ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
የውልደት ቅደም ተከተልና ባህርይ | Birth order traits
🔶 አልፍሬድ አድለር በ20ኛው ክፍለ ዘመን የራሳቸውን አሻራ ካሳረፋ ጉምቱ የስለ-ልቡና ባለሙያዎች አንዱ ነው::
🔶 አድለር የ Individual psychology መስራች ሲሆን:: በዚህ አስተምህሮውም የተለያዩ ሃሳቦችን ያነሳል::
🔶 ለጊዜው ስለ ውልደት ቅደም ተከተልና የባህርይ ምልከታው በተወሰነ መልኩ እንዳስሳለን::
🔶 እንደ አድለር ገለጻ: የልጆች ባህርይ እንደ ውልደት ቅደም ተከተላቸው ይለያያል::
🔷 የበኩር ልጆች
▫️ሌላ ወንድም/አህት ሲወለድለት የባህርይ መለወጦችን ያሳያል::
▫️ ምናልባትም ብቸኛ በሆነበት ሰአት የነበሩት ትኩረቶች ስለሚቀሩበት:: ይህ ሁነት ለአለም ያለውን ምልከታም ይቀይረዋል::
▫️ለምሳሌ ወላጆቹ 3 አመት ከሞላው በኋላ ሌላ ልጅ ቢወልዱ: ይህ ልጅ self centered (ግለኛ) የሆነ አኗኗር አዳብሮ ከሆነ: አዲስ ለተወለደው ልጅ ጥላቻ ሊያድርበት ይችላል:: ይህ ባህርይው ግን ቀስ በቀስ እየተስተካከለ የመሄዱ ነገር ከፍተኛ ነው:: ይህ ነገር ከሶስት አመቱ በፊት ቢሆን ግን የጥላቻና የበቀል ስሜቱ የሚመነጨው Unconsciously (በደመነብስ) ስለሆነ: ለመቀየር አዳጋች ሊሆንና አብሮት የማደግ እድሉ ከፍ ያለ ይሆናል:: (ምናልባት አራርቆ መውለዱ አንዱ ጥቅሙ ይህ ይሆን?😏)
▪️በጎ ባህርያት- ታታሪነት: ሌሎችን የመንከባከብና ከችግር የመከላከል ሃላፊነትን ይወስዳሉ፣የማስተባበር አቅማቸው ያየለ ነው::
▪️አሉታዊ ባህርዮቻቸው በጭንቀት የተወጠሩ፣ ከፍ ያለ ልዕልናን የሚሹ፣ ደመነብሳቸው ነውጠኝነት የታከለበት፣ ተቀባይነትን ለማግኘት የሚታትሩ፣ ሁሌም ሌሎች ተሳስተው ነው እንጂ እኔስ ትክክል ነኝ ባዮች፣ ወቀሳን የሚያበዙ እና ለመተባበር እምብዛም ፈቃደኛ የማይሆኑ ሁነው ሊገኙ ይችላሉ::
🔶 አማካይ ልጆች-
▫️ የተሻለ ተነሳሽነት ያላቸው እና ከማህበረሰቡ ጋር ስሙም ሁነው የማደግ እድላቸው ከፍ ያለ ይሆናል::ባህርያቸው በተወሰነ መልኩ ታላቃቸውን በማየትና: ታላቃቸው ለነሱ በሚያሳየውን አመለካከት ተመስርቶ ይቃኛል:: ለመተባበር የማይታክቱ: ፋክክራቸው የተመጠነ ይሆናል::
▫️ምናልባት ታላቃቸው ጥላቻንና በቀልና እያሳያቸው ካደጉ: ሃይለኛ ተቀናቃኞች: በነገሮች በቀላሉ ተስፋ ሊቆርጡ የሚችሉ ሊሆኑ ይችላሉ::
▫️ ብዙውን ጊዜ ግን ከማህበረሰቡ ጋር የተስማሙ: ጤናማ የሆነ ፋክክር የሚያሳዩ ልጆች የመሆን እድላቸው ከፍ ያለ ይሆናል ይለናል::
🔶 የመጨረሻ ልጆች-
▫️እነዚህ ልጆች ቅምጥል ሁነው ስለሚያድጉ ይህ አስተዳደጋቸው ለችግር ተጋላጭ ሲያደርጋቸው ይስተዋላል::
▫️ከችግሮቻቸው መሃል: የበታችነት ስሜት: ጥገኝነት እና ነጻ ሰዎች እንዳልሆኑ የማሰብ ስሜት ሊያስቸግራቸው ይችላል::
▫️ በሌላ ጎኑ ደሞ ተስፈኞች እና ተነሳሽነት ያላቸው ስለሚሆኑ ባለ ልዩ ተሰጥኦ አትሌቶች: ግሩም ሙዚቀኞች እና ታታሪ ተማሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ ይለናል::
አሉታዊ ባህርያቶቻቸው- የተቀማጠሉ እና ጥገኞች ሆነው ሊገኙ ይችላሉ:: በሁሉም ነገር ለመላቅና ከልክ በላይ የሆነ ተስፈኝነት ሊታይባቸው ይችላል::
🔶 ብቸኛ ልጆች-
▫️እነዚህ ልጆች የሚፎካከሩት ወንድም ወይንም እህት የላቸውም:: ተፎካካሪነታቸው ከወላጆቻቸው ጋር ይሆናል:: የወላጆች ግብረ መልስ ለባህርያቸው እጅግ ወሳኝ ነው::
▫️በወጣትነት ዘመናቸው የተጋነነ የእችላለሁና የበላይነት ስሜት ያላየው: ለራሳቸው የሚሰጡት ግምት የተጋነነ ይሆንባቸዋል:: በዚህም ምክንያት ተባባሪነት እምብዛም የማይታይባቸው:: ጥቅመኞች እና የሌሎችን ክብካቤ አጥብቀው የሚሹ ሊሆኑ ይችላሉ::
በመልካም አስተዳደግ ታንጸው ካደጉ ደሞ በማህበረሰቡ ዘንድ የበሰሉ ሁነው ሊገኙ የሚችሉበት አድል ይኖራል::
ቸር ይግጠመን!
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው: የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት
https://t.me/DrEstif
https://www.facebook.com/DrEstif
መጽሃፍ የማንበብ እና የመወያየት ፍላጎቱ ያላችሁ ተቀላቀሉን
4ቱ ከኦቲዝም ጋር በተያያዘ የተፃፉ መፅሐፍት
እነዚህ መፃሕፍት በሁሉም ማኅበረሰብ ሊነበቡ የሚገቡ ናቸው። በተለይም ወላጆች፣ ልዩ-ልዩ ባለሞያዎች በትኩረት አንብበው ግንዛቤያቸውንና ዕውቀታቸውን ሊያሠፋ ይገባል።
1. 👁ኔን ተመልከተኝ
ጸሐፊ፦ በዶ/ር ዮናስ ባሕረጥበብ
2. ሁሉም በአንድ ( ተግባር-ተኮር የሕክምና መፅሐፍ )
ጸሐፊ፦ በእጩ ዶክተር መዓዛ መንክር
3. የኦቲዝም ምስጢሮች
ጸሐፊ፦ በዶክተር ሐዲያ ይማም
አርታዒ፦ ጋዜጠኛ መላኩ ብርሃኑ
4. በኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖሩ ልጆች እንድናውቃቸው የሚፈልጓቸው 10 ነገሮች
ተርጓሚና አዘጋጅ፦ በወ/ሮ ትዕግስት ኃይሉ
አርታዒ፦ እዝራ እጅጉ
ዋኖስ መስፍን (@WanosMesfin)
የልዩ-ፍላጎት ትምህርት ባለሞያ
Paraphillia/አፈንጋጭ ወሲባዊ ስሜቶች
Para- Next to
Phillia- Love
በዚህም መሰረት Paraphilia ማለት 'ከተለመደው ያፈነገጠ የወሲብ ስሜት' የሚል አንድምታ ይኖረዋል::
Diagnostic and Statistical Manual በ አምስተኛው እትሙ ስምንት የ Paraphilia Disorder/አፈንጋጭ የወሲብ ስሜት አይነቶችን አካቷል::
እነዚህም:-
1- Exhibitionistic disorder:- ሃፍረተ ገላቸውን ለእንግዳ ሰዎች በአደባባይ ማሳየት የሚወሰውሳቸው
2- Pedophilic disorder- ለአቅመአዳም/ሄዋን ያልደረሱ(ማለትም ከ13 አመት በታች በሆኑ) ሰዎች ላይ የፍትወት ስሜት የሚያይልባቸው
3- Voyeuristic disorder:- ሌሎች ሰዎች እርቃናቸውን ሲሆኑ ወይንም ወሲብ ሲፈጽሙ በመመልከት የፍትወት ስሜታቸውን የሚፈጽሙ
4- Fetishistic Disorder:- ግዑዝ ነገሮችን(እንደ ውስጥ ልብስ፣ ጡት ማስያዣ...) በመጠቀም የፍትወት ስሜታቸውን የሚፈጽሙ
5- Transvestic disorder:- እንደ ሌላ ጾታ በመልበስ የፍትወት ስሜታቸውን የሚፈጽሙ
6- Sexual Sadism Disorder :- ሌሎችን በማሰቃየት የፍትወት ስሜታቸውን የሚፈጽሙ
7- Sexual Masochism disorder :- ሌሎች እንዲያሰቃዩዋቸው በማድረግ የፍትወት ፍላጎታቸውን የሚፈጽሙ
8- Frotteuristic Disorder- ሰዎችን ካለፈቃዳቸው በመታከክ የፍትወት ፍላጎታቸውን የሚፈጽሙ
በፊት ላይ Homosexuality እንደ አንድ Paraphiliac Disorder ይቆጠር ነበር:: ከ1973 ጀምሮ ግን ከአዕምሮ ህመሞች ዝርዝር እንዲወጣ ተደርጓል::
ይህን ሃሳብ የሚሞግቱ ብዙዎች አሉ:: በዚህ ፍላጎታቸው ምክንያት የተለያዩ ማህበራዊ እና ስነልቦናዊ ጫናዎች የሚያጋጥማቸው ሰዎች ካሉ እና ወደህክምና ከመጡ: ችግራቸው ቢያንስ 'Culture Bound Syndrome' በሚለው ስር ተካቶ መታየት ይኖርበታል በማለት::
በቀጣይ ለ Paraphila ምክንያት ናቸው ተብለው ስለሚታሰቡ ስነህይወታዊ እና ስነልቦናዊ እሳቤዎች የምናይ ይሆናል::
አሻም አሻም!
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት
ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ይወዳጁ:-
Facebook:- https://www.facebook.com/DrEstif
Telegram:- https://t.me/DrEstif
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana