Getachew shiferaw

Description
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

2 months, 3 weeks ago

የጓዳ ስምምነት ስንል የከረምነው ይህን ነው!

ጌታቸው ረዳ ትናንት ባደረገው ቃለ መጠይቅ ስለ ጓዳ ድርድሮቹ ብዙ ተናግሯል።

1) ፕሪቶሪያ ላይ የነበሩት ተደራዳሪዎች እንዲቀሩ ተደርገው ኬንያ ላይ እነ ብርሃኑ ጁላ ሲገኙ ጌታቸው ረዳ የደቡብ አፍሪካውን ስምምነት በሚቀይር ሁኔታ በእጅ ፅሁፍ ሁሉ ማስተካከሉን ይናገራል። በአጭሩ የጓዳ ስምምነቱ ዋናውን ስምምነት በእስክርቢቶ ያስደለዘ ያሰረዘ ጭምር ነው። ከእነ ብርሃኑ ጁላ ጋር ከበው ሲያጨሱ፣ ሬድዋን ሁሴን የትህነግ ተደራዳሪዎች ማረፊያ ክፍላቸው ድረስ ሲሄድ "ራስህ በእጅህ ፅፈህ ቢሆን አስተካክለው" ተብሎ እንጅ እንዲሁ ማስተካከል አይችልም።

2) በደቡብ አፍሪካ የነበረው ድርድር ላይ ስለ አስተዳደር ጉዳዮች የተቀመጠው በኋላ በተደረጉ ድርድሮች መቀየሩን ይገልፃል።

3) መከላከያ የያዛቸውን አካባቢዎች በኋላ በተደረጉ ድርድሮች መቀየሩን ይናገራል። የዚህኛው አላማ መከላከያ ወደ አማራ ክልል ዞሮ ፋኖን ትጥቅ በማስፈታት ስም አማራ ላይ ጦርነት እንዲያውጅ የተስማሙበት ነው። ከኬንያው የጓዳ ስምምነት ማግስት እነ ጌታቸው ረዳ ከእነ ሽመልስ አብዲሳ ጋር እየተቃቀፉ የተነሱበት ፎቶ በትግራይና ኦሮሞ አክቲቪስቶችና ሚዲያዎች ዘንድ "አማራ መጣንልህ ጠብቀን" ሲባል የነበረው ከጓዳ ስምምነቱ አላማ አንፃር ነው። በጓዳ ስምምነቶቹ መሰረት አማራ ልዩ ኃይልን ቀጥሎ ፋኖን ትጥቅ አስፈትቶ የአማራን ርስቶችና ጥቅሞች አሳልፎ መስጠት ነው። አንዴ ናዝሬት፣ ሌላ ጊዜ ደብረዘይትና ሀላላ ኬላ ድረስ የተደረጉት ስምምነቶችና የኦህዴድና ትህነግ ዳግም ጋብቻ እስኪመስል ድረስ የነበረው ሁኔታ በአማራ ላይ ለመዝመት የተደረገ ስምምነት ነው። አንዳንድ ወገኖች አሜሪካ ያሉ የብአዴን ሰዎች ከትህነግ ጋር ግንኙነት ስለጀመሩ ብቻ ያን ሁሉ የጋራ ዘመቻ ይረሱታል። በአማራ ላይ ጦርነት እንደተከፈተ ታስረው የነበሩ የትህነግ ወታደሮች በታሰሩ ጊዜ ያልተከፈላቸው የሁለት አመት ደሞዝ ተከፍሏቸው ነው ጦርነቱን የተቀላቀሉት። ይህ ሁሉ የሆነው በጓዳ ስምምነቱ ነው። አማራ ላይ ጦርነት የታወጀው ጌታቸው ረዳ የሚነግረን የኋላ ድርድሮች መሰረት ነው። የትህነግ ጀኔራሎች ቤተ መንግስትና ጦር ኃይሎች እየተመላለሱ ጭምር ፀረ አማራውን ዘመቻ አማክረዋል። የፋኖ አቅም ሲበረታ ነው ሌላ አማራጭ ማየት የጀመሩት። አሁን ስለ ጓዳ ድርድሮቹ ሌሎች በርካቶች ያልነገረን ሚስጥሮች አሉ።

ነገር ግን በዛ የጓዳ ስምምነት ለአማራና ኤርትራ ብለው ትጥቅ እንዳይፈታ ያደረጉት ታጣቂ አሁን ጌታቸው ረዳ ላይ ተነስቷል። ነገ አማራና ኤርትራን ብቻ የሚያጠቃ የሚመስለው ካለ እየሆነ ያለውን ያልተገነዘበ መሆን አለበት።

በነገራችን ላይ ብዙ ነሁላሎች የትህነግ ሚዲያዎችም ሆኑ ሌሎች የትህነግ ኃይሎች በጦርነቱ ፋኖን የደገፉ ይመስላቸዋል። ውሸት ነው። ዋናዎቹ የጦርነት አጫፋሪዎችና የጓዳ ተዋዋዮች ናቸው። ትህነግ የአማራውን ጦርነት የሚፈልገው ወግተውኛል የሚላቸው ኃይሎች ተዳክመው ወደ አራት ኪሎ ሾልኮ ለመግባት ብቻ ነው። ይህን ለመረዳት የትህነግ ጀኔራሎች በየመድረኩ ጠላቶቻቸው እርስ በእርስ እየተፋጁ ነው ብለው በተደጋጋሚ የተናገሩትን ማዳመጥ ነው።

3 months ago

ለእናንተ መውጫ ብቻ አትፈልጉን!

ይች ሰውዬ አማራን ሲረግም ነው የከረመው። የሆነ የትግራይ ፓርቲ አመራር ነው። አሁን ሚዲያ ቀርቦ "መውጫችን ከአማራና ኤርትራ ጋር መስራት ነው" ይላል።

1) የሚፈልጉን ለእነሱ ችግር መውጫ መሆኑ ነው። ያው ኦሮማራ እንደተባለው እነሱም አማራ ላይ ሊቆምሩ መሆኑ ነው። ለራሳችሁ መውጫ ስትሉ አትፈልጉን ማለት ይገባል።

2) አሁንም 'ከአማራ ጋር እንሰራለን" ሲሉ ከድሮው ሳይማሩ ነው። ቢችለ የአማራን ግዛት ለመውረር እየተዘጋጁ፣ ሲያስፈልግ ከአገዛዙ ጋር እየተሞዳሞዱ።

አንድ በውጭ አገር የሚኖር ወዳጀ "አንተ ህወሓትን ተውት ከአማራና ኤርትራ ጋር እሰራለሁ እያለ ነው።" አለኝ። የአሜሪካን ዲፕሎማት ምንጭ ጠቅሶ። ዝርዝር ጠየኩት። ትህነግም ቃል በቃል የሚለው ይህ በቃለመጠይቁ ላይ ያለው ሰውየ ያለውን ነው። "መውጫ መንገዳችን አማራና ኤርትራ ጋር መስራት ነው ብለዋል። አታክርሩ" አለኝ። "ለምን ከችግር ለመውጫ ይፈልጉናል? ብዬ ተቃውሞዬን ነገርኩት። ቀጥዬም አይማሩም። በአማራ ርስቶች ጉዳይ አብይ አሳልፎ ይሰጠናል ብለው አብረው እየሰሩ እንደሆነ፣ እውነታውን መቀበል እንደማይፈልጉ፣ የዘር ፍጅት የፈፀሙበት አካባቢ ላይ አሁንም ቢችሉ ሌላ ወረራ እንደሚያደርጉ መከራከሪያ አቀረብኩ። አጣጣለብኝ። እንግዲያውስ ምንጭህን ጠይቀህ ተመለስ አልኩ።

ከቀናት በኋላ ያው ወዳጀ ደወለ። "በአማራ ግዛቶች ጉዳይ ለውጥ አላደረጉም። እንዳልከው ነው። አብረን እንሰራለን የሚሉት በጦርነቱ ወቅት ተከፍሏቸው አብረዋቸው የከረሙትን ከሃዲዎች ጋር ነው" አለኝ።

ለዚህ ነው መውጫ እንድንሆናቸው የሚፈልጉት። ለምን ጥልቅ ጉድጓድ ላይ ገብተው አይቀሩም? ምን ያገባናል?

አማራ ለጋራ ህልውና እንጅ ለሌላ አካል መዳን ሲል አሳልፎ የሚሰጠው ጉዳይ የለም። አማራ የራሱን ህልውና ለማዳን፣ የጋራ ህልውና ለመመስረት እንጅ ለሌላ ህልውና ብቻ ሲል የሚከፍለው ዋጋ የለም። አማራ ለአገርና ህዝብ ሲል የተዋቸው ጉዳዮች እንደ ተላላነት ቆጥራችሁ ተራ በተራ የምትቆምሩበት ህዝብ አይደለም። መረማመጃ ይሆነናል ብላችሁ አስባችሁ ከሆነ እንጦሮጦስ መውረድ ትችላላችሁ። ለጋራ ህልውና፣ ለጋራ አላማ፣ አትማሩም እንጅ ተምራችሁ ቢሆን ግን አብሮ ከመስራት ወደኋላ ሊል አይችልም። የእናንተው ግን የእነ ሽመልስ አብዲሳን በትግርኛ ተርጉማችሁ ነው። አይሆንም! ከደቡብ አፍሪካው ስምምነት ማግስት "መውጫችን ከኦህዴድ ጋር አብሮ አማራና ኤርትራን መምታት ነው" ብላችሁ እንዘጭ እንዘጭ ማለታችሁን አንረሳውም። አማራ የሆነ ጊዜ ሲቸግራችሁ ትግሉንና ወዳጅነቱን የምትዋሱት ህዝብ አይደለም። በዚህ ሞኛሞኝ ፖለቲካ የሚስማማ ካገኛችሁ ሌላ መውጫ ፈልጉ!

3 months, 1 week ago

እነ ሽመልስ አብዲሳ ያስገደሉት ዋና አስተዳዳሪ ጉዳይ!

ከሶስት ወር በፊት መከላከያ ባሕርዳር ላይ ሕዝባዊ ስብሰባ በሚል የተለያዩ አካላት ጋር ውይይት አደረገ። በዚህ ውይይት የኦሮሞ ብልፅግና አዲስ አበባና ናዝሬት ላይ እየሰበሰበ አማራ ክልል ውስጥ የክልልነት ጥያቄ እንዲያነሱ የሚደግፋቸው አካላት በይፋ "ክልል መሆን አለብን" የሚል ጥያቄ አነሱ።

ከከሚሴ ዞን የመጣው ግን ያልተጠበቀ ነበር። የከሚኬ ዋና አስተዳዳሪ የነበረው አቶ አህመድ አሊ በመድረኩ "ሕዝባችን ቋንቋውን እየተጠቀመ፣ በልጆቹ እየተዳደረ ነው። ከአማራ ክልል ያጣነው፣ አሁን ካለው የተለየ የምንጠይቀው ነገር የለም።" ሲል ተናገረ። በሶስተኛው ቀን በጠራራ ፀሐይ ገደሉት። ከቀናት በኋላ ገዳዩ "እጅ አልሰጥም ብሎ ተገደለ" ብለው ቀለዱ። ገዳዩን መጀመሪያ ሸኔ ቀጥለው ደግሞ ግለሰብ አደረጉት። ተገድሏል ብለው ነገሩን "አለቀ ደቀቀ" አሉ።
ሰውየው የተገደለው በእነ ሽመልስ አብዲሳ ቀጥታ ትዕዛዝ ነው።

7 months ago

የሱዳን ዋና ዋና ሚዲያዎችኀ ትህነግ/ህወሓት የአልቡርሃን ቆጥረኛ ሆኖ በሱዳን እየተዋጋ መሆኑን ቀዳሚ አጀንዳ አድርገዋል። ይህን ቅጥረኛ ኃይል ነው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ተፈናቃይ ብላችሁ መልሱ እየተባለ ያለው።

7 months ago

የፕሪቶሪያ ስምምነት መቆመሪያቸው ነው!

ስምምነቱ እነ ጌታቸው ረዳ ከአማራ ለመንጠቅ የሚፈልጓቸውን ግዛቶች "የተወረሩ" አይላቸውም። "አወዛጋቢ" ነው የሚላቸው። በዚሁ ስምምነት መሰረት የጥላቻና የጦርነት ቅስቀሳ የተከለከለ ነው። በትህነግ በኩል ፈራሚው ጌታቸው ረዳ ግን አሁንም "ወራሪ" እያለ እየፃፈ ነው። የሰላም ስምምነት ተብሎም ለእሱ አማራ ወራሪ ነው። ስምምነቱ መቋመሪያ ካርድ እንጅ እንደማያከብሩት ይታወቃል። በጓዳ ግዛቶቹን አሳልፎ ለመስጠት የሚስማማው የአብይ አገዛዝም በስምምነቱ መሰረት ባቋቋመው ኮሚቴ ይህን እንደማይገመግም ይታወቃል።

የአማራ ክልል ጉልት ካድሬ ደግሞ በስምምነቱ መሰረት በስሩ እንዲቆይ የተወሰነውንም አስተዳደር አፍርሶ ትግራይ ውስጥ አንድ ቀበሌ በቅጡ ለማያስተዳድረው፣ ስካይ ላይት መቀመጫውን ላደረገው ጌታቸው ረዳ አሳልፎ ሰጥቷል። በዚህ ከቀጠለ አብይ አጠቃላይ አማራ ክልልን ለጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ቢሰጠውም ከዝምታ የተሻለ ከአማራ ክልል ካድሬ እንደ አማራጭ የሚቆጠር ስልት ያለ አይመስልም።

በዚህ በዓል መልዕክት ቀርቶ በሌላም ጊዜ በአማራ ላይ አፍ መክፈትን የህዝብ መሰብሰቢያ ካደረጉት የትህነግ አመራሮች ውጭ ጦርነት እየቀሰቀሰ ያለ አይመስልም። ለትንሳኤ በዓል መልዕክት እንኳን አማራን በለመዱት ክፍታፍነታቸው ከመዝረፍና ከመውቀስ የሚመለሱ አይደሉም።

7 months ago

የባልደራስን ንቁ አባላት ያሳሰረው ኤርሚያስ ለገሰን ተንኮል ተመልከቱ!

የኤርሚያስ ወዳጅ የነበረው ቴድሮስ ፀጋዬ ሰሞኑን ኤርሚያስ የባልደራስ ንቁ አባላትንና የአዲስ አበባ ወጣቶችን እየጠቆመ እያሳሰረ እንደሚገኝ በቀጥታ ስርጭት ተናግሯል። ይህን የባልደራስ የቅርብ አመራሮችም አረጋግጠውልኛል።

ትናንት የሰራውን ፕሮግራም እንኳን ተመልከቱ። ያሳሰራቸው የባልደራስ ንቁ አባላት መካከል ናቲን ፎቶ የፊት ገፅ ላይ ሆን ብሎ አቀናብሮ ከሚከሳቸው የፋኖ አባላት ጋር አቅርቧል። ኤርሚያስ ለፕሮፖጋንዳ የሚጠቀምበትን እያንዳንዱን ጉዳይ የሚያውቅ ሰው ነው። የፊት ገፅ ሲያሰራ ምን ማስተላለፍ እንደፈለገ ግልፅ ነው። ከሰላማዊ መንገድ ውጭ የትጥቅ ትግሉ ላይ ፈፅሞ የሌሉበትን ወጣቶች ፎቶ ሾፕ እየሰራ ጭምር የሀሰት ጥቆማውን እውነት ለማስመሰል እየሰራ ያለ አደገኛ ሰው ነው።

ከቅርቡ የአዲስ አበባ ክስተት በኋላ አዲስ አበባ ላይ ሽብር የሚፈፅሙት የከተማው ተወላጆች ጭምር አሉ ብሎ የአዲስ አበባን ወጣት በሀሰት ከስሷል። በተለይ በተለይ ባልደራስ ሰልፍና ስብሰባ ሲያደርግ ንቁ እንቅስቃሴ ያደርጉ የነበሩ፣ በሚዲያ ያግዛል ተብሎ መረጃ የሚሰጡትና ለፓርቲው ሰላማዊ እንቅስቃሴ በተለያያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ግሩፕ ውስጥ የነበሩትን ለአገዛዙ እየጠቆመ አሳስሯል። የባልደራስ አመራሮችም ያረጋገጡት መረጃ ነው።

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago