ በዘርና በቋንቋ በተሸነሸነ ሀገር ውስጥ የዘርና ቋንቋ ፖለቲካ ትሩፋቶች ከሚያስገኙት ጥቅም ይልቅ የሚፈጥሩት ችግር የበለጠ ነውና በዚህ ከረጢት ውስጥ ተሰፍቼ ከመኖር ይልቅ ሀገራዊ ራእይ ባለው የዜግነት ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎየን ማድረግ እመርጣለሁ ባለበት ጊዜ ውስጥ በታሪክ የመዛግብት ገፅ በተመሰከረና መሬት ላይ በእውኑ አለም ተፈፀም ባየነው ግፍና መከራ ልክ የተረፈው ነገር የዘርና ቋንቋ ፖለቲካ ከሚያስገኙት ትሩፋቶች ተጋሪ መሆንን ሳይሆን በዘርና ቋንቋ የተሸነሸነው ፖለቲካ ጥቅም ያስገኘላቸው አካላት ለብቻው ተለይቶ እንዲጠቃ የሚያደርግ ፖለቲካን ነበር የመሰረቱት። ከዚያም ህዝባችን በጊዜ ቀመር ውስጥ በሚቀያየሩ መንግስታት ልክ ሊፈታ የማይችል መከራ እንደወደቀበት ተረድቶ ለዚያ የሚመጥን የአቋም ሽግሽግ ሲያደርግ በዘርና ቋንቋ በተሰፋው የዘር ፖለቲካ ውስጥ የአንደኛነት ዜግነትና የብሄር ፖለቲካ መልካም ፍሬዎችን ተቋድሰው ፣ጊዜ በሰጣቸው ስልጣን የሀምሳ አምት ወልጋዳ ትርክት ፍሬ የሆነውን የበቀል በትራቸውን በአማራ ህዝብ ላይ ባሳረፉ የብሄር ፖለቲከኞች ጫማ ልክ አማራን በመለካት አማራ ለህለውናው የሚያደርገውን ትግል ማራከስ የጠላቶቻችን ዋነኛ አጀንዳ ከሆነ ቆየት ብሏል።
Dr. Khalid Muhammed በጥቁር አሜሪካውያኔን የእኩልነት ትግል ውስጥ በ 1980 እና 1990 ዎቹ በ black panther እና ከዚያም በ Nation of Islam ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ እስከ መሪነት የደረሰ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረጉ ሰው ነበሩ። እንደ እኤአ አቆጣጠር በ1994 በአሜሪካ ዝነኛ የቴሌቪዥን Host ከነበረው ሚስተር Phil Donahue show ጋር በነጮች ዘረኝነትና በጥቁሮች የነፃነት ትግል ዙሪያ ከተለያዩ ክፍል የተሰባሰቡ ሰዎች በተገኙበት መድረክ ትልቅ ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር። ጥቁር አሜሪካውያን በጥቁርነታቸው የሚደርስባቸውን ዘረኝነትና የፖለቲካ በደል ለመታገል የተሰባሰቡት በዘር መለያቸው በጥቁርነታቸው ነበር። ጥቁርነትን ይሰብካሉ። በጥቁርነታቸው የደረሰባቸውን በደል ዘርዝረው ህዝባቸውን ያስተምራሉ። ጥቁሮች በጥቁርነታቸው እንዲሰባሰቡና በጥቁርነታቸው ቆመው እንዲታገሉ ያነቃሉ፣ ይመክራሉ፣ ህዝባቸውንም ያስተምራሉ። ይህ በሌሎችዘንድ አልተወደደም።
እናም በ Phil Donahue በሚዘጋጀው Phil Donahue show ላይ አንዱ የሚከተለውን ጥያቄ ጠየቀ።
"Are we going to preach hate, or Are we gonna have a race war? Where are we going, or what would you like to do or promote? Where do you think we should go? " የሚል ነበር ጥያቄው።
"We are told by the honorable minister Luis Farrakhan to show courtesy, respect, and kindness. To be polite to all people as long as they are courteous and respectful, kind and polite to us. But we must look at the fact that we don't teach hatred. Everywhere we go as black people we face hatred. Look at it, look at it. Angels food in white people is a white cake, devil food in cake is you said black, you wear white clothes at weddings and black at funerals. Blackball, blackmail. Our won babies