Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

ግጥምና ታሪኮች

Description
በዚ Channel ★የራሴን የግጥም ስራዎችና በሌሎች ገጣሚያን የተሠሩ አሪፍ አሪፍ የግጥም ስራዎች★ እንዲሁም ተከታታይ መሳጭ ታሪኮችየምታገኙ ይሆናል አብራቹኝ ሁኑ★ግራፋክስ ዲዛይን ማሰራት የምትፈልጉ @darkniha ላይ አውሩን

★ Anything አስተያየት እና ሀሳብ ካለዎት💛 for any comment
@darkniha
@dark_niha_bot
@Hanan_Akmel
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 days, 17 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 week ago

Last updated 1 week ago

3 weeks, 2 days ago
3 weeks, 5 days ago

♡ዩስራ♡😍**

☆ፀሐፊ፦ ኢፍሩህ

《ክፍል 6》**
ሱቅ ደርሼ ብድሩን ልከፍል ስል ብሩ አልሞላልኝም ግን ዛሬ ግዴታ ብር ያስፈልገኛል  ባለ ሱቁን የበፊቱን ሙሉ እንዳላመጣሁ እና ዛሬም እንደሚያስፈልገኝ ስነግረው እንደማይሰጠኝ እና ከሰጠኝ ነገ ብድሩ እንደሚበዛብኝ ነገረኝ ምን ላርግ ባዶ እጄን በህመም ወደምትሰቃየው እናቴ ልሂድ አይኖቼ በእንባ ተጋርደዋል   ልሄድ ወደ ሁዋላ ስዞር የቅድሟ ልጅ ከሁዋላዬ ነበረች... ምን ሆንክ አለችኝ ለማውራት እንባዬ እንዳይወርድ እየፈራሁ.... ምንም.... አብሽር አንተ ባታውቀኝም እኔ አውቅሀለው  ጠብቀኝ አብረን እንሄዳለን ብላኝ ወደ ሱቅ  ሄደች ከዛ ጠራችኝ እሺ ብዬ እኔም ወደሷ ሄድኩኝ ባለ ሱቁ የፈለኩትን እንድወስድ ነገረኝ እንዴ ለምን ስለው እሷ ቀጠል አርጋ አብሽር ነገ እኔ አመታለታለሁ ስትለኝ በቃ ምን ልበልሽ አላህ የላከልኝ መለይካ ነው የመሰለችኝ ለእራት እና ለቁርስ የሚሆን ዕቃ ወስጄ  አብረን መንገድ ጀመርን.

ካልተሳሳትኩ የዑስታዝ ቢላል ልጅ ነህ ማለቴ አላህ ይራህማቸው እና ከአመታት በፊት ነው ወደ አኪራህ  የሄዱት ልጅ ብሆንም  አስታውሳለሁ በጣም ምወዳቸው ኡስታዜ ነበሩ..... አው አላህ ይራህመው ግን እኔን እንዴት አወቅሽኝ?.... የሳቸው ልጅ እንደሆንክ ያወኩት ከአንድ ዓመት በፊት መርከዝ ወንድሜን ለመጠየቅ ስሄድ የሱ ቅርብ ጕደኛ እንደሆንክ ነግሮኝ ነው ግን አንተ የመርከዝ ትምህርት ሳትጨርስ ነው ከመርከዝ  የወታሄው  ከዛ ቡሃላ ትምህርት ቤት አየሁክ እምምም በጣም ጎበዝ ተማሪ ነህ ካንተ ቀጥዬ ደረጃዉን የያዝኩት እኔ ነኝ  ለማንኛዉም በስሜ ታውቀኝ ይሆናል  ዩስራ  ጂሃድ እባላለሁ   ያንተን ባትነግረኝ  ጃሲም ቢላል ነዋ? አው ንግግሯ ሁሉ በፈገግታ የታጀበ ነበር.... እምም አው   እሺ ግን ቁማር ለምን ማለቴ ትምህርት ትተህ ቂርዓት አቁመህ ወደዚህ ነገር ለምን ገባህ? ባጭሩ ንገረኝ

እህህህ ምን መሰለሽ የታመመች እናት አለችኝ እሷን ለማሳከም ደሞ ብር ያስፈልገኛል ሸክም እና ሊስትሮ በየቀኑ መድሃኒት እና ምግብ አይችልልኝም ቁማር ግን በደንብ ስለማገኝ ይችልልኛል በቃ አለ አ በየቀኑ ባይሆንም የተበላሁ ቀን ተበድሬ ነው ምገዛላት ለዛ ነው ከምወደው ትምህርቴ እና ቁርአን ቤት የተባረርኩት....
እና እናትህ አሁንም ተኝተዋል? አው ለሷ ነው ይሄን የገዛሁት መድሃኒቱን ቅድም ስለገዛሁ አሁን ምግብ ነው.... እሺ ፍቃደኛ ከሆንክ አብሬህ ሂጄ ልዘይራቸው? መርሃባ ትችያለሽ  ወደቤታችን ምወስደንን መንገድ እንዲሁ በወሬ ጠምዳኝ ቤት ደረስን

ወደ ውስጥ ገብታ እናቴን ዘይራት ወድያው ቦርሳዋን አስቀምጣ ተነሳች  እ ወዴት ነው... አረ የትም ቤቱን አብረን እናፅዳ?... አረ እኔው አፀዳለሁ ተቀመጭ.... አይ ችግር የለዉም አታስብ.. ብላ ቤቱን አብረን አፀዳድተን ምግቡንም አብረን ሰርተን ለዑሚ መድኃንቷን ሰጥችቻት እሷን ለመሸኘት ወጣሁ

በቃ ልክ እህት እንዳገኘው ተሰማኝ ዛሬ ያወቀችኝ ሳይሆን አብረን ያደግነን ነው የምንመስለው እስከሰፈር ሸኝቻት እዛ ስንደርስ ጠንቀቅ በል ልጁን ቅድም በደንብ ስለመታሁት ቂም ይዞ እዳይመታህ እራስህን ጠብቅ ጥዋት እመጣለው ደህና ደር እናትህንም ኢንሻ አላህ እናሳክማታለን ብላኝ ተሰናብታኝ ወደ ቤቷ ሄደች ወደ ቤት ስመለስ እናቴ የት ነው ምታውቃት እቺን ቆንጅዬ ደሞ እንደስሟ ዩስራ ናት  እ ብላ ጥያቄ ስታቀርብ አይ ትምህርት ቤት ጕደኛዬ ናት  ብዬ ባጭሩ አለፍኩአት ምክንያቱም ለሷ ብዬ ትምሮ እና ቂርዓት ማቆሜን እንድታውቅ አልፈለኩም እሷም ብዙ ሳታፋጥጠኝ መድሃኒቱ ስለሚያስተኛት ተኛች

በንጋታው ዩስራ ቃሏን ጠብቃ ቤት መጣች እናቴን ከዘየረቻት ቡሃላ ሀኪም ቤት እንድንወስዳት ነገረችኝ ብሩንስ? አባቴ ውጪ ለይ ነው እሱ ይሸፍናል አለችኝ  ወይኔ እንዴት እንደተደሰትኩ ብታይልኝ  ..... ተዋ ስሜን ሰርቃለች እኮ ዩስራ በንግግሩ ጣልቃ ገባች... ዝም በይ ያለዝያ አልነግርሽም... እህህህ ይሄን ሁሉ ሄደን አልነግርሽም ልትለኝ ነው የምር ለከሊል ነው ምነግርልህ... ኡፍ እሺ በቃ ዝም በያ... እሺ ልብ ሰራቂ ፈገግታዋን ለገሰችው..

ይቀጥል የምትሉ 👍❤️

❯❯ ክፍል7 ይቀጥላል..........

3 weeks, 5 days ago

♡ዩስራ♡ 😍**

《ክፍል 5》

☆ፀሐፊ ኢፍሩህ**

አንድም ቦታ ሳትሳሳት ነበር የሰራችው አስተማሪው ምንም ሳይላት በመዋሏ ደስ አላት ጃሲም በትክክል እንደተከታተለችው ገብቶታል

ሳምንቱ ተጠናቆ ቅዳሜ ደረሰ የቅዳሜ ውሎ ከእናቱ ጋር ጀምረዋል እንደለመደው ጫማ እየጠረገ እና ዕቃ ለሰዎች እያደረሰ ውሎዉን እየገፋ ነው የዕለተ ደንበኛው ስትመጣ ያቀረበችለትን ጥያቄ እንደተቀበላት እና ነገ መጀመር እንደሚችል ነገሯት ዕቃዋን ቤት ካደረሰላት ቡሃላ ብሩን ተቀብሎ ወደ እናቱ ተመለሰ ለእናቱ ስለ ስራው ከነጋራት ቡሃላ ትንሽ ትካዜ ተጫነው... ጃሲም ልጄ አብሽር እሺ የ ዩስሪን ቃል ከግብ ለማድረስ ስትል ሁሉንም ታገስ እሺ የኔ ልጅ እኔም እኮ ፈልጌ አይደለም ቢሆንልኝ አንተ እንድትኖር ምፈልገው ህይወት ሌላ ነበር ግን አላህ ሁሉንም ሲያረግ በምክንያት ነው  ስለዚህ አልሃምዱሊላህ... ኡሚ ዩስሪን መርሳት አልችልም አሁንም ከጎኔ ናት እንደዛ ነው ሚሰማኝ...  ድንች ስጪኝ ወረያቸዉን  ያቋረጠው የገበያ ጥሪ ነበር

ዛሬ እሁድ ነው ዩስራ በጥዋቱ ከወንድሞቿ ጋር እየተጫወተች ነው ከሊል በባህሪው ቀለል ያለ ነው ከዩስራ ጋር መጫወት ያስደስተዋል ኢብራህም ኮስተር ያለ እና የታላቅነት ግርማ የተላበሰ ነው እነሱ ሲጫወቱ ቁጭ ብሎ እያያቸው ነው በመሃል እናቷ ጠራቻት  ኳሱን በእጇ ታቅፋ ወደ እናቷ አመራች.. ወዬ ማም.. ቡሃላ ዓንድ አስጠኚ ይመጣልሻል እና ከቤት እዳቶጭ.... እንዴ ማነው እሱ ማም.... ሲመጣ ታይዋለሽ በይ ሕጂ ተጫወቺ እሺ በቃ ማም እናቷን ግንባሯ ለይ ስማት ወደ ጨዋታዋ ተመለሰች  ከሊል ኳሱን እየተቀበላት... ምን አጠፋሽ ደሞ..... ባክህ ምንም አላጠፋሁም..... እና ለምንድነው የጠራችሽ.... አረ አስጠኚ ልትቀጥርልኝ ነው..... አይይይ የመጨረሻ ልጅ መሆን ታድለሽ..... ምነው.. እኛ እኮ አስጠኚ አልነበረንም.... ቢሆንስ እኔኮ ሴት ነኝ... Hhh እና.. እናማ ግድ ነው... አባቢ እንዳይሰማሽ... ማለቅያ የሌለው ጨቅጭቃቸዉን ኢብራህም በዝምታ እያዳመጠ ነበር

አስር ከተሰገደ ቡሃላ ጃሲም ወደ አዲሱ ስራው ለመሄድ ተዘገጃጅቶ ወጣ ውስጡ እየፈራ  ግብዉን አንኳኳ  የቤታቸው ዘበኛ በሩን  ከፈተለት ወደ ውስጥ እንዲገባ ከጋበዘው ቡሃላ የቤቱ ካዲም ለዩስራ እናት አስተኚው መምጣቱን ነገረቻት እናቷ ወደ ውስጥ ካስገባችው ቡሃላ ዩስራን ጠራቻት ዩስራ ከደረጃው እየወረደች ከሳሎን የተቀመጠው ጃሲም መሆኑን ስትመለከት አላመነችም እንዴ ምን ይሰራል ለራሷ እራሷን እየጠየቀች እነሱ ጋር ደረሰች... እህህህህ ጃሲም ሰላሙ አለይኩም... ዋለይኩም ሰላም ዩስራ.. እሱም በድንጋጤ አስተያየት ነበር ያያት...  እንዴ ታውቂዋለሽ እንዴ... አው ማም የክፍላችን ተማሪ እና የትምህርት ቤቱ  ሰቃይ ተማሪ ነው.... Oh ማሻአላህ በቃ እንዲያስጠናሽ ነው.... እሺ ማም በቃ በሉ ጃሲም ልጄ እንግዲህ በዚህ ዓመት ካንተ ቀጥሎ ሰቃይ ተማሪ እንደምትሆን ተስፋ አረጋለው በርቱልኝ ብላ ትታቸው ወጣች

ጃሲም እና ዩስራ ከትምህርም አልፎ የቂርዓት ሰዓት እያመቻቹ እያስቀራት ነው በትምህርቷም ጎበዝ ሁናለች ያስሚን ከትንሽ ጊዜ ቡሃላ ከዩስራ መራቅ አብዝታለች ብቻዋን ነው ሚመቻት ወደ ቤትም ብቻዋን መሄድ ጀምራለች የፀባይዋ መለዋወጥ ግራ የገባት ዩስራ ተጨንቃለች  ጃሲምን እንዲያናግራት ጠይቃዋለች  ነገር ግን ሰላም ነኝ ትንሽ ጊዜ ብቻዬን ልሁን ከሚል መልስ ውጪ ምንም ልትነግራቸው ፍቃደኛ አይደለችም ዩስራ እብደቷን በትንሹም ቢሆን ቀንሳዋለች ይበልጥ ደሞ ያስሚን ከሷ መራቋ እያሳሰባት ነው

ጃሲም ዓንድ ጥያቄ ልጠይቅህ... እምም ይቻላል... ለምንድነው ብዙ ጊዜ ምትተክዘው እና ዩስራ ሚባል ስም ስትሰማ ፊትህ ሚለዋወጠው.... ኡፍፍፍፍፍ እሱን ነገር ባናነሳው... እህህህ እህትህ አይደለው ንገረኛ... እሺ. ማለቴ ነግርሻለው... ግን.... ግን ሚባል ነገር የለም ንገረኝ በቃ... እህህህህ ዕለቱ ቅዳሜ ነበር እንደተለመደው የቁማር ጨዋታ ተጫውቼ ቁማሩን የበላሁት ልጅ ብሩን አልሰጥም ብሎኝ በጣም ተጣላን  በዛ ጊዜ የድብድብ ስልቱን ስለማላውቅበት ልጁ በጣም ደበደበኝ ቁማር ምጫወቱ ልጆች ልያላቅቁን አልቻሉም በመሃል ከየት መጣ ሳይታሰብ አንዲት ልጅ ልጁን ከኔ ለይታ ቅጥቅጥ አደረግችው ሁሉም ሰው እሷን ነበር ምያየው  እኔም በጣም ገርማኝ ነበር... ስንት ነው የበላሀው...50ብር.... አምጣ ብሩን ልጁ ከተኛበት እየተጎተተ ብሩን አውጥቶ ሰጠኝ..... ልጅቷ ወድያው እኔ እንደሄድ  ሄድ ነግራኝ እሷ ትንሽ እዛው ቆየች እኔም ብሬን ወስጄ የዑሚን ብድር ለመክፈል ወደ ሱቅ አመራሁ....

❯ ክፍል 6 ይቀጥላል..........😍****

[‍](http://axnegar.fahares.com/axnegar/6d5eaab1f07d540969d8a.jpg) **♡ዩስራ♡ ***😍***
3 weeks, 5 days ago

♡ዩስራ♡😍**

《 ክፍል 4》

☆ፀሐፊ፦ኢፍሩህ**
አይነጋ ነገር ነግቶ ወደ ትምህርት ቤት ሄደ ትላንት ቃል የገባዉን አልረሳም ዛሬ ዩስራን ያስጠናታል  ዩስራ ማይነጋ የመሰላት ለሊት ነግቶ በጥዋት ትምህርት ቤት ተገኝታለች   አንደኛው ክፍለ ጊዜ አስተማሪ ስላልገባ ጃሲም ልጆቹን ሲያስተምራቸው እና እርስ በእርስ እንዲማማሩ ሲመክራቸው  አሳለፉ  ሁለታኛው ክፍለ ጊዜም አስተማሪ አልገባም ጃሲም መጠበቅ ስላስጠላው ላይብረሪ ሄደ  ዩስራ እዛ መሄዱ ስለገባት ተከትላው ሄደች  ትላንት እሺ ስላላት በምልክት ነገረችው እና ጉዋሮ ወዳለው መናፈሻ ሄደች እሱም ተንስቶ አብሯት ሄደ  ቁጭ ብሎ እያስጠናት እሷም ቀልቧን ለጥናቱ ሰጥታ ስታዳምጠው ሳያስቡት ልጆች እረፍት ወጥተው ተመልሰው አራተኛው ክፍለ ጊዜ ተምረው አምስተኛው ተደወለ እሱንም አላወቁም በድንገት ሳያስቡት የትምህርት ቤቱ ኃላፊ  ሰይፉ ሲጠራቸው ሁለቱም እኩል ዞሩ እሱ መሆኑን ስታውቅ ምንም አልፈራችም ጃሲም ግን ደንግጦ ነበር

በ አምስተኛው ክፍለ ጊዜ እናንተ እዚህ ምን ትሰራላችሁ እ እሱንም ሁለታችሁ ብቻችሁን  ንገሩኝ  እ መምህር ይቅርታ  አስተናኝ ብላኝ ነበር እና በሁለት እና በአንደኛው ክፍለ ጊዜ መምህር ስላልነበረን ላስጠናት ወጥቼ ነው  አለው ዩስራ ምንም ሳትፈራ እየሳቀች  ትቸር ምነው ችግር አለው እንደ እያስጠናኝ ነበር ምክንያቱም ማትስ አስተማሪ ምያስተምረው ነገር አይገባኝም እሱ ደሞ ሁሌ ይሰድበኛል ለዛ ነው   ድጋሚ በትምህርት ሰዓት ውጪ እንዳላያቹ ለዛሬ አለፍያለው አንተ ደሞ መጨረሻ ዓመት ነው ብለህ ነው መሰለኝ አደብ እያጣህ ነው ተስተካከለ ምመክርህ ምወደው ተማሪ የዚህ ትምህርት ቤት ኩራት ስለሆንክ ነው ገባህ   አው ትቸር  አይለምደኝም  እሺ አንቺ ቀበጥ  አትረብሺኝ ዋ.   እሺ ትቸር እየሳቀች  ለዛሬው በደንብ ገብቶኛል በጣም አመሰግናለው መርሀባ ነገ በደንብ ሰርተሽ ማየት እፈልጋለው በደንብ ደጋግመሽ አጥኚ እሺ ወንድሜ...

እንደለመደችው  ያስሚን ጋር እየተመናቀረች ሄደች  ያስሚ የኔውድ... ወዬ ዩዬ .. አለሽልኝ..  እንዴ ዛሬ ደሞ ሁለቴ ሰላምታ ሳቀችባት  ባክሽ ተይ... እሺ ምንድነው  ቅድም እኮ አስተናኝ አሁን በደንብ ገንቶኛል.. እሺ ነገ ሲያነሳሽ እንዳታሳፍሪው  አረ አላሳፍረዉም ታያለሽ ባላኮራው  እሺ እናያለን እሺ     ጃሲም እናቱ ጋር ለመዋል ስላሰበ የመድረሳ ጕደኛዉን ጠርቶ   እንዲያስፈቅድለት ነገረው እሱም በእሺታ ተሰናብቶት ሄደ  ጃሲም ዙሁር ሰግዶ ምሳዉን ለእናቱም ለራሱም በሰሃን አርጎ ገበያ ሄደ  እዛ ሲደርስ እናቱ ትንሽ ፊቷ ተለውጦ ነበር እማ ምን ሁነሽ ነው እ  አረ ምንም  ልጄ ምንም አልሆንኩም እኮ  አይ እማ ፊትሽ ጥቁርር ብሏል ምን ተፈጥሮ ነው እ  ልጄ ዛሬም ንግድ የለም የሱቅ ብድር ዛሬ መግባት አለበት እኔ ደሞ እራስምታት አሞኛል  አለችው  እሺ እናቴ ተነሽ ግቢ እኔ ይሄን ሽጬ ብድሩን ከፍዬ መጣለው  እሺ ልጄ አላህ ያግራው ካልተሸጠም  ትተህ ና ብርዱ ከባድ ነው  እሺ ኡሚ ሕጂ አንቺ እኔ መጣለው እሺ በቃ አላህ ይርዳህ  ትታው ወደቤት አመራች

ጃሲም እቃዉን እንደምንም እሸጠ  ተሸካሚ     ለሚፈልጉ ሰዎች ዕቃ ቤት እያደረሰላቸው  ያገኘውን ብር እያየ ብድሩን ቢከፍል ለእናቱ እራት ገዝቶ ሚገባበትን ብር ማግኘት ስላልቻለ  እሱን እስኪያገኝ ቀኑ መሸበት እናቱ ተጨንቃ ነበር ጃሲም በሩን ሲያንኳኳ  በፍጥነት ከፈተችለት  ምነው ልጄ ለምን አመሸህ እ መግሪብ አለፈብህ እኮ አይ እማ እየተሰገደ ነው መስገድ እችላለው  እሺ ግባና ስገድ ብላ አሳለፈችው ጃሲም ቶሎ ወዱዕ አርጎ መግሪብ ከሰገደ ቡሃላ እናቱ ውሎዉን ጠየቀችው ብድሩንም እንደከፈለ እና  ለእራት ሚሆን ነገርም ይዞላት እንደመጣ ነገራት እናቱም በልጇ እየኮራች መርቃው እራት ልትሰራ ስትነሳ እኔ ሰራለው ስላላት ተመልሳ  ተኛች

ጥዋት ተምህርት ቤት  አንደኛው ክፍለ ጊዜ ማትስ ስለነበር የማትስ አስተማሪ እንደለመደው ዩስራን አነሳት ዩስራ ተዘጋጅታበት ስለመጣች ያለምንም ፍርሃት ተነስታ ወደ ብላክቦርድ አመራች   አሰራሩ ለይ ዓንድ ቦታ.....

Like 🙌

❯ ክፍል 5 ይቀጥላል..........

1 month, 3 weeks ago

♡ዩስራ♡😍**

《ክፍል...3》

ፀሐፊ.. ኢፍሩህ**

ሰኞ ጥዋት እንደለመደው ከፍጅር መልስ ለእናቱ እና ለራሱ ቁርስ ሰርቶ  የራሱን በልቶ እናቱ ስትነሳ እንድትበላ አስቀምጦላት ወደ ትምህርት ቤት አመራ  አረማመዱ ሰከን ያለ ነው መሮጥ መጣደፍ አይወድም ብዙ ከመናገር ብዙ ማዳመጥ ደስ ይለዋል     መግቢው ሲገባ ነበር ከዩስራ ጋር የተገጣጠሙት  ዩስራ ሰላም ይለኛል ብላ ብትጠብቅም እሱ ግን አልፏት ወደ ክፍል ገባ  ትንሽ እንደቆየ  አስተማሪ መጥቶ ክፍል ገባ ሁሉም ተማሪ ወሬ ይዟል ማንም አስተምሪውን ያስተዋለ የለም አስተምሪው ለማስተምር ያመጣቸዉን እቃዎች አስቀምጦ በወሬ ወደተጠመደው ጀምዓ አመራ  ዩስራ እና ያስሚን ምንም ሳያስተውሉ በተለያየ ርዕስ ይጨቃጨቃሉ  ... እሺ የኛ ወረኛ ክርክሩን ጨረሳችሁ? ሁሉም በድንጋጤ አንገታቸዉን ደፉ .... እ መምህር ይቅርታ አላየንም ነበር  ዩስራ እየተርበተበተች የተናገርችው ቃል ነበር.... እሺ ባክሽ አላየሽኝም መቼስ እንዴት እኔን ታይኛለሽ ስንት ሚታዩ ሚፈቀሩ ወጣቶች እያሉ.... እባብ መሳይ ምላሱን ዘረጋባት  ዩስራ በፀባይዋ  ወንድን ስለማፍቀር አታስብም መምህሩ እንዲህ ብሎ ስለተናገራት በጣም ተሰማት.... ንግግሩን አላቆመም ቀጠለ... አው አሁንማ አደጋችሁ ፍቅሬ ውዴ ማሬ ተብሎ የተላከዉን text እንጂ መች መፃፍ ትገልጡና እ   ዛሬ ስንቶች ናችሁ ቀጠሮ ያለባችሁ ምትቀባቡትን ይዛቹሃል?    .... ምላሱን አሁንም ቀጥሎዋል የማትስ አስተማሪያቸው በምላስ አይታማም

ጃሲም ከዚህ በላይ ሊታገሰው አልቻለም... ንግግሩን አቁዋረጠው... ይቅርታ አርግልኝ እና ግን ከነሱ ይልቅ አንተ ነህ ዝቃጭ እንዴት እነዚህን ሕፃናት በንደዚህ አይነት ነገር ታስባቸዋለህ እነሱ ቢያስቡት እራሱ መክረህ መመለስ እንጂ መሳደቡን ምን አመጣው? ቆይ መምህር ነህ  ውይስ መንገድ ዳር የሚዉሉ ወያላዎች እ ትንሽ አታስብም ልጅህ የት ናት እህትህ እናትህ  አክስትህ ሚስትህ  ሴት ልጅ ሁሉ ነገርህ ናት እንዲህ ሁሉ ነግርህን መሳደብ አይከብድም?   ለማንኛውም ግን ይህ ከመምህር አይጠበቅም  አመሰግናለሁ ብሎ ተቀመጠ መምህሩ ሌላ ንግግር ሳይጀምር ወደ ትምህርት አመራ    

ሶስቱን ክፍለ ጊዜ ጨርሰው እረፍት ሰዓት ደረሰ  ጃሲም ተነስቶ ወጣ ትንሽ ግቢው ውስጥ ሊራመድ ነበር እንደአጋጣሚ የቁርአን ቤት  ጕደኛዉን አገኘ... ሙአዝ. ለበይክ ጃሲም ወንሜ.... አሰላሙ አለይኩም... ዋለይኩሙሰላም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ... እንዴት ነህ... አልሃምዱሊላህ.. በዚህ መሃል ከሁዋላው  ሚጠራው ሰው እንዳለ ተሰማው ዙሮ ሲመለከት ዩስራ ነበረች... አቤት መጣሁ እህቴ... ብሎ ወደ ጕደኛው ዞር እኔ ምልህ ቡሃላ ትንሽ ላረፍድ እችላለሁ ኡስታዝ ዛሬም የሉም  ስለዚህ በጊዜ ሂድና ልጆቹን እያስቀራህ ጠብቀኝ... መርሀባ ኡስታዝ አብሽር... ኡስታዝ ለመባል አልደረስኩም አንተ እረፍ ፈገግ አለለት... እንደ ከዚህ በላይ አሁንማ ሸይክ ልልህ ነው ተሳሳቁ በል በቃ ብሎት ወደ ዩስራ አመራ  አይኑን ከመሬት ተክሎ... ለምን ነበር የፈለግሽኝ.... ይቅርታ ስምህን አላውቅም ግን ቅድም የተማርነው አልገባኝም... የትኛው ክፍለ ጊዜ?   ማትስ... እሺ እኔ ጃሲም እበላለሁ ኢንሻ አላህ ነገ ሰዓት ካገኘው አስጠናሻለሁ አሁን ተደውሏል ክፍል ልግባ.... እሺ እኔም ዩስራ እባላለሁ እና አመሰግናለሁ ብላ በደስታ እየተፍነከነከች ወደ ያስሚን አመራች

ያስሚ.. ፊቷ በደስታ በርቷል... ወዬ የኔ ፍልቅልቅ ምን ተገኝቶ ነው?   እስኪ ገምቺ ... እህህህህ ንገሪኝ እንጂ.... ጃሲም ጋር ተዋወቅን ነገ ማትስ ያስጠናኛል yesssss... እና ምንድነው እንዲህ ያፍነከነከሽ... ምክንያቱማ እራሱን ብቸኛ ያደረገበትን ምክንያት ማወቅ ነው ከዛ ሰዎችን እንዲቀርብ መምከር ነው ሌላ ምን ያፍነከንከኛል?  እሺ የኔዋ ዋናው ሃሳብሽ መሳካቱ ነው... እሺ እንደ ሕፃን  እየተጫወቱ ወደ ክፍል አመሩ  ቀሪዉን ክፍለ ጊዜ ተምረው ከጨረሱ ቡሃላ ወደ ቤት መግቢያ ሰዓት ያስሚን እና ዩስራ ተያይዘው እየተሳሳቁ ከክፍሉ ወጡ  ጃሲም እንደለመደው እርምጃዉን በእርጋታ  እየተራመደ ቤት ደረሰ ዙሁር ሰግዶ ምሳዉን ከበላ ቡሃላ  ለእናቱ ምሳ በሰሃን አርጎ እሷ ወደ ምትውልበት ገቢያ አመራ.... ኡሙ አሰላሙ አለይኩም ደህና ዋልሽልኝ... ዋለይኩም ሰላም አልሃምዱሊላህ የኔ ልጅ አንተስ... አልሃምዱሊላህ ኡሚ ዙሁር ሰገድሽ ... አው ሰግጃለሁ አልሃምዱሊላህ  እሺ  ምሳ ጉረሺ... መርሃባ ልጄ....

ምሳዋን ካቃበላት ቡሃላ እሱ ወደ መድረሳ አመራ

**❯❯ ክፍል 4  ይቀጥላል..........

🩵   ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ     🩵
@achacher ♡**

[‍](http://axnegar.fahares.com/axnegar/2893ba1fd6cb1be38de42.jpg) **♡ዩስራ♡***😍***
2 months, 1 week ago

♡ዩስራ♡ 😍**

《ክፍል 1》

☆ፀሐፊ.... ኢፍሩህ**

የክረምቱን ማለቅ አስከትሎ ትምህርት  ቤት ተለፍቷል   ተማሪዎች ትንሽ ቢሆኑም አስተምሪው የመጡትን እያስተማረ ነው   ጃሲም  እንደለመደው መጨረሻ ወንበር ለይ ብቻዉን ተቀምጧል    የማትስ አስተማሪ ከዚህ በፊት   11ኛ  ክፍል ለይ የተማሩትን   ፎርሙላ ለማስታወስ ያክል ድጋሚ እያስተማረ  ነው    ግማሽ ተማሪ ሞክሮ ግማሹ ጭራሽ ረስተውታል

እ... ማነህ እዛጋር መጨረሻ ብቻህን ምን ትሰራለህ?  አቤት መምህር እዚሁ ተመችቶኛል... ... እሺ ና እሄን ፎርሙላ ሥራልኝ  ደሞ አትዘንጋ መልሱ ይሄ መሆን አለበት አሰራሩን  11ኛ ክፍል እያላችሁ ተምራቹሃል... እሺ.. ከቦታው ተነስቶ ወደ ብላክቦርድ አመራ የታዘዘዉን በትክክል ሰርቶ ያጠናቀቅው እሱ ብቻ ነበር.. መምህሩ ይሄን ሲያይ በጉብዝናው እየተደሰተ... ያለፈው ዓመት ስንተኛ ወጣህ..... ጃሲም ሊመልስ ቀና ሲል ሌላ ድምፅ ቀደመው.....99.9%አምጥቶ እንደትምርት ቤቱ  1ኛ ነው የወጣው.... አረ ጎበዝ በርታ ጨርሰሃል ተቀመጥ... እሺ አሁን የሱን ውጤት የነገርሽኝ ልጅ ነይ ብሎ ጃሲም የሰራዉን አጠፋ.... ድጋሚ አሁን እሱ የሰራዉን ስሪ... እሺ ብላ የቻለችዉን ሞክረች ግን አልሆነም.... ስምሽ ማነው? መምህሩ በሥራዋ ተናዶ ነበር... ዩስራ.. ዩስራ ስምሽ ያምራል ግን አይምሮ አይሆንም ስለዚህ አይምሮሽን አሰሪው.... ጃሲም በአስተማሪው ንግግር ተበሳጨ... አስተማሪው ለዛሬ ጨርሰናል  ሃሳብ ማቅረብ ምትፈልጉ ብሎ ስጠይቅ ጃሲም እጁን አወጣ... እሺ ቀጥል ልስማህ.... በመጀመሪያ አመሰግናለሁ.. ቀጥሎ ግን ተማሪዎችን በዚህ መልኩ መናገር ተገቢ አይደለም የተማሪ ጭንቅላት የማሰብ እና የማስተዋል አቅሙ እያነሰ ይመጣል እና እሷን እንደተናገርከው ሌሎች ለይ እንዳትደግመው.... እሺ የኛ አስቃባጭ ዝጋ አርፈህ ተቀመጥ አስተማሪው ይህን ቃል ከአፉ ሲተፋ ጃሲም ከመቀመጫው ተነሳ ተማሪ በሙሉ አስተምሪዉን ሊመታው መስሎት ፈዞ እያያቸው ነው ጃሲም ግን አጠገቡ አልፎ ወደ ቢሮ አመራ

ቢሮ ደርሶ አስተማሪዉን ካስፈረመው ቡሃላ ወደ ክፍል ተመለሰ

ጃሲም ይባላል  የ 12ኛ ክፍል ተማሪ ነው  አባቱ በልጅነቱ ነበር ወደ አኪራ የሄዱበት እናት ብቻዋን ነው ያሳደገችው  ጃሲም   ሰው አይቀርብም ብከፋው ቢደሰት ቢናደድ ቢታመም ከእናቱ ውጪ ማንም አያውቅም ትምህርት ቤት ብቻዉን ይቀመጣል  ትምህርት እና ቂርዓቱ ለይ በጣም ጎበዝ ነው   ሰው አክባሪ ለትንሹም ለትልቁም ሚተናነስ ልጅ ነው አብዛሃኛዉን ጊዜዉን እናቱን በሥራ በማገዝ ያሳልፋል  የደሃ ቤት በፍቅር የደመቀ ጎጆ ነው ሲያገኙ በልተው ካጡም ትተው ያድራሉ ይውላሉ  የጃሲም እናት መርየም ጎበዝ ታታሪ ሰራተኛ ናት ሥራ አትንቅም ሁሉንም ትሰራለች ስራዋ ከዲኗ ጋር እንዲጋጭ አትፈቅድም

ጁን የትምህርት ቤት ቆይታዉን አጠናቆ ወደ ቤት መግቢያ ሰዓት ደረሰ ወደ ቤት ለመግባት መንገድ ሲጀምር   ሳያስበው የአንድ ተምሪ እግር ጠልፎት ወደቀ   ወይኔ ዩስራ ነበረች ደንግጣ   እንዴ ምን ሆናችሁ እያያችሁ ተራመዱ እንጂ... ይቅርታ አላየሁም... ይቅርታ ትላለህ እንዴ ልጁን በአፍጢሙ ደፍተሀው... ከወደቀበት ተነስቶ አቧራ እያራገፈ.. እህቴ ተያቸው አላዩም ይሆናል... አይ እያዩ እንዲራመዱ እየነገርቁአቸው ነው  አልተጎዳህማ? አይ አልሃምዱሊላህ ተርፍያለው.... እሺ..... መልሶ ልያያትም መልስ ሊሰጣትም አልፈለገም መንገዱን ቀጠለ

ዩስራ ግን ተበሳጭታ ነበር ምንም ቢሆም ሴት ልጅ ስትከራከርለት ወንድ ልጅ ችላ አይላትም ይሄ ግን ምን አይነት ነው ቆይ አውሬ ነው እንዴ ሁሌ ብቻዉን መሄደ መምጣት መቀመጥ ማጥናት ሁሌም
ብቸኛ... እና ለምን ተበሳጨሽ .. የ ያስሚን ጥያቄ ነበር... እህ ያስሚ ምን ሆንሽ ሰዎችን ቀርበን መረዳቱ ጥሩ ነው ብዬ አስባለው እኔ ደሞ የዚህ ልጅ ብቸኚነት ዝምብሎ የተፈጠረ ነገር አይመስለኝም ለዛ ልቀርበው አስቤ ነው.... ዩ ግን እኮ ቅድም ዩስራ ስትይ ፊቱ በጣም ተለዋወጠ የምር  ወድያ አይኑ ቀላ ብቻ እኔንጃ.... ማለት ስትይ?

❯❯ክፍል 2  ይቀጥላል..........

*🩵 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ   🩵
@achacher*

9 months ago

የሠርግ ማታ ባል ለሚስቱ የሰጠው ምክር||

የኔ ፍቅር ከእንግዲህ አንቺ ማለት ለኔ የመኖር ትርጉሜ ነሽ
በእኔ እና ባንቺ መሃል ከእንግዲህ ምንም አይነት ድብብቆሽ ሊኖር አይገባም።

የኔ ውድ በፊት እኔ ትልቅ ልጅ ነበርኩ አሁን ግን በድጋሚ ህፃን እሆናለሁ፣
ትዝ ይለኛል ህፃን እያለሁ ምግብ ባልቼ እንደሆነ ወይንም እርቦኝ እንደሆነ የምታውቃኝ እናቴ ነበራች
ጥዋት ከእንቅልፍ የምትቀሰቅሰኝ እናቴ ነበራች
ከቤት ከመውጣቴ በፊት መስተካከል ያለበትን ነገሮች አስተከክለ የምትሸናኝ እናቴ ነበራች

ከእንግዲህ ግን እናቴ አንቺ ነሽ
ከእንግዲህ የኔን ደካማ ጎን የምታውቅ ሌላ እናት የለችም
ከእንግዲህ ጥማቴን የምታውቅ ሌላ እናት የለችም
አየሽ ፍቅር ልጅ እያለሁ የሆንኩትን ነገር ሁሉ ለእናቴ ነበረ መጥቼ የምናግራት እሷም ምስጢሬን ለማንም ነግራ አታውቅም
አሁን ግን እናቴ አንቺ ነሽ ምስጢሬን የምነግርሽ ላንቺ ብቻ ነው
ለማንም ምስጢሬን አሳልፈሽ አትስጪ

ልጅ እያለሁ ብዙ ጥፋቶችን አጠፋ ነበረ እናቴም ለጊዜው በጣም ትቆጠኝ ነበረ ግን ቁጣዋ ብዙም አይቆይም ወዲያውኑ ተመልሳ መሳቅ ትጀምራለች
የኔ ፍቅር ምናልባት አንቺንም ሊያስከፋሽ እችላለሁ እባክሽን ግን ቂም አትያዥብኝ ጥፍቴን ግን አይተሽ ዝም አትበይ ምክር ስጪኝ እቀበላለሁ

የኔ ማር ወደ ጣፋጭ የአልጋ ጨዋታ ከመሄደችን በፊት ደግሜ የምነግርሽ ነገር ለሰዎች ወሬ በፍጹም ጆሮ አትስጪ
ከእንግዲህ ወዲህ ላንቺ ከእኔ የሚቀርብ ማንም ሊኖር አይችልም መኖር የለበትም።

የኔ ፍቅር የብዙ ሰዎች ትዳር መፍረስ ምክንያት ጎሮቤት አልያም የጓደኛ ብዛት ነው ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ከልክ በላይ አታቅርቢ

በፈጣሪ ፊት ቃል እገባለሁ እኔም ምርጡ አባትሽ ሁሌም ከጎንሽ መቆም የምችል ከማንም አስቀድሜ ለልጄ ለሚስቴ የሚል መልካም ባል እሆንልሻለሁ!!

የባል ምክር የተመቻው ብቻ ሼር ያድርግ

#ሼር_ሼር

9 months ago

😊🤦‍♂️

ማድቤት ናቸው።

ግን፦

ቡና እያፈሉ ፤ የሻይ ቅጠል እየቀቀሉም አይደልም።

ምግብ ለመስራት እየተጋገዙ ነው፤ እሱ ለመስራት ተዘጋጀ።

ፍርፍር ነው።

መጠበሻውን እሷ አጠበች ፤ እሱ ሊያለቀልቅ ተቀበላት።

ሽንኩርት ላጠ ፤ ሲከትፍ አይኑ እንባ አቀረረ ፤ ሽንኩርት በላጠው እጁ አይኑን ነካ፦

እንባው;
;

;

;
ዱብ አለ!፤ ቃሪያ ቢሆንስ ?!

ሚስኪን ፦ የሽንኩርቱን ልጣጭ ጆሮ ላይ ሲያደርግ።የእንባው ኔትወርክ ተቋረጠ። [ በሂጃቧ ጠረገችለት :) ]

ቀጠለ..ቲማቲም አዘጋጀ።

መጥበሻውን 'ስቶፍ ላይ አድርጎ ፤ ዘይት አድርጎ ሽንኩርቱ ጨመረ- አቁላላ ፤ ቲማቲም ፤ በርበሬ አደረገ።

በደንብ ሲቁላላ። የፈላ ውሃ በአናቱ ከለሰ።

ጨውም አልረሳም!

ሲንተከተክ፤ በስሱ አንድ ማንኪያ የቡና ዱቄት ፦ ይቅርታ አንድ ማንኪያ ሽሮ ማለቴ ነው፤ እላዩ ላይ ነሰነሰ።[ ውሃው ትንሽ! ብቻ እንዲወፍር ነው።]

ውሃው ላይ የተነሰነሰው ሽሮ በደንቡ ተንተክትኮ ሲፈላ ፤

አወረደ።

እንጀራ ጠቅልሎ ቆራርጦ ጨመረ።ጨረሰ።

እሷ ወደ ሳሎን ሄዳ ፤ የማዕድ እቃ አቀራርባ ፦አዘጋጅታ ምግቡ ቀረበ።

ታጠቡ።

" ቢስሚላህ " ብሎ! ጠቅልሎ በመጠኗ አጎረሳት።

" ቢስሚላህ! ሲጥም! " ፤ አለች። ፈገግ አለ!

ሊደግማት እጁን ዳግም ዘረጋ።

" ሀቢቢ አንተ-ም ጉረሳ" አለችው

" አይ አንድ ያጣላል ይሉ የለ ?! መጣላት ደግሞ ከኛ አያምርማ! ፤ አንድ ሰው ሲፆም 70,ዐዐዐ ሺህ ዓመት ከጀሃነም አንደሚርቀው ከኛ መሀል ፤ ከቤታችን ይራቅ! "

ሁለተኛ ደገማት።

ሁለት ያፋቅራላ፤ በሁለቱ መሀል ያለውን ፍቅር እና እዝነትን ጎልቶ ያሳያላ!

ሶስተኛ ደግሞ ፦ ምን ብሎ ያጉርሳት ?! ፤ ስትበላ የጠገበች አይመስለውም ፤

የሁለቱን ትስስር ጠንከር አድርጎ ፤ ፍቅራቸውን አጎልብቶ ይበልጥ የሚያቀራርባቸውን ድርጊት አሰበ።

" ታውቂያለሽ የኔ ውድ ? " እያለ..ጉርሻ ጠቀለለ

" ወዬ! "

" አንድ ሰው ሚስቱን ምግብ ሲያጎርስ፦ ሰደቃ ነው ፤ መፅዋት እያደረገ ነው። የሚል አስተምህሮት በኢስላም እንዳለ ታውቂ የለ ?! " አላት

ፈገግ ብላ ፦ ጎረሰችለት።

እሱም ለነገ ቤቱ፦ ለአኪራ-ትንሳኤ ስንቅን ሰነቀ! ።

እሷም፦

በተረዋ አጎረሰችው ፤ በሉም ፤ አል ሐምዱ ሊላህ" ሲሉ ምስጋናን አደረሱ።1

9 months, 2 weeks ago

እናት ልጃቸውን ለመጎብኘት ከወራት በፊት ወደተከራየው ኮንዶሚኒየም
ይሄዳሉ። ለወትሮው የሚያውቁት ዝርክርኩ ልጃቸው ቤቱ ጽድት ብሎ፣
እቃው
በስርዓቱ ቦታ ቦታውን ይዞ በማግኘታቸው በጣም ተገርመዋል። ከእዚያ
ባሻገር
የላጤው ልጃቸው ቆንጅዬ ጎረቤት ቡና አፍልታ፣ ምሳ አዘጋጅታ ቤቷ
ጠራቻቸው።
የልጂትና የልጃቸው ተግባቦት ከጉርብትና በላይ እንደኾነ የጠረጠሩት
እናት ወደ
ልጃቸው ቤት ሲመለሱ <<ዮኒዬ ሁለት የቤት ኪራይ ለምን? ለምን
ጠቅለኻት
አብራችኹ አትኖሩም?! በእዚያ ላይ ቆንጆ ናት፣ ባለሙያም ጭምር!>> ሲሉ
ቡራኬም ጥያቄም አከሉ።
<<እማ አንቺ እንደምታስቢው አይደለም። በቃ ጥሩ ጎረቤቴ ናት።
ግንኙነታችንም
የእህትና የወንድም ነው።>>
<<እህቶች ከቤት ሞልተውኻል አስብበት>> ብለውት ወደቤታቸው ሄዱ።
በሳምንቱ ቆንጆዋ ጎረቤቱ <<ስማማ ማዘር እዚህ ቤት ከመጡ በኋላ ከእኔ
አንተ
በቀር እዚህ ቤት የገባ ሰው የለም። ይኹንና ቤቴ ውስጥ የነበረውን አይ-
ፓድ
ብፈልገው ብፈልገው ላገኘው አልቻልኩም። ማሚ ትወስደዋለች ብዬ
አላስብም።
ምን ጉድ ነው የሰለበው?>>
<<እኔም ትወስደዋለች ብዬ አላስብም። ምናልባት የኔ መስሏት ለእህቶቼ
ሰርቃው
ከሆነ ሚሴጅ ልኬ በዘዴ እጠይቃታለሁ።>>
ብሎ ስልኩን አውጥቶ ወደ እናቱ መልእክት ይጽፍ ጀመር። <<እማ አንቺ
የጎረቤቴ
ቤት ምሳ ከተጋበዝሽበት ቀን አንስቶ አይ-ፓዷ ከቤቷ መጥፋቱን
ነግራኛለች።
<ሌባ ነሽ አንቺ ነሽ የወሰድሽው> ብዬ እየከሰስኩሽ አይደለም። ብቻ
እቃው
ስለመጥፋቱ ልንገርሽ ብዬ ነው።
እወድሻለሁ - ያንቺው ዮኒ>>
እናት ከልጃቸው የተጻፈላቸውን መልእክት አንብበው ሲጨርሱ ስልካቸውን
አንስተው መልእክት መጻፍ ጀመሩ።
<<ውድ ዮኒ፣
ከጎረቤትህ ጋር ትተኛለህ ብዬ እየከሰስኩህ አይደለም። ከእርሷ ጋር
አልተኛህም
እያልኩህም አይደለም። ብቻ እርሷ ቤቷ ብታድር ኖሮ የጠፋውን አይ-ፓድ
አልጋዋ
ውስጥ፣ ብርድ ልብሱን ስትገልጽ ታገኘው ነበር።
እወድሃለሁ!
ያንተው እናት>>

9 months, 2 weeks ago

አስቂኝ ክስተት ፈገግ በሉበት‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
የመን ውስጥ ዘማር የተባለ ቦታ ላይ አንድ መስጂድ ውስጥ የተከሰተ በጣም አስቂኝ ክስተት ነው አንብበው ሳይጨርሱ በሳቅ ሟቋረጥ ግን አይቻልም¡
||
ይህ ክስተት እዚያው መስጂዱ ውስጥ ሶ'ፈል አወል (የመጀመሪያው ሰፍ) ላይ ቆሞ ሲሰግድ የነበረ አንድ ሰጋጅ ነው የሚያስተላልፍልን...
*
እናም ይህ ሰው እንዲህ ይለናል:-
«አንድ ሰው ይሞትና ተሰግዶበት ተቀበረ ከዚያም ከኢሻ ሶላት በኋላ ነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ሊመልሱት ይዘውት ወደ መስጂድ ሲመጡ ሰአት ሄዶ ስለነበር መስጂዱ ተዘግቷል።

ስለዚህ ኻዲሞች ለፈጅር ሶላት ሲመጡ እንዲያነሱት በሚል ጀናዛ መሸከሚያው ከመስጂዱ በር ከደረጃ ላይ ያስቀምጡታል።
:
ነገር ግን ሌሊት 9:30 ሰአት አካባቢ አንድ ሰውዬ ወደ መስጂድ ሲመጣ መስጂዱ ዝግ ሆኖ እና በረንዳው ተከፍቶ አገኘው የተወሰነ ቢጠብቅም መስጂዱን የሚከፍተው አጣ ብርዱ በጣም ሲበረታበት ዞር ብሎ ሲያይ ጀናዛ መሸከሚያው ከአጠገቡ አገኘ በውስጡም ብርድልብስ ነገር አለ።
:
እና ይህ ሰው አገኘሁ ብሎ ጀናዛ መሸከሚያው ውስጥ ብርድ-ልብሱን ለብሶ ለጥ ብሎ እንቅልፉን ተኛ አባቴ! በብርድ ደንዝዞ የነበረው ሰውነቱ ትንሽ ምቾት ሲያገኝ ነፍሱንም አያውቅ ለጥ ብሎ ተኝቶልሀል...
ሃሃሃ!

ትንሽ እንደቆየ የመስጂዱ ኻዲም መጥቶ መሲጂዱ ሊከፍት ሲል በረንዳ ላይ ከነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ላይ የተኛ ሰውዬ ይመለከታል ከፈጅር በኋላ ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ መሰለው...
:
ከኋላውም ሌሎች ሰዎች መጥቶ ግማሹ ሽንት ቤት ሌላው ውዱእ ሊያደርግ ይሄዳሉ ይህ በረንዳ ላይ ተኝቶ የሚያዩት ሰውዬ (ጀናዛ) ደግሞ ሁሉም ቀድመውኝ የመጡ ሰዎች ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ ነው ብሎ ያስባል በውስጡ...
(ያዝ እንግዲህ¡)

በዚያ ላይ ፈጅር ነው ሰው ከእንቅልፉ ተነስቶ እየመጣ ነው ያለው ገና በደንብ ያልነቃ ህዝብ ነው።

ሊሰገድበት የመጣ ጀናዛ ይሆናል በማለት ተጋግዘው ወደ መስጂድ ኢማሙ ጋር ወደ ሚህራብ አስገቡት።
ሃሃ!
:
ብ ር ድ የቀጠቀጠው ሰውዬ ሲሸከሙት አያውቅ ተኝቷል¡ ህእ! ሰዎቹም የማን ይሁን ብለው አይጠይቁ ገና ከእንቅልፋቸው በደንብ አልነቁም እና ተሸክመው መስጂድ ውስጥ አስገቡት።

ፈጅር አዛን ብሎ ለመስገድ ወደ 50 የሚሆኑ ሰዎች ተሰበሰቡ።

ይህንን ታሪክ የሚያስተላልፍልን ሰው እኔም ከሰጋጆቹ አንዱ ነኝ የመጀመሪያው ሶፍ ላይ ነበርኩ ይላል።

ከፈርድ በኋላ ልንሰግድበት ጀናዛው ከፊት ተደርጎ የፈጅር ሶላት እየሰገድን ነው።
እህእ!
:
ልክ ለሁለተኛው ረከአ ስንነሳ ጂናዛው ሲንቀሳቀስ አየሁ እንዴዴዴ አይኔ ነው ወይስ ምንድ ነው¿ ብዬ አይኔን አበስኩ ጨፍኜም ገለጥኩ መንቀሳቀሱን ግን አልተወም በቃ እንቅልፍ አለቀቀኝም ይሆናል ብዬ አሰብኩ።

ነገር ግን ነእሹ በደንብ መንቀሳቀስ ጀመረ ያኔ መረባበሽና መፍራት ጀመርኩ።

ይህ የተኛው ሰውዬ ከብርድ ልብሱ ውስጥ ድንገት አንገቱ አውጥቶ ሰገዳችሁ? ብሎ ጠየቀ።
:
ያኔ! ሁሉም ሰጋጆች ደንግጦ መተረማመስና መሮጥ ጀመሩ እኔም አጠገቤ ከነበረው በር ወጥቼ በባዶ እግሬ ሮጥኩኝ ወደ 1 ኪ.ሜ ያክል የሚርቀውን ቤቴን በትንሽ ደቂቃዎች ደረስኩ ደግሞ ባዶ እግሬ መሆኔም የማውቀው ነገር የለም።
ኢማሙ (አሰጋጁም) ሲያየው ደንግጦ መሬት ላይ ይወድቋል ሌሎች ሰዎች ግማሹ ከግድግዳ ጋር ይጋጫል ሌላው ደግሞ ልክ እንደኔው በባዶ እግሩ ይሮጣል መስጂድ ውስጥ አንድ ሰው አልቀረም።
:
አሁንም ሌላኛው በጣጣጣም የሚያስቀው ክስተት ተከሰተ

ያ ከሬሳ መሸከሚያ(ከነእሹ) ላይ ተኝቶ የነበረው ሰውዬ ሲነሳ ሰዎች ሲሸሹ ሲሮጡ ሲያይ ከኋላቸው ተከትሎ መሮጥ ጀመረ።
እናንተ ምን ሆናችሁ ነው ? ቂያማ ቆሞ ነው እንዴ? እያለ ከኋላ ኋላቸው መሮጥ ጀመረ።
ሃሃሃ!
:
ሰዎቹ ደግሞ ወደ ኋላቸው ሲዞሩ ይህ ሰውዬ እየተከተላቸው መሆኑ ያያሉ ያኔ ይብስባቸዋል ባለ በሌለ ሀይላቸው ይሮጣሉ።
በዚህ መልኩ ሁሉም ሰላታቸውን አቋርጠው ሮጡ...»
ይለናል ቦታው ላይ የነበረ አንዱ ሰጋጅ።
:
መቼም ይህንን አንብቦ ያልሳቀ ካለ እኔንጃ¡
ሳቃችሁን በኮመንት!
||😂😂😂😂

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 days, 17 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 week ago

Last updated 1 week ago