SUNRISE BOOKS

Description
የፀሐይ መውጣት የአዲስ ቀን ጅማሬን ያመላክታል :: ብርሃንን ፣ ተስፋን እና ጉልበትን ያመጣል :: በተመሳሳይ መጽሐፍ ማንበብ አእምሮን ለአዳዲስ ዕውቀቶች ፣ ሐሳቦች እና አመለካከቶች መውጪያ መንገድ ይከፍታል :: ለስብዕና ብስለትና ለሚጨበጥ ዕውቀት መነሻም መዳረሻም ይሆናል :: የፀሓይ መውጣትም የመጽሐፍ ንባብም ራስን ለማደስ ዓለምን ለማላቅ እንደ የብርሃን ፍኖት ናቸው ::
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 month, 4 weeks ago
*" ያለፈው በሚመጣው ላይ ምንም ጥቀርሻ …

*" ያለፈው በሚመጣው ላይ ምንም ጥቀርሻ መተው የለበትም ብዬ ያለፈውን ከኔ አርቄ የጣልኩ ይመስለኝ ነበር። ምናልባት አይቻል ይሆናል። ዛሬ ከተከሰተው ክስተት ምኑ ከኔጋ እንደሚያያዝ አላውቅም። የሰው ልጅ ሁሉ ከትላንቱ ተጋብቶ ሳይሆን አይቀርም የሚኖረው። ዛሬው የትላንት ጭማቂ ነዋ!! የዛሬ ግቡ የትናንት ምክኒያቱ ነበራ! ከዓመታት በፊት እናቴ ወይ አባቴ ያነቡት እንባ ምክንያቱን እንኳን ሳይቀይር በልጃቸው  ጉንጭ ላይ ሊወርድ ይችላል። አባቶች በበሉት መራር ፍሬ የልጆች ጥርስ በለዘ አይነት ሆኖብኝ ትላንት ትዝታ ብቻ አለመሆኑ የገባኝ ዛሬ ነው፡፡ ትናንት ትውልድን እንኳን ጥሶ እንደሚያልፍ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ ሀበሻ ሙዚቃው ውስጥ እንኳን ትዝታ ስልት መኖሩ ከትናንት መፋታት አለመፈለጉ ወይ አለመቻሉ ይሆናል። "

ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ
አምስተኛ ዕትም*

2 months ago
አዲስ አድማስ ጋዜጣ በነገ ዕትሟ

አዲስ አድማስ ጋዜጣ በነገ ዕትሟ

በማለዳ ይጠብቁን !

2 months ago

በመኖር አጸድ ውስጥ
(በእውቀቱ ስዩም)

ጊዜ ከሰው መሀል- መርጦ ሲያቀማጥል
ማጣት አለ ደሞ፥
የወለዱትን ልጅ፥ ጉድፍ ላይ የሚያስጥል
በተፈሰከ ቀን፥ ጾምን የሚያስቀጥል::

እድልና ትግል በሚጫወቱበት
በደልዳላው ስፍራ
አለቃና ጭፍራ-
-ቃል ሲለዋወጡ፥ ውልና መሀላ
“አብረን እናድጋለን” ቢባል ለይስሙላ
ወንዙን ሳያጎድል ፥ሐይቁ መች ሊሞላ፤

ጸሐይ ብትወጣ
ፍጥረት በጠቅላላው ጸጋዋን ቢቀበል
የደመናም ጠበል፥
ለሁሉ ቢደርስም
አንደኛው አያድግም፥ አንዱን ሳያከስም::

2 months ago
SUNRISE BOOKS
2 months ago
ሐዋሳ ከተማ ላይ የመጽሐፍ ዕውደ-ርዕይ ተከፍቷል …

ሐዋሳ ከተማ ላይ የመጽሐፍ ዕውደ-ርዕይ ተከፍቷል :: 

ቦታ:- የሲዳማ ባሕል አዳራሽ አጠገብ።

የሜሪ ፈለቀ " ጠበኛ እውነቶች ". አምስተኛውን እትም እዛው ታገኛላችሁ ::

2 months ago
*" ... ቹቹ እኔ በምሰራበት መንግስታዊ …

" ... ቹቹ እኔ በምሰራበት መንግስታዊ ያልሆነ የውጪ ሀገር  በጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ የስራ ባልደረባዬ ናት ። ወሬ አፍቃሪነቷ ቅጥ የለሽ ቢሆንም የልቧ ገራገርነት ይይዘኛል ። ቁርስና ወሬ ቀርቦላት ምርጫ ቢሰጣት ወሬ በሻይ ትመርጣለች ። አንዳንዴ ከእውነቴ አወራታለሁ ።  ብዙ ጊዜ ግን ትሰለቸኛለች ። ቢሆንም ስለራሷ የወደቀ ስሜት ስለሚሰማት ታሳዝነኛለች ። ወሬዋ እበጂ እበጂ ቢለኝም ‘አልሰማሽም’ ብያት አላውቅም ። እሷም ሰሚ አገኘሁ ብላ ነው መሰለኝ አታዝንልኝም ። የረብ የለሽ ቀደዳዋ ማራገፊያ ታደርገኛለች ። የዛሬ ስልቀጣዋን ለየት የሚያደርገው ጆሮ የሚይዝ ረብ ስላለው ነው ። ቢያንስ ቅደም ተከተል አለው ። እና ደግሞ አጓጊው ነገር የስልቀጣው  መሪ ተዋናይ እኔ እንድሆን መፈለጓ የሆነ ‘ቶሎ ቢያልቅ’ የሚያሰኝ ልብ አንጠልጣይ ትረካ ይመስላል ። ነገሩ  በእርግጥ የሆነ የእብደት ግማሽም ይመስላል  ።  ... "
*ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ
አምስተኛ ዕትም

የጃዕፈር መጻሕፍትን አማራጭ  የሶሻል ሚዲያ ተቀላቀሉን
👇*👇👇

Telegram FacebookInstagramTiktokWebsite

2 months, 1 week ago
*" የሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የማይታወቅ …

*" የሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የማይታወቅ ክስተት እንኳን ቢሆን ቀጣይ አለው ። ከመጀመሪያ ወይ ካለፈው የሚያይዘው ግምድ የድር ያህል የቀጠነ ቢሆንም ... ሁሌም ከመሃል ቆመህ ራስህን ስታገኘው መጀመሪያውን የምትጠይቀው ለዛ ነው ። "

ከገጽ 101
ርዕስ - ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ

አምስተኛው ልዩ ዕትም ወደማለቁ ነው :: በሁሉም መጻሕፍት መደብር ያገኙታል ::

መልካም ንባብ !*

2 months, 1 week ago
SUNRISE BOOKS
2 months, 1 week ago
SUNRISE BOOKS
2 months, 2 weeks ago
*" ጥንቅቅ ያለ ስርዓታም መሆኑ ልብ …

" ጥንቅቅ ያለ ስርዓታም መሆኑ ልብ የሚሰቅዝ ነገር አለው። ሰዎች በየቦታው ፍፁም ትክክል መስለው ሲታዩ ሰውኛ አይመስለኝም። ከራሱ እየተቧቀሰ አካባቢው በቀረፀለት የትክክለኛነት ሳጥን ውስጥ የሚንፈራገጥ ሰው ራሱን ያጣ አሳዛኝ ይመስለኛል።  ለእያንዳንዱ ነገሩ የሚጠነቀቅ ሰው ራሱን እየሆነ እንዳልሆነ ነው የሚገባኝ። ራስን መሆን እርማት አይጠይቅም ። ራስን ለመሆን ጥንቃቄ አያሻም። መጠኑ ቢለያይም ሁላችንምጋ ጥቂት እብደት፣ ጥቂትም ስህተት፣ ጥቂትም ፀፀት እና ጥቂትም ውድቀት አለ ብዬ አስባለሁ ።  "

ጠበኛ እውነቶች
በሜሪ ፈለቀ
አምስተኛ ዕትም

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana