ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
የውጭ ምንዛሪ ማግኘት የሚችሉት ተለይተው ታውቀዋል።
1? የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የተፈቀደላቸው የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ከኢትዮጵያ ውጭ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊውያን ወይም በአገሪቱ ውስጥ የሚኖር የውጭ ዜጎች ናቸው።
2? ምንዛሪ ለማግኘት የሚፈልጉ ግለሰቦች ለበዓል ፣ ለትምህርት ፣ ለህክምና ጉዞዎች እና ሌሎች የግል ጉዳዮች እንደሚጓዙ የሚያሳይ ፓስፖርት፣ ሕጋዊ የመግቢያ ቪዛ እና የአየር ትኬት የማቅረብ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
3? ተጓዦች ከምንዛሪ ቢሮዎች እስከ 5 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወይም የዚህ አቻ የሆነ የሌላ አገር ገንዘብ በጥሬ ወይም በክፍያ መፈጸሚያ ካርድ (debit card) አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ።
4? የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሂሳብ ያላቸው ተጓዦች እስከ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ድረስ ማግኘት ተፈቅዶላቸዋል።
5? በብሔራዊ ባንክ ካልተፈቀደ በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነዋሪ በአንድ ጉዞ ላይ ከ10,000 የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣጣኝ ገንዘብ በካሽ መያዝ አይችልም።
6? ለንግድ የሚጓዙ ግለሰቦችም የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ይችላሉ።
7? የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ ፓስፖርት እና የአየር ትኬት ለሚያቀርቡ ለንግድ ድርጅት ተወካዮች የውጭ ምንዛሪ መሸጥ እንዲችሉ ተፈቅዷል። እነዚሁ ቢሮዎች ፦
- ለንግድ ድርጅቶች፣
- ለበጎ አድራጎት ተቋማት
- ለሃይማኖት ማኅበራት፣
- ለንግድ ትርኢቶች፣
- ለቱሪዝም
- ለባህል እና ለስፖርቶች አዘጋጆች የውጭ ምንዛሪ መሸጥ ይችላሉ።
8? የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ለመንግሥት ተጓዦች ለምግብ፣ ለማረፊያ እና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ከ10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣጣኝ ገንዘብ የማይበልጥ የውጭ ምንዛሬ ሊሸጡ ይችላሉ።
9? ነዋሪ ላልሆኑ የውጭ አገር ዜጎች እና ቱሪስቶች ብርን ወደ ውጭ ምንዛሬ ሊለውጡ የሚችሉበት አሠራርም አለ። ፓስፖርት፣ ትክክለኛ ቪዛ እና የአየር ትኬት የሚያቀርቡ ሰዎች ያለማስረጃ እስከ 500 የአሜሪካን ዶላር መለወጥ ይችላሉ። ከ500 ዶላር በላይ መለወጥ የሚፈልጉ ከሆነ ፓስፖርት፣ ሕጋዊ ቪዛ፣ የአየር ትኬት እና ተመጣጣኝ የሆነው የውጭ ምንዛሪ በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ገንዘብ መቀየሩን የሚያሳይ የተረጋገጠ የባንክ ማስረጃ ማቅርብ ይጠበቅባቸዋል።
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው?**በዚህ ይከታተሉ
Telegram :https://t.me/+Tukd3DqklsixtDDQ YouTube :**https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
ጠ/ሚ ዐቢይ ስልጣን ሲይዙ 27.5 ብር ይሸጥ የነበረዉ አንድ የአሜሪካ ዶላር በስድስት አመታት ዉስጥ አድጎ ከ 76 ብር በላይ እየተሸጠ ነዉ
ኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘቧ ከዶላር አኳያ ያለውን የምንዛሬ ተመን፤ ባለፉት 33 ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ መጠን ያዳከመችው ለሶስት ጊዜያት ነው።
የመጀመሪያው ከደርግ መንግስት መውደቅ በኋላ በኢህአዴግ መንግስት በ1984 ዓ.ም. የተደረገ ነው።
በወቅቱ 2.07 ብር የነበረው የዶላር ምንዛሬ 5 ብር ገብቷል። የእዚህ የምንዛሬ ምጣኔ በመቶኛ ሲሰላ የ142 ፐርሰንት ማሻቀብ የታየበት ነበር። ሀገሪቱ ሁለተኛውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ተመን ማሻሻያ ይፋ ያደረገችው በመስከረም 2003 ዓ.ም ነው። በዚህ ጊዜ ብር ከዶላር ጋር ያለው የምንዛሬ ተመን በ16.7 ፐርሰንት ጭማሪ አስመዝግቧል።
በዚህም መሰረት አንድ የአሜሪካ ዶላር ሲመነዘርበት ከቆየው 13.6 ብር ወደ 16.3 ብር ከፍ ብሏል። የዛሬ 13 ዓመት ገደማ በውጭ ምንዛሬ ረገድ የተመዘገበው ሶስት ብር የሚጠጋ ጭማሪ ነበር። ከሰባት አመት በኋላ በተመሳሳይ ሁኔታ የውጭ ምንዛሬ ተመን ማሻሻያ ይፋ ሲደረግ፤ በወቅቱ የነበረው የመመንዘሪያ ዋጋ ወደ አራት ብር በሚጠጋ መጠን ከፍ ብሏል።
በህዳር 2010 ዓ.ም የተደረገው ይህ የውጭ ምንዛሬ ተመን ማሻሻያ የ15 በመቶ ጭማሪ የታየበት ነበር። በእዚህ ጊዜ በ23.3 ብር ይመነዘር የነበረው አንድ የአሜሪካ ዶላር፤ በአንድ ጊዜ ወደ 27 ብር ተመደንጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡት፤ የውጭ ምንዛሬ ተመን ማሻሻያው ከመንፈቅ በኋላ ነው።
አብይ ስራቸውን ሲጀምሩ 27.5 ብር የነበረው የአንድ ዶላር ይፋ የባንክ ምንዛሬ ተመን፤ በስድስት ዓመት የስልጣን ዘመናቸው 58.6 ብር ደርሷል። የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት በብር እና ዶላር መካከል ያለውን የምንዛሬ ተመን፤ በሽርፍራፊ ሳንቲም ደረጃ በየጊዜው የማዳከም አካሄድ ሲተገብር ቆይቷል።
Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው?**በዚህ ይከታተሉ
Telegram :https://t.me/+Tukd3DqklsixtDDQ YouTube :**https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
ባህርዳር ከተማ ክልከላ ተቀመጠ‼️
በአማራ ክልል የባህር ዳር ከተማ አሥተዳደር ጸጥታ ምክር ቤት የሚከተሉትን የክልከላ ውሳኔዎችን አስተላልፏል?
1ኛ - በተሽከርካሪዎች ላይ የተጣሉ ክልከላዎች:-
?ማንኛውም ተሽከርካሪ ታርጋ ሳይኖረው ወይም ሳያስር መንቀሣቀሥ የተከለከለ ነው።
? ከተፈቀደላቸው ተሽከርካሪዎች ውጭ ስቲከር መለጠፍ የተከለከለ ነው።
2ኛ- የባጃጅ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች እና ማኅበራት ላይ የተደረጉ ክልከላዎች እና ለባሕር ዳር ከተማ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የተሰጡ ግዴታዎች:-
? ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ባጃጅ መጋረጃ እና የግራ ጎን ሸራን ሳያነሱ ማሽከርከር በፍጹም የተከለከለ ነው።
?የባጃጅ ተሽከርካሪ ማኀበራት ከተሰጣችው የሥምሪት ቦታ ውጭ ማሽከርከር አይፈቀድም።
? በባሕዳር ከተማ አሥተዳደር ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት ተመዝግበው በማኀበራት ተደራጅተው ሥምሪት ከተሰጣቸው ባጃጆች ውጭ ማሽከርከር የተከለከለ ነው።
? የባጃጅ ተሸከርካሪዎች የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት በአዲስ የሚሰጠውን መለያ ወይም ባር ኮድ ግልጽ እና በሚታይ መንገድ የመለጠፍ ግዴታ አለባችው።
?የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ትራንስፓርት ጽሕፈት ቤት ከላይ የተገለጹትን ግዴታዎች ላላሟሉ የባጃጅ ተሽከርካሪዎች ምንም አይነት ሥምሪት እንዳይሰጥ ተወስኗል።
? የባጃጅ ባለ ንብረቶች ለቀን ገቢ ወይም ለተለያዩ የጊዜ ገደብ ለሚያከራዮቸው ግለሰቦች የውል ስምምነት በመያዝ ለፓሊስ እና ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት ማሳወቅ አለባቸው።
? ለባጃጅ ተሸከርካሪዎች ከቀኑ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ማሽከርከር የተከለከለ ነው። ወይም ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ማሽከርከር የተከለከለ ነው።
3ኛ. ባለ 2 እግር ሞተር ተሽከርካሪ በከተማው ላልተወሰነ ጊዜ ማሽከርከር የተከለከለ ነው።
4ኛ. የመኪና እና የሰው እንቅሥቃሤን በተመለከተ:-
?ለኅብረተሰቡ ቀጥተኛ አገልግሎት የሚሰጡ የቤት መኪና፣ ታክሲ፣ የመንግሥት መኪና፣ ማንኛውም የጭነት መኪና ተሽከርካሪ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድረስ ብቻ ማሽከርከር የተፈቀደ ሲኾን ከተፈቀደው ሰዓት እላፊ ሲያሽከረክሩ መገኘት ግን በሕግ ያስቀጣል።
?የሰው እንቅስቃሴም በተመሳሳይ እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት የተፈቀደ ሲኾን ከተፈቀደው ሰዓት በኋላ መንቀሣቀሥ ግን የተከለከለ ነው።
5ኛ. ይህ ክልከላ የማይመለከታቸው ተሽከርካሪዎች በጸጥታ ሥምሪት ላይ የሚገኙ፣ አንቡላሶች፣ የእሳት አደጋ መኪናዎች ናቸው። ነገር ግን በማንኛውም ሰዓት በአንቡላንስም ኾነ በሌሎች ተሽከርካሪዎች ላይ ፍተሻ ይደረጋል ።
6ኛ. በጦር መሣሪያ አያያዝ ላይ የተደረገ ክልከላ:-
?ከጸጥታ መዋቅሩ አባላት እና ለጸጥታ ሥራ ተሰማርተው የመንቀሣቀሻ ፈቃድ ከተሰጣቸው ሰዎች ውጭ የጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሣቀሥ የተከለከለ ነው።
?ማንኛውም የጸጥታ አባል ከሥምሪት ውጭ በሚኾንበት ጊዜ ሲቪል ለብሶ የጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሣቀሥ ክልክል ነው።
7ኛ. በከተማችን የሚገኙ ቤት አከራዮች እና ተከራዮች ማሟላት የሚኖርባቸው ግዴታዎች፦
? አከራዮች የአከራይ ተከራይ ውል በመያዝ ለቀበሌው አሥተዳደር እና በአቅራቢያቸው ለሚገኙ ፓሊስ ጣቢያዎች የውል ኮፒ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
? በተመሳሳይ ተከራይ የተከራየበትን ውል ይዞ መገኘት ይጠበቅበታል። ይህ ሳይኾን ቀርቶ ተከራይ በወንጀል ወይም በሌላ በሕገ-ወጥ ድርጊት ተሠማርቶ ቢገኝ አከራይ ጭምር በሕግ ተጠያቂ ይኾናል።
8ኛ. የክልከላዎች እና ግዴታዎች ተፈጻሚነትን በተመለከተ:-
? የተሽከርካሪ ክልከላዎችን ተላልፎ በተገኘ ማንኛውም ተሽከርካሪ ላይ የከተማ አሥተዳደሩ ትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት እንደየ አግባቡ እርምጃ ይወስዳል፣ በሌሎች የሕግ አካላትም ተጠያቂ እንደኾን ይደረጋል።
? ክልከላውን ጥሶ የጦር መሣሪያ ይዞ የሚገኝ የጦር መሣሪያውን እንደሚነጠቅ ከባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ኮሙኒኬሽን የተገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው?**በዚህ ይከታተሉ
Telegram :https://t.me/+Tukd3DqklsixtDDQ YouTube :**https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
ቀሲስ ግርማ አዳነ ለአገልግሎት ባመሩበት አሜሪካ ህይወታቸዉ አለፈ
ከጥቂት ቀናት በፊት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ወደ አሜሪካ ያቀኑት ቀሲስ ግርማ በቦስተን ግዛት ባረፉበት ቤት ትናንት ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት ሕይወታቸው አልፎ ተገኝቷል::
ከአሜሪካ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን መረጃ ያደረሱን አገልጋዮች እንደገለጹት ከኢትዮጵያ ከሄዱ ጀምሮ በነበሩ ቀናት በቦስተን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ዜማና ሥርዓት ጠብቀው ከሚያገለግሉ ወጣት አገልጋዮች አንዱ የነበሩት ቀሲስ ግርማ ሁለት የመዝሙር አልበሞች አሏቸው::
ዘማሪ ቀሲስ ግርማ አዳነ ከ1 ዓመት በፊት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ጋብቻቸውን የፈጸሙ ሲሆን የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበሩ።
Via :የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው?በዚህ ይከታተሉ
Telegram :https://t.me/+Tukd3DqklsixtDDQ
YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
ፈጣንና ታዕማኝ መረጃዎችን ለማገኘት የቴሌግራም የመረጃ አማራጮች?*?
1/ ጎጃም ሚዲያ https://t.me/gojjammedia 2/ ቢዛሞ ሚዲያhttps://t.me/Bizamo_media 3/ ነገደ አምሓራ - Negede Amharahttps://t.me/Negedeamharas 4/ ጊወን ፕርስhttps://t.me/gion_press1 5/1845 amhara revolution*https://t.me/minilik28
6/ነገደ አማራ ግሩፕ
7/ነገደ አማራ ሚዲያ
8/ደራሽ ሚዲያ
https://t.me/+Tukd3DqklsixtDDQ
9/አማራ ንቅናቄ https://t.me/fannomedia27
10ልዩ መረጃ
https://t.me/Liyumereja9
Telegram
ጎጃም ሚዲያ gojjam media
ይህ ትክክለኛ መርጃ ለህዝብ የምናደርስበት ነው! እብባክወ ማንኛውም መረጃ ሲኖርወት በዚህ ሊንክ ይላኩልን ፣እናመሰግናለን ! @Gojjamet
"በቂ ኮንዶም አዘጋጅቻለው ካነሰም እጨምራለሁ" ፓሪስ ?****
የኦልምፒክ ተወዳዳሪዎች ዋነኛ ትኩረት ስፖርቱ ላይ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም። ከፈለጉ ግን የግብረስጋ ግንኙነት መፈጸም ይችላሉ።
በፓሪስ ለውድድሩ ተሳታፊዎች 200ሺ የወንዶች ኮንዶም እና 20ሺ ገደማ የሴቶች ኮንዶም በአትሌቶች መንደር ተቀምጧል።
"ምን ያህል ሰዎች ኮንዶሞቹን እንደሚጠቀሙ አናውቅም። ፍላጎቱ ከገመትነው በላይ ከሆነ ተጨማሪ ኮንዶሞችን ለማቅረብ ዝግጁዎች ነን" ብለዋል የፓሪስ 2024 ኦልምፒክ የመጀመሪያ እርዳታ እና የጤና አገልግሎት ሂደቱን የሚመሩት ለውረን ዳላርድ።
በ1988ቱ የሴኡል ኦልምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአትሌቶች በነጻ የተወሰኑ ሺ ኮንዶሞች ተከፋፍለዋል። በወቅቱ ያንን ማድረግ ያስፈለገው የHIV-AIDS ወረርሽኝን በተመለከተ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ ነበር።
ከዚያ በኋላ በተደረጉ ውድድሮች የተከፋፈለው ኮንዶም ቁጥር በአስገራሚ ሁኔታ ከፍ ብሏል። በ1992 የባርሴሎና ኦልምፒክ 50ሺ፣ በ2008 የቤዢንግ ኦልምፒክ 100ሺ እንደዚሁም በ2012 የለንደን ኦልምፒክ 150ሺ ኮንዶሞች ተከፋፍለዋል።
ከእስካሁኖቹ ኦልምፒኮች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ኮንዶሞች በመጠቀም ቀዳሚ ሆኖ ሪከርዱን የያዘው ግን የ2016ቱ የሪዮ ኦልምፒክ ነው። 450ሺ ኮንዶሞች ተከፋፍለዋል። በአማካይ ለአንድ አትሌት 42 ኮንዶም ደርሷል።
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው?በዚህ ይከታተሉ
Telegram :https://t.me/+Tukd3DqklsixtDDQ
YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
ጠ/ሚ አብይ አሕመድ በተቃዋሚዎች ስብሰባ ላይ ህወሓትን አስጠነቀቁ‼️****
ህወሃት አካሄዱን ካላስተካከለ ወደ ጦርነት ልንገባ እንችላለን
የገባንበት ቀዉስ ይታወሳል:: ምን ያክል ሰው እንደወደመ፣ ምን ያክል ሃብት እንደወደመ መገመት ትችላላቹህ:: ያ የወደመ ሃብት፣ የወደመ የሰው ህይወት በትክክል ሳይገመገም ፣ እንዴት ጠፋ ሳይባል ፣ ሌላ ጥፋት ማምጣት ጥሩ አይደለም፣ ህዝብ ይጎዳል::......
TPLF አሁን ማድረግ ያለበት ምርጫ ቦርድ ጋ ሄዶ፣ በ 2-3 ሳምንት ዉስጥ የሚጠበቅበትን ዶክመንት አሟልቶ፣ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ፣ ነው ጉባኤ ማካሄድ ያለበት:: ባያደርግ'ሳ ? እኔ ብፈልግም ባልፈልግም ዋጋ የለዉም፣ ምርጫ ቦርድ ካልተቀበለው፣ TPLF'ን ሕጋዊ ፓርቲ ካላለው ፣ በምርጫ ሊሳተፍ አይችልም ፣ መንግስት ሊሆን አይችልም:: ምን ማለት ነው ? ተመልሰን ደግሞ ጦርነት እንገባለን ማለት ነው::
ስለዚህ ፣ ተመልሰን ጦርነት ከምንገባ ፣ ተመልሰን ጭቅጭቅ ከምንገባ ፣ ቀላል ነው፤ ዋናው አልፏል፣ ሕግ ተበጅቷል፣ ተስማምተናል ፣ የቀረችው ጉዳይ አሟልቶ፣ በሕጋዊ መንገድ ጉባኤ ኣካሂዶ ፣ ፓርቲው መልሶ ወደ ፓለቲካው ስርዓት መመለስ ከሁሉ በላይ TPLF'ን ፣ ከ TPLF ቀጥሎ የትግራይ ህዝብን ፣ ከዚያ ቀጥሎ ሁላችንም ይጠቅመናል:: TPLF
ዓዉዱ ተመችቶ ሳለ፣ ሕግ ተመልሶ እያለ፣ በሰላም መፍታት የሚያስችል ነገር እያለ ፣ ያን ወደ ጎን ትቶ መሄድ ጥሩ አይደለም:: ለትግራይ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ጥፋት ስለሚያመጣ"ሲሉ ተደምጠዋል።
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው?በዚህ ይከታተሉ
Telegram :https://t.me/+Tukd3DqklsixtDDQ
YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
ጎፋ‼️?
በጎፋ ዞን በደረሰ የመሬት ናዳ የሟቾች
ቁጥር ከ265 በላይ መድረሱ ተነገረ‼️
? 30 ሰዎች በአፈር ናዳ ውስጥ ይገኛሉ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበል በትላንትናው እለት ሀምሌ 15 ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የመሬት ናዳ የሟቾች ቁጥር ከ265 በላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡
በቀበሌው ናዳው ከደረሰ በኋላ የሠው ህይወት ለመታደግ ወደ በስፍራው ለነፍስ አድን ተግባር የተሰበሰቡ የአካባቢው ነዋሪዎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸውን ከደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
በትላንትናው እለት የወረዳው ፖሊስ አዛዥ የተለያዩ የፖሊስ አባላትን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ ተንሸራተው የነበረ ሲሆን በገመድ ተጓትተው በህይወት መትረፍ መቻላቸው ተሰምቷል።
ከተለያዩ አካባቢዎች ለእርዳታ የመጡ ነዋሪዎች በቀበሌው በርካቶች በመሆናቸው የነዋሪዎች ቁጥር በውል እንደማይታወቅ ነው የተነገረው፤ በአደጋው ሰለባ ከሆኑት ሰዎች መካከል የወረዳው ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሴቶችና ሕፃናት የሚገኙ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የአስክሬን ፍለጋና የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልፆል።
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው?በዚህ ይከታተሉ
Telegram :https://t.me/+Tukd3DqklsixtDDQ
YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
በሀገራችን ጎፋ ዞን በተከሰተው አደጋ ውድ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎቻችን እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ያሳርፍ።
በዚህ አደጋ መራር ሀዘን የደረሰባችሁ ሁሉ ፈጣሪ ያፅናችሁ።
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው?በዚህ ይከታተሉ
Telegram :https://t.me/+Tukd3DqklsixtDDQ
YouTube :https://www.youtube.com/channel/UClb3koVjtIzB37_2pKN-cVw
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana