# ብሩክ 22

Description
በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን አመስግን 🙏🙏🙏

https://t.me/biruk_223
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

2 weeks, 4 days ago

የዚህ ቻናል የክርስትና እምነት ተከታዮች

1⃣9⃣

እንኳን ለ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

3 weeks, 1 day ago

እንድቀርባት እድሉን ትሰጠኝና ስጠጋት ደሞ ሌላ ሰው ትሆንብኛለች

አንዳንዴ ሰው አላት ብዬ አስባለሁ በስልክ ከወንድ ጋር ስታወራ ስደርስባት ትደነግጣለች ለምን??? እኔ ማነኝ ስታየኝ ምትደነግጠው???

ግራ ይገባኛል ስሜቷን ስረዳው ከኔጋር የፍቅር ግንኙነት ይፈልጋል ለስሜቷ መልስ ለመስጠት ስሞክር ደሞ ወንድምነቴን ጓደኝነቴን ታስታውሰኛለች

ለምን

ማንነቴ ፈልጋኛለች አልፈለገችኝም በሚል እሳቤ ውስጤ ተውጧል

የተመታ ፆታ👩‍🦱 ...ብሩክ

3 weeks, 2 days ago

ቺት ስታረግብኝ ዝም ስላልኩ ሞኝ መሠልኳት

ወንድ መደሯረቧ እርድና ከሆነ የኔ ናት ብዬ ስላሰብኩ እሺ እኔ ፋራ ነኝ???

ማርያምን እንደደረበችብኝ አውቃለሁ እኮ ግን ትመለሳለች በሚል ተስፋ ነፃነት ሰጠኋት

እኔም እኮ ፃድቅ አይደለሁም ግን ከእሷ ሌላ አስቤ አላውቅም

ፋራ ነኝ ......22

3 weeks, 4 days ago

አምኛል

ነይና በጠረንሽ ጤና አዳምነት የማስነጠሴን ገደብ ወስኚልኝ

ነይና በክናፍሮችሽ ሙቀት ሰርፆ የመታኝን ብርድ አራግፊልኝ

ነይና የአካሌን ስንፍና በአካልሽ ጀግንነት ነፃ አውጪው

ነይና በውስጥሽ ብርሀንነት የውስጤን ጨለማ አሽሺልኝ

ነይ ብሩክ

3 weeks, 5 days ago

አስፋልቱን ሳይ 👇

ፈገግ እያልሽ ስትመጪ ትዝ ይለኛል
በትዝታ እዚያ ማዶ ስቦ አሻግሮ ይወስደኛል

እዚያ ማዶ👇
ወንበሩን ሳይ የተቀመጥንበት እምነበረድ
ይሰማኛል አንዳች ነገር በልቤ ላይ ሲነጉድ

ይሰማኛል👇
ጥፍጥ ያለ ለዛ ከጆሮዬ
ሳቅሽ ጭምር ያቃጭላል ከጀርባዬ

የት ነሽ??? ወዴት ነሽ አካሌ?
ወዴት ነሽ የግሌ?
ወዴት ነሽ መውደዴ፣
እረ እኔስ አልቻልኩም መጠበቅ ደከመኝ
መናፈቅ ታከተኝ ከአቅሜ አለፈ በሀሳብ መንጎዴ፣

እስቲ በቃህ በይኝ ይበቃሀል ብለሽ
ከናፍቆቴ እንዳርፍ ነይልኝ ተመለሽ
👇
ትመጫለሽ???
ልጠብቅሽ???

ኢዚያው ልሁን እዚያው ልቁም
እ???
ሂድ አትበይ ሺ ብትሄጂ ሺ መጠበቄ አያልቅም

ሂድ አትበይ ሂድ ማለትሽ ነው ሞቴ
አንቺ የሌለሽበት ባዶ ነው ህይወቴ

ትመጫለሽ???
ልጠብቅሽ???

#ብሩክ_22

3 weeks, 5 days ago

እንደእግዛብሄር ፍቃድ ከፍቅረኛዬ ጋር በፍቅር ህይወት 7 አመት ሞላን

የሴት ጓደኛ ስለሌላት ::

4 weeks ago

ፅናት ትባላለች የ 11 ክፍል ተማሪ ነበረች በትምህርቷ በጣም ጎበዝ የመሆንን ልክ ከማለፏ የተነሳ ጓደኞቿ ይቀኑባታል

1ደኛ እየወጣች ነው ዛሬን የደረሰችው ሰቃይ ተማሪ ናት ምንም ነገር አታልሏት አያውቅም ፍቅር ፍቅረኛ ወንድ ጭራሽ ከአላማዋ ጋር ማታወዳድራቸው ናቸው ትኩረቷ ትምህርቷና ትምህርቷ ላይ ነው

የአንድ ጓደኛዋ ቅናት ከማየሉ የተነሳ ክፉ ሀሳብን ወደ አእምሮዋ መራች ፅናትን በወንድ ፈተነቻት ልታሸንፋት አልቻለችም

በስተመጨረሻ በመድሀኒት ለህመም ዳረገቻት ፅናት ከራሷጋር እንዳትሆን አደረገች ቀሪ ዘመኗን ባክና እንድትቀር አሻት

ፅናት ፀበል ከጀመረች ብዙ ጊዜያት አለፉ ውስጧ ያለውን መንፈስ ለማሸነፍ ቀን ሌት ተግታ ትሰግዳለች ትፀልያለች

ከፀሎቷ መሀል እንባዬን ያሻው ምን አይነት ሴት ብትሆን ነው ለጠላቶቿ የመፀለይን ያህል የዋህነት ያደላት

እንደሰበራቷ ከአላማዋ እንደጎተቷት እንዳሰናከሏት እያወቀች ልቦና ስጣቸው ብላ የምትፀልይ ሴት

ለሰጧት ህመም ላባከኑት እድሜዋ ቂም ይዞ ለበቀል መሮጥን ከጀርቧ ጥላ በቀል የእግዛብሄር ነው ብላ

ከፀሎት መሀል ልቦና ስጣቸው ብቻ ትላለች

የእምነቷ ጥንካሬ ተስፋዋ የዋህነቷ እና የልቧ ንፅህን የሚገዛ ሴት

ከፅናት አንደበት...✍️#ብሩክ_22

4 weeks, 1 day ago

ጎህ ሲቀድ መስኮቱ ዳር ቆሞ አፍሮ ፀጉሩን ያበጥራል

ሳይጠይቀኝ ጫማውን ልቦርሽለት ፈር ቀዳጅ ጓደኛውን "ኪዊን ከነ ብሩሹ ይዤ እግሩ ስር እርመሰመሳለሁ

ቱ ቱ ቱቱ ቱቱ እያለ ተባረክ በኩሬ ሲለኝ ነገዬ በይፋ ምራቆቹ ላይ ይገለጥልኛል ተነስ ልጄ ይበቃሀል ብሎ ፀጉሬን በእጆቹ ሲያሻሸኝ በትዝታ የማላውቀውን ነገ በደስታ ቃኘዋለሁ

ሰፈር ውስጥ እሱ ሲመጣ የሰፈሩ ሰው እንዳለ ያጎበድድለታል ለሰላምታ እጃቸውን ዘርግተው ከወገባቸው ጎንበስ ይላሉ

ተከባሪ ነው ሸምጋይ ነው

እቀናበታለሁ: ቆፍጣናነቱ አለባበሱ ወንዳወንድነቱ ግርማው ይገርመኛል

በሄደበት ሁሉ አንጠልጥሎኝ ነው ሚሄደው ማወቅ ያለብኝን በእድሜዬ ልክ ያስቃርመኛል

የእንትና አባት የእሱ አባት እኮ ነው ሲባል ስሰማ ልጅነቴን ወደዋለሁ

ኩራቴ ነው
ማንነቴ ነው
መመኪያዬ ነው
ጋሻዬ ነው
.... ለአባትነት ....#ብሩክ_22

1 month ago

ማስመስል የእለት ተለት ማንነቴ ነው ምክንያቱም እውነተኛ ልሁን ብል እንደምጎዳ ስለማውቅ

...biruk

1 month, 1 week ago

ለጋበዝኩሽ ክፋት ይቅርታ የሚለው ቃል ከከተትኩሽ የሰበራ ባህር መረብ ሆኖ ከአስከፊው ቁስል እንደማይታደግሽ አውቃለሁ

ከአይኖችሽ ለፈሰሱት እንባ ልካስሽ የሚለው ቋንቋ አንዲቷን ዘለላ መጥረግ እንደማይችል አውቃለሁ

ግን ማሪኝ 🙏 .....#ብሩክ_22

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana