Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

Meleket Tube

Description
መንፈሳዊ መረጃዎችን እንዲሁም ዝማሬዎችና የወንጌል ትምህርቶች በየእለቱ ከዚህ ገፅ ያገኛሉ።
ኢየሱስ በክብር ይመጣል!

Find us on more- https://linktr.ee/meleket_tube

Contact us - @LiveMeleket_Bot
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 5 days, 4 hours ago

Last updated 3 weeks, 1 day ago

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Last updated 1 month, 3 weeks ago

5 months, 2 weeks ago

#ካውንስሉ_አስቸኳይ_መግለጫ_ሰጠ
በወንጌላዊያን አማኞች እና አብያተክርስቲናት ላይ እየደረሰ ስላለዉ ጥቃት ህዳር 27 ቀን 2016ዓ/ም መግለጫ_ሰጠ።

1-ባለፋት ዘመናት በተለይ በደርግ ዘመን የተወረሱ የቤተክርስቲያን ይዞታዎች በኢሕአዴግ ዘመን በከፊል ቢመለሱም እስካሁን ያልተመለሱ የኦሎምፒያ መሰረተክርስቶስ፣ የአዲስ ከተማ ገነት፣ የኢትዮጵያ ወንንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ብረት የሆነው የጉድ ሼፐርድ ማዕከል ፣ቄራ አካባቢ ያለው የብርሃነ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ፣እና ሌሎች እስካሁን ያልተመለሱ ይዞታዎች ሲሆኑ እነዚህ ይዞታዎች የቤተክርስቲያን ንብረት በመሆናቸዉ እንዲመለሱ ተጠይቋል።

2-የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ይዞታዋን ለቃ እንድትነሳ የከተማዉ አስተዳደር የወሰንኑ ቢሆንም የከተማዉ አስተዳደር እና የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እንዲሁም የካውንስሉ አመራሮች ሰፊ ዉይይት አድርገዉ የከተማዉ አስተዳደር ጉዳዩን እየመከረበት ይገኛል።የከተማዉ አስተዳደር የደረሰበትን ደረጃ በአጭር ጊዜ ግልፅ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

3-የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ይዞታ ነጥቆ የራሱ ጽህፈት ቤት አድርጎት ይገኛል።እንዲሁም የቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ይዞታ የሆነዉን የኩሪፍቱ የጸሎት ማዕከል በተመለከተም በማእከሉ ምንም አይነት የልማት ስራ ቤተ ክርስቲያን እንዳታከናወን በማገድ የቤተክርስቲያኑን ይዞታ ለመንጠቅ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝኝ ተገልጾ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከዚህ ህገወጥ ድርጊቱ እንዲቆጠብ እና የወሰደዉን የቤተክርስቲያን ንብረት እንዲመልስ ተጠይቋል።

4-በአዲስ አበባ ዙሪያ ባለችው የሸገር ከተማም የፈረሱ የወንጌላዊያን የእምነት ተቋማት ይዞታቸዉ እንዲመለስ እንዲሁም በከተማዋ ለ23 አብያተክርስቲያናት ከካቢኔ ቦታ ተወስኖላቸዉ ቦታቸዉን መረከብ ላልቻሉ በአፋጣኝ ካቢኔ የወሰነዉ ዉሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን ተጠይቋል።

5-የመቃብር ስፍራን ጥሶ በመግባት እየተደረገ የሚገኘዉ አግባብ ያልሆነ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም

6-በምዕራብ ኢትዮጵያ በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሜ ወረዳ ዘጠኝ ምእመናንን የአምልኮ ስነስርአት እየፈፀሙ ካሉበት ሌሊት ላይ ተወስደዉ መረሸናችው እጅግ አሳዛኝ እንደሆነና ለነዚህ ንፁሃን ፍትህ እንዲሰጥ ተጠይቋል።
በአጠቃላይ ፍትህ ያስፈልጋል ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ሊከበሩ ይገባል ይህ ሁሉ እየሆነ ያለዉ የታችኛዉ የመንግስት አካል የመንግስትን ስልጣን በመጠቀም ጥቂት ግለሰቦች የግል አጀንዳ ይዘዉ የሚፈፅሙት ተግባር ነዉ። የፌደራል መንግስት ጣልቃ በመግባት ፍትህ ሊያሰፍን ይገባል ሲል የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል በመግለጫዉ አስታዉቋል።

Join➴
@MELEKET_TUBE

5 months, 2 weeks ago
5 months, 2 weeks ago
**አስደሳች ዜና!**

አስደሳች ዜና!

እንደ "ዴስፓሲቶ" እና "ጋሶሊና" በመሳሰሉት በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂው ሙዚቃዎቹ የሚታወቀው የአለማዊ ዘፈን አቀንቃኝ የነበረው የፖርቶ ሪኮ ራፐር ዳዲ ያንኪ ህይወቱን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለመስጠት እንደወሰነ እና ከአለማዊው ሙዚቃ እራሱን እንዳገለለ አሳውቋል።

"እንደ ሙዚቃ፣ ማህበራዊ ሚዲያ፣ መድረኮች፣ ማይክራፎን ኢየሱስ የሰጠኝ በእጄ ውስጥ ያሉኝ መሳሪያዎች ሁሉ አሁን ለመንግስቱ ነው ሲል ተናግሯል።"

Join➴
@MELEKET_TUBE

5 months, 2 weeks ago
Meleket Tube
5 months, 2 weeks ago
Godina Qellem Wallagaa, Aanaa Gidaamiitti ajjeechaa …

Godina Qellem Wallagaa, Aanaa Gidaamiitti ajjeechaa Amantoota irratti raawwate ilaalchise Ibsa WKWW Mekane Yesus Itiyoophiyaatiin kenname.
Sadaasa 24-2016

ህዳር 25 ቀን 2016 የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በቄለም ወለጋ ዞን በተለይም በጊዳሚ አውራጃ በአባላቶቹ ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል።

Join➴
@MELEKET_TUBE

5 months, 2 weeks ago
5 months, 3 weeks ago
Meleket Tube
5 months, 3 weeks ago
Meleket Tube
5 months, 3 weeks ago
[#ይድረስ\_ለወንጌል\_አማኞች\_በሙሉ](?q=%23%E1%8B%AD%E1%8B%B5%E1%88%A8%E1%88%B5_%E1%88%88%E1%8B%88%E1%8A%95%E1%8C%8C%E1%88%8D_%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%8A%9E%E1%89%BD_%E1%89%A0%E1%88%99%E1%88%89)***📌******📌***

#ይድረስ_ለወንጌል_አማኞች_በሙሉ📌📌

(እባክዎ መልዕክቱን ሼር ያድርጉ)

በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ኩሪፍቱ ማዕከል የቃለህይወት ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የሁሉም ወንጌላውያን አማኞች ንብረት የሆነ፣ ብዙዎቻችን በግል እና በቡድን እየሄድን ለቀናት የፀለይንበት ስፍራ ነው።
በዚህ ስፍራ ሄዶ ያልተገለገለ፣ ያልፀለዬ አማኝ ይኖራል ማለት ዘበትነው። በአዲሳባ ያሉ ሁሉም ቸርቾች ወጣ ብለው የሪትሪት፣ የፆምፀሎት ፣ የህብረት ጊዜ ማሳለፍ ሲፈልጉ የመጀመሪያም የመጨረሻም ተመራጩ ቦታ ይህ የኩሪፍቱ ቃለህይወት ነው። ይህ ስፍራ በከተማ አስተዳደሩ ከቸርች ተነጥቆ ለግለሰቦች ሊሰጥ መሆኑን በትናንትናው ዕለት ቸርቿ ይፋ አድርጋለች። ይህ የሁሉም አማኝ ቅርስ ከቤተክርስቲያን በግፍ ከመነጠቁ በፊት ሁላችሁም የወንጌል አማኞች ድምፃችሁን እንድታሰሙ ጥሪ እናቀርባለን።

እባኮ መልዕክቱን ሼር ያድርጉ

Join➴
@MELEKET_TUBE

6 months ago
[#ቤቱ\_ራሱ\_ይናገራል](?q=%23%E1%89%A4%E1%89%B1_%E1%88%AB%E1%88%B1_%E1%8B%AD%E1%8A%93%E1%8C%88%E1%88%AB%E1%88%8D)፤ ለጸሎት ቤት እንጂ ለሌላ አልተፈጠርኩም …

#ቤቱ_ራሱ_ይናገራል፤ ለጸሎት ቤት እንጂ ለሌላ አልተፈጠርኩም ይላል።

በአዲስአበባ ከተማ ከ1954 ዓም አንስቶ የመጀመሪያው የመሠረተ ክርስቶስ ጸሎት ቤት በደርግ ያለሕግ ወርሶ ግቢውን ትምህርት ቤት "#የአብዮት_እርምጃ" ብሎ ሰየሙት ጸሎት ቤቱን ግን የስፖርት መሥሪያ አደረጉት።
#ቤቱ_የጸሎት_ቤት_ይሁን!!

#MKCchurch

@meleket_tube

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 5 days, 4 hours ago

Last updated 3 weeks, 1 day ago

በዚህ ቻናል ወቅታዊ፣ታማኝ እና ፈጣን መረጃ ያገኛሉ❗
መረጃ ለማድረስ እና ማስታወቂያ ለማሰራት ከስር ባለው ሊንክ ይጻፉልን👉http://t.me/ayulaw

Last updated 1 month, 3 weeks ago