Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

Bekulu Entertainment

Description
ትኩስ መረጃወች በየደቂቃ የሚለቀቁበት channel እዲሁም:-
፠ አጫጭር ታሪኮች
፠ስፖርት እና ወቅታዊ ጉዳዮች ይዘገቡበታል።

https://t.me/joinchat/AAAAAEdTBZdXx8xrHyomTg
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info_bot
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 day, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 3 days, 13 hours ago

Last updated 2 months ago

9 months, 3 weeks ago

https://youtu.be/suh8OCoGFbQ

YouTube

ባንኮች ሻውር በብድር መስጠት ጀመሩ 2023 @BekuluEntertainment #funny #entertainment #entertainment

Welcome to our channel this is official bekulu entertainment youtube channel if you subscribe our channel you get more benefit entertainment news ,standup comedy ,music , short comedy movies ….all entertainment are available in our channel subscribe now …

1 year ago
Bekulu Entertainment
1 year ago
1 year, 3 months ago

https://youtu.be/8EfiNyCBR-M

YouTube

ጆሮ የሌለው እንስሳ መ*ግስት ........2023@BekuluEntertainment @MikoMikee @seifuonebs @ArtsTvWorld

1 year, 3 months ago
Bekulu Entertainment
1 year, 3 months ago

https://youtu.be/qMJvbGH2d7A

YouTube

የሙዙ ዛፍ ለካ ፖለቲካ ነው Ethiopia Comedian Zedo 2023

1 year, 4 months ago
**ከአርባ በላይ የአማርኛ ፊልሞች ላይ የተወነው …

ከአርባ በላይ የአማርኛ ፊልሞች ላይ የተወነው ተዋናይ ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በድንገተኛ ህመም ዛሬ ጠዋት አርፏል ።

ተዋናዩ ካባለቤቱ የፊልም ተዋናይት
ቃልኪዳን ጥበቡ ጋር ከተለያየ በኋላ ድብርት ተደጋግሞ ያጠቃው እንደነበር ፊደል ፖስት ከቅርብ ወዳጆቹ ሰምቷል።

ዕድሜው በሰላሳዎቹ አጋማሽ የሚገኘው ተዋናይ ታሪኩ ተውልዶ ያደገው ተክለ ሐይማኖት አካባቢ ሲሆን የአንድ ልጅም አባት ነው።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝናን አና በብዙዎች ተወዳጅነትን ያተረፈ ተዋናይ ነው። በጉዳዬ ፊልም ላይ ደግሞ በድርሰት ፣ በዳይሬክተርነት እንዲሁም በትወና ተሳትፎበታል።

ከተወነባቸው ፊልሞች መካከል :- 300ሺ፣ የፍቅር ABCD ፣ ብላቴና፣ ቦሌ ማነቂያ ፣ እንደ ባል እና ሚስት ፣ ኢንጂነሮቹ ፣ እርቅ ይሁን ፣ ኢዮሪካ ፣ ጉዳዬ ፣ ሀገርሽ ሀገሬ ፣ ሕይወቴ ፣ ህይወት እና ሳቅ ፣ ከባድ ሚዛን ፣ ፍቅር እና ፌስቡክ ፣ ከቃል በላይ፣ላውንድሪ ቦይ ፣ ኮከባችን ፣ ማርትሬዛ ፣ ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2 ፣ ሞኙ የአራዳ ልጅ ፣ ትዳርን ፍለጋ ፣ አንድ ሁለት ፣ ብር ርርር ፣ ወደው አይሰርቁ፣ ወፌ ቆመች፣ ወንድሜ ያዕቆብ ፣ እንደ ቀልድ ፣ ወቶ አደር፣ አባት ሀገር፣ የሞግዚቷ ልጆች፣ ይዋጣልን ፣ ዋሻው፣ ወሬ ነጋሪ ፣ ወጣት በ97 ተጠቃሽ ናቸዉ።

#የኔቲዩብ ለአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅና አድናቂዎች መፅናናትን ይመኛል።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info

1 year, 5 months ago
**ለአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የኮማንደርነት ማዕረግ ተሰጣት!** …

ለአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የኮማንደርነት ማዕረግ ተሰጣት! የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ልዩ የኒሻን ሽልማት እና የኮማንደርነት ማዕረግ አበርክቶላታል፡፡

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በተሰማሩበት የሥራ መስክ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 78 የኮሚሽኑ ስፖርት ክለብ አባላት የማዕረግ፣ የገንዘብና የልዩ ኒሻን ሽልማት አበርክቷል፡፡

በሽልማት ፕሮጋራሙ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ልዩ የኒሻን ሽልማት የተበረከተላት ሲሆን በኮሚሽኑ የኮማንደርነት ማዕረግም ተሰጥቷታል፡፡

ኮማንደር አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በተሰጣት ሽልማት መደሰቷን ገልጻ በማረሚያ ቤት ስፖርት ክለብ ትንሽ ልጅ ሆና በመቀጠር አሁን ለደረሰችበት ደረጃ መብቃቷንም አንስታለች፡፡

ሽልማቱ የማረሚያ ስፖርት ክለብ ወጣት አትሌቶች ጠንክረው እንዲሰሩ፣ እንዲበረታቱና የተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ያደርጋል ያለችው አትሌቷ በተለያዩ የውድድር መስኮች የኮሚሽኑ አትሌቶች ውጤታማ መሆናቸውን ገልፃለች፡፡

ኮሚሽኑ ለ34 ስፖርተኞች ከረዳት ሳጅን እስከ ኮማንደር ድረስ የማዕረግ ዕድገት ሲሰጥ ለ19 ስፖርተኞች ደግሞ የገንዘብ እና ለ13 ስፖርተኞች የእርከን ጭማሪና የገንዘብ ሽልማት ሰጥቷል፡፡

ለአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የተበረከተው ልዩ የሜዳሊያ ሽልማት ከረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ቀጥሎ ለ2ኛ ጊዜ መሆኑን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info

1 year, 5 months ago
**በኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አማካኝነት ከ1.5 ሚልዮን …

በኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አማካኝነት ከ1.5 ሚልዮን ዶላር በላይ ተሰበሰበ!

ኮመዲያን እሸቱ መለሰ "በሀገረ አሜሪካ ለሚቋቋመው ግዙፍ ስፋት ያለው ገዳም ቦታ መግዣ" ከ 1,500,000 የአሜሪካ ዶላር በላይ በአንድ ቀን መሰብሰብ ችሏል።

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በአሜሪካ ካሊፎርኒያ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ ገዳም ሥም ከ1497 ሄክታር በላይ ስፋት ያለው መሬት ልትገዛ እንደሆነ ማስታወቋ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ለገዳሙ መግዣ የሚሆነው ቅድመ ክፍያ ገንዘብ ለማሰባሰብ ኮሜዲያን እሸቱ በትናንትናው እለት ባዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ከ15ሰአት በላይ በላይቭ(live) በመቆየት በአጠቃላይ ከ1.5ሚሊዮን ዶላር በላይ በማሰባሰብ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው የሆነውን ፈጣን የገቢ ማሰባሰብ ስራን አከናዉኗል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የሰሜን ካሊፎርኒያ፣ ኔቫዳ እና አሪዞና ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስም የገቢ ማሰባሰቡን ያካሄዱትን ኮሜዲያን እሸቱን እና የዶንኪ ቲዩብ አባላቶችን ከልብ አመስግነዋል።

በዚህ ሰፊ ይዞታ ላይም የአብነት ትምህርት ቤት፣ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ ዘመናዊ ዩኒቨርሲቲ፣ ሆስፒታል እንዲሁም ሌሎች በርካታ ተቋማትን ለማቋቋም እንደታቀደ የገለጹት ሊቀ ጳጳሱ፣ ለቦታው መግዣ የሚሆነውን 8 ሚሊዮን ዶላር ከምዕመናን ለማሰባሰብ እንደታሰበም ተናግረዋል።

Via:- Fidel Post
ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info

1 year, 5 months ago
**ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በነገው ዕለት ለህዝብ …

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በነገው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ  ይሰጣሉ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በነገው ዕለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች ማብራሪያ  እንደሚሰጡ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ነገ ኀዳር 06 ቀን 2015 ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ለኢዜአ ገልጿል፡፡

በመደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 30 ቀን 2015 ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተመላክቷል።

በዚህም ምክር ቤቱ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል፡፡

በዕለቱ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙም ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃና ጥቆማ በዚህ ላኩልን፡፡
@ethio27info_bot @ethio27info

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 day, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 3 days, 13 hours ago

Last updated 2 months ago