according to behavioral scientists, our baby girls, when confronted with choosing between a black doll and a white doll, there has been so much damage done, they chose the white doll and say the black doll is ugly. So, Racism is everywhere and it is institutionalized. We (blacks) can't be racist. Because racism is prejudice power. Nothing I say up here or anywhere in the world will impact any white fox audience on your job, in politics, in economics, in housing, in society. We don't have the power to do that. So we can't be racist. Do you know what I am saying? " በማለት ነበር ማብራሪያቸውን የጨረሱት።
#ይሄን ጉፋይ በቀጥታ ወደኛ ሀገር ስናመጣው አማራ ላይ የተሰራው ethnic discrimination ነው። አማራ በብሄሩ ከሌላው ተለይቶ በማንነቱ፣በዘሩ በቋንቋው፣ በአለባበሱ፣ በባህሉ፣በሀይማኖቱ፣ በርስት፣በቦታው እና በአጠቃላይ በአማራ በሆነ ነገር ላይ የተፈፀመ ፍፁም ወንጀል የሆነ ነገር ነበር የተሰራበት። እና አማራ ታግሶ፣ታግሶ ሁሉንም አይነት መከራ ተሽክሞ፣ተሽክሞ ሌላው ቢቀር የተለወጠ መንግስትና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ተደረገ በተባለበት ሀገር ውስጥ የማይለወጥና በጥላቻ የታወረ ማእከላዊ መንግስትም ሆነ ሌሎች የፖለቲካ ተዋንያን ባሉበት ሀገር ውስጥ አማራ ጥቁር አሜሪካውያን በጥቁርነታቸው ቆመው መታገል እንደጀመሩት ሁሉ ከእንግዲህ በቃኝ ብሎ በአማራነቱ መሰባሰብ ሲጀምር የጥቁር አሜሪካውያን መሰባሰብና በጥቁርነታቸው መቆም ያስፈራቸው አካላት "የዘር ጦርነት ልትጀምሩ ነው ? ፣ ጥቁር ጥቁር እያላችሁ ጥላቻን እየሰባካችሁ ነው? ወይስ ምንድን ነው ብለው ማሸማቀቅ እንደሞከሩት የኛም ሀገር ፖለቲካ አማራው አማራ ነኝ ብሎ መቆም ሲጀምር ተመሳሰሰዩን ነገር ለመፈለፀም የተሞከረበት አጋጣሚ ብዙ ሆኖ አይተነዋል።እያያነውም ነው።
ዶር ካሊድ መሀመድ ግን ዘረኝነት ማለት ~ prejudice +power ማለት ነው ይላሉ። እና እኛ ጥቁሮች መድረክ ላይ በመውጣት ለህዝባችን የምናደርገው ማንቃት ወይም በክርክሮች ተሳትፈን የምንናገረው በሙሉ ህዝባችንን ከማንቃት ባለፈ ሌሎች በስራቸው፣ በኢኮኖሚያቸው፣ በቤቶች ፕሮጀክት (የኛ ሀገር ኮንዶሚኒየም) ሆነ በሌሎች ነገራችሁ ላይ የሚያመጣው ተፅእኖ የለም ይላሉ። ምክኒያቱም ስልጣን (የፖለቲካ ስልጣን) እጃችን ላይ የለም። የፖለቲካ ስልጣን እጃችን ላይ ከሌለ ለጥቁር ህዝቦች የምናደርገው ትግልና ተጋድሎ በፍፁም ዘረኝነት ሊሆን አይችልም ነበር ያሉት።
ኢትዬጵያ አንድነቷ ተጠብቆ፣የባህር በሯ ተከብሮ ይኖር ዘንድ ~ ተብሎ በተነገረ የጦርነት ታሪክ ውስጥ :–
መሪው ~ መንግስቱ ሀይለማርያም
መሪነቱን የወሰደው ~ ከ ጄኔራል አማን አምዶም
ከ ተፈሪ በንቲ
ከ ደበላ ዲንሳ
ወደ ዚምባቡዌ ሲሰደድ የተካው ~ ጄኔራል ተስፋዬ ገ/ኪዳን ገለቱ
ሆኖ
ጦርነቱ ሲጠናቀቅ ~ የሀገር አንድነቱ ጉዳይ፣የባህር በሩ ጉዳይ ተረስቶ:– ያሸነፉት አማራን እንደሆነ ሲደሰኮር
ጦርነቱ የአማራ የነበረ ይመስል በጦርነቱ ለደረሰው ጥፋት ይቅርታ ለመጠየቅ ኤርትራ ሄደው አማራን አሲዘው ይቅርታ ሲጠይቁ
ወያኔዎች ከአማራዎቹ ኢህዴን ጋ ሆነው መንግስቱ ሀይለማርያም ይመራው የነበረውን የኢትዬጵያን መንግስት በጦርነት አሸነፍን ባሉ ማግስት ~ አማራን አሽንፈን እንደ ሲጋራ አጭሰን ጥለነዋል ሲሉ
There was something very wrong with Ethiopian politics.
ወያኔዎች 27 አመታት ሀገር እያስተዳደሩም ~ አማራን ሲወቅሱ ኖረው ከስልጣን ገለል ብለው ከአብይ አህመድ ጋ በገጠሙት ጦርነት አሁንም አማራን እየወቀሱ ያሉበትና ወቀሳ ያላቆሙበት ሁበት ~ There still something very wrong with Ethiopian politics ~ ተብሎ ሊታሰብ ከሚችለውም በላይ የሆነ ነገር ነው።
አብይ አህመድ ፣ለማ መገርሳና ሽመልስ አብዲሳ ከአማራዎቹ እነ ገዱ አንዳርጋቸውና ደመቀ መኮንን ጋ ሆነው በአማራ ማስተኛዋ ክኒን ኦሮማራ ድራማ ወያኔን ገለል ባደረጉ ማግስት አቦ ሸመልስ አብዲሳ በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ ነፍጠኛን የሰበረን ቦታ ሰብረነዋል ሲል ስልጣን የተረከበው ከአማራ እጅ እንጂ ከወያኔ ከዚያ አለፍ ሲልም በጦርነት ሜዳ ግዳይ ጥሎ እንደሚፎክር የጦር ሜዳ ጀግና ይመስል የነበረበት ንግግር ~ There was and still something very wrong with Ethiopian politics ~ ለማለት የሚያስገደድ ሁነት ነበረው።
ትናንት ወያኔ ዛሬ እነ አብይ አህመድ እጃቸው ላይ ያለው ስልጣን ትናንት የአማራ ገዢ መደብ ናቸው ብለው ሲወቅሷቸው የነበሩ መሪዎች ይዘውት የነበረው አይነት ~ with a little bit of modernity and money ~ ስልጣን ነው።
Maybe they can'tt fitinto it ~ የአማራ ስም ከአፋቸው በፍፁም ሊጠፋ ያልቻለበት ጉዳይ ~ There still something very wrong with Ethiopian politics ~ የሚያስብል ጉዳይ ነው። አሁንም!!!
አማራን በክልልህ በአማራነቱ መርጠህ ደሙን አፍስሰህ ፣በጅምላ ጨፍጭፈህ፣ ያለ ፍታትና ሶላተል ጀናዛ በጊሪደር በጀምላ መቃብር ቀብረህ፣ንብረቱን ዘርፈህና አቃጥለህ መግደል ያልቻልከውን አፈናቅለህ፣ የማንነተ መለያ የመታወቂያ ካርዱን አይተህ በአማራነቱ ወደ አዲስ አበባ አትገባም ብለህ ክልክለህ ይሄም አልበቃ ብሎ በቀየውና በርስቱ የሀገር ድንበር እንዲጠብቅ የተቋቋመውን ተቋም አማራን እንዲወር ጦር አዝምተህ ፣ታንክ፣የጦር ጄትና ድሮን አሰማርተህ በአማራ ላይ መከራ ማዝነባቸው ሳያንስ ፋኖዎች ኦሮሚያ ክልል ገብተው ሰው አረዱ ስትል ~ There must be in essence something very,very, very wrong with Ethiopian politics.
ጀግኖቹ አንድ ሄሊኮፕተር መትተው ? ጥለዋል ???
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago