እስልምና እና ክርስትና የንፅፅር ቻናል

Description
t.me//AkeelComparative
የእስልምና እና የክርስትና ሐይማኖት ንፅፅሮችን በጥልቀት ይዳስሳል። ቻናሉን #join ሌሎችንም #add ያድርጉ!!
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 weeks, 3 days ago

Last updated 2 weeks, 5 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month, 1 week ago

4 months ago
7 months ago

.
አብርሐም ለእርድ ያቀረበው የበኩር ልጅ
ኢስሐቅ? ወይስ ኢስማኤል?
( #መስዕዋት እና #ኢድ #አል #አድሃ #አረፋ )
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ታሪካዊ ዳራው ነብዩ ኢብራሂም የበኩር ልጃቸውን ለአላህ ለመስዋት ያደረጉት ቁርጠኝነት የተመላበት ውሳኔ እና ለመስዋዕትነት የቀረበውም ልጅ ያሳየው የተለየ ጽናት ነው። በዚህም ደግሞ የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል ይከበራል። ዋናው ነጥብ ግን የዚህ የመስዕዋት ጉዳይ ሲነሳ ብዙ ጊዜ በእስልምና እና የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ዘርፈ ብዙ ክርክር ይነሳበታል።
ታድያም ነብዩ አብረሃም/ ኢብራሂም (ዐሰ) የበኩር ልጃቸውን ያገኙት በእርጅና ዘመናቸው ነበር። አብረሃም/ኢብራሂም (ዐሰ) ታላቅ ሚስታቸው ሳራ መሐን ስለነበረች(ዘፍጥረት 11፥30) እና ለፍሬ ባለመብቃቷም " ያ አላህ ያለ ዘር አታስቀረኝ፤ እኔን የሚተካ ሷሊህ ልጅ ስጠኝ" ብለው ዱዓ አደረጉ።
በዚህም መሠረት በሳራ ፈቃደኝነት ነብዩ አብረሃም/ ኢብራሂም (ዐሰ) #ሐጀር ወይም አጋር# የምትባለውን ግብጻዊ የሆነችውን የቤት ሰራተኛቸውን አገቡ።
- ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 16
1፤ የአብራም ሚስት #ሳራ ግን #ለአብራም #ልጅ #አልወለደችለትም ነበር፤ ስምዋ #አጋር የተባለ ግብፃዊት ባሪያም ነበረቻት።
2፤ ሳራም አብራምን። እነሆ፥ እንዳልወልድ እግዚአብሔር ዘጋኝ፤ ምናልባት ከእርስዋ በልጅ እታነጽ እንደ ሆነ ወደ እርስዋ #ግባ #አለችው
3፤ አብራምም የሳራን ቃል ሰማ። አብራምም በከነዓን ምድር አሥር ዓመት ከተቀመጠ በኋላ፥ የአብራም ሚስት #ሳራ ግብፃዊት ባሪያዋን #አጋርን ወስዳ #ለባልዋ #ለአብራም #ሚስት #ትሆነው ዘንድ ሰጠችው።
4፤ እርሱም ወደ #አጋር #ገባ#አረገዘችም

ከዚህም በኋላ የነብዩ አብረሃም/ ኢብራሂም(ዐሰ) ሁለተኛዋ ሚስት የሆነችው ሐጀር/አጋር ለአብረሃምም የመጀመሪያቸው የሆነውን #እስማኤል የሚባል ወንድ ልጅን ወለደችላቸው።
- ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 16
11፤ የእግዚአብሔር መልአክም አላት። እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም #እስማኤል #ብለሽ #ትጠሪዋለሽ፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና።
15፤ #አጋርም ለአብራም ወንድ ልጅን ወለደችለት፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን የልጁን ስም #እስማኤል ብሎ ጠራው።
16፤ አጋር እስማኤልን ለአብራም በወለደችለት ጊዜ አብራም የሰማንያ ስድስት (86) ዓመት ሰው ነበረ።
የእስማኤል እናት ሐጀር/አጋር እስማኤልን ከወለደች ከ14 አመት በኋላም መሐን የነበረችውና የአብረሀም የመጀመሪያዋ ሚስት የሆነችው ሳራም ደግሞ በእርጅናዋ ዘመንም #ኢስሐቅን አረገዘች።
-ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 17
19፤ እግዚአብሔርም አለ። በእውነት ሚስትህ #ሳራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች፥ ስሙንም #ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤...
እንግዲህ ሁሉን ማድረግ የሚችለው አምላክም በእርጅና ዘመንዋ ለሳራ ወንድ ልጅ ሰጣት ስሙንም #ኢስሐቅ ተብሎ ተጠራ። ይህንን አውነት በመፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ ተጠቅሷል፦
- ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 21
2፤ #ሳራም #ፀነሰች፥...
3፤ አብርሃምም የተወለደለትን #ሳራም #የወለደችለትን የልጁን ስም #ይስሐቅ ብሎ ጠራው።
ከዚህ ቀጥሎም ደግሞ አብረሐም ለመስዋዕትነት ያቀረበው #የበኩር #ልጅ ማነው? እስማኤል ወይስ ኢስሐቅ ወደሚለው የመከራከሪያ ነጥብ እናምራ፦
ሙግት 1፦ አጋር እስማኤልን ስትወልድ አብረሐም 86 አመታቸው ነበር። (ዘፍጥ 16፥16)
ሙግት 2 ፦ አብረሐምና እስማኤል ቁልፈተ ስጋቸው ሲገረዙ አብረሐም 99 ዓመቱ ነበረ። እስማኤልም 13 አመቱ ነበረ።
- ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 17
23፤ #አብርሃምም #ልጁን #እስማኤልን፥ በቤቱም የተወለዱትን ሁሉ፥ በብሩም የገዛቸውን ሁሉ፥ ከአብርሃም ቤተ ሰብ ወንዶቹን ሁሉ ወሰደ፥ የቍልፈታቸውንም ሥጋ እግዚአብሔር እንዳለው በዚያው ቀን #ገረዘ
24፤ አብርሃምም የቍልፈቱን ሥጋ በተገረዘ ጊዜ የዘጠና ዘጠኝ (99) ዓመት ሰው ነበረ፤
25፤ #ልጁ #እስማኤልም የቍልፈቱን ሥጋ በተገረዘ ጊዜ የአሥራ ሦስት(13) ዓመት ልጅ ነበረ።
26፤ በዚያው ቀን አብርሃም ተገረዘ፥ ልጁ እስማኤልም።
-ሙግት 3፦ ኢስሐቅ ሲወለድና በስምንተኛው ቀን ሲገረዝ የአብረሐም እድሜ 100 አመት ነበረ
- ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 21
3፤ አብርሃምም የተወለደለትን ሳራ የወለደችለትን የልጁን ስም #ይስሐቅ ብሎ ጠራው።
4፤ አብርሃምም ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር እንዳዘዘው በስምንተኛ ቀን ገረዘው።
5፤ አብርሃምም ልጁ #ይስሐቅ በተወለደለት ጊዜ የመቶ(100) ዓመት ዕድሜ ነበረ።
በዚህም የመፅሐፍ ቅዱስ መረጃ መሠረት ብቻ የሔድን እንደሆነ አብረሐም ለመስዋዕትነት ያቀረበው የበኩር ልጁ #እስማኤል ነበረ ማለት ነው። ምክንያቱም ደግሞ የእስማኤል እድሜ ለማግኘት፦
አጋር እስማኤልን ስትወልድ አብረሐም 86 አመቱ ነበረ፣ አብረሐምና እሰማኤል ሲገረዙ አብረሐም 99 አመቱ ነበረ፣ እንዲሁም እስማኤል ሲገረዝ 13 ዓመቱ ነበረ። 99-86= 13
ይስሐቅ ሲወለድ አብረሐም እድሜው 100 ነበረ። 100 - 99 = 1
ስለዚህ (13+1 =14) እስማኤል ከኢስሐቅ በ14 አመት ይበልጣል ማለት ነው።

ታድያም እንደ አዲስ ኪዳን ምዕራፎች በተለይም እንደ የጳውሎስ አስተምህሮ ከሆነ አብረሐም ለመስዋዕትነት ያቀረበው አንደኛው ልጁ ኢስሐቅ እንደሆነ ይናገራል። ለዚህም፦
- ወደ ዕብራውያን 11፡17-18
" አብርሃም በተፈተነበት ጊዜ #ይስሐቅን #በእምነት #አቀረበ፥ የተስፋን ቃል የተቀበለው። በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል የተባለለት እርሱም #አንድ #ልጁን #አቀረበ፤"
- የያዕቆብ መልእክት ምዕ. 2
21፤ አባታችን #አብርሃም #ልጁን #ይስሐቅን #በመሠዊያው #ባቀረበ #ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?

እናም እውነቱ ከላይ እንደተመለከትነው ነው በዚህም መሠረት ለእርድ የቀረቡት እስማኤል(ዐሰ) ናቸው ማለት ነው።
ይህንንም ጉዳይ አስመልክቶ አሏህ(ሱወ) በቁርዓን ሲናገር፦
37፡ 102
فلما بلغ معه السعي قال يا بني إني أرى في المنام أني أذبحك فانظر ماذا ترى ۚ قال يا أبت افعل ما تؤمر ۖ ستجدني إن شاء الله من الصابرين
ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡
37፡ 103- 107
فلما أسلما وتله للجبين وناديناه أن يا إبراهيم قد صدقت الرؤيا ۚ إنا كذلك نجزي المحسنين إن هذا لهو البلاء المبين وفديناه بذبح عظيم
ሁለቱም ትዕዛዙን በተቀበሉና በግንባሩም ጎን ላይ በጣለው ጊዜ (የሆነው ሆነ)፡፡ ጠራነውም፤ (አልነው) «ኢብራሂም ሆይ! ራእይቱን በእውነት አረጋገጥክ፡፡» እኛ እንደዚሁ መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡ በታላቅ ዕርድም (መስዋዕት) ተቤዠነው፡፡

ነብዩ አብረሃም/ኢብራሒም (ዐሰ) ለእርድ ያቀረቡት ልጃቸው ጉዳይ ይህንን የሚመስል ሲሆን የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓልም የሚከበረው ከዚህ አንፃር ነው።

የተለያዩ የንፅፅር ስራዎችን ለማግኘት ቻናላችንን t.me//AkeelComparative ይቀላቀሉ

7 months, 3 weeks ago

የሚስጥረ ስላሴ ሚስጥር እና
የስላሴ ፅንሰ ሀሳብ

ክፍል -5
ታድያም አምሳያ የሌለውና የዓለማት ብቸኛው ጌታ የሆነው አምላካችን አሏህ ስለዚህ ሚስጥረ ስላሴ ጉዳይ ሲናገር እንዲህ ይላል፦
4፡ 171
يا أهل الكتاب لا تغلوا في دينكم ولا تقولوا على الله إلا الحق ۚ إنما المسيح عيسى ابن مريم رسول الله وكلمته ألقاها إلى مريم وروح منه ۖ فآمنوا بالله ورسله ۖ ولا تقولوا ثلاثة ۚ انتهوا خيرا لكم ۚ إنما الله إله واحد ۖ سبحانه أن يكون له ولد ۘ له ما في السماوات وما في الأرض ۗ وكفى بالله وكيلا
እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ የአላህ መልክተኛ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃሉም ከእርሱ የኾነ መንፈስም ብቻ ነው፡፡ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ፡፡ « ( #አማልክት ) #ሦስት ናቸው» #አትበሉም፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ ልጅ ያለው ከመኾን የጠራ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ የርሱ ነው፡፡ መመኪያም በአላህ በቃ፡፡

? በመጨረሻም ፦
ይህንንም በተመለከተ በመጨረሻው ዘመን ለእየሱስ(ዓሰ) ከአሏህ(ሱወ) የሚከተለውን ጥያቄ ይቀርብላቸውና እንዲህ ይላሉ፦
5 ፡ 116
وإذ قال الله يا عيسى ابن مريم أأنت قلت للناس اتخذوني وأمي إلهين من دون الله ۖ قال سبحانك ما يكون لي أن أقول ما ليس لي بحق ۚ إن كنت قلته فقد علمته ۚ تعلم ما في نفسي ولا أعلم ما في نفسك ۚ إنك أنت علام الغيوب
አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- እኔንና እናቴን ከአላህ ሌላ ሁለት አምላኮች አድርጋችሁ ያዙ ብላሃልን» በሚለው ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «ጥራት ይገባህ፤ ለእኔ ተገቢዬ ያልኾነን ነገር ማለት ለኔ አይገባኝም፡፡ ብዬው እንደ ኾነም በእርግጥ ዐውቀኸዋል፡፡ በነፍሴ ውስጥ ያለውን ሁሉ ታውቃለህ፡፡ ግን አንተ ዘንድ ያለውን አላውቅም፡፡ አንተ ሩቆችን ሁሉ በጣም ዐዋቂ አንተ ብቻ ነህና» ይላል፡፡

የእየሱስ አስተምህሮም እንዲህ ይላል፦
- የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 7
21፤ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።
22፤ በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።
23፤ የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።
24፤ ስለዚህ ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዓለት ላይ የሠራ ልባም ሰውን ይመስላል።
25፤ ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም።
26፤ ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል።
27፤ ዝናብም ወረደ ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንም ቤት መታው፥ ወደቀም፥ አወዳደቁም ታላቅ ሆነ።

አሏህ ቀጥተኛው መንገድ ይምራን። በሌላ ርዕስ ይመለሳል አበቃ!!
t.me//AkeelComparative

7 months, 3 weeks ago

የሚስጥረ ስላሴ ሚስጥር እና
የስላሴ ፅንሰ ሀሳብ

ክፍል - 4

እየሱስ መንፈስ ያለመሆናቸውን ከተናገሩት
- የሉቃስ ወንጌል 24፥ 39
" እኔ ራሴ እንደሆንኩ እጆቼና እግሮቼ ዳስሳችሁ እዩኝ ፥ በእኔ እንደምታዩት ፥ መንፈስ ስጋና አጥንት የለውምና፤ እኔን ዳስሳችሁ እዩኝ አላቸው።" ስለዚህ እየሱስ ስጋ ለባሽ ናቸው ማለት ነው!!።

የእግዚአብሔርንም ጉዳይ በተመለከተ ደግሞ እግዚአብሔር ስለራሱ ሲናገር እንዲህ ይላል፦
- ትንቢተ ኤርሚያስ 32፥47
" እነሆ እኔ የስጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ።"
- ትንቢተ ሆሴዕ 11፥9
" እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁም።"
- ትንቢተ ኢሳያስ 46፥5
" በማን ትመስሉኛላችሁ?፥ ከማንስ ጋር ታስተያዩኛላችሁ?፥ እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታስተካክሉኛላችሁ?" ይላል እግዚአብሔር
በአንጻሩ ተቃዋሚው ጳውሎስ ግን እየሱስ የእግዚአብሔር ምሳሌ ነው ይላል፦
- 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፥4
" እየሱስ የእግዚአብሔር ምሳሌ ነው።"
- ወደ ሮሜ ሰዎች 14፥18
" እየሱስ የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው።"
ከዚህም በተጨማሪ እየሱስ ስለእግዚአብሔር ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፦
- የዮሐንስ ወንጌል 4፥24
" እግዚአብሔር መንፈስ ነው።" ይላሉ!!

እናም አስተውል !!!
1) እግዚአብሔር መንፈስ ከሆነ
2) እግዚአብሔር ስጋ ለባሽና ሰው ካልሆነ
3) እግዚአብሔርን የሚመስል ከቶ ከሌለ
4) የአምላክ የማንነነቱ መገለጫዎች ከሆኑት ሶስቱን ዘርፎች ውስጥ በእግዚአብሔርና እየሱስ መካከል ልዩነቶች ካሉ
5) እግዚአብሔር እየሱስ ካልሆነ
6) መንፈስ ስጋና አጥንት ከሌለው
7) መንፈስ ካልተወለደ
8) መንፈስ ርግብ መሣይ ከሆነ
9) እየሱስ ስጋ ለባሽ ሰው ከሆኑ
10) እየሱስ መንፈስ ካልሆኑና መንፈስ እየሱስ ካልሆነ
11) እየሱስ የአምላክን የማንነቱን መገለጫዎች የሆኑትን ሶስቱን ዘርፎች ካላሟሉ
12) እየሱስ እግዚአብሔር ካልሆኑ

⓵ኛ) አብ + ወልድ + መንፈስ ቅዱስ = 1 አምላክ ይሆናሉ (ሶስቱ ስላሴ አንድ አምላክ ናቸው) ብሎ ማመን የለም!!! ምክንያቱም፦
? እግዚአብሔርም ዘንድ የነበረውና ቃል የተባለውን እርሱም መንፈስ ነውና በዚህም ደግሞ ቃል ስጋ አልሆነም!
( መንፈስ ስጋና አጥንት የለውምና)
? ቃል ስጋ ሆኖ ስላልተወለደና ስጋ ለብሶ የተወለደውም ደግሞ ሰው የሆነውን እየሱስ ነውና በዚህም ደግሞ የተወለደውንም ቃል እግዚአብሔር አልነበረም! ( እግዚአብሔር የስጋ ለባሽ አምላክ ነው እንጂ ሰው አይደለምና)

⓶ኛ) እየሱስ አምላክ አይደሉምና እየሱስ አምላክ ነው ብሎ ማመን የለም!!! ምክንያቱም ፦
? እየሱስ ስጋ ለብሰው ተወልደዋል፤ መንፈስ ግን ስጋ ሆኖ ስጋ ለብሶ አልተወለደምና በዚህም ደግሞ እየሱስ መንፈስ አይደሉም! ( መንፈስ ስጋና አጥንት የለውምና)
? እየሱስ ስጋ ለባሽ የሆኑ ሰው በመሆናቸውና አምላክ ደግሞ ስጋ ለባሽ አይደለም በዚህም ደግሞ እግዚአብሔር አምሳያ ስለሌለው!
( እግዚአብሔር የስጋ ለባሽ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁም ስለሚል)
? እግዚአብሔር በሰው ልጅ አይን የማይታይ አምላክ ነው፤ መንፈስም የማይታይ ነው እየሱስ ግን በአካል ታይተዋል!
(እግዚአብሔርም አለ ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም፤ ፊቴን አታይም") ዘፀአት 33፥ 19-23)) &
( እየሱስም እንዲህ አለ፦ እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለም" የዮሐንስ ወንጌል 6፥46))
ስለዚህ እየሱስ አምላክ(እግዚአብሔር) ነው የሚለውን የጳውሎስ አስተምህሮ ከእየሱስ የወንጌል ስብከት ጋር ስለሚፃረር ጳውሎስ የእየሱስና የእየሱስ ስብከት ተቃዋሚ ነው!!።

ክፍል - 5 ይቀጥላል

t.me//AkeelComparative

7 months, 3 weeks ago

.
የሚስጥረ ስላሴ ሚስጥር እና
የስላሴ ፅንሰ ሀሳብ
✉️✉️✉️✉️✉️✉️✉️✉️✉️

ክፍል 3

እናም በሚስጥረ ስላሴ ሚስጥር ውስጥ እየሱስ እንደዚህ ባለ መልኩ እግዚአብሔር እንደሆኑ ይታመናል። በዚህም ጳውሎስ አብ(እግዚአብሄር) + ወልድ(እየሱስ)= 1 አምላክ እንደሆኑ የገለፀ ሲሆን ቀጥሎም ጳውሎስ ስላስተማረውና እየሱስ በመንፈስ መልክ ይኖሩ እንደነበር እንዲሁም መንፈስ ስለመሆናቸውንም ጭምር መናገሩን ቀጥሎ እንመልከት፦

እየሱስ መንፈስ መሆናቸውን ጳውሎስ ሲናገር፦
1ኛ) 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፥ 2-4
"የሙሴ ህዝቦች ከግብፅ በወጡ ጊዜ እየሱስ በመንፈስ መልክ ይከተላቸው ነበር።
2ኛ) 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፥ 17
" ጌታ እየሱስ መንፈስ ነው።"
3ኛ) 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፥10
" ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው።"
እንዚህ በማለት ጳውሎስ የእየሱስ መንፈስ መሆንን ይናገራል።

ታድያ እየሱስ መንፈስ ነው፣ እየሱስ መንፈስ ነበርና የሙሴን ህዝቦች ተባብሯል እንዲሁም እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው የሚለው ጳውሎስ ውሸት እየተናገረ መሆኑን ባጭሩ መገንዘብ ይቻላል። ምክንያቱም
- እየሱስ ከተወለዱ በኋላ መንፈስ አልነበሩም።ምክንያቱም በሉቃስ ወንጌል 24፥39 ላይ እኔ መንፈስ አደለሁም መንፈስ ስጋና አጥንት የለውምና በማለት እየሱስ ስለራሳቸው ይመሰክራሉ።
- የሙሴ ህዝቦች ከግብፅ ምድር ሲወጡ እየሱስ ገና አልተወለዱም ነበር።
- እየሱስ በስጋ ተወለዱ እንጂ በመንፈስ አልተገለጡምና።
4ኛ) የሐዋርያት ስራ 10፥38
" እግዚአብሔር የናዝሬቱን እየሱስ በመንፈስ ቅዱስ በሀይልም ቀባው።" ይላል።
በጳውሎስ አስተምህሮት መሠረት መንፈስ የተለያየ ገፅታ አለው። እንደ እርሱ አገላለጽ ከሆነ መንፈስ ማለት እየሱስ ነው፣ ርግብ መልክ ያለው፣ በቃል መልክ የሚፈስ(የሐዋርያት ስራ 2፥32)፣ የሚቀባ እና ሌላም ሌላም ገፅታ የተላበሰ መሆኑን ይናገራል። እናም ርዕሳችን ጳውሎስ የእየሱስና የእየሱስ ስብከት ተቃዋሚ ሰው ነው የሚል ነውና ለዚህም ደግሞ እየሱስ ጌታ ነው ብሎ የማስተማሩን ጉዳይ ዋናው አጀንዳችን ስለሆነ እየሱስ ጌታ ናቸው ለማለት ደግሞ የመንፈስ ማንነት መመልከት ተገቢ ሆኖ ተገኘ በዚህም ምክንያት የስላሴን ሚስጥር ዋናውና አስፈላጊው ነጥብ ሆነ።
በስላሴ ውስጥም አብ መንፈስና እየሱስ አንድ አምላክ መሆናቸውን የውሸት ትወና ያስተማረውን የጳውሎስ ትምህርት ሲፈተሽም መንፈስና እየሱስ አንድ ሆነው ተገኙ እንዲሁም ደግሞ በመደምደሚያውም ላይ እየሱስ መንፈስ መሆናቸውን መሠከረ። በዚህም ምክንያት ጳውሎስ የእየሱስና የእየሱስ የስብከታቸውም ተቃዋሚ ለመሆን ቻለ። ምክንያቱም ደግሞ እየሱስም ሆነ እግዚአብሔር ስለራሳቸው ሲመሰክሩ እንዲህ ይናገራሉ፦

እየሱስ መንፈስ ያለመሆናቸውን ከተናገሩት
- የሉቃስ ወንጌል 24፥ 39
" እኔ ራሴ እንደሆንኩ እጆቼና እግሮቼ ዳስሳችሁ እዩኝ ፥ በእኔ እንደምታዩት ፥ መንፈስ ስጋና አጥንት የለውምና፤ እኔን ዳስሳችሁ እዩኝ አላቸው።" ስለዚህ እየሱስ ስጋ ለባሽ ናቸው ማለት ነው!!።

የእግዚአብሔርንም ጉዳይ በተመለከተ ደግሞ እግዚአብሔር ስለራሱ ሲናገር እንዲህ ይላል፦
- ትንቢተ ኤርሚያስ 32፥47
" እነሆ እኔ የስጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ።"

@@@@ ክፍል 4 ይቀጥላል @@@@@@

t.me//AkeelComparative

7 months, 3 weeks ago

.
የሚስጥረ ስላሴ ሚስጥር እና
የስላሴ ፅንሰ ሀሳብ
✉️✉️✉️✉️✉️✉️✉️✉️✉️
ክፍል 2

የዚህ ፅንሰ ሀሳብ ተዋናዩ ጳውሎስ ሲናገር እንዲህ ይላል፦
ፍጥረታት ሁሉ በእየሱስ ተፈጥሯል
- ወደ ቆላስይስ 1፥ 15-16
" በሠማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእየሱስ ተፈጥሮዋልና ከፍጥረታት ሁሉ በኩር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሯል።"
እየሱስ በመንፈስ መልክ ይኖር ነበር
- 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፥ 2-4
" አባቶች ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባህር መካከል ተሻገሩ ፥ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመና በባህር ተጠመቁ፥ ሁሉም ያንን መንፈሳዊ መብል በሉም ጠጡምም።ይከተላቸው ከነበረው መንፈሳዊ መጠጥ ጠጥተዋልና ያም አለት ክርስቶስ ነበረ።"
እየሱስ በእግዚአብሔር መልክ ይኖር ነበረ
- ወደ ፊልጵስዩስ 2 ፥ 6-8
" እየሱስ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቆጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ። በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም የታዘዘ ሆነ። በዚህም እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው ፤ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው። ይህም በሠማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በእየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር እየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።"
እየሱስ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ህዝቡን ከራሱ ጋር ሊያስታርቅ በስጋ ተወለደ
- 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፥ 19
" እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ አለሙን ከራሱ ጋራ ያስታርቅ ነበር።"
- ወደ ሮሜ ሰዎች 9፥5
" ክርስቶስ በስጋ መጣ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው።"
እናም በሚስጥረ ስላሴ ሚስጥር ውስጥ እየሱስ እንደዚህ ባለ መልኩ እግዚአብሔር እንደሆኑ ይታመናል። በዚህም ጳውሎስ አብ(እግዚአብሄር) + ወልድ(እየሱስ)= 1 አምላክ እንደሆኑ የገለፀ ሲሆን ቀጥሎም ጳውሎስ ስላስተማረውና እየሱስ በመንፈስ መልክ ይኖሩ እንደነበር እንዲሁም መንፈስ ስለመሆናቸውንም ጭምር መናገሩን ቀጥሎ እንመልከት፦

እየሱስ መንፈስ መሆናቸውን ጳውሎስ ሲናገር፦
1ኛ) 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፥ 2-4
"የሙሴ ህዝቦች ከግብፅ በወጡ ጊዜ እየሱስ በመንፈስ መልክ ይከተላቸው ነበር።
2ኛ) 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፥ 17
" ጌታ እየሱስ መንፈስ ነው።"
3ኛ) 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፥10
" ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው።"
እንዚህ በማለት ጳውሎስ የእየሱስ መንፈስ መሆንን ይናገራል።

ታድያ እየሱስ መንፈስ ነው፣ እየሱስ መንፈስ ነበርና የሙሴን ህዝቦች ተባብሯል እንዲሁም እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው የሚለው ጳውሎስ ውሸት እየተናገረ መሆኑን ባጭሩ መገንዘብ ይቻላል። ምክንያቱም
- እየሱስ ከተወለዱ በኋላ መንፈስ አልነበሩም።ምክንያቱም በሉቃስ ወንጌል 24፥39 ላይ እኔ መንፈስ አደለሁም መንፈስ ስጋና አጥንት የለውምና በማለት እየሱስ ስለራሳቸው ይመሰክራሉ።
- የሙሴ ህዝቦች ከግብፅ ምድር ሲወጡ እየሱስ ገና አልተወለዱም ነበር።
- እየሱስ በስጋ ተወለዱ እንጂ በመንፈስ አልተገለጡምና።
4ኛ) የሐዋርያት ስራ 10፥38
" እግዚአብሔር የናዝሬቱን እየሱስ በመንፈስ ቅዱስ በሀይልም ቀባው።" ይላል።

ክፍል- 3 ይቀጥላል...

t.me//AkeelComparative

7 months, 3 weeks ago

የሚስጥረ ስላሴ ሚስጥር እና
የስላሴ ፅንሰ ሀሳብ

ክፍል-1

ለክርስትና እምነት አስተማሪዎች የሚስጥረ ስላሴ ሚስጥሩ ምንድ ነው ተብለው ሲጠየቁ የሚስጥሩ ትርጉም እንዲህ ነው በማለት አይናገሩም ምክንያቱም <<የስላሴን ሚስጥር ይታመናል እንጂ አይነገርም >> በማለት ያልፉታል። እናም የዚህን የሚስጥረ ስላሴ ሚስጥር ስናወራ ስለ አብ + ወልድ + መንፈስ ቅዱስን ጉዳይ ማውራት የግድ ይሆናል። ምክንያቱም ደግሞ እንደ የጳውሎሱ ክርስትና እምነት አስተምህሮ ከሆነ እየሱስ አምላክ ሊሆኑ የሚችለው የሚስጥረ ስላሴን ፅንሰ ሀሳብ አምኖ በመቀበል ብቻ ነው። ይህንም አምኖ መቀበል ማለት አብ + ወልድ + መንፈስ ቅዱስ = 1 አምላክ ይሆናሉ የሚል እምነት ነው።
በሚስጥረ ስላሴ ፅንሰ ሀሳብ ውስጥ
- አብ ማለት እግዚአብሔር
- ወልድ ማለት እየሱስ ሲሆኑ
- መንፈስ ቅዱስ ማለት ደግሞ ከሁለቱ የተለየ የሆነ ሌላ ሶስተኛ አካል እንደሆነ ይታመናል።
በአብዛኛዎቹ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ መንፈስ ቅዱስን ሲገልፁት በዮሐንስ ወንጌል 1፥32 ላይ እንደተገለፀው ርግብ አይነት አካል አድርገው ይመስሉታል።
- የዮሐንስ ወንጌል 1 ፥ 32
" መንፈስ ከሠማይ እንደ ርግብ ሆኖ ሲወርድ አየሁ።" ይላል። በዚህም መሠረት እነዚህ ሶስት የተለያዩ ማንነቶች አንድ አምላክ አድርጎ ማመን ማለት በሚስጥረ ስላሴ ማመን ማለት ነው።
ታድያም እነኚህ ሶስቱ በአንድ አካል ሆነው አንድን አምላክ ይተካሉ ብለው ለማመናቸውም እንደ ዋነኛ መረጃና የመከራከሪያ ነጥብ የሚያቀርቡት ጉዳይ ቢኖር በዮሐንስ ወንጌል 1፥1 ላይ የተጠቀሰው ነው። እንዲህም ይላል፦
- የዮሐንስ ወንጌል 1፥ 1 - 14
" ቃል ነበረ ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ ፥ ቃልም ስጋ ሆነ።"
ይላል። እናም የስላሴን ሚስጥር ማመንና መረዳት እንጂ መገንዘብ አይቻልም በማለት የሚያምኑ ቢሆንም እስቲ ይህን ጉዳይ ጥርሱን ይዘን ድዱን ነቅሰን እንተንትነው!!።
<< ቃል>> ተብሎ የተጠቀሠው << መንፈስ >>
<< ስጋ >> የተባለው << ወልድ/እየሱስ >> ሲሆን
<< በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረውና እግዚአብሔር የነበረውም ቃል >> ሲያብራሩት የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መንፈስ በማርያም አደረና ስጋ ሆነ፤ ይህም ስጋ የሆነው ቃል እየሱስ ሲሆን እርሱም << እግዚአብሔር >> ነው፤ በዚህም እግዚአብሔር ራሱን በማዋረድና ስጋ በመልበስ በሰው መልክ የተገለጠ እየሱስ ነው በማለት የስላሴን ሚስጥር እንዲህ በመረዳት ያምናሉ።
እንደ የስላሴ ሚስጥር አራማጁ ጳውሎስ እና መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ሀሳብና እምነት እየሱስ ማለት ከመወለዱና አለም ከመፈጠሩ በፊት አምላክ ሆኖ ፍጥረታትን እየፈጠረም በእግዚአብሔር መልክ ይኖር እንደነበርና የሙሴ ህዝቦች ከግብፅ ምድር በወጡበት ወቅትም በመንፈስ መልክ የነበረ ከዛም በኋላ ደግሞ አዳም በሰራው ሀጢአት ምክንያት የሰው ልጆች ከሀጢአት ሊያድናቸው ብሎ ከማረያም ጋር በስጋዊ ንክኪ ግንኙነትም ተወልዶ ስጋ ለብሶ ወደዚች ምድር በሰው መልክ የተገለጠ ሲሆን በውርስ ሀጢያትም የሠው ልጆች ከራሱ ጋር ሊያስታርቃቸውም ሲል በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሞተ አምላክ ነው ይላሉ።
የዚህ ፅንሰ ሀሳብ ተዋናዩ ጳውሎስ ሲናገር እንዲህ ይላል፦
ፍጥረታት ሁሉ በእየሱስ ተፈጥሯል
- ወደ ቆላስይስ 1፥ 15-16
" በሠማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእየሱስ ተፈጥሮዋልና ከፍጥረታት ሁሉ በኩር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሯል።"
እየሱስ በመንፈስ መልክ ይኖር ነበር
- 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፥ 2-4
" አባቶች ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባህር መካከል ተሻገሩ ፥ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመና በባህር ተጠመቁ፥ ሁሉም ያንን መንፈሳዊ መብል በሉም ጠጡምም።ይከተላቸው ከነበረው መንፈሳዊ መጠጥ ጠጥተዋልና ያም አለት ክርስቶስ ነበረ።"
እየሱስ በእግዚአብሔር መልክ ይኖር ነበረ
- ወደ ፊልጵስዩስ 2 ፥ 6-8
" እየሱስ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቆጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ። በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም የታዘዘ ሆነ። በዚህም እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው ፤ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው። ይህም በሠማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በእየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር እየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።"
እየሱስ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ህዝቡን ከራሱ ጋር ሊያስታርቅ በስጋ ተወለደ
- 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፥ 19
" እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ አለሙን ከራሱ ጋራ ያስታርቅ ነበር።"
- ወደ ሮሜ ሰዎች 9፥5
" ክርስቶስ በስጋ መጣ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው።"
።።።።።።።።።።።።///።።።።።።።።።።።።።።

ክፍል 2 ይቀጥላል....

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ይህንን የቴሌግራም ግሩፕ #Join #invite & #add ያድርጉ
t.me//AkeelComparative የሐይማኖት የንፅፅር ግሩፕ

8 months ago

? የእስልምና እና የክርስትና መነሻ ታሪክ በኢትዮጵያ

ክፍል-2
#የክርስትና #ሀይማኖት #ታሪክ #በኢትዮጵያ

እስልምናንም ሆነ ክርስትና መነሻቸው ከኢትዮጵያ ውጪ በመካከለኛው ምስራቅ ነው። ሁለቱንም ሀይማኖቶች ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡትና የሠበኩት ስደተኞች ነበሩ። ክርስትና ወደ አክሱም ያስገቡት የሶሪያ ስደተኞች ሲሆኑ እነርሱም #ፍሪምናጦስ (አባ ሰላማ ፣ ከሳቴ ብርሃን) መሆናቸው ታሪክ ያስረዳል። በተለይም በ5ተኛው ክፍለ ዘመን በሰሜን ኢትዮጵያ ክርስትናን ለህዝቡ የሠበኩትና << ዘጠኙ ቅዱሳን >> በሚል የሚታወቁት የሃይማኖት አባቶች ሁሉም የመካከለኛው ምስራቅ ስደተኞች ናቸው። ስደተኞቹ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ተሰደው የመጡት እ.አ.አ በ451 ከተካሄደው <<ቻልኬዶን ጉባኤ>> በኋላ ነበር። ስደተኞቹ የሐይማኖት አባቶች አባ አፍፄ ፣አባ አሌፍ፣አባ ገሪማ፣አባ ጉባ፣አባ ጻህማ ሊቃኖስ ፣አባ ጴንጤሌዎን ፣አባ የማታ እና አባ ዘሚካኤል ዓረጋዊ ናቸው። ምንጭ፦(The dictionary of Ethiopian Biography, Vol 1, from early times to the end of the Zagwe Dynasty C,1270 AD.institute of Ethiopian studies AAU, 1975, Pp.209-210)

#የእስልምና #መነሻ #ታሪክ #በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ውስጥ ከኢስላምና ሙስሊሞች ጋር በተገናኘ በሂልቃኑ ድርሳን ላይ የሚታየው ቅኝት የታመኑ የታሪክ ጥናት መረጃዎች ከሚያስረዱት በተቃራኒ <<ኢስላም ወደ ኢትዮጵያ ከጊዜ በኋላ የመጣ (መጤ) ሃይማኖት>>እንደሆነ ወይም <የኢትዮጵያን አንድነት የሚያናጋ አደገኛ ሃይማኖት> እንደሆነ ተደርጎ ይሳላል። ለምሳሌ ፦ ኢስላምን በኢትዮጵያ ርዕስ አድርገው ከተጻፉ የታሪክ መጻሕፍት ውስጥ በስፋት የሚታወቀው የታሪክ ምሁሩ ጄ ስፔንሰር ትሪሚንግሃም የጻፉት ( Islam in Ethiopia) ዓበይት ታሪካዊ ክስተቶች እና ወቅቶችን ከብቦ የተፃፈ መሆኑ እንዳለ ሆኖ፤ እንደ ርእሱ ኢስላም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያለውን ስፍራ የሚያሳይ ከመሆኑ ይልቅ <<ኢስላም ለኢትዮጵያ እንዴት አደጋ እንደሆነ>> ለማሳየት የሚሞክር መጽሐፍ ነው። የመጽሐፉ አጠቃላይ ቅኝት እና መልዕክት ክርስቲያን ኢትዮጵያ እንዴት ለብዙ ዘመናት በሙስሊሞች አደጋ እንደተጋረጠባት ለማሳየት ነው የሚሞክረው። በአጠቃላይ በሂልቃኑ ድርሳን ውስጥ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች <<የውጭ ኢስላማዊ ኀይሎች ወኪል>> (Agents) ተደርገው ነው የተሳሉት።
በሂልቃኑ የተጻፉ ብዙዎቹ የታሪክ መጻህፍት የኢማም አህመድ ኢብን ኢብራሂምን ዘመቻ <<ወረራ>> ብለው ሲጠሩት የምንታዘበው አሳዛኙ ታሪክ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያዊነቱ በመካዳቸውም ነው። ታድያ እንደነርሱ አመለካከት ከሆነ በታሪኳ በውጭ ወራሪ ኋይል በቅኝ ተገዝታ የማታውቀው ኢትዮጵያ በአንድ ወቅት ግን ግራኝ አህመድ በሚባልና መሪ በነበረው የውጭ መንግስት ለ16 ዓመታት ተገዝታለች>> ማለት ነው።

- ሌላው በዛጉዌ ዘመነ መንግስት ስር የነበሩት የአፄዎቹ የፀረ-ኢስላም አገዛዝ ጉዳይ ሲሆን ይህም ከገብረ መስቀል ላሊበላ(1189-1229) ዘመነ መንግስት ጀምሮ እስከ አፄ አምደ ፅዮን (1315-1344) ከአፄውም አንስቶ እስከ አፄ ዘርዓያዕቆብ (1434-1468) ከዚያም በመቀጠል በኢማም አህመድ ዘመን የነበረው አፄ ልብነ ድንግል(1508-1540) ድረስ እንዲሁም ሲቀጥል ከአፄ ገላውዲዎስ 1542 እስከ አፄ ኀይለ ስላሴ ድረስ የነበሩት ክርስቲያን መሪዎች እስልምና እና ሙስሊሞችን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ያልፈነቀሉት ድንጋይ አልነበረም።
እናም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝበ ሙስሊም ታሪክ እንደሌለውና አፍራሽ ሚና ሲጫወት እንደነበር ፣ ወራሪና መጤ እንደሆነም አድርገው ሳሉት። የግፍ በትር ቀማሽ የነበረው ሙስሊም በአገሪቱ ላይ ችግር ሲፈጥር የኖረ ተደርጎ ቀረበ። የ1923ቱ የዓፄ ሀይለስላሴ ህገመንግስት ለዚህ ጥሩ ማሳያ ይሆናል። እንዲህ ይላል፦
" ከክርስቶስ ልደት በኋላ እስከ አፄ ቴዎድሮስ ዘመን ድረስ አረመኔና እስላም ፈላሻም ዙርያዋን ስለከበባት ወደ ሀይማኖት ትግል ተመልሳ ይህ የሀይማኖት ትግል በግዛቷ ውስጥ እየባሰና እየከፋ በመሄዱ በሀይልና በጉልበት የቀድሞ ግዛቷን ለማስፋፋት ሳይመቻት ቀረ። ይልቁንም አረመኔና እስላም..." (ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት በቀዳማዊ ሀይለስላሴ የቆመ ህገመንግስት ፣ ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ፣ የኢትዮ.ህገመንግስት ከ1923-1983 ልዩ እትም፣ ቁጥር አንድ ፥ገፅ 1))
ይህን ሁሉ ስለ ታሪክ መቀባጠር ያስፈለገኝ በምክንያት ነው። እርሱም ባለንበት ወቅት ክርስቲያኖች ለእስልምና በጎ አመለካከት የሌላቸው በመሆኑና ይህም ከጥንት ጀምሮ ሲነገር እና ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው ስም የማጠልሸት ሴራ መሆኑን ለመገንዘብ ያህል ነው።
ታድያ የሁሉንም አፄዎች አገዛዝ አንድና ተመሳሳይ የሚያደርጋቸው ፀረ-ኢስላም በመሆናቸው ነው። ለአብነትም ያክል ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብን እንውሰድ። አፄው በ1434 ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ቀጥሎም በ1436 እና 37 በሙስሊሞች ላይ መጠነ ሰፊ ዘመቻውን ጀመረ። በ1441 ኢስላምን እና ነብዩን(ሰዐወ) እጅግ የሚያንቋሽሸው ክርስቲያናዊ የሆነ << #ተዓምረ_ማርያም >> የተሰኘውን መጽሐፍ በግዕዝ እንዲዘጋጅ አደረገ። ዘወትር እሁድ በአብያተ ክርስቲያናቱ እንዲነበብ ደነገገ።
#ምንጭ፦ ( Haggai Ehrlich, The cross and River, Ethiopia, Egypt and the Nile. P.47)
ይህም ጸረ ኢስላም አስተሳሰብ በህዝቡና በቀጣዩ ትውልድ ልብ እንዲሰርፅ በማለም ነበር።

በአጠቃላይ ወደዋናው ነጥቤ ስመለስ የኢስላም መነሻ ታሪክ በኢትዮጵያ የሚጀምረው እአአ በ615 ሲሆን ኢስላም ወደ የትኛውም ሀገር ከመድረሱ በፊት ነበር አስቀድሞ ወደ ሀገራችን የደረሠው። ኢስላም ወደ ኢትዮጵያ የደረሠው ከቅድስቲቷ መካ ከተማ በመነሳት መዲና እንኳን ሳይደርስ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ።
ይህ ሊሆን የቻለው መካ ውስጥ ፈጣሪያቸውን በነፃነት ማምለክ ስላልቻሉ በአምስተኛው የነቢይነት ዓመት በረጀብ ወር እአአ በ615 ወደ ሐበሻ (አክሱም) እንዲሰደዱ ነብዩ ሙሐመድ(ሰዐወ) ተከታዮቻቸውን በመምከራቸው ነበር። ሆኖም የመጀመሪያው ስደት ሲያደርጉ 12 በመሆን ነበር ወደ ሐበሻይቱ አገር የተሰደዱት።
በዚህም መሠረት እንደ ክርስትናው ሁሉ እስልምናንም በስደት ወደ አክሱም በመምጣት የሰበኩት እነዚህ የአረብ ስደተኞች ናቸው። ታድያ ኢትዮጵያ በታሪኳ ክርስቲያናዊና ኢስላማዊ መንግስታትን አስተናግዳለች። የመጀመሪያው ኢስላማዊ መንግስት የተቋቋመው እአአ በ896/7 በሸዋ ሲሆን ሸዋ ሱልጣኔት በመባል ይጠራ ነበር። በኋላ ላይም ሌሎች ሰባት ሱልጣኔቶች እንደነበሩና እነርሱም ኢፋት፣ ደዋሮ፣ አራቢኒ(እርእኝ)፣ ሐዲያ፣ ሻርካ፣ ባሌ እና ደራህ ናቸው። #ምንጭ፦ Maqrizi፡ The book of the true knowledge of the History of Moslem Kings in Abyssinia. G. W. S Hunfingford Trans, p.7 )

t.me//AkeelComparative

8 months ago
9 months, 2 weeks ago

አል-ሐሊም ክፍል- 4
? አል-ሐሊም ማለት በአጠቃላይ ለቅጣት የማይቸኩል ታጋሽ የሆነ ማለት ነው። ሁሉን ማድረግ ቻይ የሆነው ይህ ታጋሹ ጌታ ልጅ አለው ብለው የሚያምኑ ሰዎችን ዱንያ ላይ የፈለገውን ቅጣት መቅጣት ይችል ነበር። ነገር ግን ትዕግስቱ ወደር የለሽ ስለሆነ ለቅጣት አይቸኩልም። እርሱም እንዲህ ይላል፦
4፡ 171
يا أهل الكتاب لا تغلوا في دينكم ولا تقولوا على الله إلا الحق ۚ إنما المسيح عيسى ابن مريم رسول الله وكلمته ألقاها إلى مريم وروح منه ۖ فآمنوا بالله ورسله ۖ ولا تقولوا ثلاثة ۚ انتهوا خيرا لكم ۚ إنما الله إله واحد ۖ سبحانه أن يكون له ولد ۘ له ما في السماوات وما في الأرض ۗ وكفى بالله وكيلا
እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ የአላህ መልክተኛ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃሉም ከእርሱ የኾነ መንፈስም ብቻ ነው፡፡ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ፡፡«(አማልክት) ሦስት ናቸው » አትበሉም፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ ልጅ ያለው ከመኾን የጠራ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ የርሱ ነው፡፡ መመኪያም በአላህ በቃ፡፡
38፡ 1-3
بسم الله الرحمن الرحيم ص ۚ والقرآن ذي الذكر
بل الذين كفروا في عزة وشقاق
كم أهلكنا من قبلهم من قرن فنادوا ولات حين مناص

ጸ. (ሷድ) የክብር ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ (ብዙ አማልክት አሉ እንደሚሉት አይደለም)፡፡
ይልቁንም እነዚያ የካዱት ሰዎች በትዕቢትና በክርክር ውስጥ ናቸው፡፡ ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙን አጥፍተናል፡፡ (ጊዜው) የመሸሻና የማምለጫ ጊዜ ሳይሆንም (ለእርዳታ) ተጣሩ፡፡

? ሌላው አል-ሐሊም (ታጋሽ) የሆነው ጌታ ለአማኝ ባሮቹ ምንም ከባድ ችግር ቢያጋጥማቸው ታጋሽ መሆን እንዳለባቸውና እንዲሁም ደግሞ ከታጋሾች (ከሰብረኞች) በስተቀር ሁሉም ኪሳራ ውስጥ መሆናቸውን በቁርዓን 103፡ 3 ላይ ይናገራል።
ከዚህም በተጨማሪም አሏህ(ሱወ) በሀዲስ አል-ቁዱስ ሲናገር ነብዩ(ሰዐወ) እንዲህ ይላሉ፦
? ጁንዱብ ኢብኑ ዐብደላ [رضي الله عنه‌‎ ] እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ [صلى الله عليه وسلم] የሚከተለውን ተናግረዋል፡- “ከናንተ በፊት ከነበሩት ሕዝቦች ውስጥ አንድ ቁስል የነበረበት ሰው ነበር፡፡ ተስፋ ቆረጠ (ትዕግስት አጣ)፡፡ አንድ ቢላዋ አንስቶም እጁን ቆረጠ፤ እስኪሞት ድረስ ደሙ መፍሰሱን አላቆመም፡፡ ሁሉን ነገር ማድረግ የሚችለው አላህ፡- “ባሪያዬ ራሱን በማጥፋት ቸኮለብኝ፤ (በመሆኑም) ጀነትን ከልክየዋለሁ” አለ፡፡”
? አቡ ሁረይራ [رضي الله عنه‌‎ ] እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ [صلى الله عليه وسلم] እንዲህ ብለዋል፡- “ኃያሉ አላህ እንዲህ ይላል፡- “እኔ ከዚህ ዓለም ነዋሪዎች መካከል ምርጥ ጓደኛውን ወስጀበት ለእኔ ሲል ታግሶ ከቻለ፣ ታማኝ ባሪያዬ ከእኔ የሚያገኘው ምንዳ ከጀነት ውጭ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡” {ሀዲሰ ቁድሲ }

በመጨረሻም
ይህንን የአላህ ስም(አል-ሐሊም) በሳህን ላይ በመፃፍ ከዛም በውሃ መጣብ በመቀጠል ውሃውን በፈለጉት ንብረት ላይ በመርጨት ንብረቱ በአላህ ፈቃድ ከመጥፋት የተጠበቀ ይሆናል።

ክፍል -24 በሌላ የአሏህ መልካም ስም ይቀጥላል...

ይህንን ደርስ ለሌሎች እንዲደርስ #share እንዲሁም ወዳጆትንም ወደ ቻናሉ በ t.me/AkeelComparative ሊንክ ይጋብዙ!

t.me/AkeelComparative

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 weeks, 3 days ago

Last updated 2 weeks, 5 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month, 1 week ago