ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 Monate, 3 Wochen her
Last updated 2 Monate, 2 Wochen her
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 Monat, 2 Wochen her
ዛሬ የሸዕባን ወር ሁለተኛ ቀን ነው። በተለያዩ ምክንያቶች የባለፈው አመት ረመዿን ጾም አልፏችሁ ቀዷውን ያላወጣችሁ ካላችሁ፤ የዚህ አመት ረመዿን ሳይገባባችሁ ባላችሁ ክፍት ቀናት አጠናቁ።
ይህ የሸዕባን ወር ከተከበሩት አራት ወራት መካከል አንዱ በሆነው በወርሃ ረጀብ እና በውዱ የረመዿን ወር መካከል የሚገኝ ስለሆነ፤ ብዙ ሰው እንደሚዘናጋበት ውዱ ነቢይ ﷺ ነግረውናል።
ሰዎች በተዘናጉ ጊዜ በዒባዳህ መበርታት ደግሞ ልዩ ምንዳ አለውና በተለይም ጾም ላይ እንበራታ፤ ራሳችንንም ለወርሃ ረመዿን ነፍሳችንን እናዘጋጃት።
ገና ከአሁኑ ከወንጀል መራቅንና በመልካም ነገር ላይ መበራታትን ያልተለማመደች ነፍስ፤ ኋላ ቀጥታ ረመዿን እንደጀመረ በቅፅበት ከመጥፎ ነገር ርቀሽ በጥሩ ነገር ተጠመጂ ብለን ስንይዛት ያልለመደችው ሆኖባት በሚጠበቀው ልክ ውጤታማ ላትሆን ትችላለች። በረመዿን ውስጥ እያንዳንዷ ሰከንድ ልዩ ቦታ ስላላት በመለማመጃ የምታልፍ ሳትሆን ውጤታማ በሆነ ነገር ማለፍ የሚገባት ናት። ስለሆነም ከወዲሁ እንስተካከል። ሌሎችንም እናስታውስ። አላህ ያግራልን!
Copy
#ጠያቂው እንዲህ ይላል:አንድ ሰው ከጀመዐ ሶላት የተወሰነ ረከዐ አምልጦት ደረሰ እናም ከኢማሙ በቅርብ ቦታ ቆመ::ከዚያም ኢማሙ ሶላቱ ላይ ከመቀጠል ሚያቅበው ነገር ቢከሰትበትና ረከዐ ያመለጠውን ሰው ለኢማምነት ተክቶት ቢወጣ;ፍርዱ ምን ይሆናል?
#መልስ:መጀመርያ:መእሙሞችን(ኢማሙን ተከትለው ሚሰግዱትን)ስለሚያዋልል ኢማሙ ረከዐ ያመለጠውን አካል(መስቡቅን) ለኢማምነት መተካት የለበትም::ነገር ግን መስቡቅን ቢተካ;መስቡቁ ለራሱ ያመለጡት ረከዐዎችን ያሰግዳቸውና ሳያሰላምት ያመለጡትን ረከዐዎች ለመሙላት ይቆማል::ሶላቱን ያሟላል::መእሙሞቹ ደግሞ ተሸሁድ ላይ በሆኑበት ሁኔታ ይቆያሉ::ከዚያም አብረው ያሰላምታሉ::
(نور على الدرب-ابن عثيمين رحمه الله)
Brother/Sister:-
I know you are doing your best as hard as you can, but let me tell you some bitter truth, you are going to die one day sooner or later...therefore, never get tired of doing a good deeds that your Rabb(Allah) wants you to do::
May you live a fruitful life here in this world and there in the hereafter! Aamiiiiin!!
ጥያቄ፡-
ከመካከላችን የዐስር ሰላት ካልሰገደን ግን የመግሪብ ሰላት ሰዓቱ ገብቶ ህዝበ ሙስሊሙ ለመግሪብ ሰላት ጀመዓ ተገኝቶ ከሆነ የዐስርን ሰላት መስገድ አለበት ወይንስ ከሰዎች ጋር መጝሪብ መስገድ አለበት?
መልስ፡ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (አላህ ይዘንላቸው)
السؤال:
إذا كان أحدنا لم يصل العصر، ودخل وقت صلاة المغرب، وحضرت الجماعة في صلاة المغرب، هل يصلي العصر، أم يصلي مع الجماعة؟ جزاكم الله خيرًا.
الجواب: (ابن باز)
إذا أمكنه أن يصلي العصر أولًا بدأ بها، ثم صلى معهم المغرب، فإن خشي أن تفوته معهم صلى معهم المغرب بنية العصر، فإذا سلموا من المغرب قام وأتى بالرابعة للعصر، ثم يصلي المغرب بعد ذلك، أما إذا أمكنه أن يصلي العصر وحده في المسجد قبل أن يصلوا المغرب؛ فإنه يصليها، ثم يدخل معهم المغرب، فإن لم يتيسر ذلك؛ صلى معهم على الصحيح بنية العصر، فإذا سلموا قام وأتى بالرابعة، ثم يصلي المغرب بعد ذلك.
ኢኽዋነል-ሙስሊሚን ችግራቸው የአቂዳ ነው ወይስ የመንሀጅ....!?
?በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ
የቢድዓ ሰዎች ግለሠቦች ላይ መናገር የጋለ ብረትን እንደመያዝ ለሚያንቀጠቅጣቸው ሰዎች ትንሽ ነቃ እንዲሉ የኢማሙ አህመድ ጓደኛ የሆኑት የየሕያ ኢብኑ መዒንን ንግግር እጋብዛለሁ።
የሕያ ኢብኑ መዒን እንዲህ ይላሉ:-
«ለሱና ጥብቅና ባለመቆሜ የተነሳ የአላህ መልዕክተኛ ክስ ከሚያቀርቡብኝ፣ የቢድዓ አራማጆች ክስ ቢያቀርቡብኝ ይሻለኛል»
አልዒልሙ ሻሚኽ (288)
በህይወታችን ላይ አንዱ በጣም የሚያሳዝነው ነገር አንዳንድ ዒባዳዎች እፈፅማቸዋለን ግን በዛ ዒባዳ የሚገኘውን አርጅር በትክክል አውቀን ባለመነየታችን ብቻ ያን አጅር ሳናገኝ እንቀራልርን። አንዳንዴ ደሞ በምንፈፅመው ዒባዳ አጅሩ ላይ ትልቅ ልዩነት ሊያመጣ የሚችልን የሆነ ቅመም እንረሳልን።
ይህ ሊሆን ግን አይገባም ነበር። ከራሴም ጭምር ብልጥ ልንሆን ይገባል። ይህ አለም ጠፊ መሆኑና ትክክለኛው ካፒታል/ሀብታችን የአኸራው መሆኑን በደንብ በውስጣችን እንዲሰርጽ ለማድረግ እንሞክር።
ለዛሬ ይህንን እናስተውል። ስንቶቻችን በዚህ እየተጠቀምን ነው?
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐
“የፈጅርን ሶላት በጀማዐ የሰገደ ከዚያም ፀሀይ እስከሚወጣ ድረስ አላህን እያወሳ የተቀመጠ እና ከዚያም ሁለት ረከዐ ሶላት(ዱሃ) የሰገደ ልክ እንደ ሐጅና ዑምራ አጅር አለው፡፡ ሙሉ! ሙሉ ! ሙሉ!”
? ሶሂህ አልጃሚዕ: 6346
**ኢማሙ_አሕመድ_ኢብኑ_ሐርብ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -
«አሏህን ለሀምሳ አመታት ያክል ተገዝቼዋለሁ። ሶስት ነገራቶችን እርግፍ አድርጌ በመተዌ ምክንያት እንጅ የዒባዳን ጥፍጥና ማግኘት አልቻልኩም ነበር:-
❶ የሰዎችን ውዴታ መፈልግን ስተው ሐቅን መናገር ቻልኩ፣
❷ አመፀኞችን መጎዳኘት ስተው ደጋጎችን መጎዳኘት ቻልኩ፣
❸ የዲንያን ጥፍጥናዋን ስተው የአኼራ ጥፍጥናን ማገኘት ቻልኩ።»
? ۞ سير أعلام النبلاء【11/34】۞**
?የሩቅ መንገደኛ?‼️
ገና ሳትፈጠር ዱኒያን ሳታስበው፣
ሁሉም ነገር አልቆ ተላልፎ ውሳኔው፣
ምን ያዘናጋሃል ለዛ ለወዳኛው።⁉️
?????????
የሩቅ መንገደኛ ስንቁን ይሰንቃል፣
ከመጥፎው እርቆ በመልካም ይኖራል፣
ስንቁ እንዳይበላሽ ይወጣል ይወርዳል፣
ደሞ እንዳያልቅበት በጣም ይሰስታል፣
ሌላም ለማገኘት እጅጉን ይለፋል፣
??
እኛግን እረሳን ያንን የሩቅ ጉዞ፣
ወደ ዱኒያ ህይወት አይናችን አማትሮ፣
ምኑንም ሳናውቀው ሁሉም ተቀይሮ፣
ሀይ የነበረው ሰው ሙታን ሲሆን ዙሮ፣
አይናችን እያዬ ልባችን ታውሮ፣
ህይወት መግፋት ሆነ በጨለማ ኑሮ፣
በደመነፍስ ሆነ የጭቃላይ ኑሮ። የሩቅ መንገደኛ በጊዜ ተነስቶ፣
ሰአቱን በአግባብ ከፋፍሎ ከፋፍሎ፣
መዋያ ማደሪያ ስፍራውን አስቦ፣
ይጓዛል በጊዜ ህይወቱን አስውቦ፣
ምን ያስተክዘዋል ስንቁን አስቀድሞ።
የሩቅ መንገደኛ መሆኑን ተረድቶ።
منقول
አቢ ሁረይራ በዘገቡት ሐዲስ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ፤ በአላህ ታገዝ፤ ደካማና ስልቹ አትሁን፤ አንድ ነገር ባጋጠመህ ጊዜ ‘ይህን ነገር እንዲህ ባደርገው ኖሮ…’ አትበል። ነገር ግን ‘አላህ የወሰነው ሆነ፤ አላህ የፈለገውን ይሰራል’ በል። ‘እንዲህ ቢሆን ኖሮ’ የሚለው ንግግር ለሰይጣን ስራ በር ይከፍታል»
?[ሙስሊም ዘግበዉታል]
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 Monate, 3 Wochen her
Last updated 2 Monate, 2 Wochen her
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 Monat, 2 Wochen her