{በቢድዓና በቢድዓ ሰዎች ላይ ምላሽ}

Description
የተለያዩ "በቢድዓና በቢድዓ ሰዎች" ላይ የሚሰጡ ምላሾች በፅሁፍና በድምፅ የሚገኝበት ቻናል ነው።
ቢድዓንና የቢድዓ ሰዎችን ለማህበረ ሰቡ ግልፅ ማድረግ ማህበረሰቡን ከተለያዩ የጥመት አንጃዎች መታደግ ነው! በዚህ ላይም የተለያዩ የሱና ዳዒዎች ትልቅ ሀላፍትና እንዳለባቸው ጠንቅቀው ሊያውቁት ይገባል!
አላህ ሆይ ሀቅን አመላክተን መከተሉንም ወፍቀን!!!
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

3 years, 9 months ago
አዲስ ወሳኝ ተከታታይ ሙሓዶራ ወሳኝ በሆኑ …

አዲስ ወሳኝ ተከታታይ ሙሓዶራ ወሳኝ በሆኑ ርእሶች!!

ክፍል 4⃣

ርዕስ:- ከሙብተዲዕዎች ጋር መቀማመጥ የሚያሳድረው ተፅእኖ እና የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ተጨባጭና አመራሮቹ ሙብተዲዕ ስለመሆናቸው።

??በሸይኽ ሐሰን ገላው (ሀፊዞሁሏህ)

የድምፅ ፋይሉን በሚከተለው ?? ሊንክ ያገኙታል
https://t.me/IbnShifa/1367

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa

3 years, 10 months ago

"ታላቅ ዲናዊ ኮርስ በጎንደር ከተማ"

በትራንስፖርት አለመመቻቸት ምክንያት በጎንደር ከተማ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሸይኽ አብዱልሐሚድ ያሲን አልለተምይ "ሃፊዞሁሏህ" ሊሰጥ የነበረው ኮርስ ተዘርዞ እንደነበር የሚታወስ ነው ሆኖም በአላህ ፈቃድ የፊታችን ጁሙዓ መጋቢት 03/ 2013 ከሰዓት በኋላ ጅማሮውን አድርጎ አስከ እሁድ መጋቢት 05/2013 ከቀኑ 10 ሰዓት ድረስ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ኮርሱን የሚሰጡት ፡- ታዋቂው ዓሊም ሸይኽ ዓብዱልሐሚድ ያሲን (አልለተምይ) - ሃፊዞሁሏህ - ይሆናሉ፡፡

ኮርሱ ፡- ሸይኽ ሙሐመድ ጀሚል ዘይኑ - ረሂመሁሏህ - “አቂደቱል ኢስላምያ ሚነልኪታቢ ወስ'ሱናህ” በሚል ርዕስ ባዘጋጁት አጭር የጥያቄና መልስ ኪታብ ዙሪያ ይሆናል፡፡

ኮርሱ የሚካሄደው ፡- “በመስጅድ አስ'ሱናህ”
አድራሻ፡- ቀበሌ 10 ብሪጋታ መውረጃ ጎን

ማሳሰቢያ ፡- - በዚህ ኮርስ ወንዶችም ሴቶችም መሳተፍ ይችላሉ፡፡

#ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በዝግጅቱ ላይ መሳተፍ ለምትፈልጉና ለምትችሉ ሁሉ ይህ ታላቅ አጋጣሚ እንዳያልፋችሁ

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

https://t.me/alateriqilhaq

كن على بصيرة

3 years, 10 months ago

የቢድዓ ሰዎች ላይ ሊኖረን የሚገባ አቋም እና
ጥቂት ነገሮች ከሰላሳ ምክሮች

ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐመድ ኑር
t.me/Muhammedsirage

3 years, 12 months ago

MuhammedSirage M.NUR

"በእኛ እና በአሕባሾች መካከል"

ተከታታይ ትምህርት

ክፍል 1-

الرحمن على العرش استوى
ወይስ
الله موجود بلا مكان ؟!

43 ደቂቃ ያህል ነው
السلفية
https://t.me/Muhammedsirage

4 years ago

? ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም
በጉራጌ ዞን እነሞር ወረዳ ኮሰድ ቀበሌ
የፊታችን ማክሰኞ ጥር 11/2013 በተጠቀሰው ቀበሌ ታላቅ የተውሒድ ዳዕዋ አዘጋጅተናል
በኮሮና ምክንያት ከዳዕዋ የራቀው ማህበረሰባችን በጣም አስከፊ በሆነ የቀብር አምልኮ ውስጥ ተዘፍቆ ይገኛል በአላህ ፈቃድ ይህ ፕሮግራም የተውሒድን ብርሃን ፈንጥቆ የሽርክን ፅልመት የሚገፍ ይሆናል
ፕሮግራሙ የሚጀመረው
ከጠዋቱ 2 : 30 ላይ ይሆናል
በፕሮግራሙ ላይ የሚሳተፉት
እንግዶቻችን
የሱናና የተውሒድ ነበልባል የሚተፉት
ታላቁ የሱና ሸይኻችን
አሽሸይኽ ዐ/ ሐሚድ አልለተሚ
ወንድማችን ሚስባሕ ሙሐመድ
ወንድማችሁ ባሕሩ ተካ
አላህ በተባለው ቀን
በተባለው ቦታ በተውሒድ ማእድ ያገናኘን
http://t.me/bahruteka

Telegram

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahruteka

***?*** ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም
4 years ago

የውይይት ጥሪ ለአሕባሾች
~~~~~
① ጠሪ: –

አቡ ዒምራን ሙሐመድ ሲራጅ
እና
ኢብኑ ሙነወር

② የጥሪው አድማስ:–

ለሁሉም አሕባሾች። ሰሞኑን "እንወያይ" ሲሉ የነበሩትን ሀቢብ እና ወሂድን ጨምሮ እስከነ ዑመር "ኮምቦልቻ" … ባጭሩ ለሁሉም።
(ማሳሰቢያ:- ንፅፅር ላይ የሚሰራው ወሒድ ዑመር አይደለም።)

③ የውይይት ርእስ:–

"አላህ ከዐርሹ በላይ ነው" የሚሉ ሙስሊሞችን እያከፈራችሁ ስለሆነ የምንጀምረው በዚህ የ"ኢስቲዋእ" ርእስ ነው። ይህንን ለመቋጨት ከበቃን እንደ "ኢስቲጋሣህ" ባሉ ሌሎች ወሳኝ ርእሶች እንቀጥላለን።

④ የውይይት መስፈርት: –

ማስረጃዎች ከቁርኣን፣ ከሐዲሥ እና ነቢዩ ﷺ ምርጥነታቸውን ከመሰከሩላቸው ቀደምት ትውልዶች ንግግር ብቻ
ይሄ ከጠበበባችሁስ?! በዚህ ምክንያት እንድትሸሹ አንፈልግም። እኛ:–

?? በሰለፎች አካሄድ ተገድባችሁ መሟገት አትችሉም ብለን ስለምናምን፣
?? በዚህ ምክንያት ከውይይቱ እንድትሸሹም ስለማንፈልግ፣
?? "እንከተላቸዋለን" ከምትሏቸው አቡል ሐሰን አልአሽዐሪ ፈፅሞ እንደማትገናኙ ማጋለጥም ስለምንሻ
እስከ አቡል ሐሰን ዘመነ–ህልፈት #ድረስ ያሉ ዓሊሞችን #ብቻ እንድታጣቅሱ እንስማማለን። ከዚያ በኋላ #ፈፅሞ አይሆንም።

በዚህ ዘመን የምንገድብበት ምክንያት:–

1⃣ ውይይቱ ልጓም የለሽ ሆኖ እንዳይለጠጥ ለመወሰን፣
2⃣ እምነታችሁ ከጊዜ በኋላ የመጣ እንጂ የዚያ ምርጥ ዘመን ትውልድ እምነት እንዳልሆነ ለማሳየት፣
3⃣ ዐቂዳችሁ "ኢማማችን" የምትሉት አቡል ሐሰንም እምነት እንዳልሆነ ለማሳየት፣
4⃣ "አላህ ከዐርሽ በላይ ነው" የሚለው ዐቂዳ "የወሃቢዮች ዐቂዳ ነው" በማለት መጤ አስተሳሰብ በማስመሰል ነጭ ውሸት በመንዛት ህዝብ እያደናገራችሁ ስለሆነ

በተቃራኒው ይህ "አላህ ከዐርሹ በላይ ነው" የሚለው እምነት በቁርኣንና በሐዲሥ የፀና፣ እነዚያ ምርጥ ትውልዶች የተጓዙበት፣ እንዲሁም የነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪ ጭምር ዐቂዳህ እንደሆነ ለማሳየት ርእሱን መገደብ ግድ ብሏል።

⑤ የውይይቱ ቦታ:–

ቴሌግራም ላይ በዚህ ግሩፕ ይሆናል:–
??
https://t.me/IbnuMuneworsb

? መልእክቱን አዳርሱልን። ምናልባት ፈቃደኛ ሆኖ የሚቀርብ ሊኖር ይችላልና።

4 years ago

ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚይ ረሒመሁላ፞ህ በስድብ፣ በማንቋሸሽ እና በመቅጠፍ ክብራቸውን ያጎደፈ ሰው ሲገጥማቸው እንዲህ ይሉ ነበር:–

"የላቀው አላህ በኔ ሰበብ አንድንም ሰው እሳት እንዳያስገባ እማፀነዋለሁ።"

ክብራቸውን ያጎደፈ ሰው ይቅርታቸውን ፈልጎ ወደሳቸው ሊመጣ እንደሆነ ሲነገራቸውም "ይቅርታ ለመጠየቅ መምጣት አያስፈልግም። እኔ ሁሉንም ሰው ይቅር ብያለሁ" ይሉ ነበር። አብረዋቸው ለሚሆኑ ሰዎችም ይህንን እንዲያደርሱ ይጠይቁ ነበር።
[ሸርሑል ኡሱሊ ሠላሣህ: 17–18]
~
እኛስ? ታሪኩን ያመጣሁት እንድንማርበት ነው። እስኪ እራሳችንን እንታዘብ። በደል የፈፀመብን፣ ክብራችንን ያጎደፈን ሰው ሳይጠይቀን ይቅር ማለቱ ቀርቶ ከልቡ እየለመነንስ ይቅር እንላለን ወይ? ለብዙዎቻችን ይሄ ከባድ ነው። የአፀፋ ዘመቻ ውስጥ የሚገባው ብዙ ነው። ጉዳዩ ከደዕዋ ወይም ከዱዓት ጋር ሲያያዝ ደግሞ ኸይሩም ሸሩም ለሌሎችም ይተርፋል።
(ٱلَّذِینَ یُنفِقُونَ فِی ٱلسَّرَّاۤءِ وَٱلضَّرَّاۤءِ وَٱلۡكَـٰظِمِینَ ٱلۡغَیۡظَ وَٱلۡعَافِینَ عَنِ ٱلنَّاسِۗ وَٱللَّهُ یُحِبُّ ٱلۡمُحۡسِنِینَ)
"ለእነዚያ በድሎትም ሆነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለሆኑት (ተደግሳለች)፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡"
[ኣሉ ዒምራን: 134]

(وَلَا یَأۡتَلِ أُو۟لُوا۟ ٱلۡفَضۡلِ مِنكُمۡ وَٱلسَّعَةِ أَن یُؤۡتُوۤا۟ أُو۟لِی ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡمَسَـٰكِینَ وَٱلۡمُهَـٰجِرِینَ فِی سَبِیلِ ٱللَّهِۖ وَلۡیَعۡفُوا۟ وَلۡیَصۡفَحُوۤا۟ۗ أَلَا تُحِبُّونَ أَن یَغۡفِرَ ٱللَّهُ لَكُمۡۚ وَٱللَّهُ غَفُورࣱ رَّحِیمٌ)

"ከእናንተም የችሮታና የክብረት ባለቤቶች የሆኑት ለቅርብ ዘመዶችና ለድሆች በአላህም መንገድ ለተሰደዱ ሰዎች ላይሰጡ አይማሉ፡፡ ይቅርታም ያድርጉ፡፡ (ጥፋተኞቹን) ይለፉም፡፡ አላህ ለእናንተ ሊምር አትወዱምን? አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡" [አነሕል: 22]
~~~
https://t.me/IbnuMunewor

Telegram

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

دروس وفوائد ابن منور

ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚይ ረሒመሁላ፞ህ በስድብ፣ በማንቋሸሽ እና በመቅጠፍ ክብራቸውን ያጎደፈ ሰው ሲገጥማቸው እንዲህ ይሉ ነበር:–
4 years, 1 month ago

ቁርኣን ውስጥ የተጠቀሱ ምኞቶች
~~~~~~~~~~~~~~~~~
(یَـٰلَیۡتَنِی كُنتُ مَعَهُمۡ فَأَفُوزَ فَوۡزًا عَظِیمࣰا)
«ዋ ምኞቴ! ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በሆንኩ!» [አኒሳእ: 73]

(یَـٰلَیۡتَنِی لَمۡ أُشۡرِكۡ بِرَبِّیۤ أَحَدࣰا)
«ዋ ምኞቴ! በጌታዬ አንድም ባላጋራሁ!» [አልከህፍ: 42]

(وَیَوۡمَ یَعَضُّ ٱلظَّالِمُ عَلَىٰ یَدَیۡهِ یَقُولُ یَـٰلَیۡتَنِی ٱتَّخَذۡتُ مَعَ ٱلرَّسُولِ سَبِیلࣰا)

በዳይም «ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በኾነ ዋ ምኞቴ!» እያለ (በጸጸት) ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)፡፡
[አልፉርቃን: 27]

(وَأَمَّا مَنۡ أُوتِیَ كِتَـٰبَهُۥ بِشِمَالِهِۦ فَیَقُولُ یَـٰلَیۡتَنِی لَمۡ أُوتَ كِتَـٰبِیَهۡ)
መጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ» ይላል፡፡ [አልሐቃህ: 25]

~~~~
ዛሬ ልንደርስባቸው የሚቻሉ የሙታን ምኞቶች ናቸው። ጊዜው ሳያልፍ ቶሎ እራሳችንን እናስተካክል። አላህ ሆይ! ልባችንን ከመዘንጋት አንቃልን። ሕይወታችንን በሂዳያ ብርሃን አብራልን።

የተተረጎመ
https://t.me/IbnuMunewor

Telegram

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

دروس وفوائد ابن منور

ቁርኣን ውስጥ የተጠቀሱ ምኞቶች
4 years, 2 months ago

ታ) በተመለከተ እነዚህን ቢድዐዎች፣ እነዚህን ነገሮች ስለሚያስፈፅም ከሆነ የሚሰጠው የሚቀበለው ነገር አስቀያሚ መሆኑ አይሰወርም። እነዚህን ነገሮች ምንም ሳይፈፅም እንዲሁ በዚህ ጊዜ የሚሰጠው ከሆነ ኢብኑ ሐቢብ ‘ለአስተማሪ በሙስሊሞች ዒድ ምንም አይወሰንለትም - ይህን መስራቱ የሚወደድ ቢሆን እንኳን’ ብለዋል። … ኢብኑ ሐቢብ ሸሪዐዊ በሆኑ በዓላት ላይ እንዲህ ካለ ሸሪዐዊ ባልሆኑት ላይ እንዴት ሊሆን ነው?!” [ዑለማኡል መግሪብ ወሙቃወመቱሁም ሊልቢደዒ ወተሶውፍ፡ 128-129]
5. አልኢማም አቡ ኢስሓቅ አሻጢቢ ረሑመሁላህ (790 ሂ.)፡-
መውሊድን ከተቃወሙ የስምንተኛው ክ/ዘመን ዐለማኦች ውስጥ አንዱ ሻጢቢ ናቸው። ሻጢቢ በቢድዐ ላይ የተሰላ ሰይፍ ነበሩ። “አልኢዕቲሷም” የተሰኘው ዳጎስ ያለ ስራቸው ቢድዐን እርቃኑን ያስቀረና ዛሬም ድረስ የቢድዐ አጋፊሪዎችን ምቾት እንደነሳ ነው። መውሊድን በተመለከተ ኢማሙ ሻጢቢ እውነትን ለሚፈልግ ሁሉ ግልፅ መልእክት ያዘለ ቅልብጭ ያለ ፈትዋ ሰጥተዋል። ይሄውና፡- “ሰዎች ዘንድ በተለመደው መልኩ የሚከበረው መውሊድ መጤ የሆነ ቢድዐ መሆኑ የታወቀ ነው። ቢድዐ ሁሉ ደግሞ ጥመት ነው። ስለሆነም ቢድዐን ለመፈፀም ገንዘብን መለገስ አይፈቀድም። በዚህ ላይ ኑዛዜ ከተላለፈም ተፈፃሚ አይደለም። እንዲያውም ቃዲው ሊያፈርሰው ይገባል።…” [ፈታዋ ሻጢቢ፡ 203-204]
በተጨማሪም ስለቢድዐ ምንነት ካብራሩ በኋላ እንዲህ ይላሉ፡- “አሁንም ከነሱ (ከቢድዐዎች) ውስጥ የሚካተተው (በዒባዳ ውስጥ) ተለይተው የተወሰኑ አፈፃፀሞችንና ሁኔታዎችን በቋሚነት መያዝ ነው። ለምሳሌ በአንድ ድምፅ በመሰባሰብ የሚደረግ ዚክር፣ የነብዩን - ﷺ - ልደት ቀን በዓል አድርጎ መያዝና እነዚህን የመሳሰሉትን ያካትታል።” [አልኢዕቲሷም፡ 1/53]
6. አልኢማም ኢብኑ ረጀብ (795 ሂ.)፡-
ሸሪዐው ዒድ ተደርጎ እንዲያዝ ያዘዘበትን ካልሆነ በስተቀር ሙስሊሞች ዒድ ሊይዙ አይፈቀድላቸውም። እነሱም (የታዘዙትም) ዒደል ፊጥር፣ ዒደል አዱሐና የተሽሪቅ (ከዒደል አድሓ ቀጥሎ ያሉት ሶስቱ) ቀናት ናቸው። እነዚህ አመታዊ በዓላት ናቸው። የጁሙዐ ቀን ደግሞ ሳምንታዊ ዒድ ነው። ከዚህ ውጭ ያለን በዓልና ዐውደ- አመት አድርጎ መያዝ በሸሪዐችን መሰረት የሌለው ቢድዐ ነው።‛ [ለጧኢፉል መዓሪፍ፡ 118]
7. አቡ ዐብዲላህ አልሐፋር አልገርናጢ (811 ሂ.)፡-
“የመውሊድ ሌሊት መልካም ቀደምቶች ማለትም የአላህ መልእክተኛ- ﷺ - ሶሐቦችና ተከታዮቻቸው ለአምልኮት የሚሰባሰቡባት አልነበሩም። ከአመቱ ሌሊቶች ተጨማሪ ስራም አይሰሩባትም ነበር። ምክንያቱም ነብዩን- ﷺ - እንዲከበሩ በተደነገገው መልኩ እንጂ አይከበሩምና። እሳቸውን ማላቅ ከትልልቅ ወደ አላህ መቃረቢያዎች ነው። ነገር ግን ልቅናው ከፍ ወዳለው አላህ እሱ በደነገገው መልኩ እንጂ (በሌላ) መቃረብ አይፈቀድም። ሰለፎች ከሌሎች ሌሊቶች በተለየ ምንም የሚጨምሩ እንዳልነበሩ መረጃው በሷ (በተወለዱበት ቀን) ላይ መወዛገባቸው ነው። ለምሳሌ እሳቸው- ﷺ - የተወለዱት በረመዳን ነው ተብሏል፣ በረቢዕ ነውም ተብሏል። በዚህም ላይ በየትኛው ቀን እንደተወለዱ አራት የተለያዩ ሀሳቦች ተሰንዝረዋል። ከፍጡራን ሁሉ በላጭ የሆኑት በመወለዳቸው ሳቢያ በማለዳዋ የተወለዱባት ሌሊት ዒባዳ የሚጠነሰስባት ብትሆን ኖሮ ውዝግብ ሳይከሰትባት በሰፊው በታወቀች ነበር። ነገር ግን ጭማሬ የሆነ ማላቅ አልተደነገገባትም።
የጁሙዐ ቀን ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናት ሁሉ በላጭ ቀን እንደሆነችና በበላጭ ቀን የሚፈፀመው በላጩ ነገር ፆም እንደሆነ አታውቅምን? ሆኖም ግን ነብዩ- ﷺ - ከትልቅ ልቅናው ጋር ከጁሙዐ ቀን ፆም ከልክለዋል። ይህም በየትኛውም ጊዜ ይሁን በየትኛውም ቦታ ካልተደነገገ በስተቀር አምልኮት መፍጠር እንደማይቻል ያመለክታል። ካልተደነገገ አይፈፀምም። ምክንያቱም የዚህች ህዝብ ኋለኛው ክፍል ከቀዳሚው የተሻለ የተቀና ነገር አያመጣምና። ይሄ በር ቢከፈትማ የሆኑ ሰዎች መጥተው ወደ መዲና የተሰደዱበትም ቀን ‘አላህ በሱ ኢስላምን ያላቀበት ቀን ነው’ በማለት ሊሰባሰቡበትና ሊያመልኩበት ነው። ሌሎች ደግሞ ተነስተው ኢስራእ ያደረጉባት ሌሊት ‘ልኬታው የማይገመት የሆነ ልቅና የተጎናፀፉባት ሌሊት ነች’ በማለት አምልኮት ሊፈጠር ነው። እናም (እንዲህ ከተከፈተ) የሆነ ወሰን ላይ ሊቆም አይቻልም። መልካም ሁሉ ያለው አላህ ለሳቸው የመረጣቸውን መልካም ቀደምቶች በመከተል ነው። የሰሩትን እንሰራለን። የተውትን እንተዋለን። ይሄ ከተረጋገጠ በዚች ሌሊት ላይ መሰባሰቡ በሸሪዐው ተፈላጊ እንዳልሆነ ግልፅ ይሆናል። እንዲያውም ይተው ዘንድ መታዘዝ አለበት። …
ይህቺ ሌሊት ደግሞ በሱፍዮች መንገድ ነው የምትዘጋጀው። በዚህ ዘመን የሱፍዮች መንገድ በዲን ውስጥ ከተፈጠሩ አስቀያሚ ነገሮች ውስጥ ነው። ምክንያቱም የጉባዔ ስርአታቸው ዘፈንና እንቶ ፈንቶ ነውና። ይሄ ነገር በነዚህ ጊዜያት ከሚፈፀሙ የላቁ መቃረቢያዎች እንደሆነና ይህ የወልዮች መንገድ እንደሆነ ለአላዋቂ ሙስሊሞች ያስተምራሉ። በሌሊትና በቀን ውስጥ ግዴታ የሆኑባቸውን ህግጋት በቅጡ የማያውቁ መሃይማን ሰዎች ናቸው። ይልቁንም አላዋቂ ሙስሊሞችን ለማጥመም ሸይጧን ምትኮች ካደረጋቸው ውስጥ ናቸው። ለሰዎች ከንቱ ነገሮችን ይሸላልማሉ። ወደ አላህ ዲንም ከሱ ያልሆነን ነገር ያስጠጋሉ። ምክንያቱም ዘፈንና እንቶ ፈንቶዎች ከዛዛታና ከጨዋታ ውስጥ ናቸውና። እነሱ ግን ወደ አላህ ወልዮች ያስጠጉታል። እነሱም በዚህ ላይ ገንዘብን ያለ አግባብ ለመብላት ይዳረሱ ዘንድ እየዋሹባቸው ነው።…” [ዑለማኡል መግሪብ ወሙቃወመቱሁም ሊልቢደዕ ወተሶውፍ፡ 128]
8. ኢብኑ ነሐስ (814 ሂ.)፡-
“አውደ-አመታትና በዓላት ውስጥ ከተፈጠሩት ውስጥ በከፊል ማውሳት” በሚል ንኡስ ርእስ ስር “ከነዚህ ውስጥ በወርሃ ረቢዐል አወል ሰዎች የፈጠሩት የመውሊድ ተግባር ነው” ይላሉ። በውስጡ ካሉ ቢድዐዎችና ጥፋቶች እንኳን ቢፀዳ ከቢድዐነት እንደማያልፍ ካጣቀሱ በኋላ ሰዎች መውሊድን ለማዘጋጀት የሚያነሳሳቸው ምክንያቶች ብለው የተወሰኑ ነጥቦችን አንስተዋል። ከነዚህም ውስጥ፡-
- ከሚጠሯቸው ቃዲዎች፣ መሪዎች፣ መሻይኾችና ከመሳሰሉት ጋር ለመተዋወቅ በማለም የሚያዘጋጁ አሉ፣
- አንዳንድ መሻይኾች ደግሞ ሰዎች በመውሊድ ምክንያት በእርዳታ መልክ ወይም በስጦታ መልክ ወይም ሃፍረት ይዞት ወይም ደግሞ ከእኩዮቹ ጋር ለመፎካከር ሲል ከሚያመጡት ነገር የሚተርፈውን ለራሳቸው ለመጠቀም በማለም መውሊድን የሚያዘጋጁ አሉ፣
- አንዳንዱ ክፉ ምላስ ያለውና ቁጡ ይሆንና ደካሞችን በመጥለፍና ምላሱንና ምግባሩን የሚፈሩ ሰዎችን በማጥመድ አላማውን የሚያሳካ አለ። … [ተንቢሁል ጋፊሊን ዐኒል አዕማሊል ጃሂሊን፡ 499]
9. ቃዱ ሺሃቡዲን ደውለት አባዲ አልሐነፊ (894 ሂ.)፡-
“በያመቱ መጀመሪያና በረቢዐል አወል ወር መሃይማን የሚሰሩት ተግባር ከምንም የሚቆጠር ነገር አይደለም። የሳቸው ﷺ ልደት ሲወሳ ይቆማሉ። ሩሐቸው ትመጣና ትካፈላለች ይላሉ። ይሄ ሙግታቸው ውድቅ ነው። ይሄ እምነት ሺርክ ነው።” [ፈታዋ ሸይኽ ሸምሲልሐቅ አዚምአባዲ፡ 166]
እንግዲህ ተመልከቱ። እነዚህ በሙሉ በ1206 ሂ. ከሞቱት ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ - ረሒመሁላህ - ዘመን ቀድሞ መውሊድን ያወገዙ ዑለማዎች ናቸው። መሃይማን ሱፍዮች ግን መውሊድን የሚቃወሙት ከ200 አመት ወዲህ የመጡ “ወሃቢዮች” ናቸው ሲሉ የራሳቸውን ድንቁርና በራሳቸው በራሳቸው አንደበትና ብእር እያጋለጡ ነው።

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የቴሌግራም ቻና

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana