Muhammed Hassen (ሙሐመድ ሐሰን)

Description
Official telegram channel
https://t.me/ibnuHassen10
https://t.me/ibnuHassen10

Durus channel
https://t.me/M_Hassen_Durus
https://t.me/M_Hassen_Durus

Hood_hood channel
https://t.me/Hood_Hood
https://t.me/Hood_Hood
.
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 month, 1 week ago

Last updated 1 month ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 day, 21 hours ago

3 Tage, 9 Stunden her
ይህ የነብዩን ﷺ መስጂድ ነው! እንኳን …

ይህ የነብዩን ﷺ መስጂድ ነው! እንኳን ቦታውና ወፎቹ ራሱ ፍቅር ናቸው! የቤቱማ ነገር ነፍስ በቦታው ስትሆን በእርካታ ትፏልላለች! ልብ በመዲነቱል ሙነወራ መስጂደ ነበውይ እና በመከቱል ሙከረማህ በይቱላሂል ሐራም! ስትሆን በደስታ ትቦርቃለች! ዱንያንም ጀነትንም በእጇ የተቆጣጠረች ያክል ይሰማታል!...አላህ ሆይ ቤትህን የናፈቁ ልቦችን ሁሉ ለቤትህ አብቃቸው!......

https://t.me/ibnuHassen10

3 Tage, 13 Stunden her
እሱ:- እወድሻለሁ አላት

እሱ:- እወድሻለሁ አላት

እሷ :-ከዚያስ አለችው

እሱ :-ሁሌ አንቺን ማየት እፈልጋለሁ አላት

እሷ :-ከዚያስ አለችው

እሱ:- ወደ ሩቅ ቦታ ወስጄ አዝናናሻለሁ አላት

እሷ:-ከዚያስ አለችው

እሱ:-ቤቴ እወስድሽና ፈታ እንላለን አላት

እሷ:-እነደዛ ከሆነ አንድ ቆንጆ ሐሳብ አለኝ አለችው

እሱ:-የደስታ ጫፍ ላይ ሆኖ በጉጉት ምንድን ነው? አላት

እሷም "ደስ ያለህ ቦታ ትወስደኛለህ ባይሆን ግን እህትህንም እኛ ጋ ትወስዳትና ከጓደኛህ ጋር ፈታ እንዲሉ የምትፈቅድ ከሆነ ነው አለችው!

እሱም:- በሀፍረት አቀረቀረ

ከዛም በመሳለቅ መልኩ በል ሂድና ፂምህን ተላጭተህ የእህትህን ልብስ ልበስ አንተ ወንድ አይደለህም አለችው።

አንዳንድ ወንድሞች አላህ ይምራቸውና እንደ ፊርዓውን ቆሽሸው የስንት እህቶችን ህይወት ካመሰቃቀሉ በኋላ ለትዳር ሲሆን ግን እንደ መርየም የሆነች ነፁህ ሴት ይፈልጋሉ!

ወንድሜ ለእህትህ የማትወደውን በሌሎች እህቶች ላይ አትፈፅም። እህቱን የሚወድ የሌላን ሰው እህት ህይወት አያላሽም። የማትሆንህ ከሆነ አገባሻለሁ እያልክ ልቧን አትስቀለው። እህትህ ብታለቅስ ደስ ይልሃል?

3 Tage, 15 Stunden her
አብሽሩ!

አብሽሩ!

ፀሐዩንም፣ ብርዱንም… ጭቆናንም፣ መገፋቱንም፣ ባይተዋርነቱንም፣ መበደሉንም፣ ጫናውንም፣ ጥላቻውንም፣ መገለሉንም፣ መንገላታቱንም… ችላችሁ በጌታችሁ ትዕዛዝ ቀጥ እስካላችሁ ድረስ፤ ጌታችሁ ቃል የገባላችሁ ጀነት አለችላችሁ።

ኒቃቢስቶች → የምድር ጌጦች → በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ደማቅ የሰማይ ኮከቦች

https://t.me/ibnuHassen10

1 Woche, 1 Tag her
"[በመካከላቹህ ውደታን እና እዝነትን አደረ](https://t.me/ibnuHassen10)ገ"

"በመካከላቹህ ውደታን እና እዝነትን አደረገ"
~
ዛሬም ድረስ ሚስቱን እወድሻለሁ ብሎ ለመናገር ተራራ የመውጣት ያክል የሚከብደው ትውልድ መኖሩ አይገርምም? እኮ ፍቅርህን በመግለፅ ከሃዲያን ይብለጡህ? Shame on you! ወዳጄ ሮማንቲክ ለመሆን ፊልም ማየት ሳይሆን ውዱ ነብይ ከውድ ሚስቶቻቸው ጋር የነበራቸውን ታሪክ ማንበብ በቂህ ነው። ሶሓቦች እና ደጋግ ቀደምቶች ከሚስቶቻቸው ጋር የነበራቸውን የፍቅር ታሪክ ከጨመርክበትማ ተወው አንተን የሚያክል ሮማንቲክ በዚች ምድር አይኖርም ስልህ!በነገራችን ላይ የዐረብኛ ቋንቋን ማለቴ ነሕው፣ሶርፍ፣በላጛ...ትምህርት ላይ አብዛሃኛዎቹ የግጥም ሸዋሂዶች ፍቅርን ለመግለፅ የተገጠሙ ግጥሞች ናቸው።
ነብዩናﷺ ሲበዛ ሮማንቲክ ነበሩ:-
1 ነብዩና ወሐቢቡናﷺ እኔ ላንቺ ያለኝ ፍቅር አቡ ዘርዓ ለኡሙ ዘርዓ እንዳለው ፍቅር ነው። ባይሆን እርሱ ፈቷታል እኔ ግን አልፈታሽም እንጅ ይሏት ነበር።የአቡ ዘርዓና የኡሙ ዘርዓ ዐጂብ የሆነ የፍቅራቸውን ታሪክ ኢንሻአላህ ሌላ ጊዜ...
2 ነብዩና ወሐቢቡናﷺ አዒሻን ሲጠሯት አንዳንዴ አዒሽ፣አንዳንዴ ሑመይራእ፣አንዳንዴ የአቡበክር ልጅ፣ አንዳንዴ የሲዲቅ ልጅ እያሉ አቆላምጠው ነበር የሚጠሯት።
3 ነብዩና ወሐቢቡናﷺ ሶፊያ ቢንት ሑየይን ባገቧት ጊዜ ግመሏ ላይ እንዲትወጣ ጉልበታቸውን በርከክ አሉላት ከዚያ ጉልበታቸውን ተረግጣ ግመሏ ላይ ትወጣ ነበር። የፍጥረታት ሁሉ ምርጥ ለሚስታቸው ካላቸው ፍቅር የተነሳ ጉልበታቸውን ረግጣ እንዲትወጣ አድርገው ያሳዩህን ውድ ነብይ ተምሳሌት ማድረግ ምን ከበደህ?
4 ነብዩና ወሐቢቡናﷺ በ60ዎቹ እድሜ ሆነው ሶሃቦቻቸውን ሂዱ እኔ ከአዒሻ ጋር ሩጫ ልወዳደር ነው ብለው ከአዒሻ ጋር ሩጫ ይወዳደሩ ነበር! አንተስ ሚስትህን ለማዝናናት እና ለማስደሰት መሽኮርመም እና ማፈርህ ከየት የመጣ ነው?
@ibnuHassen10

1 Woche, 1 Tag her
አይናፋሯ ልዕልት

አይናፋሯ ልዕልት

ለአባቷ~ኩራት
ለወንድሟ~ክብር
ለባሏ ~ስጦታ
ለልጇ ~ተምሳሌት
ለሙስሊሙ~ጡብ ናት

እናማ እህቴዋ ትሁት፣አይናፋር፣ጨዋ፣አደበኛ ልእልት/ንግስት ሁኚ እነዚያ በምዕራባውያን ቫይረስ ተፈትነው ርቃናቸውን የሚሄዱት ሞልቃቃ እንስሳቶች እንዳያታልሉሽ።

https://t.me/ibnuHassen10

1 Woche, 1 Tag her

ኒቃቢስቷ

ከውብ አልባሳትሽ እንዳትላቀቂ
ኒቃብ ስለ-ለበስሽ እንዳትሳቀቂ
ብርታት ነሽ የድካም ሞራል አነቃቂ
በጥቁሩ ልብስ ስር ታምሪያለሽ ስትደምቂ
ሴት ወንዱ ይቀናል ይህንን እወቂ!

Credit:ኑረዲን አል ዐረቢ

1 Woche, 2 Tage her
1 Woche, 2 Tage her
ሶላት ሰጋጇን ትለውጣለች......

ሶላት ሰጋጇን ትለውጣለች......

የኛ ሶላትስ ከነበርንበት መጥፎ ገፀ ባህሪ ለውጣናለች?....

1 Woche, 2 Tage her
በመጥፎ ጥርጣሪያችን ምክንያት

በመጥፎ ጥርጣሪያችን ምክንያት
-ስንትና ስንት ወዳጆቻችንን ጠላን?
-ስንትና ስንት በዙሪያችን ያሉ ቅርብ ሰዎችን በደልን?
-ግንኙነታችን ላልቶ ስንትና ስንት ዝምድናችን ቆረጥን?!

ወዳጄ:-ስለ ሰዎች ስታስብ ራስህን ወንጀለኛ አድርገህ ተመልከት ሌላውን ደግሞ ምን ደካማ ቢሆን ከኔ በኸይር ነገር ይሻል ይሆናል ብለህ ጠርጥር። መጥፎ ጥርጣሬን ግን አስፈላጊ መሆኑን ካላመንክ በስተቀር ብዙውን ተጠንቀቅ። ጌታችንም አላህ በተከበረ ቃሉ "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙውን ራቁ፤ ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና፡፡ ብሎናል

1 Woche, 3 Tage her
የማይቀና ደዩስ ነው።

የማይቀና ደዩስ ነው።
..........///..........
ሰዕድ ኢብኑ ዑባዳህ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና ከቅናቱ የተነሳ አንድን ወንድ ከባለቤቴ ጋር ባየው ያለምንም ይቅርታ በሰይፍ እቀላዋለሁ ይል ነበር።ታዲያ ይሄ ወሬ ለነብዩﷺ ደረሳቸውና "በዚህ ትገረማላቹህን? በአላህ ይሁንብኝ ከሱ የበለጠ እኔ በጣም ቅናተኛ ነኝ አላህ ደሞ ከኔ የበለጠ ቅናተኛ ስለሆነ ግልፅንም ሆነ ድብቅ ፀያፍ ነገሮችን ሁሉ ከልክሏል። ከአላህ በላይ የሚቀና ማንም የለም"አሉ

ሚስትን በኒቃብ ማስዋብ ቢቀር ሚዲያ ላይ አውጥቶ ቲክቶከር ማድረግ ምን የሚሉት ደዩስነት ነው?!

https://t.me/ibnuHassen10
https://t.me/ibnuHassen10

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 month, 1 week ago

Last updated 1 month ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 day, 21 hours ago