ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago
በልጅነታችን ንፁህ ልብ እንጂ ንፁህ ልብስ አልነበረንም፤ ዛሬ ግን ልብሳችን ፀድቶ ልባችን ቆሸሽ!
#ርዕስ ≈ የግብፅ እና የዓባይ ግድብ ታሪክ
~ የግብፅ ታሪካዊ ተንኮል
~ የኢትዮጵያውና ጀግንነት
••••
#በንጉሥ_ይምርሐነ_ክርስቶስ ~ ከዐፄ ይኩኖ አምላክ ጀምሮ
ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ብዙ በደል መፈጸም ጀምራለች።
የኢትዮጵያ ንጉሥ ግርማ ስዩም በነበረበት ጊዜ ግብፅ
የሚገኘው ንጉሥ በዚያ ያሉትን ቤተክርስቲያናት ማፍረስ
ሲጀምር ኢትዮጵያም የአጸፋ መልስ ትሰጥ ነበር። በመካከልም
መልእክት ሲጻጻፉ የኢትዮጵያው ንጉሥ ለግብፅ ቀርቶ ሰማይ
የሚያስደነግጥ መልስ ላከበት። በግርማ ሥዩም የተተካው
ልጃቸው ይምርሐነ ክርስቶስ ሲተካም እንደገና መካረር ጀመሩ።
የግብፅ ነገሥታት በክርስቲያኖች ላይ መከራ ማብዛቱ ሲሰማ
ንጉሥ ይምርሐነ ክርስቶስ # የዐባይን_ወንዝ መገደብ ጀመሩ።
ወደ ግብፅም የሚወርደው የዐባይ ውሃ እየቀነሰ ሲሄድ በግብፅ
ወሬው ተሰማ። በዚያን ጊዜ (1084 - 1093 ዓ.ም) ወዲያውኑ
የእስክንድርያው ሊቀጳጳስ ሳይቀር አማላጅ ተልከው እጅ መንሻ
ሰጥተው «በውሃ ጥም» ሊያልቁ እንደሆነ አሳስበው
ተለማምጠው አስለቅቀው ሄዱ። ከዚያ ግብፅ ተኮማትራ ትኖር
ነበር። (አቡነ ጎርጎዮስ "የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ታሪክ ገፅ 32 - 35)
••••
#ዐፄ_ዓምደ_ጽዮን ~ የብጽፅ ነገሥታት በነገሡ ቁጥር በተለይ
በክርስቲያንች ላይ መከራ ካላበዙ አያስደሳቸውም ነበር። በዐፄ
ዓምደ ጽዮንም ጊዜ ይኸው በደል ስለተሰማ ለግብፁ ንጉሥ
«መግሥትን በክርስቲያኖች ላይ የሚያደርሰውን መከራ ካላቆመ
#ዓባይን እገድባለሁ» ብለው እንዳስቆሙት ተመዝግቧል።
••••
#ዐፄ_ዳዊት ~ በነገራችን ላይ የዐፄ ዳዊት አያት የነበሩት (ዐፄ
ሰይፈ አርዕድ) የግብፅን ሱልጣኖችን በኃይል ያንቀጠቅጧቸው
ነበር። ጀግንነትን የወረሱት ብልሁ የልጅ ልጃቸው ዐፄ ዳዊት
ደግሞ በነገሡበት ጊዜ ለኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ሲላክ የነበረው
“ግብፃዊ ጳጳስ”ን ምክንያት ግብፅ ስታደርሰው የነበረው ታሪካዊ
በደል በማሰብ « #ዐባይን_ልገድብ ነው» የሚል እንቅስቃሴ
ጀመሩ። («ገድበው ነበር፣ በሱዳን በረሃ እንዲፈስ አድርገውትም
ነበር» የሚሉ ታሪኮችም አሉ) ይህም እንደገና በግብፅ ሲሰማ
የኢየሩሳሌሙን ሊቀጳጳስ አባ ዮሐንስን፣ የእስክንድርያውን
ሊቀጳጳስ አባ ቄርሎስንና አባ ማዕማር የተብሉ አባቶችን ልከው
የመማለጃ እጅ መንሻ ይቀርብላቸው ዘንድ ተጠየቁ።
እርሳቸውም «ጌታ ሲሰቀል ቀኝ እጁ ያረፈበት የግማደ መስቀሉ
ክፍል ለግብፅ ደርሷት ነበርና ለኢትዮጵያ የግብፅ ካሳ ይሆን
ዘንድ እሱን ስጡኝ፣ ተጨማሪም ቅዱስ ሉቃስ የሳላትን ምስለ
ፍቁር ወልዳ እና አክሊለ ሦኩን ስጡን» ብለው ጠይቀው
በምትኩ ወርቅና አልማዝ ሰጥተው አምጥተዋል።
•••
#ዐፄ_ዘዓያዕቆብም በዘመናቸው የተለመደው የግብፅ
ክርስቲያኖች ሲቃይ መብዛት እና ግብፅ የነበረችው
ደብረምጥማቅ መፍረሷ ሲሰማ ደብዳቤ ልከው ነበር።
በደብዳቤያቸውም «በግብፅ ክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው
በደል ካልቆመ #ዐባይ እኛ ጋ ነውን ልናቆመው እንደምንች
አያውቁምን? እግዚአብሔርን ፈርተን እንጂ ሌላ ያገደን ነገር
የለምኮ። አሁን ግን በቤቱ እና በልጆቹ መጥተሃልና ብታስብበት
ይሻላል» ብለው አስፈራተው ነበር። በዚህም ደንግጠው የግብፁ
ንጉሥ አርፈው ተቀምጠዋል። በነገራችን ላይ አሁን በመላው
ዓለም የምትታወቀው # ጻድቃኔ ማርያም «ደብረ ምጥማቅ»
ተብላ መሰየሟ የግብጿ ደብረምጥማቅ ስለፈረሰች በሱባኤ
ተጠይቆ በምትኳ ትሠራ እና ትሰየም ዘንድ ተነግሮ እንደሆነ ልብ
ይሏል።
_
#ምንጭ- የተክለጻዲቅ መኩሪያ የኢ/ታሪክ መጻሕፍት፣ አቡነ
ጎርጎዮስ "የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ታሪክ፣ African language
litrature by Albert S.Gerard፣ Travels to discover
the source of nile by James bruce፣ Mordechai
Abril, Ethiopia and the red sea 1980፣ haggai
Erlich, the cross and river Ethiopia Egypt and nile,
2002፣ ሉሌ መልአኩ የቤ/ክ ታሪክ
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia
ለፈገግታ
አንዲት አሜሪካዊት ወጣት ከኢትዮጵያ ከመጣ ጓደኛዋ ጋር
ትጨዋወታለች።
አሜሪካዊቷ ወጣት ምናለች፦"በእኛ በኦክላሆማ ቁፋሮ ወቅት
የጥንት የድሮ ቀጫጭን ሽቦዎች ተገኝተዋል። ይህ ምን
እንደሚያስረዳ ታውቃለህ? እኛ አሜሪካውያን ከ200ዓመት
በፊት ስልክ ተጠቃሚዎች እንደነበርን ነው።
ኢትዩጵያዊው ጓደኛዋ ቀበል አድርጎ፦ "በኛ ሀገር በኢትዮጵያ ግን
በቁፋሮ ምንም አይነት የድሮ ሽቦዎች አልተገኘም። ይሄ ምንን
እንደ ሚያረጋግጥ ታውቂያለሽ?"እኛ ኢትዮጵያዊ ን ከ200ዓመት
በፊት ገመድ አልባ(ሞባይል) እንጠቀም እንደነበር ነው።"
ድል ለኢትዮጵያ !!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia
#አመሰግናለሁ *?*?
ውድ የታሪካዊት ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በ አስተያየት መስጫ (@Abel_balehager_bot ) ላይ የማይገባኝን ክብር ሰጥታችሁ ትልቅ አክብሮት ስለሰጣችሁኝ በእውነት እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ።
" በርታ ፣ጠንክር እንዳትሸበር " እያላችሁ ከጎኔ የምታበረታቱኝ ሁሉ ከልቤ አመሰግናለሁ ?።
እንዲሁም በሀገርም ሆነ ከሀገር ውጪ ያላችሁ ውድ የታሪካዊት ኢትዮጵያ ቤተሰቦች እና ወዳጆቼ ላቅ ያለ ምስጋናዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ ?።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!#አቤል_ባለሀገር ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!
YOUTUBE : https://youtube.com/@Historical_Ethiopia ጥያቄ ካለዎት❓ ? @Historical_Ethiopia_Discussion የቴሌግራም ቻናል -** @Historical_Ethiopia
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago