ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
የአላህ መልእክተኛ(ﷺ) አላህን ጤንነትን ሁሌ ይለምኑት ነበር። ከሚያደርጉት ዱአዎች መካከል አምስቱን ልጋብዛቹ!
[اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي الدُّنْيَا
وَاْلآخِرَةِ، ...]
አላህ ሆይ በዚህችም ሆነ በቀጣዩ ዓለም ይቅርታንና #ጤንነትን እጠይቅሃለሁ፡፡[ አቡ ዳዉድ ዘግበዉታል]
[اَللَّهُمَّ عَافِنِيْ فِيْ بَدَنِيْ...]
አላህ ሆይ #አካሌን ጤናማ አድርግልኝ፡፡ [አቡ ዳውድ አህመድ እና ነሰእይ ዘግበውታል]
﴿اللَّهُمَّ إنِّي أَعُوذُ بكَ مِن زَوالِ نِعْمَتِكَ، وَتَحَوُّلِ عافِيَتِكَ، وَفُجاءَةِ نِقْمَتِكَ، وَجَمِيعِ سَخَطِكَ﴾
“አላህ ሆይ! ከፀጋህ መወገድ፣ ከለገስከኝ #ጤንነት እጦት፣ ከድንገተኛ ብቀላህ፣ ከቁጣህ ሁሉ በአንተ እጠበቃለሁ።” [ሙስሊም ዘግበውታል፡ 2739]
﴿يا عباسُ عمَّ النبيِّ ! أَكثِرْ من الدُّعاءِ بالعافيةِ﴾
“አንተ አባስ ሆይ! የነቢዩ አጎት! አብዛኛው ዱዓህን ስለ አፊያ (#ጤንነት) አድርገው።” [ሶሂህ አተርጊብ፡ 3390]
اَلْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِيْ عَافَانِيْ فِيْ جَسَدِيْ، وَرَدَّ عَلَيَّ رُوْحِيْ، وَأَذِنَ لِيْ بِذِكْرِه_ِ
[አካላዊ #ጤንነት ለለገሠኝ ነፍሴንም ለመለሰልኝ እንዳወሳውም ለፈቀደልኝ አላህ ምስጋና ይገባው።]
የአላህ ጥበቃ ያልተለያቸዉ ነብይ ይህን ያህል ስለ ጤና አሳስቧቸዉ ዱአ ካደረጉ እኔ እና አንተስ?
እናንተ ደግሞ ያልተጠቀሰዉን ጨምሩበት!
ረሱል(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
( ﺍﻟْﻌَﻴْﻦُ ﺣَﻖٌّ )
«በአይን (መጎዳት) ያለ እውነታ ነው»
[ቡኻሪና (5740) ሙስሊም (2187)ዘግበውታል]
ልብ ልንለው የሚገባ ቁምነገር አለ። ይኸውም፣ ዐይን-ናስ፣ ድግምትና መሰል ሀይላት ከአላህ ይሁንታ በቀር አንዳችም ጉዳት የማድረስ አቅም የሌላቸው መሆኑ ነው። የአይነ-ናስ ተፅእኖ በእይታ ብቻ የሚከሰት አይሆንም። ይልቁንም፤ ማየት በተሳነው ሰው(አይነ ስውር) አማካኝነት ሳይቀር ሊከሰት የሚችል ነው። ምክንያቱም ደግሞ ዐይነ-ናስ የሚከሰተው ከተቀናቃኝነት ክፋት(ምቀኝነት) በተጨማሪ ከአድናቆትም የሚመነጭበት ዕድል በመኖሩ ነው። ላቅ ሲልም እጅግ በሚዋደዱ እና አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ በሚባባሉ ወንድሞችና እህቶች መካከል ሊከሰት ይችላል። ሂስድ(ምቀኝነት) ወይም አይነ-ናስ(ቡዳ) ላይ በማስመልከት ኢብን አልቀይም አልጀውዚይ(አላህ ይዘንላችው) እንዲህ ይላሉ፦
ዐይነ-ናስ እና ሂስድ ሂደቱ እንደጦር(ተምዘግዛጊ) ነው። ከሚመቀኝ ወይም በዐይኑ ከሚጎዳ ወይም በዐይኑ ከሚጎዳ ሰው ይሰነዘራሉ። አንዳንዴ ኢላማቸውን ይመታሉ፤ በሌላ ጊዜ ደግሞ ኢላማቸውን ይስታሉ።
ዐይነ-ናስ(ቡዳው) ተመልካቹ ሰው ሲሆን፤ ሂስድ(ምቀኝነት) ግን ከመደመምና መደነቅ ባለፈ የዚያ ሰው ፀጋ ይጠፋ ዘንድ ከሚመኝ የምቀኝነት ዐይን የሚመነጭ ነው። በሰለባው ላይ ባስተዋለው አንዳች አይነት ፀጋ አብዝቶ ከመደመሙ የተነሳ ሊደርስ የሚችል "ለምን አገኘ?፣ ምነው ባልኖረው፣ ባልታደለ" ወዘተ ብሎ ሁኔታን የሚመለከት ይሆናል።
የሚያምር ነገር ስናይ ተበሩክ(መባረክን መፀለይ) ማድረግ!
አንድ አማኝ በወንድሙ(በእህቷ) ላይ የሚያስደምም ነገር ሲመለከት "ማሻአላህ ላቁወተ ኢላ ቢላህ፣ ማሻአላህ"(አላህ ያሻው ተፈፀመ። በአላህ እንጂ ሀይል የለም! እና መሰል ዱአዎችን ልንል ይገባል።
መልካም ነገር አይቶ ይህንን ዱአ ያለ ጉዳት አይደርስበትም!
አነስ(ረዲየላሁ አንሁ) የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ማለታቸውን አውስተዋል፦ "አንዳች የሚያስደምመውን(የማረከውን) ነገር ባየ ጊዜ እንዲህ ያለ አንዳችም አይጎዳውም። ማሻ አላህ ላቁወተ ኢላ ቢላህ ለም የዲሩ(አላህ የሻው ተፈፃሚ ሆነ፣ በአላህ እንጂ ሃይል የለም።) [ኢብኑ ስሪን ዘግበውታል]
ስናጣዉ ብቻ የሚገባን ትልቁ ፀጋ!
የአላህ መልእክተኛ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-
«ራሱን በሆነ ነገር የገደለ። የጀሀነም እሳት ዉስጥ ይገባል።» [ሶሂህ አል ቡኻሪ]
ተመልከቱ ይሄ ሁሉ ሰልፍ የምታዩት በትግራይ ክልል የረሱል(ﷺ) ፀጉር ነዉ ተሳለሙ በሚሉ አሳሳቾች ህዝቡን ወደ ጥፋት ሲመሩ!
ይይ ይመልከት አእምሮ ላለዉ ሰዉ። የአላህ መልእክተኛ(ﷺ) በእኔ ላይ የዋሸ መቀመጫዉን ከእሳት ያድርግ ብለዋል። (ሙስሊም) እረ ይሄ ህዝብ የረሱል(ﷺ) ሙሀባ እያላቹ አትሸዉዱት። ምንጩ ባልታወቀ ነገር ህዝቡን አታሳስቱ። ረሱል(ﷺ) ለህዝቦቼ የተዉኩት ቁርአንና ሀዲስ እንጂ ፀጉሬን ትቺያለዉ ያሉበት አጋጣሚም ሶሀቦችም የተናገሩበትም የለም።
የኛ ሀይማኖት ከሌሎች ሀይማኖት የተለየና ግልፅ ነዉ። መንገዳችን(መመሪያችን) በእዉቀትና በረሱል(ﷺ) መንገድ ሊሆን ይገባል። እያንዳንዱ የምንሰራዉ ስራ አላህና መልእክተኛ ያዘዙትና የሚወዱት ነዉ ብሎ መጠየቅ ይኖርብናል።
ዝሙትና አደጋዎቹ!
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
🟢 ۞ "ዝሙትንም አትቅረቡ፤ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፤ መንገድነቱም ከፋ!”። ۞ (📖 ሱረቱል ኢስራእ 32)
⚠️ ኢስላም ዝሙትን ዱንያዊ ቅጣት የወሰነበት ወንጀል ነው። በዚህ ተግባሩ ላይ ኾኖ በአራት የአይን ምስክሮች እጅ ከፍንጅ የተያዘንም ሰው ቅጣትን ደንግጎበታል …
ቅጣቱም ትዳር የሌለው ሰው ከኾነ መቶ ግርፋትን መገረፍ ሲኾን፣ በትዳር ዓለም ላይ ያለና ያገባ የነበረ ከኾነ ደግሞ ተወግሮ መሞትን ነው፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-
🟢 ۞ "ዝሙተኛይቱና ዝሙተኛው ከሁለቱ እያንዳንዳቸውን (ያላገቡ ከሆኑ) መቶ ግርፋትን ግረፉዋቸው፤ በእነርሱም በአላህ ፍርድ ርህራሄ አትያዛችሁ፡፡ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ እንደሆናችሁ (አትራሩ)፡፡ ቅጣታቸውንም ከምእምናን ጭፍሮች ይገኙበት፡፡" ۞ (📖አንኑር: 2)
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
⚠️ ዝሙትን ፈፅሞ ሳይቶብት የሞተ ሰው የሚኖረው አኺራዊ ቅጣቱ ደግሞ የከፋ ነው የሚሆነው። ዝሙት በቀብር (የበርዘኽ ህይወት) አስፈሪ ቅጣት ያለበት ጥፋት ነው፡-
📗የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-
"ዛሬ ሌሊት ሁለት ሰዎች ወደኔ መጥተው አየሁኝ። ይዘውኝ ወጡ። ከነሱ ጋር ተጓዝኩ። እንደ ምድጃ ባለ ግንብ ዘንድ ደረስኩ። ላዩ ጠባብ ታቹ ሰፊ ነው። ከስሩ እሳት ይቀጣጠላል።…
በውስጡ እርቃን የሆኑ ወንዶችና ሴቶች አሉ። እሳቱ ሲቀጣጠል ሊወጡ እስከሚቀርቡ ወደላይ ይወጣሉ። ሲከስም ይመለሳሉ። ‘እነማን ናቸው እነዚህ?’ ብየ ሁለቱን ሰዎች ስጠይቅ ‘ዝመተኞች ናቸው’ ይላሉ።" 📗 (ቡኻሪ: 7047)
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
⚠️ ዝሙት በአኺራ ድርብርብ ቅጣት ከተዛተባቸው ሺርክና ሰው መግደል ጋር አብሮ የተጠቀሰ የወንጀል አይነቶች ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-
🟢 ۞ "እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡…
ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል፡፡ በትንሣኤ ቀን ቅጣቱ ለእርሱ ይደራረባል፡፡ በእርሱም ውስጥ የተዋረደ ኾኖ ይኖራል፡፡" ۞ (📖 አልፉርቃን: 68–69)
⛔ ኢማሙ አሕመድ "ከግድያ ቀጥሎ ከዝሙት የከፋ ወንጀል አላውቅም" ይላሉ
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
📗 ዑባደተ ኢብኑ-ሷሚት (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ፡-
"ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጋር በአንድ ላይ ተቀምጠን ሳለ እንዲህ አሉ፡-
‹‹በአላህ ላታጋሩ፣ ዝሙትን ላትፈጽሙ፣ ላትሰርቁ፣ ነፍስን ያለ-አግባብ ላትገድሉ ቃል ግቡልኝ›› ከናንተ ውስጥ ቃሉን ሞልቶ የተገኘ ምንዳው በአላህ ዘንድ ነው፡፡…
ከነዚህ ውስጥ አንዱን የፈጸመ ሰው ደግሞ (በዱንያ) ተቀጥቶ ከሆነ ለአኼራ ማካካሻው ነው…
አላህ ደብቆለት ከሆነና ካልተቀጣ ደግሞ ጉዳዩ ወደ አላህ ይመለሳል፡፡ ከፈለገ ይምረዋል ከፈለገ ደግሞ ይቀጣዋል”።
📗(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
⚠️ ዝሙት ከባድ ማስጠንቀቂያ የመጣበት የባለጌዎች መንገድ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-
🟢 ۞ "ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ ብልግና ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ!"۞📖 ኢስራእ32)
⚠️ ዝሙት ኢማንን የሚያራቁት አደገኛ ወንጀል ነው። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-
"ዝሙት በሚፈፅመው ጊዜ ሙእሚን ሆኖ አይፈፅመውም።"📗(ቡኻሪና ሙስሊም)
እናንተ የሙሐመድ ህዝቦች ሆይ! ወላሂ እኔ የማውቀውን ብታውቁ ኖሮ ጥቂትን በሳቃችሁና ብዙ ባለቀሳችሁ ነበር።" 📗(ቡኻሪና ሙስሊም)
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
💬 አቡበክር አስ ስዲቅ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በአንድ ወቅት ባደረጉት ንግግር ይህን ብለዋል፡-
⚠️ ዝሙት በህዝቦች ውስጥ አይስፋፋም አላህ መከራ የለቀቀባቸው ቢሆን እንጂ።
⛔ እንደምታውቁት አሁን ባለንበት በዚህ ዘመን ዝሙት በጣም ተንሰራፍቷል። ወደ ዝሙት የሚገፉ ምክንያቶች በዝተዋል። ብዙዎች አላህን ከመፍራት ይልቅ ስጋዊ ስሜታቸውን በሐራም ማርካትን አስቀድመዋል
⛔ ጥፋቱን ለሚፈልጉ ሰዎች ሁኔታዎች በጣም ቀለዋል። ስለዚህ እባካችሁን ያላገቡ ልጆቻችሁን፣ እህት ወንድሞቻችሁን፣ ዘመድ ጓደኞቻችሁን ትዳር እንዲመሰርቱ አመቻቹ፣ አግባቡ፣ ወትወቱ፣ ጫና አድርጉ
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
⭕️ ሰው ነጻ ፈቃድ ያለው ፍጡር ነው
⚠️ ከአላህ ዘንድ አድርግ የተባለውን ትእዛዝ ለመፈጸምም ሆነ ለመተው፣ አታድርግ ተብሎ የታቀበውንም ነገር ለመራቅም ሆነ ለመዳፈር የሚያስችለው ምርጫና ውስን አቅም ተሰጥቶታል።
⛔ አላህ ትዳርን ፈቅዶ ዝሙትን መከልከሉ፣ ንግድን ፈቅዶ ወለድን መከልከሉ፣ ውሀና መሰል መጠጦችን ፈቅዶ መጠጥና አስካሪ ነገሮችን በመላ መከልከሉ ፈተና ነው። ለማድረግም ሆነ ለመተው ነጻ ፈቃዱ ተሰጥቶሀል።
⚠️ አላህ በቁርኣን ውስጥ አማኝ ባሪያዎቹን ሲያወድሳቸው ከፊል ባሕሪያቸውን በማውሳት ነው፡፡ ከነዚህም ባሕሪያት መካከል አንዱ ‹‹ከዝሙት የራቁና ብልቶቻቸውን የጠበቁ›› መሆናቸውን በመግለጽ ነው፡፡ ቁርኣን እንዲህ ይላል፡-
🟢 ۞ "ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)….እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት (አገኙ)፡፡" ۞ (📖 ሱረቱል ሙእሚኑን 1–5)
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
⚠️ የአላህ ባሮች ሆይ፣ እራሳችንንም ከዝሙት እናቅብ፣ ለሰራነውም ዝሙት ከልብ እንጸጸት፣ ዳግመኛ ወደሱ ላለመመለስም ቁርጥ ሃሳብ እንወስን፣ ከዛም ጌታችንን ምህረቱንና ይቅርታውን እንለምን
🟢 ۞ "አላህ እርሱ ከባሮቹ ንስሐን የሚቀበል፣ ምጽዋቶችንም የሚወስድ መሆኑን አላህም እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ መሆኑን አያዉቁምን?" ۞ (📖 ሱረቱ-ተውባህ 104)
⭕️አላህ ይምረኝ ይሆን? ብሎ ማሰብና ተስፋ መቁረጥ የለብንም፣ አላህ እንዲህ ይላል
🟢 ۞ "«በእውነት አበሰርንህ፡፡ ከተሰፋ ቆራጮችም አትኹን» አሉ፡፡ «ከጠማማዎችም በስተቀር ከጌታው እዝነት ተስፋን የሚቆርጥ ማነው» አለ፡፡" ۞ (📖 ሱረቱል ሒጅር 55-56)
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
⚠️ ትክክለኛ ተውበት ካሰብንም ሊታየን የሚገባው የጌታችን አላህ የራሕመቱ ስፋት እንጂ የወንጀላችን መብዛትና መክፋት አይደለም
📗በሀዲሱል-ቁድሲይ ላይ አላህ በነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) አንደበት ሲያናግረን፡-
"….የአደም ልጅ ሆይ! ወንጀሎችህ ተከምረው ሰማይ ጣሪያ ቢደርሱና ከዛም ጌታዬ ሆይ! ማረኝ ብለህ ብትጠይቀኝ ምንም ሳይመስለኝ እምርሀለሁ”። 📗 (አል-ጃሚዑ ሰጊር 6065)
⚠️ ወደ ዝሙት ሊገፋፉ፣ ሊነሽጡ፣ ሊወሰውሱ የሚችሉ ነገሮች ሁሉ አትቅረቡ፣ አላህ ይጠብቀን
🗓️ በቀጣይ ፖስት ከዝሙት መጠበቂያ መንገዶች እናኛለን ኢንሻ’አላህ
🔹🔹🔹🔸🔸🔸
📨 ይህን መልእክት ለእህት ወንድሞች ሼር ያድርጉላቸው
ወደ ቅን መንገድ የተጣራ ሰው፣ የተከተሉት ሰዎች ሁሉ የሚያገኙት አጅር ምንም ሳይጎድልባቸው ለሱም ይኖረዋል…" (ቡኻሪና ሙስሊም)
#ካሊድ ዘመን
ያስነጠሰ ሰው አላህን ካመሰገነ ከአላህ እዝነትን ለምኑለት! ካላመሰገነ ግን...
وعن أَبي موسى رضي الله عنه، قَالَ: سَمِعْتُ رسول الله صلى الله عليه وسلم، يقولُ: إِذَا عَطَسَ أحَدُكُمْ فَحَمِدَ اللهَ فَشَمِّتُوهُ، فَإنْ لَمْ يَحْمَدِ الله فَلاَ تُشَمِّتُوهُ [رواه مسلم]
የአላህ መልእክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ተከታዩን ሲናገሩ ሰምቺያለው በማለት አቡ ሙሳ(ረዲያላሁ አንሁ) አሰተላልፈዋል፦
”ከእናንተ አንዳንቹ ሲያስነጥስ አላህን ካመሰገነ ከአላህ እዝነትን በመመኘት መልሱለት። አላህን ካላመሰገነ አትመልሱለት።” [ሙስሊም ዘግቦታል]
عن أَبي هريرة رضي الله عنه، عن النبيِّ صلى الله عليه وسلم،
قَالَ: إِذَا عَطَسَ أحَدُكُمْ فَلْيَقُلْ: الحَمْدُ للهِ، وَلْيَقُلْ لَهُ أخُوهُ أَوْ صَاحِبُهُ: يَرْحَمُكَ الله. فإذَا قَالَ لَهُ: يَرْحَمُكَ اللهُ، فَليَقُلْ: يَهْدِيكُمُ اللهُ وَيُصْلِحُ بَالَكُمْ [رواه البخاري]
አቡ ሁረይራ(ረዲያላሁ አንሁ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)እንዲህ ብለዋል፦
"ከናንተ አንዳቹ በሚያነጥስ ጊዜ 'አልሐምዱ ሊላህ' (ለአላህ ምስጋና ይድረሰው) ይበል፡፡ ወንድሙም 'የርሐሙከላህ አላህ ይዘንልህ) ይበለው፡፡ እርሱም መልሶ 'የህዲኩሙላህ ወዩስሊሕ ባለኩም' (አላህ ቅኑን መንገድ ይምራቹ፣ ጉዳያቹንም ያስተካክልላቹ)' ይበል፡፡ [ቡኻሪ ዘግበዉታል]
ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን
Click and like
በቴሌ ግራም ለመከታተል
https://t.me/islamictrueth
በቲክቶክ ለመከታተል
tiktok.com/@sadamsuleyman
በወርድ ፕረስ ለመከታተል
https://wincdaawa.wordpress.com
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago