Let's Save Orthodoxy and humanity( ሰብእናንና ኦርቶዶክሳዊነትን እንታደግ)!!⁉️

Description
ሰብእናንና የመንፈስ ልዕልናን ካዳበሩ ቤተሰቦች ጋር በመተባበር በሰብእናና በኦርቶዶክሳዊነት ላይ የሚፈጸምን(የተፈጸመን) ሥርዓታዊ፣መዋቅራዊ፣ሕጋዊ፣መናፍስታዊ፣ስነልቦናዊ ..ጥቃቶችንና አጥቂዎችን እንዲሁም ከጥቃት የመዳኛ መንገዶችን(መፍትሔ) የሚመለከትበት ቻናል ነው::
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

3 weeks, 2 days ago
[#ምሥራቅ](?q=%23%E1%88%9D%E1%88%A5%E1%88%AB%E1%89%85) \_አርሲ\_ሮቤ ዲደዓ

#ምሥራቅ _አርሲ_ሮቤ ዲደዓ

በምሥራቅ አርሲ ዞን በሚኖሩት ኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ተባብሶ ቀጥሏል።  በሮቤ ዲደዓ ወረዳ ጄና ገደምሳ ገበሬ ማኅበር ቀበሌ ውስጥ በልዩ ስሙ መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን አከባቢ ትናንት  ከቀኑ 11:00 ላይ   በኦርቶዶክሳውያን ላይ የግድያና የእገታ ጥቃት ተፈጽሟል።በጥቃቱም አቶ ጣፋ በቀላ የሚባሉ  ኦርቶዶክሳዊ የተገደሉ ሲሆን፣ዲ/ን ገዛኸኝ ለማ ፣ከተማ ካሳ፣ጋሻሁንና ደሲ የተባሉት ደግሞ ታግተው ተወስደዋል።ጥቃቱን የከፈቱት  "የኦሮሞ እስልምና መንግሥት" እንመሠርታለን የሚሉ ታጣቂዎች መሆናቸው ታውቋል።ይህ እንዲህ እንዳላ  ታጣቂዎቹ በኦርቶዶክሳውያን የግድያና የእገታ ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ ቁጥራቸው የማይባል ከብቶቻቸውንም ጭምር ዘርፈው መሄዳቸውን ነው የተነገረው።ጥር 21/2016  ዓ/ም ከቤተ ክርስቲያን እየተመለሱ ባሉ ምዕመናን የተጀመረው ግድያ እስከ ዛሬ  እልባት ሳይገኝ የብዙ ኦርቶዶክሳውያንን ሕይወት እየቀጠፈ ተባብሶ ቀጥሏል።በዚሁ በጄና ቀበሌ ማኅበር በተደጋጋሚ ጥቃቶች መፈጸማቸውን መዘገባችን  ይታወሳል።

@ኢዮሳፍጥ ጌታቸው

3 weeks, 3 days ago

መነሻውን ከአዲስ አበባ አድርጎ ወደ ደብረ ማርቆስ በመጓዝ ላይ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከነ ሙሉ ተሳፋሪው መታገቱ ተሰምቷል።

ተሽከርካሪው ከነ ሙሉ ተሳፋሪዎቹ የታገተው በኦሮሚያ ክልል ልዩ ስሙ ቱሉ ሚሊኪ ላይ ሲሆን አጋቾቹ በገዢው ቡድን እንደሚደገፉ የሚነገርላቸው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መሆናቸውን የታጋች ቤተሰቦች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።

ከተሳፋሪዎቹ መካከል ጨቅላ ህፃናትና ሴቶች እንዲሁም የሐይማኖት አባቶች እንደሚገኙበት የተጠቆመ ሲሆን ታጣቂዎቹ ለእያንዳንዳቸው ታጋቾች ከሦስት ሚሊየን ብር በላይ መጠየቃቸውን ነው የታጋች ቤተሰቦች ለጣቢያችን ጨምረው የገለፁት።

እገታው የተፈፀመው ዛሬ ታህሳስ 13/2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5 ሰዓት ገደማ ላይ ሲሆን ተሽከርካሪው ከ60 በላይ ተጓዦችን አሳፍሮ እንደነበር ነው የታወቀው።

ከመረብ ሚድያ

3 weeks, 3 days ago
"የእግዚአብሔር ሀገር የድንግል ማርያም የአስራት ልጆች …

"የእግዚአብሔር ሀገር የድንግል ማርያም የአስራት ልጆች ከሆን ይህ ሁሉ ለምን ደረሰብን? መውጫውስ?" #የጌዴዎንና_ የእግዚአብሔር_ሠይፍ! https://youtu.be/3GKKQ4A7IM8?si=WfTC8bNxhY7wIkWz

1 month ago
ህዝባችን በቸነፈር አለንጋ እየተሰቃየ ነው::

ህዝባችን በቸነፈር አለንጋ እየተሰቃየ ነው::
በ21ኛው ክ/ዘመን ይህን የመሰለ ስቃይ እንዲከፍልም ተፈርዶበታል ::😭😭😭

1 month ago
**ኢሰመጉ፣ በጸጥታ ኃይሎች ዛቻና ማዋከብ ሳቢያ …

ኢሰመጉ፣ በጸጥታ ኃይሎች ዛቻና ማዋከብ ሳቢያ ዋና ዳይሬክተሩና የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል የቦርድ አባል የነበሩት ዳን ይርጋ ለሕይወታቸው በመስጋታቸው ከአገር መሰደዳቸውን ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል‼️****

ኢሰመጉ፣ በርካታ ሠራተኞቹ በሚደርሱባቸው የተለያዩ ጫናዎች ምክንያት ሥራቸውን ለመልቀቅ እንደተገደዱም ገልጧል።

ኢሰመጉ፣ የመንግሥት ጸጥታ አካላት የሚያደርሱበትን ጫናዎችና የማዋከብ ድርጊቶች እንዲያቆሙ ለጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤትና ሌሎች ተቋማት ባለፈው ዓመት ግንቦት አቤቱታ አስገብቶ እንደነበር ጠቅሶ፣ ኾኖም መንግሥታዊ አካላት ተገቢውን ርምጃ ባለመውሰዳቸው የመብት ጥሰቱ ተባብሶ ቀጥሏል ብሏል።

ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በሲቪል ማኅበራትና ሠራተኞቻቸው ላይ የጸጥታ አካላት የሚፈጽሟቸው ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲቆሙ ተገቢውን ርምጃ እንዲወስዱ በድጋሚ ጥሪ አድርጓል፡፡

1 month ago

የእናት ፓርቲ የአርባምንጭ ማስተባበሪያ ኃላፊዎች ታሰሩ!

የእናት ፓርቲ አርባምንጭ ማስተባበሪያ ሰብሳቢ እጩ ዶክተር ቴዎድሮስ ፋንታዬ ታህሣስ ፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ከሃያ፣ የእናት ፓርቲ አርባምንጭ ማስተባበሪያ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ክፍል ኃላፊ አቶ ኤፍሬም አበበ ታህሣስ ፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ከሃያ ላይ እንዲሁም የእናት ፓርቲ አርባምንጭ ማስተባበሪያ የፋይናስ ኃላፊ አቶ ኃብተ ገብርኤል ቃይደ ቅዳሜ ታህሣስ ፭ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ የእስር ትዕዛዝ ሳይደርሳቸዉ ከአዲስ አበባ የፌደራል ደህንነት መስሪያ ቤት እንደመጡ በገለፁ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዉለዉ አርባ ምንጭ ከተማ መዉጫ ቦላ ጉርባ ቀበሌ በሚገኘዉ የፌዴራል ፖሊስ ካምፕ ታስረዉ ቤተሰብ እንዳያገኛቸዉ ተደርጎ ምግብ በፖሊሶች አማካይነት ብቻ እየደረሳቸዉ መሆኑን አረጋግጠናል፡፡

በተጨማሪም ከፓርቲያችን አመራሮች ዉጪ የማኅበራዊ ሚድያ አንቂ ወጣት መለሰ ደመላሽ እንዲሁም አቶ ታምራት ሰይፉ የሚባሉ ግለሰቦች አብረዋቸዉ በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡ ፓርቲያችን ሰላማዊ ትግልን የሚከተልና በዚሁ መንገድ እየታገለ የሚገኝ ሲሆን በአመራርና አባለቶቻችን ላይ በመንግስት የሚደርሰዉ እስርና አፈና እንዲሁም ኢሰብአዊ ድርጊት እንዲቆም በዚህ መንገድም የሚመጣ ለዉጥ እንደሌለ በአፅንኦት እየገለፅን ያለ አግባብ የታሰሩ አመራሮቻችን በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡ (እናት ፓርቲ)

1 month, 1 week ago

"ሕዝቡ ከንጉሱ ተዋግቶ ሊያስጥለው ቢነሳም፤ እርሱ ስለ ሕዝቡ ደህንነት በስውር ራሱን የሰጠው ድንቅ እረኛ"

በዚህች ቀን ኅዳር 29 ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ዐሥራ ሰባተኛ የሆነ የተመሰገነና የከበረ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ጴጥሮስ በሰማዕትነት አረፈ እርሱም የሰማዕታት መፈጸሚያ በመሆን ነው።

የዚህ አባት ወላጅ አባቱ በእስክንድርያ አገር ሊቀ ካህናት ነው ስሙም ቴዎድሮስ ነው የእናቱም ስም ሶፍያ እነርሱም እግዚአብሔርን እጅግ የሚፈሩ ጻድቃን ናቸው ነገር ግን ልጅ አልነበራቸውም። በሐምሌ ወር በአምስት የቅዱሳን ሐዋርያት የጴጥሮስና የጳውሎስ በዓላቸው በሆነ ጊዜ ብዙ ክርስቲያኖች ያማሩ ልብሶችን ከልጆቻቸው ጋር ተሸልመው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጡ የዚህ ቅዱስ እናት ሶፍያ አየች። በከበረ መሠዊያውም አንጻር ቁማ ልጅን ይሰጣት ዘንድ በብዙ እንባ ክብር ይግባውና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነችው።

በዚያችም ሌሊት ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ ተገለጡላትና እነሆ ክብር ይግባውና እግዚአብሔር የተባረከ ልጅን ይስጥሽ ዘንድ ልመናሽን ተቀበለ ስሙንም ጴጥሮስ በዪው አልዋት ከዚህም በኋላ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎናስ እንድትሔድና እንዲጸልይላት አዘዙዋት።

እርሷም ወደ አባ ቴዎናስ ሔዳ ጸለየላት ከዚህም በኋላ ፀንሳ ይህን ቅዱስ ወለደችው ስሙንም ጴጥሮስ ብላ ሰየመችው ዕድሜውም ሰባት ዓመት ሲሆነው ነቢይ ሳሙኤል እንደ ተሰጠ ለሊቀ ጳጳሳት ቴዎናስ ሰጠችው። ለርሱም ተወዳጅ ልጅን ሆነው አስተምሮም አናጉንስጢስነት ሾመው ከዚህም በኋላ ዲቁና ደግሞም ቅስና ሾመው በሊቀ ጵጵስናው ሥራ የቤተ ክርስቲያንም በሆኑ በብዙ መልካም ሥራዎች ሁሉ የሚረዳው ሆነ።

የሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎናስ የሚያርፍበት ጊዜ ሲደርስ በእርሱ ፈንታ አባ ጴጥሮስን ሊቀ ጵጵስና እንዲሾሙት ኤጲስ ቆጶሳቱንና ካህናቱን አዘዛቸው እርሱም በሞተ ጊዜ ይህን አባ ጴጥሮስን ሾሙት እርሱም ለአብያተ ክርስቲያን ካህናትን ሾመ።

እንዲህም ሆነ በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በአንጾኪያ ከተማ አንድ መስፍን ነበረ የሚስቱም ስም ሣራ ይባላል እርሱም ከከሀዲው ንጉሥ ጋር ተስማማ እርሷ ግን በሃይማኖቷ ጸናች በአንድነትም ሳሉ ሁለት ልጆችን ወለደች። ነገር ግን በአንጾኪያ አገር የክርስትና ጥምቀትን ልታስጠምቃቸው አልተቻላትም ስለዚህም ወደ እስክንድርያ ትሔድ ዘንድ ልጆቿን ይዛ በመርከብ ተሳፈረች።

በጉዞ ላይም ሳሉ ጽኑዕ የሆነ ማዕበል ተነሣባቸው እርሷም ልጆቿ የክርስትና ጥምቀትን ሳይጠመቁ እንዳይሞቱ ፈራች ጡቷንም በምላጭ ሠንጥቃ በደሟ ግምባራቸውን በመስቀል ምልክት ቀብታ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቀቻቸው በዚያንም ጊዜ ታላቅ ጸጥታ ሆኖ ከመሥጠም ዳኑ።

ወደ እስክንድርያ አገርም በደረሰች ጊዜ ያጠምቃቸው ዘንድ ልጆቿን ከሀገር ልጆች ጋር ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ጴጥሮስ አቀረበች ይህም አባት ያጠምቃቸው ዘንድ ወደ ልጆቿ በደረሰ ጊዜ ውኃው እንደ ሰም ሁኖ ረጋ ወደ ሌሎች ሲሔድ ግን ይፈሳል ወደዚች ሴት ልጆች ሲመለስም እንደ ሰም የረጋ ይሆናል እንዲህም ሦስት ጊዜ አደረገ አደነቀም ከእርሷም ስለሆነው ነገር ጠየቃት እርሷም የባሕር ማዕበል እንደተነሣባት ጡቷንም ሠንጥቃ በደሟ የልጆቿን ግምባራቸውን እንደቀባችና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዳጠመቀቻቸው ነገረችው። ሊቀ
ጳጳሳት አባ ጴጥሮስም ሰምቶ እጅግ አደነቀ አንዲት ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ትላለች እንዲህ ትሠራለች ብሎ እግዚአብሔርን አመሰገነው።

በዚህም አባት ጴጥሮስ ዘመን ከሀዲ አርዮስ ተነሣ ከክህደቱም ይመለስ ዘንድ ይህ አባት ብዙ ጊዜ መከረው ገሠጸው ቃሉንም ባልሰማው ጊዜ ረግሞ አወገዘው።

ከዚህም በኋላ የንጉሥን አማልክት እንዳያመልኩ በሁሉ ቦታ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደሚያስተምር ዜናውን ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ስለዚህ ይዘው እብዲአሥሩት መልእክተኞችን ላከ። የሀገር ሰዎችም በአወቁ ጊዜ የንጉሥ መልእክተኞችን ይወጓቸው ዘንድ የጦር መሣሪያቸውን ይዘው ተሰበሰቡ።

ቅዱስ አባት ጴጥሮስም ስለርሱ ታላቅ ሁከት እንደሚሆን በአየ ጊዜ ስለ ሕዝቡ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሊሰጥ ወደደ ሕዝቡንም ሁሉ ወደርሱ አቅርቦ በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ አዘዛቸው አጽናንቶ አረጋግቶ ወደ ቤቶቻቸው እንዲገቡ አሰናበታቸው።

አርዮስም ቅዱስ አባት ጴጥሮስ ከዓለም በሞት እንደሚለይ በአወቀ ጊዜ ይህ አባት ጴጥሮስ ከውግዘቱ እንዲፈታው ያማልዱት ዘንድ አኪላስንና እለእስክንድሮስን ለመናቸው እነርሱም እንዲፈታው በለመኑት ጊዜ በውግዘት ላይ ውግዘትን ጨመረ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የተቀደደ ልብስ ለብሶ እንዳየው ልብስህን ማን ቀደዳት ባለውም ጊዜ ልብሴን አርዮስ ቀደዳት እንዳለው አስረዳቸው። ይህም ማለት ከአባቴ ለየኝ ማለት ነው ሁለተኛም ከእርሱ ተጠበቁ በክህነት ሥራም አትሳተፉት እርሱ ለክብር ባለቤት ክርስቶስ ጠላቱ ነውና አላቸው ። አንተም አኪላስ ከእኔ በኋላ ሊቀ ጵጵስና ትሾም ዘንድ አለህ አንተም አርዮስን ትቀበለዋለህ ፈጥነህም ትሞታለህ አለው።

ከዚህም ነገር በኋላ ቅዱሳ አባት ጴጥሮስ ከንጉሥ መልክተኞች ጋር በሥውር ተማከረ በእሥር ቤት ከውስጥ ሲያንኳኳላቸው እነርሱ ወደ መስኮት እንዲቀርቡ እርሱም ራሱን ሊሰጣቸው ንጉሡ እንዳዘዛቸው ይፈጽሙ ዘንድ በዚያንም ጊዜ የወንጌላዊ ማርቆስ መቃብር ወዳለበት ከከተማው ውጭ ይዘው ወሰዱት በዚያም ወደ ክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደሜ መፍሰስ ለጣዖታት አምልኮ መጨረሻ ይሁን ከሁሉ ዓለምም ይጥፋ ብሎ ጸለየ። ከሰማይም አሜን ይሁን ይደረግ የሚል ቃል መጣ።

ለዚያ ቦታም በአቅራቢያው የነበረች አንዲት ብላቴና ድንግል ይህን ቃል ሰምታ ተናገረች።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ አባት ጴጥሮስ ወታደሮችን የታዘዛችሁትን ፈጽሙ አላቸው በዚያንም ጊዜ የከበረች ራሱን ቆረጡ በድኑም ሁለት ሰዓት ያህል ቆመ ሕዝቡም ከከተማ ፈጥነው በመውጣት ወደ እሥር ቤት መጡ እስከ ነገሩአቸውም ድረስ የሆነውንም አላወቁም ነበር ከዚህም በኋላ የቸር ጠባቂያቸውን ሥጋ አንሥተው ወደ ከተማ አመጡ አክብረውም ገነዙትና ወደ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አግብተው በወንበሩ ላይ አስቀመጡት።

ከዚህ አስቀድሞ በወንበሩ ላይ ሲቀመጥ ከቶ ማንም አላየውም በወንበርህ ላይ የማትቀመጥ ለምንድን ነው ብለው በጠየቁት ጊዜ እኔ የእግዚአብሔር ኃይል በወንበር ላይ ተቀምጦ አያለሁና ስለዚህ በዚህ ወንበር ላይ መቀመጥን እፈራለሁ ብሎ መለሰላቸው።

ግንዘቱንም አከናውነው ከተመረጡ ሊቃነ ጳጳሳት ከሥጋቸው ጋር ሥጋውን አኖሩ እርሱም በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር በሹመት የኖረው ዐሥራ አራት ዓመት ነው የተሾመውም ዲዮቅልጥያኖስ በነገሠ በሃያ ስድስት ዓመት ነው ከሥጋውም ብዙ ድንቅ ተአምር ተገለጠ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን

1 month, 1 week ago

በአፋረ ክልል በዳሊፋጌ ወረዳ  ዞን 5 የ3ቱ ጤና ጣቢያ እንዱሁም አንቦሴ ፣ዳባገሶ፣ጃራ ጤናጣቢያዎች በዱቲና በደመወዝ አለመከፈል ምክኒያት እንደተዘጉ ጤና  ሚኒስቴር ይወቅልን፣በርካታ ታካሚዎች ለከፍተኛ አደጋ ተጋልጠዋል ብለዋል።አዩዘሀበሻ

ለድሮን፣ቅንቡላ፣ቤተመንግሥት እና መናፈሻ ገንዘብ ቸገረኝ የማያውቀው፣ የሀገር መሰረት መምህራን እንዲሁም የጤና ባለሙያ ሐኪሞችን ደሞዝ እየከለከለ ሕዝቡን ቀውስ መክተቱን ገፍቶበታል።

1 month, 1 week ago

🤔የጦርነት ምድጃ በሆነችው ምድር በእሳት መካከል አሳልፎ እንባቸው አልቆ ደም የሚያልቅሱ አረጋውያንን ሊቃውንቱን የነገ የቤተክርስቲያን ተስፋዎች የቆሎ ተማሪዎችን በብዙ ነገር የተጎዳውን ህዝብ አሳይቶ አስተምሮ መድኃኔዓለም በሰላም ወደነበርኩበት መልሶኛል ክብር ለስሙ ይሁንልን አሜን

በእናታችን ጽዮን ዓመታዊ ክብረበዓል ቀን በዓሉን በተመለከተ በማስተምርበት ሰዓት የገጠመኝን ላካፍላችሁ

በአካባቢው እየሆነ ያለውን እና የተፈጠረውን ያየ ብቻ ነው ማመን የሚችለው ከአዕምሮ በላይ ነው

🤔ወደገጠመኙ ልመልሳችሁ

በትምህርቱ መካከል አንድ አባት እጅ አወጡ ጥያቄ ነው መስሎኝ እሸ አባቴ ይናገሩ አልኳቸው

እሳቸውም አባታችን አሁን ለእኛ የሚያስፈልገን ትምህርት ሳይሆን ቁጭ ብሎ የሚያላቅሰን በእንባ የሚጋራን ነው ከቻሉ ትንሽ ያልቅሱልን እኛ እንባ ጨርሰናል አሉኝ ። እንደዚያን ቀን ግራ ገብቶኝ አያውቅም ። ይህን ቃል በእኔ ቦታ ሁናችሁ ብትሰሙት ሁላችሁም ግራ እንደምትጋቡ እርግጠኛ ነኝ

ይህን ጥያቄ በምንም ልመልሰው ስለማልችል ለአንድ ደቂቃ ዝም ጸጥ ረጭ ብየ ከቆየሁኝ በኋላ

🤔እግዚአብሔር የለም ወይ ብላ የእንባ መስዋዕት ያቀረበችው ራሄል የተባለች አንዲት ታላቅ ሴት ትዝ አለቸኝ
ቁስሉን ለማቀዝቀዝ እስዋን ምሳሌ አድርጌ ከልቅሶ ብዛት የተነሳው የዓይኑን ብርሃን ያጣው ያዕቆብን ጠቅሼ የችግሩ ሁሉ መፍትሔ ጸሎት ይቅርታ ንስሐ መሆኑን ገልጬ በዚህ ተሰነባበትን እላችኋለሁ

ከበዓሉ አራት ቀን በፊት አንድ ታላቅ ካህን ለአገልግሎት ወደ ቤተመቅደስ ሲሄዱ ታግተው ጥንድ በሬዎቻቸው ተሽጠው ተከፍሎ እንደተለቀቁ ሰማሁኝ

ካህን እንደ እግዚአብሔር በሚፈራበት ሀገር ይህ ሆነ

ያውም ጎንደር ላይ ይህ ሆነ ቢባል ማን ያምናል
የኢየሩሳሌም ከተማ ቤተአይሁድ ዛሬ ሁሉ እንዳዲስ የሚወቀሱት ከሁለት ሺህ ዘመን በፊት ካህኑ ዘካርያስን በቤተመቅደስ አረዱ ተብሎ እኮ ነው

በዚህ አካባቢ ሌሊት ለቅዳሴ ለማህሌት ለሰዓታት የሚሄድ ለሀገር የሚጸልይ መስዋዕት የሚያቀርብ ካህን መንቀሳቀስ እንዳያቆም እፈራለሁ

መድኃኔዓለም ይታረቀን በቃችሁ ይበለን 🙏🙏🙏

ሁሉንም አንድ ጊዜ ከምዘረግፈው እንዳይከብዳችሁ አንድ አንድ እያልኩኝ አካፍላችኋለሁ

ከአባ ገብረማርያም

1 month, 1 week ago

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ሻካ ዞን፣ አንዳራቻ ወረዳ፣ ታጣቂዎች ባለፈው ሳምንት በፈጸሟቸው ጥቃቶች አብዛኞቹ አርሶ አደሮች የኾኑ 20 ሰዎች እንደተገደሉ ዶቸቨለ ዘግቧል። ታጣቂዎቹ ሸኬቢዶ በተባለ ቀበሌ በፈጸሟቸው ጥቃቶች ከተገደሉት መካከል፣ የቀበሌው ሊቀመንበር ገዛኸኝ ወንድሙ እንደሚገኙበት መረዳቱን ዘገባው አመልክቷል። ታጣቂዎቹ ከጋምቤላ ክልል ከመዣንግ ብሔረሰብ ዞን የሄዱ ናቸው ተብሏል። የወረዳው አስተዳደር ከጋምቤላ ክልል የሚነሱ ታጣቂዎች የፈጠሩት የጸጥታ ስጋት ከአቅሙ በላይ መኾኑ ገልጦ፣ ለዞኑ አስተዳደርና ለክልሉ መንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን የዜና ምንጩ ጠቅሷል።
ዋዜማ ኅዳር 23

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana