ግጥምና ታሪኮች

Description
በዚ Channel ★የራሴን የግጥም ስራዎችና በሌሎች ገጣሚያን የተሠሩ አሪፍ አሪፍ የግጥም ስራዎች★ እንዲሁም ተከታታይ መሳጭ ታሪኮችየምታገኙ ይሆናል አብራቹኝ ሁኑ @darkniha ላይ አውሩን

★ Anything አስተያየት እና ሀሳብ ካለዎት💛 for any comment
@darkniha
@dark_niha_bot
@Hanan_Akmel
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 month, 1 week ago

❝የሰው ቄራ!❞

ሰድናያ ከደማስቆ 30 ኪሎሜትር ላይ የሚገኝ እስርቤት ነው። በእስርቤቱ ክስም ፍርድም የለም። አንድ ሰው ወደዚህ እስርቤት ከገባ አስከሬኑ እንጅ አይወጣም። በዚህም የተነሳ «የሰው ቄራ» ይሉታል።

የተገነባው በበሽር አሳድ አባት ሐፊዝ ዘመን ነው። ፎቶ ማንሳት ስለሚከለከል ዓለም ብዙም አያውቀው። ከላይ የሚታዩ ሁለት ህንፃዎች አሉት። ዋነኛው እስርቤት ግን ከምድር በታች ያለው ፎቅ ነው። እስርቤቱ የተሰራው ለ20ሺህ ሰዎች ቢሆንም እስከ 100ሺህ ሰው ያጉሩበታል።

በርካታ ሰዎች በእስርቤቱ መታሰር የጀመሩት በ2011 የሶርያ አመፅ ከተነሳ በኋላ ነው። በዚህም ከ2011-2015 ባሉት 5 ዓመታት ከ140ሺህ ሰዎች በላይ ታስረዋል። ከእነሱም 4ሺህ ህፃናት 8ሺህ ደግሞ ሴቶች ይገኛሉ። የሶርያ ሰብዓዊ መብት ተማጋች ድርጅት እንዳለው በ5 ዓመታቱ ውስጥ ከታሰሩት 30ሺህ ያህሉ በአሰቃቂ መንገድ ተገድለዋል።

እስርቤቱ በሰው ልጅ ላይ ሊታሰቡ የማይችሉ ግፎች ሁሉ የሚፈፀሙበት በመሆኑ የምድራችን ጀሐነም ይሉታል።

እስረኞቹ ሞት ከተበየነባቸው ቤተሰቦች ከሆኑ አንዱ ሌላኛውን እንዲገድል ወይም ራሱን እንዲያጠፋ ምርጫ ይሰጣቸዋል። አልያም ጨዋማ ምግብ ከሰጡ በኋላ በውሃ ጥም ይገሏቸዋል። በረሃብ ብዛት ወይም በመድሃኒት እጦት እንዲሞቱም ይደረጋሉ። ቀላል ግድያ የሚባለው ስቅላት ወይም ርሸና ነው።

አዳዲስ ወታደሮች ከመመረቃቸው በፊት ወደ እስርቤት ተልከው ሰውን እንዴት ማሰቃየት እንዳለባቸው ይሰለጥኑበታል።

እስረኞቹን በብዙ መንገዶች የሚሰቃዩ ሲሆን ለአብነት ቆዳቸውን እየገፈፉ ይጥላሉ። በረሃብ በማሰቃየት የሰው ስጋ እንዲበሉ ያስገድዷቸዋል። በኤሌትሪክ እሳት ብልታቸውን ያቃጥሏቸዋል። ወንዶች አንዱ ሌላኛውን እንዲደፍር ያደርጋሉ። ለረጅም ሰዓታት ዘቅዝቀው ይሰቅሏቸዋል።

ክፍሉ ሰዎች ምግብ ሲበሉ ጭምር ድምፃቸው እንዲያስተጋባ ተደርጎ የተሰራ ሲሆን የእስረኞችን የሲቃ ድምፅ እየሰሙ እንዲሰቃዩ ያደርጓቸዋል።

ሴቶች በቡድን የሚደፈሩ ሲሆን ብዙዎቹም ወልደዋል። አሳሪዎቹም ልጆቹን መልሰው ይደፍሯቸዋል።

ከእስረኞቹ በርካቶች በድብደባ ብዛት ይሞታሉ። ወይም ፓላራይዝድ ይሆናሉ። በርካቶችም አዕምሯቸው ተቃውሶ ስማቸውን ጭምር ረስተዋል። ለበርካታ ዓመታት ብርሃን ባለማየታቸው ዐይናቸው የጠፋም አሉ።

ሰዎቹ ይህን ሁሉ በካሜራ ይከታተላሉ። እስረኞቹ ራሳቸውን ለማጥፋት ቢሞክሩ እንኳን ዕድል አይሰጧቸውም።

በእስርቤቱ ቴሌቪዥን ወይም ሬዲዮ የለም። ቤተሰቦቻቸውም እንዲጠይቋቸው ቀርቷ በህይወት እንዳሉ እንኳን እንዲያውቁ አይፈቀድም። ከፊሎቹ እስረኞች ለብቻቸው ለዓመታት ይታሰራሉ። በዚህ የተነሳ መረጃ ስለማያገኙ ውጭ ስለሚደረገው ዓለም አያውቁም።

ግፍ ሞልቶ የፈሰሰባቸው እስረኞች አመፅ ለማስነሳት የሞከሩባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ። ሆኖም አሳድ የታጠቀ ሰራዊት በማስገባት ፈጅቷቸዋል።

እነሆ የሰው ቄራው አላህ በቃ ያለው ቀን ደረሰና አሳድ ሲገረሰስ ተከፈተ። በእስርቤቱም ከ40 ዓመታት በላይ የታሰሩ፥ ሞተዋል ወይም ጠፍተዋል የተባሉና የሌላ አገራት ዜጎች ጭምር ተገኙ።

ከእነዚህ ሰዎች ብዙዎቹ የውጩን ዓለም የማያውቁ በመሆኑ ❝አስሃቡል ከህፍ❞ ሊባሉ ይችላሉ።

ከተፈቱት መካከልም የአሳድ አባት ሐፊዝ መሞቱን የማያውቁ አሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ የሳዳም ሁሴን ሰራዊት ሊያድናቸው እንደመጣ ገምተው ነበር። ከፍርሃት የተነሳ አንወጣም ያሉም ነበሩ።

ከእስረኞቹ አንዱ በሐፊዝ ዘመን ሐማ ከተማን በጄት አልደበድብም ብሎ የታሰረው ፓይለት ረጊድ አህመድ አት-ተታሪይ ሲሆን ከ43 ዓመታት በኋላ በህይወት ወጥቷል። በ14 ዓመቱ ታስሮ በ54 የወጣም አለ።

እነዚህ ሰዎች በህይወት ቢወጡትም የደረሰባቸው ስቃይና እጅጉን የተለዋወጠው ዓለም ተስማምቶ ለመኖር ስለማይገራላቸው ሌላኛው እስርቤት እንደሚሆንባቸው እርግጥ ነው። አላህ ሁሉን ቻዩ ይርዳቸው እንጅ።

ሶርያውያን ኢትዮጵያ ሳትቀር በደሃ አገራት ጭምር የተበተኑት እንዲህ አይነት ጨካኝነቱ ገደብ የሌለው መሪ ስለነበራቸው ነው። ዛሬ የተገላገሉትም ይህንን የዘመኑ ፊራዑን ነው። የአሳድ ደጋፊዎችም ይህንን ግፍ እንደ ትክክለኛ ተግባር የሚያዩ የምድራችን ክፉ እንስሳት ናቸው። አሳድንና ግብረአበሮቹን አላህ ከሰድናያ በከፋው ጀሐነም ይቀበላቸውና። 🤲

@achacher

1 month, 2 weeks ago

📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
✍️ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ አስር ➓

አያቷ የተለያዪ ደረሳዎችን እቤታቸዉ ያስቀራሉ አንተም ደረሳ ሁነህ መግባት ትችላለህ ግን ትንሽ ከበድ ይላል  ትስማማለህ??? እሽ ግን ከበድ ይላል ያልከኝ ለምንድን ነዉ ሙሀሜ??? እዛ ደረሳ ከሆንክ  ቁርአን ማህፈዝ፤ብዙ ኪታባችን ማወቅ ሌላም ብዙ ብዙ ነገሮችን ትማራለህ። ደከመኝ ሰለቸኝ አይሰራም ሰአትም አክባሪ መሆን ይገባሀል። ካልሆነ ግን ከበድ ያለ ቅጣት ትቀጣለህ። ምናልባትም ለተወሰኑ ቀናቶች ከቂርአትህ ልትታገድ ትችላለህ።ይሄን አዉቀህ ግባበት ኋላ ወይኔ ወይኔ አይሰራም። ሙሀሜ  በስአት ጉዳይ እንኳን ችግር የለዉም ቀላል ነዉ።   ግን መቸ ነዉ ደረሳዎች የሚገቡ? ሀሱርን ሰግደዉ ይገቡና ሱቢህን ሰግደዉ ይወጣሉ። እሽ መቸ ነዉ የሚቀሩት አይ ወንድሜ ለሊቱን ሙሉ ነዉ የሚቀሩት ሱቢህ ሲደርስ ሰግደዉ ይተኛሉ።

እንግዲህ እችላለሁ ካልክ ግባበት ችግር የለዉም ሙሀሜ። አሁን ሀሱር እየደረሰ ነዉ ሰግደን ሸኘኝ። በቃ ተስማማህ ማለት ነዉ ወንድሜ? አወ ሙሀሜ ተስማምቻለሁ። እንግዲህ ዱአ አድርግልኝ  አላህ ካለ እዉቀቱንም እሷንም ይዜ እወጣለሁ አላህ ካላለም አልጎዳም ዲኔን አዉቄ እመለሳለሁ። በል አሁን እንዳይረፍድብን እንስገድና ሸኘኝ አልኩት  ሙሀሜም እሽ  ብሎኝ ሰግደን ቤቱን አሳየኝና አላህ ያሳካልህ ጠንክር  አይዞህ ተስፋ እንዳትቆርጥ..... ብሎኝ ሄደ። እኔም ወደ ቤቱ በራፍ ተጠግቸ ለማንኳኳት ፈራዉ እጀ ተንቀጠቀጠ ጭንጭ ጭንቅ አለኝ። ግን እንደምንም ብየ አንኳኳሁት ማን ነዉ የሚል ድምፅ ሰማሁ ግን ማን ልበል ዝም አልኩ። ከትንሽ ቆይታ ቡኋላ በሩ ተከፈተ  እኔም አሰላሙ አለይኩም ይሄ የኡስታዝ... ቤት አይደለም እንዴ አልኩ።  አልተሰሳትክም የኡስታዝ ቤት ነዉ ግን አሁን ኡስታዝ ከመስጊድ አልተመለሱም....

ፈልግያቸዉ ነበር ይቆያሉ አንዴ? አይ አይቆዩም አሁን ይመጣሉ ወደ ቤት ግባና ጠብቃቸዉ አለችን በእርጋታ አንደበት  መሬት መሬቱን እያየች አንድ በጣም የምታምር ወጣት እንስት ።   እኔም በጣም ፈርቻለሁ ግን  እንደምንም ብየ ገባሁ።
ከገባሁ ብዙም ሳልቆይ አሰላሙ አለይኩም እያሉ አንድ የሚያምሩ ፂማቸዉ ረዥም በቀይ ቀለም የተዋበት እጠር ያለ ጀለብያ የበሱ
አባት።  እኔም ዉአለይኩም እሰላም አልኳቸዉ አዲስ ደረሳ ነህ መሰል አይቸህ አላቅም ልጀ ።  አወ ኡስታዝ ገና ዛሬ ነዉ ቁርአን ለመቅራት ሀገር አቋርጨ የመጣሁ ። ኡስታዝም አስቀጥለዉ አሁን ቁርአን ገና መጀመሪያህን ልትጀምር ነዉ  ነዉስ ከዚህ በፊት ቀርተሀል አሉኝ።

እኔም የመጀመሪያየ አይደለም ቁርአንኳን   ጨርሻለሁ።   ጎበዝ ልጀ እና ኪታብ ነዉ የምትጀምር?  አይ ኡስታዝ  ኪታብ ብቻ ሳይሆን የቁርአን ሂፍዝም፤ተፍሲርም መጀመር እፈልጋለሁ።    ጥሩ ልጀ የአሁን ልጆች ጊዜቸዉን አልባሌ ቦታ ነዉ የሚያሳልፉት አንተ ግን ኢልምን ፍለጋ ሀገር አቋርጠህ መጣህ ማሻ አላህ ግን ልጀ ቁርአን ማህፈዝ ብዙ ጊዜ ይፈጂብህ ይሆናል ፈፅሞ ተስፋ እንዳትቋርጥ ኢንሻ አላህ አንተ ብቻ ጠንክር  እንጂ የመጣህበት አላማ ይሳካል እሽ ልጀ...   እሽ ኡስታዝ አልኳቸዉ። እንዴት ደግ ሰዉ ናቸዉ ጪንቀቴ ሁሉ ቀለለኝ።

ከዚህ ቀን ጀምሮ እኔም ጠንከር ብየ  ቁርአን ማህፈዝ ኪታብ መቅራ፣የቁርአን ተፍሲር ጀመርኩ   መርየምም ቡና ታፈላልናለች፣ ምግብ ትሰጠናለች። የምር ከተነገረላት በላይ ደግ ና ዉብ እንስት ናት። እኔም እዛዉ ብዙ ደረሳዎችን ተተዋወኩ ከአያቷ ጋርም መቀራረብ ጀመርኩ አንድ ቀን ከቂርአት ቡኋላ ልጀ አሉኝ እኔም አቤትኡስታዝ  አልኳቸዉ  እንደዉ እዚህ ሳትመጣ በፊት ስራ ነበረህ ብለዉ ጠየቁኝ?   ስራ አንኳን አልነበረኝም  ኡስታዝም ለምን ልጀ ብለዉ ጥያቄቸዉን ቀጠሉ? መጀመሪያ የዲን እዉቀት ይቀድማል ብየ ነዉ። ግን ኡስታዝ ልክ እንደ ጨረስኩ ወደ ስራ እገባለሁ ኢንሻ አላህ።  በንግግሬ በጣም የተገረሙ ይመስላሉ።ለምን ማታ ማታ እኔ ላይ አየቀራህ ቀንቀን እኔ ወፍጫ ቤት አትሰራም ማለትም የሚመዝ፣ ሰራተኞችን የሚቆጣጠር.... ታማኝ ሰዉ እፈልጋለሁ አንተ ደግሞ እንደዛ አይነት ልጂ ነህ።  በዛ ላይ ልጀ ወፍጮ ቤቱ እየከሰረ ነዉ የሚያስፈጨዉ ሰዉ እንኳን ከጊዜ ወደ ጊዜ ቀንሷል እና ፍቃድህ ከሆነ እኔ ወፍጫ ቤት መስራት ትችላለህ። እኔም በጣም ደስ አለኝ ይሄ ከኡስታዝ ጋር አሪፍ የመቀራረቢያ እድል ነዉ ብየ ስራዉን በደስታ እንደተቀበልኩ በፈገግታ መለስኩላቸዉ። ጥሩ ልጀ  ከነገ ጀምረህ ስራ መጀመር ትችላለህ አሉኝ እንግዲህ አላማየን ለማሳካት ስራዉን ባልወደዉም መስራት ግድ ነዉ።

ይሄዉ ዛሬ ሰኞ ነዉ ስራ ጀምሬለሁ ዱቄቱ  በላይህ ላይ ይቦላል፤ አይንህ ዉስጥ ይገባል፤ ልብስህን ያበላሸዋል ብቻ ስራዉ አድካሚ ነዉ። ግን ይህን ሁሉ ችየ አምስት አመታትን አሳለፍኩ። ያሁሉ የራቀዉ ደንበኛ ሁሉም መጡ እኔም በፊት በምን ምክንያት ነበር እዚህ የማታስፈጩ ብየ ጠየኳቸዉ እነሱም አደራ በደንብ ፍጩልን ብለናቸዉ ሰራተኞችን ሂደን ስንመለስ ግን ጤፉን ቀይረዉ አንዳንዴም ሚዛኑን አጉድለዉ ወይም ሌላ ነገር እጤፉ ላይ አደባልቀዉ  ፈጭተዉ ይሰጡናል እንጀራዉም አያምርም ነበር። አንተ ከመጣህ ጀምሮ ግን ጤፋችን ተቀይሮ አያቅም ሚዛኑም አይጎልም እንጀራዉም በጣም ያምራል አሉኝ እኔም ለካ ሌሎች ሰራተኞች አደራቸዉን ስለ ማይወጡ ነበር የሚርቋቸዉ እያልኩ።  ገቢዉን ሳስብ ቀን በቀን አሪፍ እየሆነ መጧል ከኡስታዝ ጋርም አባትና ልጂ ሁነናል ኧረ ከዛም በላይ.......

ቂርአቴንም ቢሆን በደንብ እየቀራሁ ነዉ ማታ ከስራ መልስ የተወሰነ ስአት እተኛለሁ ወደ ለሊቱ አካባቢ ደግሞ ከደረሳዎች ጋር ቁርአኔንና ኪታቤን እቀራለሁ የኔ ሂወት እንዲህ ሁኗል። መሬም ጋርም ቢሆን አንዳንዴ አሰላሙ አለይኩም መባባል ጀምረናል ከዚህ ዉጭ ግን ምንም አዉርቻት አላቅም እሷም ለማዉራት ፍቃደኛ አይደለችም። አንድ ቀን ግን......
ይቀጥላል....
@achacher
ክፍል 11

1 month, 2 weeks ago

በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
✍️ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ አስር ➓

አያቷ የተለያዪ ደረሳዎችን እቤታቸዉ ያስቀራሉ አንተም ደረሳ ሁነህ መግባት ትችላለህ ግን ትንሽ ከበድ ይላል  ትስማማለህ??? እሽ ግን ከበድ ይላል ያልከኝ ለምንድን ነዉ ሙሀሜ??? እዛ ደረሳ ከሆንክ  ቁርአን ማህፈዝ፤ብዙ ኪታባችን ማወቅ ሌላም ብዙ ብዙ ነገሮችን ትማራለህ። ደከመኝ ሰለቸኝ አይሰራም ሰአትም አክባሪ መሆን ይገባሀል። ካልሆነ ግን ከበድ ያለ ቅጣት ትቀጣለህ። ምናልባትም ለተወሰኑ ቀናቶች ከቂርአትህ ልትታገድ ትችላለህ።ይሄን አዉቀህ ግባበት ኋላ ወይኔ ወይኔ አይሰራም። ሙሀሜ  በስአት ጉዳይ እንኳን ችግር የለዉም ቀላል ነዉ።   ግን መቸ ነዉ ደረሳዎች የሚገቡ? ሀሱርን ሰግደዉ ይገቡና ሱቢህን ሰግደዉ ይወጣሉ። እሽ መቸ ነዉ የሚቀሩት አይ ወንድሜ ለሊቱን ሙሉ ነዉ የሚቀሩት ሱቢህ ሲደርስ ሰግደዉ ይተኛሉ።

እንግዲህ እችላለሁ ካልክ ግባበት ችግር የለዉም ሙሀሜ። አሁን ሀሱር እየደረሰ ነዉ ሰግደን ሸኘኝ። በቃ ተስማማህ ማለት ነዉ ወንድሜ? አወ ሙሀሜ ተስማምቻለሁ። እንግዲህ ዱአ አድርግልኝ  አላህ ካለ እዉቀቱንም እሷንም ይዜ እወጣለሁ አላህ ካላለም አልጎዳም ዲኔን አዉቄ እመለሳለሁ። በል አሁን እንዳይረፍድብን እንስገድና ሸኘኝ አልኩት  ሙሀሜም እሽ  ብሎኝ ሰግደን ቤቱን አሳየኝና አላህ ያሳካልህ ጠንክር  አይዞህ ተስፋ እንዳትቆርጥ..... ብሎኝ ሄደ። እኔም ወደ ቤቱ በራፍ ተጠግቸ ለማንኳኳት ፈራዉ እጀ ተንቀጠቀጠ ጭንጭ ጭንቅ አለኝ። ግን እንደምንም ብየ አንኳኳሁት ማን ነዉ የሚል ድምፅ ሰማሁ ግን ማን ልበል ዝም አልኩ። ከትንሽ ቆይታ ቡኋላ በሩ ተከፈተ  እኔም አሰላሙ አለይኩም ይሄ የኡስታዝ... ቤት አይደለም እንዴ አልኩ።  አልተሰሳትክም የኡስታዝ ቤት ነዉ ግን አሁን ኡስታዝ ከመስጊድ አልተመለሱም....

ፈልግያቸዉ ነበር ይቆያሉ አንዴ? አይ አይቆዩም አሁን ይመጣሉ ወደ ቤት ግባና ጠብቃቸዉ አለችን በእርጋታ አንደበት  መሬት መሬቱን እያየች አንድ በጣም የምታምር ወጣት እንስት ።   እኔም በጣም ፈርቻለሁ ግን  እንደምንም ብየ ገባሁ።
ከገባሁ ብዙም ሳልቆይ አሰላሙ አለይኩም እያሉ አንድ የሚያምሩ ፂማቸዉ ረዥም በቀይ ቀለም የተዋበት እጠር ያለ ጀለብያ የበሱ
አባት።  እኔም ዉአለይኩም እሰላም አልኳቸዉ አዲስ ደረሳ ነህ መሰል አይቸህ አላቅም ልጀ ።  አወ ኡስታዝ ገና ዛሬ ነዉ ቁርአን ለመቅራት ሀገር አቋርጨ የመጣሁ ። ኡስታዝም አስቀጥለዉ አሁን ቁርአን ገና መጀመሪያህን ልትጀምር ነዉ  ነዉስ ከዚህ በፊት ቀርተሀል አሉኝ።

እኔም የመጀመሪያየ አይደለም ቁርአንኳን   ጨርሻለሁ።   ጎበዝ ልጀ እና ኪታብ ነዉ የምትጀምር?  አይ ኡስታዝ  ኪታብ ብቻ ሳይሆን የቁርአን ሂፍዝም፤ተፍሲርም መጀመር እፈልጋለሁ።    ጥሩ ልጀ የአሁን ልጆች ጊዜቸዉን አልባሌ ቦታ ነዉ የሚያሳልፉት አንተ ግን ኢልምን ፍለጋ ሀገር አቋርጠህ መጣህ ማሻ አላህ ግን ልጀ ቁርአን ማህፈዝ ብዙ ጊዜ ይፈጂብህ ይሆናል ፈፅሞ ተስፋ እንዳትቋርጥ ኢንሻ አላህ አንተ ብቻ ጠንክር  እንጂ የመጣህበት አላማ ይሳካል እሽ ልጀ...   እሽ ኡስታዝ አልኳቸዉ። እንዴት ደግ ሰዉ ናቸዉ ጪንቀቴ ሁሉ ቀለለኝ።

ከዚህ ቀን ጀምሮ እኔም ጠንከር ብየ  ቁርአን ማህፈዝ ኪታብ መቅራ፣የቁርአን ተፍሲር ጀመርኩ   መርየምም ቡና ታፈላልናለች፣ ምግብ ትሰጠናለች። የምር ከተነገረላት በላይ ደግ ና ዉብ እንስት ናት። እኔም እዛዉ ብዙ ደረሳዎችን ተተዋወኩ ከአያቷ ጋርም መቀራረብ ጀመርኩ አንድ ቀን ከቂርአት ቡኋላ ልጀ አሉኝ እኔም አቤትኡስታዝ  አልኳቸዉ  እንደዉ እዚህ ሳትመጣ በፊት ስራ ነበረህ ብለዉ ጠየቁኝ?   ስራ አንኳን አልነበረኝም  ኡስታዝም ለምን ልጀ ብለዉ ጥያቄቸዉን ቀጠሉ? መጀመሪያ የዲን እዉቀት ይቀድማል ብየ ነዉ። ግን ኡስታዝ ልክ እንደ ጨረስኩ ወደ ስራ እገባለሁ ኢንሻ አላህ።  በንግግሬ በጣም የተገረሙ ይመስላሉ።ለምን ማታ ማታ እኔ ላይ አየቀራህ ቀንቀን እኔ ወፍጫ ቤት አትሰራም ማለትም የሚመዝ፣ ሰራተኞችን የሚቆጣጠር.... ታማኝ ሰዉ እፈልጋለሁ አንተ ደግሞ እንደዛ አይነት ልጂ ነህ።  በዛ ላይ ልጀ ወፍጮ ቤቱ እየከሰረ ነዉ የሚያስፈጨዉ ሰዉ እንኳን ከጊዜ ወደ ጊዜ ቀንሷል እና ፍቃድህ ከሆነ እኔ ወፍጫ ቤት መስራት ትችላለህ። እኔም በጣም ደስ አለኝ ይሄ ከኡስታዝ ጋር አሪፍ የመቀራረቢያ እድል ነዉ ብየ ስራዉን በደስታ እንደተቀበልኩ በፈገግታ መለስኩላቸዉ። ጥሩ ልጀ  ከነገ ጀምረህ ስራ መጀመር ትችላለህ አሉኝ እንግዲህ አላማየን ለማሳካት ስራዉን ባልወደዉም መስራት ግድ ነዉ።

ይሄዉ ዛሬ ሰኞ ነዉ ስራ ጀምሬለሁ ዱቄቱ  በላይህ ላይ ይቦላል፤ አይንህ ዉስጥ ይገባል፤ ልብስህን ያበላሸዋል ብቻ ስራዉ አድካሚ ነዉ። ግን ይህን ሁሉ ችየ አምስት አመታትን አሳለፍኩ። ያሁሉ የራቀዉ ደንበኛ ሁሉም መጡ እኔም በፊት በምን ምክንያት ነበር እዚህ የማታስፈጩ ብየ ጠየኳቸዉ እነሱም አደራ በደንብ ፍጩልን ብለናቸዉ ሰራተኞችን ሂደን ስንመለስ ግን ጤፉን ቀይረዉ አንዳንዴም ሚዛኑን አጉድለዉ ወይም ሌላ ነገር እጤፉ ላይ አደባልቀዉ  ፈጭተዉ ይሰጡናል እንጀራዉም አያምርም ነበር። አንተ ከመጣህ ጀምሮ ግን ጤፋችን ተቀይሮ አያቅም ሚዛኑም አይጎልም እንጀራዉም በጣም ያምራል አሉኝ እኔም ለካ ሌሎች ሰራተኞች አደራቸዉን ስለ ማይወጡ ነበር የሚርቋቸዉ እያልኩ።  ገቢዉን ሳስብ ቀን በቀን አሪፍ እየሆነ መጧል ከኡስታዝ ጋርም አባትና ልጂ ሁነናል ኧረ ከዛም በላይ.......

ቂርአቴንም ቢሆን በደንብ እየቀራሁ ነዉ ማታ ከስራ መልስ የተወሰነ ስአት እተኛለሁ ወደ ለሊቱ አካባቢ ደግሞ ከደረሳዎች ጋር ቁርአኔንና ኪታቤን እቀራለሁ የኔ ሂወት እንዲህ ሁኗል። መሬም ጋርም ቢሆን አንዳንዴ አሰላሙ አለይኩም መባባል ጀምረናል ከዚህ ዉጭ ግን ምንም አዉርቻት አላቅም እሷም ለማዉራት ፍቃደኛ አይደለችም። አንድ ቀን ግን......

ክፍል 10 ይቀጥላል
@achacher

1 month, 2 weeks ago

በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ ዘጠኝ ➒

እኔ እናትሽ በመምጣቴ ደስተኛ አይደለሽም አለችኝ? አወ ደስተኛ አይደለሁም... እናትሽ... ይገርማል! ግን ለምን ዋሻቹሁኝ  አክስቴ ! ለምን!!! ለምን . አያቴ ??? ምን በደልኳቹህ ምናለበት የቲም ነሽ ብትሉኝ ???ምን አልሽ ፊርዶሴ  አወ ሁሉንም አዉቂያለሁ እኔን የገረመኝ ዉሸታቹህ... እሽ መልሱልኝ ለምን ዋሻቹህኝ አያቴ??? ቆይ አሁን ይሻልሽና እኔ ሁሉንም ነገር አስረዳሻለሁ አለችኝ። አክስቴ እኔኮ በሽታየ  የናንተዉ ዉሸት ነዉ ሀኪም አይደለም የሚያድነዉ እዉነቱን ስታስረዱኝ ያኔ እድናለሁ።

እሽ የኛዉሸት ከሆነ በሽታሽ....... እንግዲያዉስ እዉነቱን ስሚዉ እኔ የአባትሽ እህት ነኝ እማ ደግሞ የአባትሽ እናት ናት እእእ... ምን ላዉራ አፌ ተያያዘብኝ እዉነት ለመናገር እስከ አሁኖ ሰአት ድረስ ተስፋ ነበረኝ አሁን ግን ተስፋየ ተሟጠጠ፣እንባየ እንደ ጎርፍ መዉረድ ጀመረ። እንደምንም ብየ እዉነቱ ቢመረኝም ለመስማት  ተዘጋጀሁ። ግንኳ አክስቴ አልኩ እሷም ምንም አትተንፍሽ ዝም ብለሽ አዳምጭኝ አለችኝ እኔም አማራጭ የለኝምና ዝም ብየ ማዳመጥ ጀመርኩ ማዉራቷን ቀጠለች....

እናትሽ በጣም ትሁት ደግ ሰዉ...  ብቻ ምን ልበልሽ በጣም ጥሩ ልጂ ነበረች።ከባህር ዳር  እኛ ቤት የመጠዉ እንግዳ  ሁሉ ስለሷ ጥሩነት ሳያወራ አይሄድም። ታድያ ይህን የሰማዉ ወንድሜ ምን አይነት ሴት ብትሆን ነዉ ብሎ ጉዞዉን ወደ እናትሽ ሀገር ባህርዳር አረገ።  ይች እንደዚህ የሚያወሩላትን ሴትማ ማየት አለብኝ  ብሎ አድራሻዋን ማፈላለግ ጀመረ ግን አድራሻዋን ለማወቅ ብዙም አልተቸገረም ምክንያቱም አንድ የአክስቴ ልጂ (ሙሀመድ) ባህር ዳር ስለሚኖር ሁሉንም መረጃ እንዲህ ብሎ ነገረዉ ልጂቷ  መርየም ትባላለች እናቷ ሀሊማ አባትዋ ደግሞ ዳዉድ ይባላል። እንደ ሰማሁት ከሆነ ልጂቷን አያቷ ናት ያሳደጓት አባቷ ሞቷል እናቷ ደግሞ መርየምን ለአያቷ እንዲያሳድጋት ጥላት አዲስ አበባ ሀብታም ባል  አግብታ  ሂዳለች።

አያቷም በጣም ሀብታም ኢማነኛ ነቸዉ አሁን ከእሱ ጋር የሚኖሩ ብዙ ወንድ ልጆች አሉት። ከቤተሰቡ ሴት መርየም ብቻ  ስለሆነች ሁሉንም ስራ የምትሰራ እሷ ናት ብቻ በጣም ታሳዝናለች የወንዶችን ሁሉ ልብስ የምታጥብ ምግብ ፣ቤት፣ እቃ ሁሉን የምትሰራ እሷ ብቻ ናት። እሽ ሙሀሜ  እሷን እንዴት ነዉ ማየት የምችል??? ዩሱፍ እኔ አላቅም ከቤት ለራሱ አትወጣም እንደዉ በአጋጣሚ ብትወጣ እንኳን መሬቱን እንጂ ሰዉ ቀና ብላ አታይም አያቷ ማሻ አላህ በዲኗ ጠንኳራ እንድትሆን በደንብ ኳትኩተዉ ነዉ ያሳደጓት ምናልባት እድሉን ካገኘከዉ አንድ አጓቷ አለ እና ልጆችም አሉት አንዳንዴ ልጃቹን እሷ ናት ትምህርት ቤት የምታደርሳቸዉ። የዛኔ ማየት ትችል ይሆናል።

እሷ ትማራለች እንዴ  ሙሀሜ??? አይ ወንድሜ ስአቱ እንኳን ለትምህርትቷ ስራዋን ለመጨረስ እንኳን የሚበቃት አይመስለኝም። የዚህን ያህል ሙሀሜ!!!   አወ ወንድሜ ብዙ እንግዶች(ደረሳዎች) እነሱ  ቤት ነዉ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያርፉ እና እነሱም መካደም የመርየም ስራ ነዉ።ምን ይሄ ብቻ..... አጓቷም እዘዉ ግቢ ነዉ የሚኖር ሚስቱ በጣም ክፉ ናት። መርየም ያያቷን ስራ ከጨረሰች ቡኋላ  ልጇን እንድታዝልላት አንዳንድ ስራዎችንም እንድትሰራላት ታዝዛታለች።  መርየምም በጣም እየደከማትም ቢሆን ትሰራላታለች። ሚስቱ ብዙ ጊዜ ታስቀይማታለች መርየም ግን ምንም ብታስቀይማት ከዝምታ ዉጭ የምትናገረዉ አንድም ቃል የለም የምር ሙሀሜ ጥሩ ሴት ናት። አይ ወንድሜ ጥሩነቷንማ ሁሉም መስክሮላታል በተለይ ጎረቢቶቻቸዉ በጣም ስለ እሷ ጥሩነት ያወራሉ በተለይ ሰደቃ አድርገዉ ከሆነ አብዛሀኛዉን ስራ የምትሰራላቸዉ እሷ መሆንዋን ያናገራሉ። እሽ ሙሀሜ እንደዚህ አይነት ጥሩ  ሴት ከሆነች እንዴት ሳታገባ ቀረች።  አይ ወንድሜ በጣም ብዙ ሀብታም ባሎች በየ ጊዜዉ ይጎርፋሉ። እሷ ግን አያቴን ለማን ትቸ ነዉ የማገባዉ ትላለች።

አያቷ ግን በዲኑ ጠንካራ ጀግና ከመጣ እድራታለሁ ይላል።  በቃ ምን አለፋህ ወንድሜ እነሱ ላይ ገንዘብ፣መልክ፣ ጉራ ምናምን..... አይሰራም። እነሱ ላይ መስፈርቱ የዲኑ ጉዳይ እንዴት ነዉ? ይሄ ነዉ መስፈርታቸዉ ግን ብዙ ወንዶች ይህን መስፈርት አያሟሉም እናሟላለን ቢሉ እንኳን አያቷ ላይ ሲሄዱ ምንም  የተጠየቁትን ሳይመልሱ አፍረዉ ይመለሳሉ... ግን ሙሀሜ ይሄን ሁሉ መረጃ እንዴት አገኘኸዉ? ነዉስ አንተም ከጠያቂዎች ነበርክ?  እኔ እንኳን የመጀመሪያ ጊዜ ባህርዳር ስመጣ የነሱን አንድ ክፍል ቤት ተከራይቸ ነበር የምኖረዉ። እና በደንብ ነዉ የማቃት  እሽ እስኪ አግዘኝ? ምኑን ነዉ የማግዝህ ወንድሜ እሷን እንዳገባት ምን!!!ይህን ካገዝከኝ የምን ጊዜም ባለዉለታየ ነህ በአላህ እሽ በለኝ በዛ ለይ አንተ ትግባባታለህ።

አይ ወንድሜ ትቀልዳለህ እንዴ?  ስንትና ስንት ምን የመሳሰሉ ባሎችን አንድርም ብለዉ ላንተ ምንም ለሌለህ ደሀ ይድሩልህ ይመስልሀል? ባክህ አጓጉል ቀልድ ይቅርብህ።  ሆሆ!... ግዴለም ወንድሜ አንተ ብቻ እንዴት እዛ ቤት እንደምገባ ንገረኝ እንጂ ሌላዉ ሁሉ ቀላል ነዉ። እሽ እኔ እንቢ ብለዉህ ከምታፍር ብየ እንጂ  እዛ ቤትማ መግባት ቀላል ነዉ በተለይ በአሁኑ ሰአት.. እሽ እንዴት?  አሁን ረመዳን አይደል  ሁሌም በረመዳን ድሀዎችን(ሀቅም የሌላቸዉን) ያስፈጥራሉ  አንተም ሀቅም የሌለህ ድሀ መስለህ ትገባለህ መርየምንም ማየት ትችላለህ ማለት ነዉ።

ይሄማ ከባድ ነዉ የዉም በረመዳን የምበላዉ ሳላጣ እንዴት አጭበርብሬ ገብቸ እበላለሁ። ሙሀሜ እኔ የምበላዉኮ ለአንድ ሚስኪን ማፍጠሪያ ይሆናል። እስኪ ሌላ ሀሳብ ካለህ.... ሌላ እንኳን.. እሽ አያቷ የተለያዪ ደረሳዎችን እቤታቸዉ ያስቀራሉ አንተም ደረሳ ሁነህ መግባት ትችላለህ ግን ትንሽ ከበድ ይላል።
ትስማማለህ???
ፍቀጥላል....
@achacher
ክፍል 10

1 month, 2 weeks ago

📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ስምንት ➑

እኔም ዞር ብየ ሳይ ያች የናፈኳት ዛሬ ነገ ትመጣለች  ብየ በተስፋ የጠበቋት እናቴ  ናት።  ይገርማል!መልኳን ለመጀመሪያ ጊዜ አየሁት በርግጥ እስከ ሁለት አመቴ ድረስ አብረኝ ብትቆይም አሁን ላይ ምንም የማስታዉሰዉ ነገር የለም።  እንዲህ እያልኩ ሳስብ አያቴና እማ ተቃቅፈዉ ሁለቱም ያለቅሳሉ።  እኔም እነሱን እያየሁ እንባየን መቆጣጠር አልቻልኩም። በጣም ደንግጫለሁ በዛ ላይ ወደ አያቴ መጠጋት እንጂ እማን መጠጋት አልቻልኩም ፈረኋት እሷ ፊርዶሴ መጠሁልሽ፤ ደስ አላለሽም? ሁል ጊዜ ለምን አትመጭም ትይኝ አልነበር። እያለች ስታወራ እኔ መልስም የለ ዝም።

እያቴም ፊርዶሴ እናትሽኝ አታወሪያትም እንዴ! እንደዛ በጉጉት ትጠብቂያት አልነበር። በድጋሚ ከዝምታ ዉጭ መልስ የለኝም። እማም አቅፋ ፀጉሬን እየዳበሰች ለምድነዉ ዝም የምትይ ብላ ጥያቄዋን ጀመረች።  አያቴም ፊርዶሴ በጣም ፈሪ ናት። ብዙ ጊዜ መምህሮቿንና መክያን ካልሆነ ሌላ ሰዉ ጋር ለማዉራት ግድ ካልሆነባት በስተቀር ዝምታን ትመርጣለች። በዛ ላይ እኔም ከህፃንነቷ ጀምሬ ዘመዶቻችንን እንድትቀርብ አላረኳትም ሁሌም ዘመድ ሲመጣ ሰላም ትልና ወደነመክያ ቤት እንግዳዎች እስከሚሄዱ ድረስ ተጫወች ብየ እልካታለሁ። መቸም ከነሱ ሌላ ምንም ጎረቢት እንደለለን ታዉቃላቹህ።

በሉ እየረፈደነዉ ወሬቹህን እቤት ትጨርሱታላቹህ ብሎ አጎቴ ይዟን ወደ ቤቱ ሄደ።በምንገድ ላይ እያለን ግን ቀይ መብራት በርቶ አጎቴ መንዳቱን አቆመ። ሲገርም አዲስ አበባ እንደዚህ ዉብ ናት?እያልኩ ሳወራ አጎቴ ወደኔ ዞር ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለመጣሽ አዲስ ሁኖብሽ ነዉ አለኝ። እማም ሱኡዲን ብታያት ከዚህ ትበልጣለች እያለች አንዳንድ ወሬዎችን ስናወራ አጎቴ መንዳት ጀመረ።  በፍጥናት ስለነበር የሚያሽከረክር ቶሎ እቤቱ ደረስን። ቤቱንም ስናንኳኳዉ የከፈተችልን እድሜዋ ከኔ አኳያ የነበረች የአጎቴ ልጂ ናት።ሀናን ትባላለች። የአጎቴ ሌላም ልጆች አሉት አንደኛዉአብዱል ሀኪም ሲሆን አንደኛዉ ደግሞ ኻሊድ ይባላሉ። እማም ሰላም ካለቻቸዉ ቡኋላ ወደ ዉስጥ ገባን።

የአጎቴ ሚስትም ብዙ ምግቦችን አዘጋጂታ ነበርና የቀረበዉን በልተን ጨዋታ ጀመሩ እኔም በጣም ደስ ስላለኝ ለመኩ ደዉየ እማ መምጣቷን በደስታ ነገርኳት።ከሷ ሌላ እማ መምጣቷን ለማን ልናገር እያልኩ ሳስብ ምንም ሌላ የማዉቀዉ ሰዉ የለኝም ለማትስ መምህሬም ልነግረዉ አሰብኩና ስልኩን አጣሁት። ወይ ፊርዶስ ሰዉ እንዲህ ሲደሰት አይቸ አላዉቅም አለችኝ ሀናን። እኔም እማ ብየ ሳልጨርስ....ወዲያዉ አያቴ መጣች ምን እያወራቹህ ነዉ ኑ ሳሎን ቤት ብላ ይዛን ሄደች። አያቴ ምንም አይነት ወሬ ከሌላ ሰዉ ጋር እንዳወራ አትፈቅድልኝም ለምን እንደሆነ ግን መልስ ያጣሁለት ጥያቄ ነዉ። እኛም ወደ ሳሎን ቤት ስንገባ እማ ሻንጣ እየበረቀሰች ነዉ።  ኑ ያመጠሁላቹህን ልብስ እዩት እያለች ብዙ ልብሷችን አወጣች።

ይሄ የፊርዶስ ይሄ ደግሞ ያንች እያለች ሂጃቦችን፤ጫማዎችን፤ቀሚሶችን..... አከፋፈለችን። ሀናን ግን በተሰጠችዉ ነገር ደስተኛ አትመስልም። እኔ ግን ደስ ብሎኛል እዉነት ለመናገር ለኔ የተሰጠሁት ሁሉም ነገሮች በጣም ያምራሉ።  የተሰጠሁትንም ሞክሬም አሳየኋቸዉ ማሻ አላህ ቢረዝምሽም በጣም ያምራል እያሉ.... ደግሞ ሀናን እስኪ ሞክሪዉ ማለት ጀመሩ። ሀናን ግን ለመሞከር ፍቃደኛ አልነበረችም። የተሰጠችዉን ሳቲዝም ወደ ዉስጥ ገባች የተናደደች ትመስላለች ። እኔም የለበስኩትን አዉልቄ በቃ ለሀናን  የተሰጠሁትን ሁሉ እሰጣታለሁ ብየ ሁሉንም የተሰጠሁትን ነገር ሰብስቤ  ወደ ገባችበት ክፍል አመራሁ።ወደ ክፍሉም ጠጋ ስል ሀናንና አባቷ እያወሩ ነዉ። እኔም አዉርተዉ እስከሚጨርሱ በቆምኩበት  ልጠብቃቸዉ ወሰንኩ....  ሲያወሩ ድምፃቸዉ ይሰማል።  አባየ ግን  ለፊርዶስ የተሰጣት ልብስ የሚያማምሩ ለኔ ግን........  እሽ ለምንድን ነዉ አክስቴ የምታዳላ ፊርዶስም የመንድሟ ልጂ እኔም የወንድሟ ልጂ።  ደሞስ እማ ለምን ትላታለች አክስቷ አይደለችም እንዴ? ልጀ ልክ ነሽ አክስቷ ናት ግን እሷ እናቷ እንደሆናች ነዉ የምታዉቅ። እናትና አባቷስ አማየ? እነሱ ሙተዋል ሚሲኪን ፊርዶስ... ቆይ እስኪ ለምን ደበቋት? ከዚህ በላይ ማዳመጥ አልቻልኩም።

ብዙ አሰብኩ ግን መክያ ያለችን እዉነት ነዉ?... አላምንም እያልኩ እግሬ ይንዘረዘር ጀመር፣ሰማያና ምድሩ ዞረብኝ፣ ትንፋሽ አጠረኝ ከዛ ቡኋላ የተፈጠረዉን አላስታዉስም..... ብቻ አይኔን ስገልፀዉ አያቴ ታለቅሳለች እማ የምላትም እጀን ይዛ ታለቅሳለች  አጎቴም ፊርዶሴ ፊርዳሴ እያለ ይጮሀል..... እኔም ግራዉ ገብቶኝ እየት ነኝ የተደረገልኝን ግልኮስ  ምንድን ነዉ? ለምን ታለቅሳላቹህ? እያልኩ ጠየኳቸዉ አያቴም አደራየ ደህናነሽ የኔ ዉድ? አወ... አያቴ ደህና ነኝ አታልቅሽ ብየ እንባዋን ልጠርግላት ስል እጀ ላይ የተተከለዉ ግልካስ አስቸገረኝ አጎቴም እጂሽን አታንቀሳቅሽዉ እኔ ዶክተሩን ጠርቸዉ ልምጣ ብሎ ወጣ እናቴም ማለትም ሀያት ፊርዶሴ ምን ሁነሽ ነዉ? ምንም አቶኝብሽም አይዞሽ ትላለች።

እዉነት ለመናገር እኔ አሁን ላይ ሁሎችም  አስጠልተዉኛል ምናለበት እናትና አባት የለሽም ብለዉ ቢነግሩኝ  እስከዛሬ በተስፋ ከምጠብቃቸዉ መሞታቸዉን ቢነግሩኝ ጥሩ ነበር  ለካ አያቴ ከሰዉ ጋር ሳወራ የምትከለክለኝ፤ ዘመድ ሲመጣ ተጫወች ብላ የምትልከኝ፤ እንዳይነግሮት ብላ ፈርታ ነዉ።...... እያልኩ አለቅስ ጀመር እዱንያንም በጣም ጠላኋት ምናለ በሞትኩ እያልኩ ተመኘሁ አሁን ላይ ማንንም ማየትም ሆነ ማናገር አልፈልግም ዝም ብየ ፊቴን አዙሬ ማልቀስ ብቻ  ሆነ ስራየ ሀያትም ፊትሽን ለምን ወደ ግድግዳዉ አዞርሽዉ ወደ እኛ አትዟሪም እሽ እኔ እናትሽ በመምጣቴ ደስተኛ አይደለሽም አለችኝ እኔም...

9 ይቀጥላል
@achacher

1 month, 2 weeks ago

📌በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
🎖#የታሪኩ_ርዕስ#አደራዬ......
ፀሀፊ ☞ ሰሚራ ሽኩር
#Part ☞ ሰባት ➐

ማን ይሆን ብየ ስልኩን ሳነሳዉ  አሰላሙ አለይኩም ፊርዶሴ እንዴት ናቹህ??? ማንነቷን ለማወቅ ጊዜ አልፈጀብኝም እማ ናት። እኔም እንባየ እየተናነቀን አልሀምዱሊላህ እኛ ደህና ነን አንች እንዴት ነሽ ስራ ሁሉ ሰላም ነዉ?  አወ ሁሉ ሰላም ነዉ እኔምልሽ ፊርዶሴ እማየ እንዴት ናት? አሁንኮ የመክያ እናት ሚስኮል አድርጋልኝ ምን ሁና ነዉ በሰላም ነዉ ብየ ስደዉልላት እማየን ትንሽ እንዳመማት ነገረችኝ አሁን እንዴት ናት??? አሁን አልሀምዱሊላህ ትኩሳቷም ትንሽ ቀዝቀዝ ብሎላታል እንደዉም እንኪ አናግሪያት ብየ ስልኩን ሰጠኋት። አያቴም...   ሀያቴ እንዴት ነሽ እኔስ አልሀምዱሊላህ አንችን ትንሽ አሞሻል ብለዉኝ እንዴት እንደ ጨነቀኝ። ኧረ ሀያቴ ወላሂ ደህና ነኝ አትጨነቂ.... አሁን እንደዉምተሽሎኝ ምግብ አየበላሁኝ ነበረ የደወልሽ ይልቅ የኔን ተይዉና ጤናሽን አንች  እንዴት ነሽ ሁሉም ነገር ሰላም ነዉ?  አወ አማ ሁሉም ሰላም ነዉ።

.... ወላሂ እማ  እንዴት እንደናፈቃቹህኝ አይ ባንናፍቅሽ ነዉ እንጂ ብንናፍቅሽማ  ትመጭ አልነበር እኔም ጤና ሲርቀኝ ምናለ  ብትመጭና ሁላችንም ደስ ባለን ወላሂ እማ አሁንስ ለመምጣት ተዘጋጂቻለሁ። ......  አይ ልጀ ሁሌም እመጣለሁ እያልሽ ተስፋ ትሰጭንና ስንጠብቅሽ አትመጭም። እማ እመኚኝ አሁን መጨረሻየ ነዉ። እሽ ከሆነ ደስ ይለኛል በደስታ እንቀበልሻለን በይ ቆጠረብሽ...... ደህና ሁኚ ብላ  ስልኩን ተዘጋቹዉ።  እኔም ወደ አያቴ ዙሬ አያቴ ምን ብላሽ ነዉ  እንደዚህ ፍንድቅ ያልሽ?   እናትሽ ልትመጣልሽ ነዉ። እእእእእ ምን???እዉነትሽን ነዉ.....   ማመን አቃተኝ የደስታ እንባ አለቀስኩ በቃ ህልሜ እዉን ሊሆን ነዉ ብየ ሱጁድ ወረድኩ አላህየ እስከ ዛሬ ለምን አትመጣም ብየ የተናደድኩትን ይቅር በለኝ ብየ መሳቅ ጀመርኩን ለካ የመክያ እናት ትክክል ነበረች ጊዜ ራሱ ይመልስልሻል ያን ጊዜ ጠብቂ.... ያለችን አሁን ግዜዉ እየደረሰ ነዉ ከጭንቀቴ ልገላገል ነዉ አልሀምዱሊላህ።

አያቴ ቤቱንም ቀለም እናስቀባዋለን አሮጌ እቃወችንም በአዲስ እንቀይራቸዋለን ሌላ ደግሞ አሀ.. አስታወስኩ የወለሉ ምንጣፍም በአዲስ መቀየር አለበት ግን ምን አይነት ከለር ይሁን....በቃ ከቤቱ ቀለም ጋር አንዳይነት ይሆናል አይሻልም  አያቴ......  በግርምት ታየኛለች....  እንዴ! አያቴ  ዛሬኮ እንደዚህ የሚያስለፈልፈኝ በጣጣጣም ደስ ስላለኝ ነዉ አንች ግን ቅድም ደስ ብሎሽ ነበር አሁን ግን እንደ ቅድሙ አይደለሽም ነዉስ እናቷ ከመጣች ትረሳኛለች እንደድሮዉ አትወደኝም ብለሽ ፈራሽ....... ሀሀሀ አይዛሽ እንደዉም በጣም ነዉ የምወድሽ  መቸም ቢሆን ደግሞ  እልቤ ዉስጥ እንዳንች ልዩ ቦታ ያለዉ ማንም የለም።    ኢላሂ የአያቴን ነገር አደራ እረዥም አድሜ ከጤና ጋር ስጥልኝ እያልኩ ሁል ግዜም ዱአ አረግልሻለሁ።

አደራየ እኔም እኮ ደስታየ ከመጠን በላይ ሲሆንብኝ ነዉ ዝምታን የመረጥኩ እንጂ በጣም ነዉ ደስ ያለኝ። እሽ  አያቴ  ከአሁኑ ጀምረን ቤታችንን ማሳመር አለብን ሆ! በስኡዲ ቤት አይነት የኛን ቤት አይታ ልመለስ እንዳትል....  አይ አደራየ ትቀልጃለሽ የምር እየቀለድኩ አይደለም  እሽ ከቀለሙ እንጀምር ምን አይነት ቀለም ይቀባ እኔ እንደሚመስለኝ ዉሀ ሰማያዊ ወይም ደግሞ ፈዘዝያለ ነጭ አንችስ አያቴ?  እኔ ምኑን አዉቀዋለሁ ብለሽ ነዉ አደራየ  በቃ እሽ ፈዘዝ ያለ ሰማያዊ ይሆናል ትስማሚያለሽ? እሽ ይሁን ከቀለሙ ቡኋላ ሌላዉን እያየን እናስተካክለዋለን........
አሁን የጀመርነዉን ምግብ እንጨርስና የምሄድበት ቦታ አለኝ። አደራየ በዚህ ስአት የት ነዉ የምትሄጂ? ሀሱር እኮ ከተሰገደ ቆየ ጀንበርም ጠልቃለች በቃ እሽ መቅሪብ ሳይደርስ ቶሎ እመለሳለሁ። አንች ብይ....
ቻዉ ቶሎ እመለሳለሁ። እሽ ወዴት ነዉ የምትሄጂ....

እነ መክያ ቤት ቶሎ እመለሳለሁ ባለፈዉ የቀለደችብኝን ዛሬ እማ ልትመጣ መሆኑን ልነግራት ነዉ አይ አደራየ ስትመጣ ታያት የለ አሁን ለምን ትነግሪያታለሽ....  ቢሆንም አያቴ ልንገራት በዛዉም ለእናቷ  እንደ ተሻለሽ ልንገራት በጣም ተጨንቃ ነበር።  እሽ ቶሎ ተመለሽ። እሽ አያቴ....  በፍጥነት ስለሆነ የሄድኩ ለመድረስ ሰአት አልወሰደብኝም ቶሎ ደረስኩ በራፉንም አንኳኳሁት መክያ ከፈተችልኝ ደንገጥ ብላ ምንድን ሁነሽ ነዉ ፊርዶስ ?

አያትሽ ደህና አደለችም እንዴ?  ኧረ ደህና ናት ዛሬ እንዴት ደስ እንዳለኝ ልነግርሽ ነዉ እየሮጥኩ የመጠሁ... ምን አይነት ደስታ ተገኝቶ ነዉ እንዲህ አሩጦ ያመጣሽ? እናቴ ልትመጣ ነዉ። እንኳን ደስ ያለሽ ፊርዶሴ ወላሂ በጣም ደስ ይላል ። እሽ ወደ ዉስጥ እንግባና እናዉራ ብርድ ነዉ። አይ! እቸኩላለሁ ይህን ደስታ ልንገርሽ ብየ ነዉ ደሞ እናትሽን ንገሪልኝ አያቴም አልሀምዱ ሊላህ ተሽሏታል ደህና ደሪ ቻዉ እሽ... ቻዉ አያትሽን ሰላም በይልኝ ብላኝ ተለያየን.....

እኔም እየሮጥኩ እቤቴ ቶሎ ደረስኩ ። አያቴ ቶሎ መጣሁ አይደል?....  አወ ግን ሳትደርሽ ከምንገድ ተመልሰሽ እንዴ? በጣም ፈጠንሽ...... እቤት አልገባሁም ከዉጭ ነዉ ለመክያ ነግሪያት የተመለስኩ  ለዛ ነዋ የፈጠንሽ። አወ አያቴ ግን መቸ ይሆን የምትመጣ እያልን ቀን መቁጠር ጀመርን ይኸዉ ሳምንት፤ወር፤ከአመትም አልፎ አመታት ተቆጠሩ። አሁን አራት አመታችን ገባ  እኔም አስራ ሁለተኛ ክፍል ደረሰኩ  አያቴም እርጂና እየተጨጫናት መጧል ብዙ ነገሮች ተቀይረዋል እኔ ለራሱ ቁርአኔን ጨርሸ ኪታብ መቅራት ጀምሬለሁ.... በዛ ላይ በትምህርቴም ከበፊቱ በጣም ጎብዛለሁ ሰሞኑን ትምህርት ይጀመራል። በአዲስ አመት አዲስ ተስፋ ሰንቀን ዘንድሮም በተስፋ እየጠበቅናት ነዉ ዘንድሮ ግን ተስፋ ሳይሆን እዉነት ነዉ ምክንያቱም ትኬት እንደቆረጠች ነግራናለች ግን ተስፋችን ስላለቀ  አላመንም።

ዛሬ ደዉላ ጥቅምት ሳስት ጁመአ ለሊት በረራዋ እንደሆነ ነገረችን አሁን ተስፋችን ቢያልቅም ትንሽም ቢሆን እዉነት እዉነት መሰለን የማይደርስ የለምና ዛሬ ጥቅምት አንድ ነዉ ሁለት ቀን ቀራት ማለት ነዉ ልትመጣ.... እያልን ልንቀበላት  ወደ አዲስ አበባ  አቀናን እዛም ብዙ ዘመዶች አሉን።ካሉን ዘመዶች መካከል የመጀመሪያዉ አጎቴ ነበርና ደመቅ ባለ አቀባበል ተቀበለን። ወደ ቤቱም ይዟን ሄደ  ማሻ አላህ ቤቱ በጣም ያምራል
እኛም እሮብና ሀሙስን ከሱ ጋር አሳልፈን።......... ጁመአ   1 ሰአት ኢትዮጲያ እንደምትገባ ነገረኛለች። ዛሬ ደግሞ ሀሙስ ምሽት ነዉ እኔ እዉነት ለመናገር  ምንም እንቅልፍ አልወሰደኝም በየ ደቂቃዉ ተነስቸ ሰአት ሳይ ነበረ። አሁን አስራአንድ ሰአት ሁኖል ሁሉንም ቀሰቀስኳቸዉ። እነሱም ተነስተዉ ሱቢሂን አንድ ላይ ከሰገድን በኋላ.....

አጎቴም መኪናዉን ይዞ አያቴን፣ እኔን እና የአክስቴን ልጂ በአንድ ላይ ወደ ቦሌ ይዞን  ሄደ። እዛም አስራ አንድ ተኩል ደረስን የኔም አይኔ ወደ ሰማይ ያይ ጀመር እዚህ ፕሌን ላይ ትሆን እማ እያልኩ ስጠባበቅ አንድ ሰአት ደረሰ  ፍራት ፍራት ይለኝ ጀመር አይኔም የሚመጣዉን የሚሄደዉን ሰዉ ይመልከታል።  ከድንገት አያቴ እልልልል አለች እኔም ዛር ብየ ሳይ........

#8 ይቀጥላል
@achacher

6 months, 1 week ago

❤️‍?አቤኒ?

ፀሀፊ: ሀያት

ክፍል አስራ ሶስት

… ይዞት የመጣው ቲንሽዬ የንብ ቀፎ ነው ሁሉም በግራ መጋባት አዩት
<ደሞ ንብ ምን ልታረግ ነው ቤት ምታስገባው>ሀኒ
<ጤነኛ ነህ>ኢቫ
<ምን ለማረግ ይመስላል አንድሽም ከኔ ጋር ፀብ ፍጠሪና አስጨርስሻለው>ተኩራራባቸው ሀኒም በምፀት
<ያረቢ የላላውን አይምሮውን አጥብቅለት>ብላ ጁሷን በአፏ አርጋ በጀርባዋ ሸርተት ብላ ተኛች ማሪያ ስላየችው ደስ ብሏት
<ስላየሁክ ደስ ብሎኛል>
<እ እንዴት ነሽ>ቅድም ያስተዋላት አይመስልም
<ደህና ነኝ>አንገቷን እየሰበረችከፀጉሯ ሸርተት ያለውን ሂጃቧን ወደፊት እየመለሰ
<ሂጃብ ጥብቅ ሲል ያምርብሻል>አፍራ ሂጃባን በስትክክል ጠመጠመች ኢቫ ሁኔታቸውን አይቶ
<እሺ ከዛስ ሌላ የላቹም?>
<አሽቃባጭ ምላስ ጨምረሀል ባክህ፣ በሉ በቃ ንቤን ይዤላቹ ልውጣና ልመራመርባት ቻው>
ሀኒ ስትበላ የነበረውን ለውዝ ወረወረችበት እሱም ሽል ብሎ ያመጣውን ቀፎ ይዞ ወጣ ማሪያ እስኪወጣ ድረስ በአይኗ ተከተለችው ኢቫ ልክ ረያን እንደወጣ ሰአቱን አየት አርጎ
<ኦ ኦ ሰአቱ ሄዷል ልሂድ ይሄን ደሞ ሊያን ነው ስጣት ያለኘ>ለሀኒ አቀበላት
<እናንተ የቆያቹ ጓደኛሞች ሁናቹ ሳላቹ እኔን ምን ለመሆን ነው ሚልከኝ>ሀኒ መፅሀፉ ላይ አይታ
<ሂድልን ወረኛ> ብላ አባረረችው እሱም እየሳቀ እየተቻኮለ ወጣ ማሪያ ቀጠል አርጋ
<ሀኒ ሲመስለኝ ከቲቸር ቢሮ ሰርቆ ነዉ>
<አረ እንዴት እንዲ ያረጋል>…

ሀኒ ወደ ት/ቤት ከሊያን ጋር ስለተጣሉ ብቻዋን ለመሄድ አስባ መንገድ ስጀምር አስፓልቱ ላይ ሳይክሉ ላይ ተቀምጦ እየጠበቃት ነበር ኮቴ ሰምቶ ዞሮ አያትና ፈገግ አለላት እና ለተሰበረው እግሯ እንድታስቀምጥበት ማታ ሲሰራላት ያደረውን ሳይክሉ ላይ የገጠመውን ትንሽዬ ጣውላ አእየዘረጋ
<ነይ ቁጭ በይ>እሷም በዝምታ ተመልክታው የዋህነቱ አሳዝኗት ሄዳ ተቀምጣ የሰራላትን የእግር ማስቀመጫ ፈገግ ብላ አየችው
<አልሆነም>አላት ፈገግ ብሎ ወደ እግሯ እያየ
<ሆኗል አንተ ሌባ መፅሀፉን ከቢሮ ሰረቀህ ነዋ>ዝም አላት እሷም ፈገግ ብላ ከቦርሳዋ ሁለት የተቀቀለ እንቁላል አውጥታ
<ትንሹን ልስጥህ ትልቁን>
<ትንሹን>ፈገግ ብላ ጭንቅላቱ ላይ ሰብራ ልጣ አጉርሳው እራሷም ጎረሰች
<እንሂድ በቃ>መንገዳቸውን ቀጠሉ…ክላስ ደርሰው ከሳይክል ወርደው ክላስ ሲገቡ ኢቫ ጭንቅላቱ ታሽጎ አገኙት ተሰብስበው ቁጭ ብለው ምን እነደሆነ እያዳመጡት ነው የአቤኒ ቦታ ላይ ቁጭ ብሎ ሌሎቹ ደሞ ከበውት ይሰሙታል በንዴት ወደ ተመታው ቦታ እየጠቆመ
<ቲቸር ግን ጨካኝ ነው ለቤተሰብ እንደሚነግርብኝ እንኳን አልነገረኝም እናቴ ከውጭ በመጣች ሰአት ነው ደሞ የነገራት ጌም ዞን መዋሌን ስሰማ ከቤት አስወጥታ ገረፈች ጭንቅላቴም አልተረፈም አባቴ ወደ ሆስፒታል ወሰደኝ አያናድም>ሀኒ ትከሻውን መታ መታ አረገችለት
<ይሄ እንዴት እንደሚቀየር ታቃለህ>ዳኒያ ነበረች ሊያንን አንድ ደብተር ይዛ ምጠይቀው ሀኒም ድምፇን ሰምታ ወደነሱ ዞረች
<አላቅም> ሀኒ ተበሳጭታ ወደሷ ምትፈለከተውን ዳኒያ አይታ እየሳቀች
<ለምንድነው እንዲ ምታይኝ>አለቻት ዳኒም ንግግሯን ችላ ብላ ከሊያን ስር ቁጭ ብላ
<እሺ ይሄ ፎርም ምንድነው>
<አላቅም>
<እሺ ልንገርህ ይሄ passive form new>ማሪያ ቀበል አርጋ
<ካወቅሽ ለምን ጠየቅሽው>
<ምክኒያቱም ሊዩን እወደዋለሁ ለዚ ከሱ ጋር መነጋገር ፈልጌ ከሆነስ>አለች ሁሉም ተማሪ ሰምቷት ስለነበር ሁሉም አንፏጩ ሀኒ እና ማሪያ ተየይተው ዝም አሉ በዚው መሀል አቤኒ በወንዳ ወንድ አረማመዱ ቆፍጠን እያለ ገባ…

ይቀጥላል…

7 months, 1 week ago

?አቤኒ❤️‍?

ፀሀፊ:ሀያት

ክፍል አስራ አንድ(11)

…በወገቡ ተሸክሟት መልሱን እየነገራት ስትፅፍ አስተማሪው አይቶ  በያዘው አጭር ዱላ ዋይት ቦርዱን መታ መታ አርጎ
<እንድትነግራት አልታዘዝክም>ብሎ አጠገባቸው ሲቆም ታፋዋ ላይ በእጁ እየፃፈ ሲነግራት ፈገግ ብላ አይታው ታፋዋ ላይ በእጁ በሚፅፈው እያዳመጠች መልሱን ትፅፋለች ሊያን እያያቸው ስለነበር በንዴት የያዘውን እስክርቢቶ ይጨፈልቀዋል ሀኒ ስጨርስ 
<ቲቸር ልክ ነው>ሚለው ግራ ገብቶት
<ወደ ቦታሽ ተመለሺ>አላት…ቁርስ ሰአት መድረሱን ደውሉ ሲያበስር አስተማሪው ክላስ ቁጭ ብሎ ወረቀት እየሰበሰበ ሁሉም ከክፍል ሲወጡ ግማሽ ተማሪ ባለበት ተቀምጧል ሀኒ ሊያን ጋር ሄዳ ፊት ለፊቱ ቆማ በእጇ ጠረጴዛውን ይዛ ቆማ ቅድም ስላነበበችው ልቦለድ ትነግረዋለች
<ፍቅር በርጅና አቤት ሲያምር ነጭ ፀጉር የተዋደዱ ልቦች የተያያዙ ሩሆች ኡፍ>ብላ በክርኗ ትከሻውን ገፋ አርጋው ቅድም የወረወረችለትን መፅሀፍ ከጠረጴዛ ስር ልታነሳ ስትል እጇን ያዛት አሁንም እጇን ስሰድ በንዴት መፅሀፉን አንስቶ ጠረጴዛው ላይ መወርወር በሚሉት መልኩ አስቀምጦ
<ስለዚ ነገር አይገባኝም አትንገሪኝ>ሰጮህ ና መፅሀፉን ሲወረውር ክላስ ውስጥ የነበሩት አቤኒ ወረቀቱን ሚሰበስበውን መምህር ጭምር ዞረው ተመለከቷቸው ሀኒ ግራ ተጋብታ
<እንዴ ምን ሆነህ ነው>ይህን እንዳለች መምህሩ ወረቀቱን ሰብስቦ ወደነ ሀኒ ሄዶ የተናደደበትን መፅሀፍ አንስቶ ካየ ቡሀላ ሁለቱንም በንዴት ተመልክቶ ምንም ሳይል ሄደ መምህሩ እንደወጣ ሊያንም እንደተናደደ ክላሱን ለቆ ወጣ ሀኒም ከኃላው እየጠራችው ትከተለዋለች
<ሊዩ ጠብቀኝ የት ነው ምትሮጠው> ልክ ስትደርስበት ዘላ ወገቡ ላይ ወታ ተጠመጠመችበት
<ምናባክ ያስኮርፍሀል መፅሀፊን መልስልኝ>
<አረ አልችልሽም ሴትዮ ውረጂ>
<አልፈልግም መልስልኝ መፅሀፌን መልስልኝ>
<እ አሁንስ ተናደሀል አንተ ነህ ለኔ እንዲ በቁጣ ምታወተራኝ> ጭቅጭቅ አይሉት ድብድብ ፀጉሩን ይዛ ይታገላሉ
<ኡፍ ውረጂልኝ>ብሎ ወረወራት ፊት ለፊቱ ቆማ ካየችው ቡሀላ እንደ ህፃን ጉንጩን እያሸች
<እውይ አቶ ሊያን ተናደዋል>እንደተበሳጨ  ፊቱን አዞረባት እጇን ወርውሮ
<የክላስ እይታ መሳብ አልቻልሽም? ጭንቅላትሽ ለነገው የካምፓስ ህይወት ሚና የለውም ልክ እንደ ክላስ መሪ ራስሽን ታያለሽ እንዴት ነው ፈተና ምታልፊው ቤተሰቦችሽ ልፋታቸውስ>ባዘነ ፊት ካየችው ቡሀላ
<እሺ ስላስታወስከኝ አመሰግናለው>ብላ ተናዳ  ስቴድ እጇን ሲይዛት ወርውራው መንገዷን እያነከሰች ሄደች
*
ዳይሬክተሩ  ከአጠገቡ ወዳለው ጌም ዞን ሊፈትሽ ሊሄድ ከግቢው ወጣ  እነ ኢቫ ጌም ዞን ሀይለኛ ፉክክር ላይ ሆነው ተመስጠዋል ዳይሬክተሩ ሁሉንም አንድ አንዴ እየመታ አስቆማቸው ኢቫ ግን ጓደኞቹ ከኋላው ስለነበሩ አላያቸውም ዳይሬክተሩ ከኃላው በዱላው ነካ ነካ አረገው ኢቫም እሱ መሆኑን አላወቀም ጓደኛው መስሎት
<ምንድነው ሰአቱ?>መጫወቱን እንደቀጠለ
<ሰአቱ የenglish class ሰአት ነው>አሁንም ድምፁን አለየም
<መምህሯ ቶሎ አጨርስም አንዱንም ፔሬድ እንጫወት ቁጭ በል>
<ዳይሬክተሩ ከመጣስ>
<ባክህ አይመጣም ቢመጣም መላ እንፈልግለታለን አንድ ቀንማ ከሱ ጋር አንላቀቃት>ጫወታውን አይፈጠነ
<ዛሬ ቢሆንስ>ብሎ ዱላወን ነካ አረገው ኢቫ ቀስ ብሎ ዱላውን አይቶ ቀና ብሎ ተመለከተው ከተቀመጠበት በድንጋጤ ተነሳ…ዳይሬክተሩ የኳስ ሜዳው ላይ አስቁሞ እየተቆጣቸው ነው ሁሉም አንገታቸውን ደፍተው ያዳምጡታል
<በትምርት ሰአት ጌም ዞን መገኘት ምን የሚሉት ነው የዘንድሮ ተፈታኝ መሆናቹን ረሳቹ እንዴ በትምርት መቀለድ እያበዛቹ ነው ከዚ ቡሀላ ሌላ ጥፋት ባገኝባቹ እስከ መጨረሻ ነው ማሰናብታቹ ለዛሬ ይሄን ግቢ ሙሉ 100 ጊዜ ዞራቹ ትንበረከካላቹ በመሀል አቤኒ ቁና ቁና እየተነፈሰ ወደነሱ ተጠጋ
<ቲቸር ይቅርታ  አለቃ እኔ ነኝ>
<አታፍርም አለቃ ነኝ ስትል እነዚ ተማሪዎች ጥሩ ተማሪ ነው ሚባሉት በትምርት ሰአት ጌም እየተጫወቱ>
<ቲቸር ትምርት አያምልጣቸው እኔ ልቀጣላቸው እንዲገቡ ፍቀድላቸው>ዳይሬክተሩ የፌዝ ሳቅ ፈገግ ብሎ
<አቃለው በሳይንስ ትምርቶች ጎበዝ እንደሆንክ በእንቅስቃሴ ግን ብዙም አትመስልም ለዚ ሂድ ግባ ራሳቸው ይቀጡ >
<አይ ቲቸር ይሄ የኔ ጥፋት ስለሆነ እራሴው እወጣለው እባክህ ቲቸር እንዲገቡ ፍቀድላቸው>ትንሽ አሰብ አደረገና
<እሺ ከሆነ ለዛሬ ግቡ ለምሳ እስኪደወል ከቻልክ ትጨርሳለህ>
<እሺ ቲቸር> እነ ኢቫ በግራ መጋባት እየተያዩ እየተደነባበሩ ወደ ክፍል ገቡ አቤኒ ሩጫውን ሀ ብሎ ጀመር የምሳ ሰአቱ ደውል እስኪያቃጭል ድረስ አንድ ፔሬድ ሙሉ እየሮጠ ተደወለ አሁንም አልጨረሰም ነበር ዳይሬክተሩ ቆሞ እየቆጠረለት ነበር ምሳ ሰአት ሲደወል የክላሱ ተማሪዎች እነ ሀኒ ኢቫ ከፎቁ ወርደው የኳስ ሜዳውን ብረት ተደግፈው ይመለከቱታል ሌሎቹ የት/ቤቱ ተማሪዎች ከበውት ፎቁንም ሞልተው ቁመው ይመለከቱታል ሁሉም ይንሾካሾካል
<አረ ቲቸር ምን ሆኗል አዲስ ተማሪ ነው በዛ ላይ የሰፈሩ ቅልሞ ነው ምን ቢያጠፋ ይሄን ያህል ቅጣት ምንድነው አረ ይደብራል>ይሄ ንግግር ከዳይሬክተሩ ጆሮ ገብቶ ሆዱ ተላወሰ…አቤኒ እየደከመ መጣ ፍጥነቱን ቀንሶ የመራመድ ያክል ተዝለፈለፈ ሀኒ ፊቷ ዳመና ለብሷል አሳዘናት ሆዷን አልስች አላት አቅፋው ብታስቀምጠው ደስ ባላት…

ይቀጥላል…

ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ!!

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana