ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago
ስሚኝማ አንድ ነገር ላማክርሽ ምክር ስጪኝ አለችኝ ከተቀመጥኩበት ፊትለፊት ተቀምጣ።
ምን?
ከሶል ጋር እኮ ተጣላሁ ያውም በራሴ ጥፋት
ምን አርገሽ?
እሱ ሲጠራኝ አሞኛል ከቤት አልወጣም ብዬ ከሰፈራችን ልጅ ጋር መንገድ ላይ አይቶኝ ተናደደብኝ።
መንገድ ላይ ስላየሽ ከተናደደ በጣም ይወድሻል።
እሱን ተዪውና ምን ላድርግ?አለች
ይቅርታ ጠይቂው አልኳት
ይቅር አይለኝም።
እግሩ ላይ ውደቂ
ምን በወጣኝ ገደል አይገባም ከፈለገ አለች።
እንደዛ ከሆነ ገደል ይግባ ተዪው።
ለምን እተወዋለሁ?
አሁን ገደል ይግባ አላልሽም ?
እራስሽ ገደል ግቢ እኔ ምክር ጠየኩሽ እንጂ አሟርቺ ብዬሻለሁ?አለችኝ።
እራስሽ እኮ ነሽ ያልሽው።
ገደል ይግባ ትያለሽ እንዴ?እኔ ብሞት ይሻለኛል እሺ
ትችያለሽ
አንቺ ግን ከኛ ያለሽ ችግር ምንድነው?
ምንም አልኳት።
ቅናት ነው እንዲህ የሚያደርግሽ? ድሮም ሰው ሲጣላ ከማስታረቅ ማጋጋል ነው ደስ የሚለው ሀበሻ።
ዝም ብዬ የያዝኩት ወረቀት ላይ ትኩረቴን መለስኩ።
አንቺን ብሎ ፀሀፊ! የሚፅፍ ሰው እንዲህ ያለ የወረደ አስተሳሰብ የለውም እሺ።
እሺ።
ለነገሩ የት ይገባሻል boyfriend የለሽ
እባክሽ ከቻልሽ ተዪኝ አልኳት በልመና መልኩ
ድሮ ማን ያዘሽ ? ምክር ስጪኝ ብልሽ ገደል ግቡ አልሽኝ።
ድንቄም ጓደኛ።
እግሩ ላይ ከምወድቅ ገደል ይግባ አልሽ፣ገደል ከሚገባ እኔ ልሙት አልሽ እኔ ምን አረኩሽ ?ከቻልሽ ከዚህ በላይ አትጨቅጭቂኝ ስላት
ይቅርታ እንደመጠየቅ ጭራሽ ታባርሪኛለሽ?
ምን አጥፍቼ ነው ይቅርታ የምጠይቀው?
ገደል ግቡ አልሽ እኮ ወይስ እራስሽ ገደል ልትከቺን ነው ከዚህ በላይ? ለእኛ ገደልን ትመኛለሽ?ክፉ.................
አንዳንድ ቀን እንዲህ ያሉትም ይገጥማሉ ከቸር ሰው ጋር በቸር ያውላችሁ።🙏
✍️N.D.
የጠይም ሰው ቢሉኝ ምንጭ ውሃ ጠጣሁ
የቀይ ሰው ቢሉኝ በርበሬ በላሁ
የጥቁር ሰው ቢሉኝ አቦሉን ጠጣሁ
ለዛ ለቀይ-ዳማ መድሀኒት አጣሁ።
Join & Share
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago