Good Christian Books Shelf

Description
This channel is created for the purpose of sharing good Christian books from the reformed Christianity world.
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

8 hours ago

ይህ ልጅ ግን ምንድነው ሚያወራ? እየገባው ነው ግን የሚጽፈው ነገር?😑
እስቲ በምናብ ከርሱ ጋር ያደረኩትን ዳይሎግ ላሳያችሁ😀

እኔ ሰላም ባሮኬ ጸጋ ይብዛልህ።
ባሮኬ ይመስገን አምላክ ሰላም ሸልፈኛው።
እኔ ጥያቄ ነበረኝ ባሮኬ?
ባሮኬ ጠይቅ ብሮዞቪስኪ።
እኔ የዮሃንስ ወንጌል infallible መሆኑን infallible በሆነ ደረጃ ታውቃለህ ወይ
ባሮኬ አዎ በትክክል።
ማን infallible በሆነ መንገድ ነግሮህ ነው Infallible በሆነ መንገድ ያወቅኸው?
ባሮኬ infallible የሆነችው ቤተክርስቲያን የዮሃንስ ወንጌል infallible እንደሆነ ነግራኝ ነው።
እኔ ቤተክርስቲያን infallible በሆነ መንገድ የዮሃንስ ወንጌል ቀኖና ውስጥ አስገብታህ infallible በሆነ መንገድ የነገረችህበት አለ?
ባሮኬ ቀኖና infallible በሆነ መንገድ ቤተክርስቲያን የሰጠችበት infallible ቀኖና የለም።
እኔ ቤተክርስቲያን የዮሃንስ ወንጌል infallible በሆነ መንገድ ካልሰጠችህ የዮሃንስ ወንጌል ቀኖና ውስጥ እንዳለ infallible በሆነ መንገድ እንዴት አወቅህ ታዲያ?
የባሮኬን መልስ እየጠበቅሁ ነው ከመለሰልኝ እነግራችኋለሁ😁

10 hours ago

ዳዊት ፋሲል ረቡእ ወተት ጠጡ የሚል የሆነች ቪዲዮ አየሁና እኔም በሱ አሳብ ላይ ልጨምር😁😁 ረቡእ በቅቤ ያበደውን ጩኮ ቁርስ ሳትበሉ ከቤታችሁ እንዳትወጡ 😁

1 day, 3 hours ago

የአቤል አዲሱን የመዝሙር አልበም ኖት እየያዝሁ በጥልቀት ሰማሁለት። 13ቱም መዝሙሮች ግጥሞቻቸውም የሙዚቃ መሳሪያዎቹም እንከን አልባ መዝሙሮች ናቸው። ያው አልበሙ 16 መዝሙሮችን የያዘ ቢሆንም ሶስቱ እንክርዳድ መዝሙሮች ስለሆኑ ዝምብለን እናልፋቸዋለን። የሆነ ቀን ተለቅሞ ይወጣሉ በሚል ጥልቅ ምኞት😁
ደረጃ ለማውጣት ቢያስቸግሩም በጥበብ እንደምንም ለይቼ በጣም ተደጋግሞ መሰማት ያለባቸው ሰባቱን መዝሙር ምረጥ ከተባልሁ….
15ኛ ትራክ እንዳላጠፋ ሰው፣ 11ኛ ትራክ በማይነገር ስጦታ፣ 8ኛ ትራክ እንግዲህ ምን ልበል፣ 9ኛ ትራክ በማለዳ፣ 5ኛ ትራክ መሸሸጋዬ ነው፣ 1ኛ ትራክ ተመስገን፣ 16ኛ ትራክ ይተካል እግዚአብሄር የሚሉት ትራኮች ከፍ ተደርጎ የተሰቀሉ መዝሙራት ናቸው!
ከመዝሙሩ አልበም አንዱን መዝሙር ብቻ የአልበሙን ውበት ለማሳየት ትንሽ ሰፋ አድርጌ አሳቡን ለማሳየት ልሞክር። ከላይ እንዳልኳችሁ ጥልቅ የሆነ መዝሙር መስማት ልምድ ላለው ሰው በነጠላ መዝሙሮቹ ራሱ ሰፋ ያለ ኮመንተሪ መጸሃፍ የሚቻል መዝሙሮች ናቸው

መዝሙሩ የሚገኝበት የአልበሙ ቁጥር: 16ኛ (የመጨረሻው የአልበሙ መዝሙር)።
ርእሱ: ይተካል እግዚአብሄር አገልጋይ ለቤቱ።
የመዝሙሩ ጠቅላላ አሳብና ይዘት:

በዘመናት ታማኝነቱ የማይነጥፍበት እግዚአብሄር አገልጋዮችን በቤቱ ይሾማል። በጉልበታቸው ያልዛሉ፣ ብርቱ የሆኑ አገልጋዮችን ጸጋውን እያካፈለ በማይሰስት ቸርነቱ ለቤቱ አገልጋዮችን ይሾማል። ጸጋው ደግሞ ከትላንት ዛሬ፤ ከዛሬ ለነገ እየበዛ ብርቱ አገልጋዮችን ለቤቱ እያበቃ እየበዛ የሚሄድ ነው።

ዘማሪውም ይህን ቅድመ ልባዌ መረዳት በመያዝ እውነትነቱን ለማስረዳት ወደ ቃሉ ይወስደናል። ሙሴ ህዝበ እግዚአብሄርን የመራበት የ40 አመቱ ጥበብ፣ ማስተዋልና በረከት ከሙሴ ጋር ወደ መቃብር አልወረደም። ይልቁን በረከቱ፣ ጥበቡ፣ ማስተዋሉና ሞገሱ በዝቶ ወደ ብላቴናው ኢያሱ ተሻገረ እንጂ። መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው የእስራኤል ንጉስ ኢያሱን ከሌሎች አገልጋዮች ይልቅ በመምረጥ በፊቱ በጸጋው እንዳቆመ ዘማሪው የአገልጋዮችን መተካካት እያሰበ ይዘምራል።
ዘማሪው ከህዝበ እስራኤል የስልጣን ተዋረድ ተሻግሮ በዘመነ ነቢያት የተከናወነውን ሌላ መተካካት በመጸሃፍ ቅዱስ የነቢዩ ኤሊያስና ኤልሳን ታሪክ እያነሳ በዜማ ያዜማል። ኤሊያስ በእሳት ሰረገላ ወደ ላይ ሲወሰድ የጸጋውን ማስተላለፊያ መጎናጸፊያውን ይዞ አልወጣም። ይልቁን ህዝበ እስራኤልን በነቢይነት ለሚያገለግል ለደቀ መዝሙሩ ለኤልሳ ተወለት እንጂ። ኤልሳም ፍጹም እጥፍ ድርብ በሚሆነው በአምላኩ ጸጋ አገለገለ።

የጸጋውን ሰጪ እየረሱ የተቀበሉትንም ጸጋ እያኮሰሱ በራሳቸው የቤቱ አገልግሎት በጥረታቸው እንደተገኘ ለሚቆጥሩ አገልጋዮች እንዲህ እያለ ያሳስባቸዋል።
ከኔ ብቻ በቀር ማነው ያለው ሌላ፣
ስሙን አገልግሎ ዝናሩ ያልላላ።
እንዲህ አትበሉ እግዚአብሄር ዘገየ፣
ይሾማል ለቤቱ ጠላት አይኑ እያየ
በዚህ ውስጥ ዘማሪው የራሳቸውን ፐርሰናል ከልት ለመፍጠር ለሚሞክሩ ለቤቱ አገልጋዮች ማሳሰቢያ ጣእም ባለው ዜማው ያሳስባል። አገልግሎት ሁሌ የጸጋ ውጤት መሆኑን ለሚረሱ አገልጋዮች ጥሩ ምክር ነው! ሿሚውም ጸጋ ሰጪውም እግዚአብሄር ነው። ተሿሚው ለቤቱ የሚሰራ የቤቱ ባላደራ ነው።

ብንቀድስ፣ ብንዘምር፣ ወንጌልን ለማያምኑ ሰዎች ብንመሰክር ወደ ሰማይ ቤት መሄዳችን አይቀርም። ታማኙ እግዚአብሄር ለቤቱ ደግሞ እንደገና ሌሎች አገልጋዮችን ያስነሳል። አገልጋዮቹ ደግሞ ከቀደሙት አገልጋዮች በበለጠ ዘመኑን መዋጀት የሚችሉ፣ በጸጋ የበረቱ፣ እጅግ የጸኑ እንደሆኑ ዘማሪው በውብ ዜማው ያስታውሰናል።
ለአቤላ ሸልፈኛው በዚህ አልበሙ እንደወደደው ንገሩልኝ። ሰርጎ የገቡ ሁለት ከግማሽ የሚሆኑ መዝሙሮችን ደግሞ በቀጣዩ አልበሙ እንዲያርማቸው። በርግጥ ከ16 መዝሙሮች 13ቱን ቃሉን ያማከለ መዝሙር እዛ ቤት መዘመር ትልቅ ስኬት ነው! እግዚአብሄር ጸጋውን አብዝቶ ያድልልን አቤላችን። ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን!

1 day, 8 hours ago

“በቀራኒዮ ቆመህ በመስቀሉ ዙፋን፣
በሰው ፊት ተዋርደህ አለሙን ስታድን።
እርቃንህን ስትሆን ነውሬ ተሸፈነ፣
በቆሰልከው ቁስልህ ለኔ መዳን ሆነ።

ሃጢአት የምትከድን ከባተ አበሳ፣
የናዝሬቱ መልካም የይሁዳ አንበሳ።
ማለዳ ማለዳ ሃጢአቴን ብትቆጥር፣
ዛሬ ለምስጋናህ እንዴት እቆም ነበር።

ከሳሾቼ አፈሩ ድንጋይን የያዙ፣
አንተ ስትምረኝ ሄደው እየተከዙ።
በሰላም ሸኘህኝ አድነህ ከሞት፣
በፍቅርህ ሸፍነህ ያለፈውን ሃጢአት….”
ዘማሪ አቤል መክብብ
በስመአብ እንዴት አይነት ውብ መዝሙር ነው

1 day, 10 hours ago

1600 አመት በፊት የነበረችው የኔዋ ቤተክርስቲያን ናት እያለኝ ነው አቡሻ በጠዋት ቁርሴን ሳልበላ 🤣🤣
በኢኩሚኒካል ጉባኤም ከጌታ ቤተክርስቲያን እየተቆረጡም እንዲህ አይነት ድፍረት ግን ከየት ነው ሚያመጡት?😁
ሳድግና ደፋር ስሆን እንደዚህ አይነት ክሌሞችን እያቀረብሁ እፋንናለሁ 😃😄

1 day, 20 hours ago

ከኤቲስት ጋር ማውራት አልወድም። ግን እስቲ እድሌን ልሞክር ብዬ 12ቱን minimal historical facts ተጠቅሜ አሪፍ እየተጓዝን ነው 😁

1 day, 23 hours ago

እስቲ ለጎረቤቶቻችን ትንሽ የማታ ሌክቸር እንስጥ😁 ሌክቸሩን ለመረዳት IQ 70+ ይፈልጋልlol
ርእስ: መጸሃፍ ቅዱስ በሃይማኖት ክርክር የበላይና የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥ ብቸኛ ባለስልጣን ነው።

ርእሱን የሚያብራሩ አውራ አናቅጽት:

በህገ መንግስታችን አንቀጽ 80 (1) እንዲህ የሚል አረፍተ ነገር ተቀምጦ እናገኛለን፤

“የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል ጉዳዮች ላይ የበላይና የመጨረሻ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል።”

የእምነታችን መግለጫ በሆነው በዌስትሚኒስቴር አንቀጽ 1 (10) እንዲህ የሚል ድንጋጌ ተቀምጦ እናገኛለን፤

“መጸሃፍ ቅዱስ በሃይማኖት ክርክር የበላይና የመጨረሻ የአቤቱታ ማሰሪያ ባለስልጣን ነው።”

ከነዚህ ሁለት ንባባት ልንረዳቸው የሚገቡን7 አንኳር ነጥቦች:

1 ጠቅላይ ፍርድቤት ብቸኛ የዳኝነት አካል አለመሆኑን። ለምሳሌ ያህል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትና የከፍተኛ ፍ/ቤት የተባሉ የዳኝነት ስልጣን ያላቸው ፍርድቤት መኖራቸው።
2 መጸሃፍ ቅዱስ በሃይማኖት ክርክር ብቸኛ ባለስልጣን አለመሆኑን። ለምሳሌ ክሪዶችና ኮንፌሽኖች በሃይማኖት ክርክር ዳኝነት የሚሰጡ ባለስልጣናት መሆናቸውን።
3 ጠቅላይ ፍ/ቤት ከመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትና ከከፍተኛ ፍ/ቤት ይልቅ በዳኝነት ውሳኔ የበላይና የመጨረሻ ብይን የሚሰጥ ባለስልጣን መሆኑን።
4 መጸሃፍ ቅዱስ ከክሪዶችና ከኮንፌሽኖች ይልቅ በሃይማኖት ክርክር የበላይና የመጨረሻ ብያኔ መስጠት የሚችል ባለስልጣን መሆኑን።
5 ጠቅላይ ፍ/ቤትን ብቸኛ ባለስልጣን ያስባለው የበላይና የመጨረሻ የዳኝነት ውሳኔ መስጠቱ እንጂ ብቸኛ የዳኝነት አካል መሆኑ አይደለም።
6 መጸሃፍ ቅዱስን ብቸኛ ባለስልጣን ያስባለው በሃይማኖት ክርክር የበላይና የመጨረሻ የዳኝነት ውሳኔ መስጠቱ እንጂ በሃይማኖት ክርክር ብቸኛ ዳኝነት የሚሰጥ ባለስልጣን መሆኑ አይደለም።
7 ስለዚህ መጸሃፍ ቅዱስ ብቻ ስንል በሃይማኖት ክርክር የበላይ፣ የማይቀለበስ፣ የማይሳሳት፣ የመጨረሻ ውሳኔ መስጠት የሚችል እያልን እንጂ በሃይማኖት ክርክር ሌላ ሊዳኘን የሚችል የዳኝነት አካል የለንም እያልን አይደለም። በተጨማሪም ሌሎች የዳኝነት አካል በሃይማኖት ክርክር ብይን መስጠት ቢችሉም በውሳኔያቸው መሳሳት የሚችሉ፣ ሊታረሙ የሚችሉና የበላይና የመጨረሻ ውሳኔ መስጠት ለሚችል ለመጸሃፍ ቅዱስ የተገዙ ባለስልጣናት ናቸው የሚል ትምህርት ነው።
ስለሰማችሁኝ አመሰግናለሁ ተማሪዎች 😁
ፈይሳ ምሽት ተመኘሁላችሁ 😀

2 days, 1 hour ago

ጤናማ የሆነ የቤተ ክርስቲያን መረዳት ጤናማ የሆነ የወንጌል መረዳትን ያስከትላል። ጤናማ ያልሆነ የቤተክርስቲያን መረዳት ደግሞ ጤናማ ላልሆኑ አስተምህሮዎች በር ከፋች ናቸው።

በክርስቶስ የሆነ ሁሉ እሱ ራስ የሆነላት ቤተክርስቲያን ውስጥ የተተከለ ነው። ራስ በሆነው በኢየሱስ ላይ የተተከለው ደግሞ በአካሉ ውስጥ በመሆን ቅቡእ ከሆነው ኢየሱስ መንፈሳዊ መብሎችን ሁልጊዜ የሚቀበል ብልት ይሆናል።

በክርስቶስ በኩል ወደ አካሉ እንጨመራለን። በአካሉ ላይ በመጣበቅ የክርስቶስ የሆኑ የመዳን በረከቶችን በሙላት እንቀበላለን።

ቤተክርስቲያንን የምንወዳት ጌታችንን ኢየሱስን ስለምንወድ ነው። የአዳኛችንን ጸጋ በግላችን ከምንቀበለው በበለጠ በአካሉ ውስጥ ሆነን የምናገኛቸው በረከቶች እጅጉን የላቁ ናቸው።

ቤተክርስቲያን መድሃኒት ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ የምታቀርበን፣ ክርስቶሳዊ ህይወትን በሙላት እንድናገኝ የምታደርግ የንጉሱ የኢየሱስ የቃልኪዳን ሙሽሪት ናት።
ReformedEcclesiology

2 days, 3 hours ago

ተስፋ ቆርጠህ፣ ረዳት ኣጥተህ፣ በድካም ተውጠህ፣ የነበረህ እምነትህ ክዶህ፣ ጉንጭህ በእንባ ታጥቦ፣ በወዳጆችህ ልብህ ተሰብሮ፣ ፈተና በስቶብህ መውጫ መንገድ ርቆህ፣ እሾህ ዙርያህን ከቦ፣ ጠላት ወጥመዱን ዘርግቶ፣ በኣለም ጫጫታና ዋይታ ነፍስህ ዝሎ ሁሌ ልትሰማ የሚገባህ መዝሙር …
….
“ተስፋ ቆርጬ በእንባ ሳለሁ፤
የኣንተን ድምጽ ስሰማ እነቃለሁ።
ኣይዞ ባይ ነህና ደካማ ኣጽናኝ፤
የፈረሰውን እምነት ጠጋኝ። “
ዶ/ር ደረጀ ከበደ

2 days, 9 hours ago

ስለ አብዛኛው የጴንጤ ነቢያቶች ምንም የማንልለው ለምንም ስለማይበቁ ነው። መገረፍ ያለባቸው ወንጀለኞች፣ አማኑኤል መግባት የነበረባቸው እብዶች፣ የአምላክን ስም የሚያስነቅፉ ጸረ ወንጌሎች፣ ክርስቶሳዊ ትምህርት ሳይሆን የጥንቆላ ልምምድ የሚለማመዱ፣ ያለ አእምሮ የሚመላለሱ ቅዠታሞች ናቸው።
ፕሮ አለሙ በዚህ 10 አመት ውስጥ በነጻ ዝውውር ለነ አኬ ማዘዋወር ከምንፈልጋቸው ሰዎች መሃል በስመ ነቢይ ቸርች ከፍተው ምእመን አስከትለው የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን እያሰብን ነው። እስቲ ጫረታ እያወጣን እንሸጥላችኋለን😁
የነርሱ ቤት ለነዚህ አይነት ማፊያዎች ጥሩ መድሃኒት አላቸው። ወስደው አስተካክለው ጠርበው ቢያንስ ኖርማል ሰው ቢያደርጓቸው።

የክርስቶስ ልደት በኬክ ካላከበርሁ የሚል ድልብ ነቢይ አይቼ ይህን ጻፍሁ

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana