ኢትዮ - ኮን ሬድዮ ፕሮግራም/Ethio con radio perogram/

Description
በግንባታው ዘርፍ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሳምንታዊ የባለሙያዎች ፕሮግራም የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ከአሀዱ ሬድዮ 94.3 ትብብር
ዘወትር ሰኞ ምሽት ከ2፡30-3፡30 ሰዓት የሚተላለፍ ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው።
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago

1 month, 1 week ago

የቤቶችን የገንዘብ ችግር ለመቅረፍ የቤቶች ፋይናንስ ሥርዓት እንደ ሀገር ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተሰማ

የቤት ችግርን ለመቅረፍ ይቋቋማል ለተባለዉ ስርዓት ጥናት መደረጉ እና የህግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል።

35 በመቶ በሀገሪቱ የሚገነባው የመኖሪያ ቤት የህብረት ስራ ማህበራት መገንባት አለበት ተብሏል። ይህን ለመገንባት ሁለት መሰረታዊ ችግሮች እንዳሉ የተገለፀ ሲሆን እነርሱም የመሬት አቅርቦት እና የፋይናንስ ችግሮች መሆናቸው ለመረዳት ተችሏል።

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የቤቶች ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ፣ አቶ ፀጋዬ ሞሼ እንደተናገሩት አዲስ በሚወጣው የመሬት ሊዝ አዋጅ 30 በመቶ የሚሆነው መሬት ከተሞች በምደባ ከሚያቀርቡት አስገዳጅ ሆኖ ለመኖሪያ ቤት መዋል እንዳለበት እና ይህም የቤት ችግርን እንደሚቀርፍ ታስቧል።

ይህን ተከትሎ የፋይናንስ ችግርይ ለመቅረፍ  " Housing Finance System" እንደሀገር ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱንና ስርዓቱን ለማቋቋም ጥናት መጠቱና የህግ ማዕቀፎች መዘጋጀታቸው አስረድቷል።

ከ 1999 ጀምሮ እስከ 2010 ዓ.ም. ድረስ የተገነባው ቤት 62 ሺህ አይበልጥም አሁን በስልጣን ላይ ያለዉ መንግስት ግን ባለፉት ስድስት ወራት 20 ሺህ 754 ቤቶች መገንባት መቻሉን ካፒታል ለመረዳት ችላለች።

(capital)

1 month, 2 weeks ago

🔷መቃብር View Apartment💀

ሰሞኑን በአንድ ስራ የሄድኩበት አካባቢ ያለ ሰፊ የመቃብር ቦታንና  የእምነት ተቋም አጎራብቶ የተገነባ የሪል እስቴት ፕሮጀክት ተመለከትኩ። የሚገርመው አብዛኛው የመኝታ ቤቶቻቸው መስኮቶቻቸው ወደ መቃብር ስፍራው ሆነው የተገነቡት ቤቶች በርካታ ናቸው።

ከእኛ ማህበረሰብ ስነልቦና አንጻር መቃብር ቦታን እናከብራለን እንፈራለንም ። የእምነት ተቋማት አጎራባች ሆኖ የመኖር ጉዳይ እንደ አማኙ ምቾትና ምርጫ ቢለያይም ከመቃብር ቦታ መጎራበት ግን ብዙም ምቾት የሚሰጥና የሚመረጥም  አይደለም።

እንደዚህ አይነት ቤቶች ለአልሚዎችም ቢሆን ጥሩና አዋጭ ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም ምክንያቱም የቤቶቹ ተፈላጊነት በአንድም በሁለትም ምክንያት ይቀንሳል።ፈላጊው ሲቀንስ ፕሮጀክቱ የተወሳሰበ ችግር ውስጥ ገብቶ መጨረሻው ኪሳራ ሊሆን ይችላል። የመሸጫ ጊዜው ይረዝማል በመርዘሙም ተፈላጊነቱ እየቀነሰ ይሄዳል፣ የመሸጫ ዋጋው ይወርዳል፣ ብድር ካለበት ለተጨማሪ ወለድ ክፍያ ይዳረጋል...ለቢዝነስ፣ ወለድ፣ገበያ ፣ ሊኩዲቲ የመሳሰሉ የ Real Estate Investment  Risk ተጋላጭ ይሆናል ይከስራል።

የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ጥቅሙ ከፍ ያለ ነው እንደሚባለው ሁሉ ኪሳራውም ይዞ የሚጠፋ እጅግ አስከፊ ነውና ኢንቨስትመንት ውስጥ የሚገቡ ሰዎች የMarket & Marketability ጥናት ቢያሰሩ በጥናቶቹ ውስጥም የቤት ገዢ ታሳቢ ደንበኞች ( Target Customers) ባህልና ንዑስ-ባህልን አብሮ እንዲጠናን ቢያደርጉ ከሚመጣባቸው ያልታሰበ ቁጣ ይድናሉ።

በአንጻሩ ጥሩ ጸጥታን ለሚሹ፣ መቃብር ስፍራን እንደ አረንጓዴ ስፍራ ለሚቆጥሩ  ሁኔታው ለማያውካቸው ጥቂቶች ቆራጦች በጥሩ ዋጋ ቤት ማግኘት ለሚሹም ጥሩ አማራጭ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን መልሶ የመሸጥ አላማ ላላቸው ተመካሪ አይደለም።

ለማንኛውም ባየሁት ፕሮጀክት ላይ በመቃብሩ በኩል ቤት የገዙ የሪል እስቴቱ ደንበኞች ከወዲሁ የማይክል ጃክሰንን Thriller ክሊፕ እያዩ ራሳቸውን  በእውንም በህልምም ከሁኔታው ጋር እንዲያለማምዱ ይመከራሉ።  

የሪል እስቴት አገበያዮች "መቃብር ቪው " ብለው ይሸጡልናል ወይስ "ግሪን ቪው"? ለዚህ አይነት ግብይት ስንት ፐርሰንት ኮሚሽን ይጠይቁ ይሆን?

በሪል እስቴት ግብይት ውስጥ እንዲህ ያሉ ንብረቶች Stigmatized Properties ይባላሉ ለማገበያየት ጊዜ ስለሚወስዱና ፈላጊያቸው ጥቂት በመሆኑ የሚከፈልባቸው የሽያጭ ኮሚሽን ከፍ እንዲል ይመከራል።

(በኢንጂነር ደሳለኝ ከበደ)

1 month, 2 weeks ago

ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጀት በጥራት እንዲጠናቀቁ ተገቢ ክትትል መደረግ እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጀት በጥራት እንዲጠናቀቁ ተገቢ ክትትል ማድረግ እንዳለበት አሳስቧል።

ቋሚ ኮሚቴው የሚንስቴር መስሪያ ቤቱን የ2017 ዓ.ም የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር እሸቱ ተመስገን፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጀት በጥራት እንዲጠናቀቁ የጀመራቸውን ተግባራት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

በዘርፋ ጥራትን ለማስጠበቅ ቁጥጥር  ማድረግና የህንጻ ደረጃዎችና ኮዶችን የሚመለከቱ መረጃዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማደራጀት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።

የአረንጓዴ ልማት ስራዎችም ከሌሎች አገሮች ጋር ለመወዳደር በሚያስችል መልኩ ደረጃ ሊኖራቸው እና ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል ።

በተጨማሪም የኮሪደር ልማት ስራው ጥሩ መሆኑን ጠቁመው የመኪና ማቆሚያ፣ የመጫኛና ማውረጃ ቦታዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ።

በዘርፉ ዲጂታላይዜሽን ማጠናከር፣ጥሩ ተሞክሮዎችን ማስፋት እና የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል ።

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ ፣ በጀትና በጥራት እንዲጠናቀቁ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የኮሪደርና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ለከተሞችና ለነዋሪዎች ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳላቸው ገልፀዋል ።

ክብርት ሚንስትሯ  ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎችን በሚመለከት በግማሽ ዓመቱ አጠቃላይ ሽፋን 175ሺ 879 ኪ.ሜ መሆኑን ገልጸዋል ።

የፕላን ዝግጅት ስራ በሚመለከት ከዚህ በፊት ፕላን ያልነበራቸው 16 አነስተኛ ከተሞችን ፕላን እንዲኖራቸው መደረጉን ገልጸዋል ።

የከተማ መሬትና ካዳስተር ስራዎች ጋር በተያያዘ በክልልና ከተማ አስተዳደሮች ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል 7ሺ ሄክታር መሬት ለማቅረብ ታቅዶ በምደባና በጫረታ ከ11ሺ ሄክታር በላይ መሬት ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል።

ያለፈቃድ የተያዙ ቦታዎችን በሚመለከት ወደ 85ሺ 256 ይዞታዎች ስርአት
እንዲይዙ መደረጉን ገልጸዋል ።

የቤቶች ልማትን በሚመለከት በግማሽ ዓመቱ 8ሺ ቤቶች ለመገንባት ታቅዶ ወደ 20ሺ 754 ቤቶች መገንባታቸውን ገልጸዋል።

በዘርፉ ከ110ሺ በላይ ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ እድል መፈጠሩን እና ሌሎች በግማሽ ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር አቅርበዋል።

(ፖርላማ)

4 months, 1 week ago

**ማስታወቂያ *

? ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር አባላት በሙሉ!

? የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚያካሂድ ቀደም ብሎ የተገለፀላችሁ መሆኑ ይታወሳል፡፡

?ይሁንና የምርጫ አመቻች ኮሚቴ አባላቱ በዚሁ ዕለት ቀደም ብለው በተያዙና  በተለያዩ ፕሮግራሞቻቸው ምክንያት መገኘት የማይችሉ መሆኑን በመረዳታችን ጉባዔውን በአንድ ሣምንት ወደፊት ለመግፋት መገደዳችንን  በታላቅ አክብሮትና ትህትና ጋር ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

- ጉባኤው የሚካሄደው ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

- ቦታው ኢንተር ላግዠሪ (የቀድሞው ኢንተር ኮንቲነታል) ሆቴል

- ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ መሆኑን እናስታውቃለን።

?የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር ዳይሬክተሮች ቦርድ

4 months, 1 week ago

ኢትዮ ኮን ጥቅምት 25፤ 2017

4 months, 1 week ago
***?*** የዛሬ ምሽት ጥቅምት 25 ቀን …

? የዛሬ ምሽት ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ኢትዮ ኮን ሳምንታዊ ፕሮግራሞቻችን

?ወቅታዊ ፕሮግራም

?የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አካሂዷል።

በዚሁ ስብሰባ ላይ ከመሰረተ ልማት፣ ከኮሪደር ልማትና ሌሎች የተያያዙ ጉዳዮች ጋር ከምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸውን ጥያቄ የሰጡትን ምላሽ በዛሬ ወቅታዊ ፕሮግራማችን እንመለከተዋለን።

? የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የሚያቀርበው ልዩ ዝግጅት የፕሮግራማችን አንድ  አካል ነው።

✍️?☎️የምታነሱት ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በዚሁ በቴሌግራም ገፃችን ላይ አድርሱን፡፡

??? ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት
ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ ከቀጥታ ስርጭት ፕሮግራማችን ጋር ይሁን!

4 months, 1 week ago

በአዲስ አበባ ከተማ #ለአፓርትመንት_ቤቶች እና #ለጋራ_መኖሪያ_ቤቶች ወይም ኮንዶሚኒየም ቤቶች አማካኝ የሽያጭ ዋጋ ተመን በ34 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።

በተሻሻለው  የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን መሰረት ከኮንደሚንየም እና አፓርትመንት ውጪ ለሆኑ ግንባታዎች፦

➡️ የግንባታ ነጠላ ዋጋ በጭቃ የተሰራ ቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 15,000 ብር፣

➡️ በብሎኬት የተሰራ የቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 20,000 ብር፣

➡️ የህንጻ ወለላቸው ከG+1 እስከ G+5 25,000 ብር እና፣

➡️ G+6 እና በላይ የሆኑ ቤት ወይም ህንጻ ነጠላ ዋጋ በካሬ 30,000 ተደርጓል፡፡

የቦታው መገኛ ዋጋ ('location value') ለከተማው የቦታ ደረጃ የጸደቀው ወቅታዊ አማካይ የሊዝ ጨረታ ዋጋ እንዲሆን መደረጉም ተገልጿል።

የቤት ስም ንብረት ዝውውር ክፍያ ማለትም አሹራ 4 በመቶ እና የቴምብር ቀረጥ 2 በመቶ ከጠቅላላ የቤቱ ሽያጭ ዋጋ ተሰልቶ ከመጋቢት17 ቀን 2016 ዓ/ም  ጀምሮ እንዲከፈልም ቢሮ አዟል።

ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር  ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን መሻሩንም ቢሮ ጠቅሷል።

በፍርድ ቤት እና በባንክ ሃራጅ ሽያጭ የስም ንብረት ዝውውር የሚጠየቅባቸው ይዞታዎችን በተመለከተ ይዞታ አገልግሎትና መብት ፈጠራ ደንብ ላይ በተቀመጠው አግባብ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል።

ይህ ማሻሻያ መምሪያ ከመውጣቱ በፊት የስም ንብረት ዝውውር አገልግሎት ጠይቀው በሂደት ላይ ሆኖ ክፍያ የፈጸሙ ተጋልጋዮች በቀድሞ አሰራር በከፈሉት ክፍያ መሰረት ይስተናገዳሉ ተብሏል።

ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ህንፃዎች የትመና ስራ የሚሰራላቸው ግንባታው በደረሰበት ወይም አሁን ላይ ባለበት ግንባታ ደረጃ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ያሳወቃል።

4 months, 1 week ago

በተሻሻለው የካሳ አዋጅ ቁጥር 1336/2016 አፈጻጸም እና  አተገባበር አስመልክቶ ውይይት ተደረገ

በተሻሻለው የካሳ አዋጅ ቁጥር 1336/2016
መሰረተ ልማት እና ማህበራዊ አገልግሎት ንብረት የመገመት፣ የመክፈል እና የማስነሳት ስራ ላይ ችግሮች እያጋጠሙ በመሆኑ ይህንን ችግር መፍታት የሚያስችል አሰራር ማዘጋጀት በማስፈለጉ እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና በቀጣይ አካሄዶች ላይ የጋራ መግባባት እንዲኖር በማስፈለጉ ነው ወይይት የተካሄደው።   

በውይይት መድረኩ የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣  ከየክልሉ፣ ከተጠሪ ተቋማት እና ከመንግስት የልማት ድርጅቶች የተወጣጡ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የውይይት መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የመሰረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ  ክቡር  አቶ የትምጌታ አስራት  መንግስት ለህዝብ ጥቅም ሲባል ካሳ የሚከፈልበት እና ተነሺዎችን የሚቋቋሙበት የተሻሻለው የካሳ አዋጅ  ረቂቅ ደንቡ ላይ ውይይት በማድረግ   በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር የውይይት መድረክ ማስፈለጉን ገልጸዋል ።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመሬትና ካዳስተር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ብዙሃለም አድማሱ ለህዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበት እና የልማት ተነሺዎችን መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1336/2016 ሰነድ እና ሀገራዊ የመሰረተ ልማት ቅንጅት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ቴዎድሮስ ተገኝ ለህዝብ ጥቅም ሲባል መሬት ሲለቀቅ ስለሚከፈለው ካሳ እና የልማት ተነሺዎችን መልሶ ለማቋቋም የወጣ የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ረቂቅ ማሻሻያ ደንብ በሚል የተዘጋጁ ሰነዶች ቀርበው ሰፊው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የቀረቡት ሰነዶች  መነሻ በማድረግ ከተሳታፊዎች  የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ተነስተው በክቡር ሚኒስትር ዴኤታው  ምላሽ እና ማብራሪያ
ተሰጥቶባቸዋል ።

(ከመልሚ)

4 months, 1 week ago

የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላላፊያ መስመር ግንባታን ተከትሎ ከመገናኛ አደባባይ ወደ ቦሌ በሁለቱም አቅጣጫ ለተሽከርካሪ ዝግ ሆኗል
- የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

በመገናኛ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመፍታት የሚያግዝ የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላላፊያ መስመር ግንባታ ተጀምሯል::

በመሆኑም በተለይ ከመገናኛ አደባባይ ወደ ቦሌ እና ከቦሌ ወደ መገናኛ አደባባይ በሁለቱም አቅጣጫ ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል::

እግረኞች በሙሉጌታ ዘለቀ ህንጻ በኩል ማለፍ ስለማይቻል በቦሌ ክ/ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ባለው የእግረኛ መንገድ እንዲጓዙ እንዲሁም አሽከርካሪዎችም ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ባለስልጣን መስርያ ቤቱ አሳስቧል፡፡

የአካባቢው መንገድ ተጠቃሚዎች ግንባታው በአጭር ጊዜ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለሚያሳዩት ትብብር የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ምስጋና አቅርቧል፡፡

4 months, 2 weeks ago

**ማስታወቂያ *

? ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር አባላት በሙሉ!

? የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚያካሂድ ቀደም ብሎ የተገለፀላችሁ መሆኑ ይታወሳል፡፡

?ይሁንና የምርጫ አመቻች ኮሚቴ አባላቱ በዚሁ ዕለት ቀደም ብለው በተያዙና  በተለያዩ ፕሮግራሞቻቸው ምክንያት መገኘት የማይችሉ መሆኑን በመረዳታችን ጉባዔውን በአንድ ሣምንት ወደፊት ለመግፋት መገደዳችንን  በታላቅ አክብሮትና ትህትና ጋር ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

- ጉባኤው የሚካሄደው ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

- ቦታው ኢንተር ላግዠሪ (የቀድሞው ኢንተር ኮንቲነታል) ሆቴል

- ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ መሆኑን እናስታውቃለን።

?የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር ዳይሬክተሮች ቦርድ

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago