Getachew shiferaw

Description
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

4 дня, 6 часов назад
Getachew shiferaw
4 дня, 6 часов назад

የትህነግ ታጣቂ ራያ ላይ እየፈፀመው ያለው ሰቆቃ በገለልተኛ ሚዲያ እይታ!

ከስር ያለው መረጃ ዓል አይን አማርኛ የትህነግ ታጣቂ እየፈፀመው ያለውን ተነግሮ የማያልቅ ሰቆቃ በወረራ ስር ያሉትን ነዋሪዎች አናግሮ ከዘገበው የተወሰደ ነው።

#የትግራይ ታጣቂዎች ከመጡበት ዕለት አንስቶ ንብረታችን እየተነጠቀ ነው፡፡ ለገበያ የደረሰ ሀብ ሀብ አትክልቴን በልተውብኛል ሲጠግቡ ደግሞ በያዙት ጦር መሳሪያ በሰደፉ እና በአፈሙዙ እየመቱብኝ ነው”

#በቀበሌያችን ከገቡበት ከሰኞ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ በገበሬው ቤት እየገቡ እየደበደቡን ነው። አርሶ አደር ጦር መሳሪያ አምጡ እያሉ እኛ ገበሬዎች ነን ፖለቲካ አናውቅም ብንልም ሊተውን አልቻሉም"

#ከዚህ በፊት አብረውን ይኖሩ የነበሩ ነገር ግን በስጋት ምክንያት ወደ ትግራይ ተፈናቅለው የነበሩ ሰዎች ካሳለፍነው ሰኔ እና ግንቦት ወር ጀምሮ እየገቡ መኖር ጀምረዋል፣ ሳይገቡ የቀሩት ከዚህ በፊት በነበረው አስተዳድር ጊዜ ህዝብን ሲያንገላቱ እና ሲያማርሩ የነበሩት ብቻ ቀርተው ነበር"

#ታጣቂዎች ሲቪል እየለበሱ ወደ ከተማዋ ነዋሪ መስለው እየገቡ ነው፣ የመንግስት ተቋማትን እየዘረፉ እና ፋይሎችን እያወደሙ የከተማዋ ነዋሪዎችንም ፍርሃት ውስጥ እንዲገባ የተለያዩ ጫናዎችን እያደረጉ ነው። በከተማዋ ያለው የፌደራል የጸጥታ ሀይል ቢኖርም ነዋሪውን ከመሰደድ አልታደገውም"

#የፌደራል መንግስት ለራያ እና አላማጣ ጉዳይ ዘለቄታዊ መፍትሔ ይሰጠዋል ብለን እየጠበቅን ለትግራይ ታጣቂዎች አሳልፎ ሰጥቶናል።

#በሰሌን ውሃ ቀበሌ የሚኖረው ሌላኛው አስተያየት ሰጪ በበኩሉ የትግራይ ታጣቂዎች የራያ እና አላማጣ የገጠር ቀበሌዎችን ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ መቆጣጠራቸውን፣ በየቀኑ አዳዲስ እና ተጨማሪ ታጣቂዎች ወደ አካባቢዎቹ እየገቡ መሆኑን አክሏል፡፡
ታጣቂዎቹ በየሰው ቤት እየገቡ የልጆችን ምግብ ሳይቀር እየበሉ እንደሆነ፣ ለባሏ የምሳ እቃ ለማድረስ ወደ እርሻ ቦታ እየሄደች ያለችን እናት ለአማራ ታጣቂ ልትሰጪ ነው በሚል እያንገላቱ ነው ያሉት እኝህ አስተያየት ሰጪ ታጣቂዎቹ ይህን ሲያደርጉም የፌደራል የጸጥታ ሀይሎች እያዩ የማስቆም ፍላጎት እንደሌላቸውም ነግሮናል፡፡

#ከዚህ በፊት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው ወደ መቀሌ እና ሽሬ የሄዱ ነዋሪዎች ወደ ቀድሞ ቤታቸው ተመልሰው አብረን በጋራ እያረስን እና እየኖርን ቢሆንም ታጣቂዎቹ በድንገት መጥተው ለእንግልት እንደዳረጓቸውም አክሏል፡፡

#ታጣቂዎቹ በየጊዜው እየሰበሰቡም ከእንግዲህ እምናስተዳድራችሁ እኛ ነን፣ የያዛችሁትም የአማራ ክልል የነዋሪነት መታወቂያ ከእንግዲህ አይጠቅማችሁም፣ ልጆቻችሁን አምጡ እና ለአማራ ታጣቂዎች ድጋፍ እያደረጋችሁ ነው የሚሉ ወከባዎችን እያደረሱባቸው እንደሆነም እኝህ አስተያየት ሰጪ ተናግረዋል፡፡

#ወቅቱ የሚያዚያ ወር አዝመራ የምናዘምርበት ቢሆንም እርሻችንን ትተን በየቀኑ ምን እንሆን ይሆን የሚል ስቃይ ውስጥ ነን"

5 дней, 10 часов назад

ተፈናቃይ ብለው የሚያስገቡት ይህንን ዘራፊ ኃይል ነው!

ትህነግ በወረራው ወቅት አማራና አፋርን መዝረፍን ጀብዱ አድርጎ ለወጣቱ አስተማረው። አትክልትና ፍራፍሬ ጭምር "ከአማራ ክልል የመጣ" እየተባለ በሞንታርቦ እየተጮኸ ሲሸጥ ነበር። የአማራ ክልል ታርጋን አንስተው ታርጋ አልባ መኪና የሚነዱት "አምጥቶ ነው" እየተባሉ በጀብድ ተነገረላቸው። እርጉዝ ሳይቀር ለዘረፋ መጥታ አማራ ወልዳ ተይዛለች። ወጣቱ "እኔም ይህን አምጥቻለሁ" እያለ በጀግንነት እንዲያወራ ተደረገ። ከጦርነቱ በኋላ ግን ዘረፋውን ትግራይ ውስጥ ቀጠሉት። አማራ ላይ ጀግና የተባሉበት ነዋ! የቀራቸው ነገር የለም። ፍርድ ቤት ስላልቻለ እንደ ድሮው በአደባባይ በዚህ መልክ መቅጣት ጀምረዋል።

ታዲያ ወደ ራያ የላኩት ይህን ዘራፊ ኃይል ነው። አዲስ ልብስና ጫማ ሳይቀር እያስወለቀ ሲወስድ የሚታወቅ ዘራፊ ራያን እያራቆተ ነው። በወረራው ወቅት ሲዘርፍ ጀግና ያሉትና ከወረራ በኋላ ትግራይን ያስመረረውን ነው ወደ ራያ የላኩት። ወደ ጠለምትና ወልቃይትም ለማስገባት የወሰኑት ይህ ሰው በላ የሆነን ኃይል ነው።

1 неделя, 5 дней назад

የአማራ ንብረት ወደ መቀሌ እየተጫነ ነው!

በትህነግ ከተወረረው ራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ንፁሃንን አነጋግሮ ሰሜን ወሎ ዞን መረጃ አጋርቷል። ከእነዚህ መካከል፦

1) የትህነግ ታጣቂ በወረራ በያዛቸው የራያ ባላ፣ የራያ አላማጣ፣ የወፍላ ወረዳ እንዲሁም የአላማጣ እና የኮረም ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ የመንግስት እና የሃይማኖት ተቋማቶች ንብረት በመቅደድ፣በማቃጠልና ወደ መሃል ትግራይ ሲጭን ሰንብቷል።

ከሞቀ ቤታቸው ወጥተው በቆቦ ከተማ ተፈናቅለው ለሚገኙት ተፈናቃዮች የምግብ ዱቄት ይዘው የመጡት የአስተዳደሩ ተወካዮች ይህ ድጋፍ ለዚህ ህዝብ የሚመጥንና የሚገባ ሆኖ ሳይሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ስንገናኝ ባዷችንን ከምንመጣ በማሰብ ሲሆን፣ የደሴ እና የኮምቦልቻ ህዝብ አምሳያው የሆነው የራያ እና የወፍላ ሕዝብ ወደ ቀየው እንዲመለስ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

2) የአርሶ አደሩን የአትክልትና የፍራፍሬ ውጤቶች የሚጫነው ተጭኖ ያልቻሉትን ማውደማቸውንና ማፈናቀላቸው ታውቋታውቋል።

3) ቤት ለቤት በመፈተሽ ወጣቶችን ባለፈው ጦርነት ተሳትፏል በሚል ግድያ እየፈፀሙ ስለሆነም ተጨማሪ መረጃዎች ወጥተዋል።

ትህነግ/ህወሓት ራያን መሬቱን እንጅ ህዝቡ የትግራይ እንዳልሆነ እንደማይክደው የሰሞኑ ክስተት ማሳያ ነው። ከራያ የህዝብ ንብረትን ዘፈው እያጓጓዙ ያሉት ወደ ራሳቸው ግዛት ወደ ትግራይ ነው። ራያ ግዛታቸው ስላልሆነ የሚዘረፍና የሚጨፈጨፍ ጠላታቸው አድርገው የፈረጁት ነው።

1 неделя, 5 дней назад
Getachew shiferaw
1 неделя, 5 дней назад
Getachew shiferaw
1 неделя, 5 дней назад

ይችን ጉድ ተመልከቷት!

የአብይ አህመድ ብልፅግና ራሱ በመራው ጦርነት "የዘር ፍጅት ተፈፀመብን" ካሉት የትህነግ አካላት ጋር አብሮ እየሰራ መሆኑን "ኮምሽን" አዋቅረው የሚንቀሳቀሱት ተናግረዋል።

ዓለም አቀፍ ገለልተኛ ምርመራ ይደረግ ተብሎ ጥረት ተደርጎ ነበር። ዶክተር ዳንኤል በቀለ የሚመራው አሰመኮና ተመድ በጋራ ይመረምራሉ ከተባለው በሻገር ሌሎችም ሙከራ አድርገው ትህነግ/ህወሓትና አብይ ተስማምተው ምርመራውን አስቁመዋል። ዓለማቀፍ አጣሪዎችን አስቁመው ትህነግ መጀመሪያ ከጥናት በፊት የዘር ፍጅት ተፈፅሟል ብሎ ደምድሞ ያስጀመረውን የትርክት ፕሮጀክቶት ግን አብይ ደግፎ እያሰራው ነው።

ትልቁ ሚስጥር ደግሞ ከአብይ ጋር ብቻ ሳይሆን ከአብይና ከዓለም ባንክ ጋር እንደሚሰሩ የገለፁበት ነው። ዝም ብሎ ትብብር አይደለም። ይህን እውቅና ካልሰጠ ገንዘብ አይሰጥህም ተብሏል። በየጊዜው የብድር ድርድር ሲኖር ትህነግ በማያገባው እግሩን እንዲያስገባ ይፈቀድለታል። የሰሞኑ የራያ ወረራም አብይ ቢሊዮን ዶላሮችን ይሰጡኛል ካላቸው የገንዘብ ተቋማት ጋር ድርድር ሲያደርግ የተፈፀመ ነው። የአማራ ርስቶችን የመበደሪያና የእርዳታ ቀብድ አድርጓቸዋል። አንድ የትህነግ ሰው "ወደራያ የገባነው በአሜሪካ ቀጭን ትዕዛዝና በአብይ ይሁንታ ነው" ብሎ ቃል በቃል ፅፏል።

ስዩም ተሾመ ደግሞ "ህወሓትን መሳሪያ ልናስፈታው ቀርቶ ተጨማሪ መሳሪያ ሰጥተነዋል።" ብሏል። ይህ ሁሉ የጓዳ ውሎቹ መገለጫ ነው። ትህነግ/ህወሓት አላማችን ያስፈፅምልናል ብለው የሚያግዙት በእርዳታና ብድር ስለመጡ ብቻ ሳይሆን አማራና ኤርትራን ካልመታን ተብሎ ብዙ ተሰርቷል። የዘር ፍጅት ተብሎ የተሰራው የትህነግ ትርክት በአብይ አህመድ ድጋፍ ማግኘቱ ሌላ የጓዳ ውል መገለጫ ነው።

1 неделя, 6 дней назад

አብይ አህመድ የሚመራው ኃይል ኦሮሚያ ውስጥ አዲስ ፀረ አማራ ጥቃት ከፍቷል። ጦርነቱን በሕዝብ ላይ አድርገውታል። ጦርነቱን ሕዝብን አሳትፈው ቀጥለዋል። ሰሞኑን አማራ ስለሆነ ብቻ እየቀረፁ ሲያሰቃዩት ታይቷል። አሁን ደግሞ ቤት ለቤት እየዞሩ እያጠቁ ነው። የአብይ አህመድ ኃይል በጀት በጅቶ የሚያንቀሳቅሰው የዘር ፍጅት ነው!

1 неделя, 6 дней назад
Getachew shiferaw
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas