ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago
Church Infallibilityን ያልተረዳ ሙግት
"ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ጠባቂና ባለ አደራ ናት ነገር ግን ይህ ብቻ ቤተክርስቲያንን infallible አያደርጋትም በአንድ ነገር ትክክል ኾነች ማለት በኹሉ ነገር ትክክል ናት ማለት አይደለምና።" የሚለው የፕሮቴስታንቶች ሙግት ነው። ነገር ግን ይህ ሙግት የቤተክርስቲያንን አይሳሳቴነት የተረዳ አይመስልም እኛ ቤተክርስቲያን በኹሉ ነገር ትክክል ናት አላልንም እኛ ያልነው ቤተክርስቲያን በአባቶች ስምምነት ባስተማረችው አስተምህሮ ላይ ስህተትን ልትሠራ አትችልም ነው።
ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ስትወስን ከተጠቀመቻቸው መሥፈርቶች ውስጥ "ሐዋርያዊ ጸሐፊነት (ከሐዋርያትና የእነርሱ ቅርብ ደቀ መዛሙርት) ፣ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነትና ትክክለኛ አስተምህሮ" ይገኙበታል። መሥፈርቶቹ እነዚህ መኾናቸውን ፕሮቴታንቶች ራሱ የሚቀበሉት ነው። እስቲ ከነዚህ መሥፈርቶች ትክክለኛ አስተምህሮን ለይተን እንየው። ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ስትወስን ከነበሩት መጽሐፍት ውስጥ ትክክለኞቹን የለየችው ከሐዋርያት በተቀበለችው ትክክለኛ አስተምህሮ መዝና ነው የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ደግሞ ሊሳሳት ስለማይችል መጽሐፉም ሊሳሳት አይችልም እንላለን።
ፕሮቴስታንቶች ግን ቤተክርስቲያን በአስተምህሮዋ ልትሳሳት ትችላለች ብቻ ሳይኾን ተሳስታለች ብለው ያምናሉ ስለዚህ ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን የመረጠችው በተሳሳተ መሥፈርት ነው። መሥፈርቱ ከተሳሳተ ደግሞ የመሥፈርቱ ውጤትም ስህተት ያለበት ነው የሚኾነው። Fallible list of infallible books ነው የምንቀበለው ቢሉ ራሱ እነዛ listኡ ብቻ ሳይኾን መጽሐፍቱም ጭምር ከመጀመሪያውኑ infallible ለመኾናቸው ምሥክርነት አይኖራቸውም መጽሐፍቱ ራሱ የተመረጡት በተሳሳተ መሥፈርት ላይ ተመርኩዘው ነውና።
የሕፃናት ቁርባን
ከካቶሊኮች እና የክርስቶስን ሥጋና ደም አማናዊነት ከሚመቀበሉ ፕሮቴስታንቶች ዘንድ አንድ ግርም ያለኝ ልምምድ ሕፃናትን ቁርባን መከልከላቸው ነው። በእነዚህ "አብያተ ክርስቲያናት" ሕፃናትን ማጥመቅ ትክክል እንደኾነ ይታመናል በተለይ በካቶሊክና በሉተራን ዘንድ ሕፃናት የሚጠመቁት ለድኅነትና ለዳግም ልደት ነው። ነገር ግን እንደዚህ ዳግመኛ በክርስቶስ የተወለዱ ሕፃናት ቁርባን ይከለከላሉ። በጥምቀት የክርስቶስ አካላት ከኾኑ የክርስቶስን አካላት ሥጋና ደሙን እንዴት ይከለከላሉ? በተለይ የጥንቷ ቤተክርስቲያን ሕፃናትም መቁረብ እንዳለባቸው በግልጽ ባስተማሩበት ኹኔታ።
ቅዱስ አውግስጢኖስ ዘሂፖ እንዲህ ይላል "በሕፃንነት ውስጥ ኢየሱስ የሚያድነው ምንም ነገር የለውም የሚሉ ለእነዚህ ለሚያምኑ ሕፃናት ክርስቶስ ኢየሱስ መኾኑን እየካዱ ነው ... ኢየሱስ ምን ማለት ነው? ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ነው። በእነርሱ ምንም የሚያድነው የለም ማለት ክርስቶስ ለእነርሱ ኢየሱስ አይደለም ማለት ነው። ለተጠመቁ ሰዎች ክርስቶስ ኢየሱስ አይኾንላቸውም የሚለውን ሃሳብ የምትታገሱ ከኾነ እምነታችሁ ጤናማና ርቱዕ ነው የሚለው ያጠራጥረኛል። አዎ ሕፃናት ናቸው ነገር ግን ምሥጢራቱን ይቀበላሉ፤ ሕፃናት ናቸው ነገር ግን በራሳቸው ሕይወት እንዲኖራቸው ከጠረጴዛው ይካፈላሉ።" (Augustine, Sermon 174, 7)
የሐዋርያት ድንጋጌም እንዲህ ይላል "ጸሎቱን የጸለያችሁ ንዑሰ ክርስቲያን ፣ ሰሚዎችና መናፍቃን ኹሉ ውጡ ማንም አይቆይ። እናቶችም ከልጆቻቸው ጋር ይቁረቡ" (Constitutions of the Holy Apostles, 8.2.12)
ኢየሱስ የሕፃናትም መድኃኒት ነው!
"Therefore, Christ Himself is the doctrine of the Father. He is the Word of the Father, and what Christ teaches is Himself so that believers may acquire Him. He is both the doctrine and the One who is of the Father. He is the divine, unchangeable doctrine—not merely a teaching expressed in words and letters, but the One who is eternally one with the Father. He leads us to the Father for reconciliation and conformity with His love." St. Augustine: On the Gospel of St. John, tractate 29:3
ኧረ ምን አይነት ንግግር ነው ቅዱስ አውግስጢኖስ ልቤን አቀለጠው የማይለወጥ ዶግማችን ኢየሱስ ነው ❤️
ስንፈጠር Vegan ነን ፤ በመጨረሻው ዘመንም ወደ Vegaንነት እንመለሳለን
“አሁን ላይ ብዙ አውሬዎች ፍሬ እንደማይበሉ አልነበረም፤ ያኔ ግን ነብር ምን ፍሬ ይበላ ነበር? አንበሳውን የሚያጠነክረው የትኛው ፍሬ ነው? ነገር ግን እነዚህ ፍጥረታት ለተፈጥሮ ሕግጋት ሲገዙ ፍሬ በልተዋል። [የመጀመሪያው] ሰው አኗኗሩን ሲቀይር እና በእርሱ ላይ የተጣለውን ገደብ ባሻረ ጊዜ፣ ጌታ፣ ከጥፋት ውሃ በኋላ፣ የሰው ልጆች አባካኝ መኾናቸውን አውቆ ፣ ኹሉንም ምግቦች እንዲጠቀሙ ፈቀደላቸው፡- “ኹሉንም ምግብ እንደ እፅዋት ይኹኑላችሁ። ” በማለት ተናግሯል። [የሰው ልጆች] ይህ ስለተፈቀደላቸው፣ ሌሎቹ እንስሳም [ሥጋ] የመብላት ነፃነት አግኝተዋል። ስለዚህ አንበሳው [አሁን] ሥጋ በላ ኾነ፣ አሞራም ሥጋን ይፈልጋል።
ያኔ ፍጥረት ገና አልተከፋፈለም ነበር ኹሉም ነገር አዲስ ነው። አዳኞች አያድኑም ሰዎች ገና ሥጋ መብላት አልጀመሩምና። አውሬዎችም ሌሎች እንስሳትን አይበሉም ነበር ገና ሥጋ ተመጋቢ አልነበሩምና ... የመጀመሪው ፍጥረት እንዲህ ነበር በመጨረሻው ዘመንም ፍጥረት ወደ ጥንቱ ይመለሳል።
ሰዎች ጠላትነትን በመተው ወደ ጥንት ፍጥረታቸው ይመለሳሉ ... የዕለት ተለት ጭንቀትን ባርነትን በመተው ወደ ደስታ ሕይወት ይመለሳሉ፤ ወደዛ በሥጋ ምኞቶች ወደ አልታሰረ ሕይወት ፤ ወደ እግዚአብሔር የቀረበ ከመላእክት ጋር ወደ ምንሳተፍበት ሕይወት። " (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፡ On the Origin of Man)
ሥጋ መብላት የኃጢአት ውጤት እንጂ የባሕርይ አይደለም፤ እንደ ጥንተ ፍጥረታችን እንኖር ዘንድ በጾም ወራት vegan በመኾን የገነት ኑሮን እንለማመዳለን። የጾመ ነቢያት ማሟሟቂያ ?
"አትሳቱ እግዚአብሔር አይዘበትበትም።( ገላትያ 6፡7) ነገር ግን የመርቅያን አምላክ ይዘበትበታል፤ እንዴት መቆጣትና መበቀል እንዳለበት አያውቅምና" (ሊቁ ጠርጡሊያኖስ ዘቅርጣግና) ?
ሊቁ ይሄን ያለው መርቅያን የብሉይ ኪዳኑ አምላክ ክፉ አምላክ ነው በብሉይ ከመጠን በላይ ቁጣውን ሲያሳይና ሲቀጣ እናየዋለንና ከሐዲስ ኪዳኑ አምላክ ጋር አንድ አይደለም በማለቱ ነው። ስለዚህም የመርቅያን የሐዲስ ኪዳኑ "ደግ" አምላክ ቁጣውን ማሳየት እና መቅጣት እንኳን የማይችል ደካማ አማላክ ነው እና ይዘበትበታል ይለናል ጠርጡሊያኖስ ቀልድ አዋቂ አይደል እንዴ ?
በእንተ ማር ይስሐቅ ሶርያዊ (St. Isaac of Nineveh)
ማር ይስሐቅ (ማር ማለት በሱርስት ቋንቋ ቅዱስ ማለት ነው) በ7ተኛው ክፍለ ዘመን የነበረ በምንኩስና ላይ በጻፋቸው ጽሑፎቹ በዓለማቀፋዊቷ ቤተክርስቲያን ያለ ልዩነት በቅድስና የሚታወቅ ታላቅ አባት ነው (በOriental and Eastern Orthodox, በCatholic , በAssrian Church of the East , በ Ancient Church of the East)። በእነዚህ ኹሉ አብያተ ክርስቲያናት ተወዳጅ ያደረገው በምንኩስና ላይ የጻፋቸው ጽሑፎቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት በማግኘታቸው ነው። እነዚህ ሥራዎች Ascetical Homilies of Isaac the Syrian ሲባሉ በኢትዮጵያም ከሦስቱ መጻሕፍተ መነኮሳት ውስጥ አንዱ ኾኖ በጉባኤ ቤት ማር ይስሐቅ በመባል ይታወቃል።
ታድያ ይህ አባት በቤተክርስቲያን ደረጃ የነበረባት የእኛዋ Oriental Orthodox ሳይኾን አሁን ላይ ወደ ብዙ ቦታ የተከካፈለችው ብዙ ጊዜ በንስጥሮሳዊነት በምትታማዋ የጥንቷ Church of the East ውስጥ ነው። (ይህቺ ቤተክርሲያን አሁን ላይ ብዙ ቦታ ተከፋፍላች እንጂ የለችም ብዙ ሰው Church of the Eastንና Assyrian Church of the Eastን አንድ አድርጎ ያስባል ነገር ግን Assyrian Church of the East , የ17ተኛው ክፍለ ዘመን የChurch of the East ክፍልፋይ ውጤት ናት እንጂ አንድ አይደሉም። )
Church of the East , የፋርስ ቤተክርስቲያን (Persian Church) ስትባል ጉባኤ ኤፌሶን ከመደረጉ ከ7 ዓመታት በፊት በ424 ዓ.እ ነው ከሮማ ቤተክርስቲያን እራሷን የለየችው። ይህ መለያየትም የፖለቲካ ውጤት ነው እንጂ የሃይማኖት አይደለም ሮምና ፋርስ ብዙ ጊዜ ወደ ጦርነት የሚገቡ እርስ በእርስ ጠላቶች በመኾናቸው በኹለቱ አብያተክርስቲያናት መካከል ግኑኝነቱን አሻክሮታል ከዚህ በተጨማሪ የቋንቋ ልዩነትም ነበር በምስራቅ ያለችው የሮሟ ቤተክርስቲያን በዋነኛነት ግሪክ ተናጋሪ ስትኾን ፣ የፋርሷ ቤተክርስቲያን ግን ሱርስት ( Syriac) ተናጋሪ ናት። በዚህ መለያየት ምክንያት በሮሟ ቤተክርቲያን 3ተኛው ዓለም አቀፍ ጉባኤ በ431 ዓ.እ በኤፌሶን ሲጠራ የፋርሷ ቤተክርስቲያን መሳተፍ አልቻለችም። በዚህ ጉባኤ ንስጥሮስ ሲወገዝ በእርሱ መወገዝ ያልተስማሙ ሰዎች ከሮም ወተው ወደ ፋርስ በመሔድ የቴዎዶሮስ ዘመፕሶስትያን (Theodore of Mopsuestia) ትምህርት ሳያስፋፉ አልቀረም። በ7ተኛው ክፍለ ዘመን ከፋርሷ ቤተክርስቲያን የተነሣው Babai the Great , (ይሑፎቹ ላይ የመፕሶስቲያው ቴዎዶር ተጽእኖ ይታይበታል) Book of Union በተባለ መጽሐፉ ክርስቶስ በአንድ Prosopa ያለ መለያየት 2 Qnoma አሉት በማለት ነገረ ክርስቶስን አብራራ (Prosopa እና Qnoma የሱርስት ቃላት ሲኾኑ Prosopa እኔ ባይነት ያለው አካል ነው፣ Qnoma ደግሞ ባሕርይ ነው።) ይህች የፋርስ ቤተክርስቲያንም የእርሱን አስተምህሮ በ7ተኛው ክፍለ ዘመን Official አስተምህሮዋ አድርጋዋ ተቀብላለች።
ታድያ ማር ይስሐቅም ከዚህች ቤተክርስቲያን ሥር በዚህ ነገር ክርስቶስ ላይ ውዝግብ ውስጥ በነበረበት ጊዜ ነው የነነዌ ሊቀ ጳጳስ ኾኖ የተሾመው። ብዙ ጊዜ ከእኛ ቤተክርስቲያን ውጪ ኾኖ ሳለ እንዴት በእኛ ቤተክርስቲያን በቅድስና ሊጠራ ቻለ ተብሎ ሲጠየቅ ይህቺ ቤተክርቲያን በነገረ ክርስቶስ ላይ ውዝግብ ላይ ሳለች እርሱ ኦርቶዶክሳዊውን ትምህርት በመያዙ ነው ተብሎ ይመለሳል። ነገር ግን ይህ መልስ አጥጋቢ አይደለም በእኛ ቤተክርስቲያን ማር ስይሐቅ ተብሎ በሚጠራው መጽሐፍ ውስጥ አዎ ምንም አይነት ም*ቅና የለም ሙሉ በሙሉ ኦርቶዶክሳዊ ነው፤ ነገር ግን የማር ይስሐቅ ሥራዎች በሙሉ አልተተረጎሙም ነበር። በቅርቡ በሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ የተጠመቀመው በሶርያ ጥናቶች (Syriac Studies) ላይ እውቅ ምሁር Dr. Sebastian Brock ያልተተረጎሙ የማር ይስሐቅ ሥራዎችን በማግኘት ማሳተም ችሏል ይህ ሥራ "Isaac of Nineveh (Isaac the Syrian): The Second Part, Chapters 4-41 (Corpus Scriptorum Christianorum Orientalium" በመባል ይታወቃል በዚህ ሥራ ላይም አንዳንድ ንስጥሮሳዊ ሃሳቦች እና ምቅናዎች ይገኛሉ ለአብነት ይህን ላሳይ፡
"ኹሉም ነገር የሚነገርለት እርሱ [መለኮት] በእርሱ [ትስብዕት ] ላይ አደረበት፤ መለኮታዊ ክብሩን እና ሥልጣኑንም ሰጠው... መላእክትም እንዲሰግዱለት አደረገ ... ከእርሱ ጋር ያለ ልዩነት እንዲመለክም አደረገው፤ ይህም ጌታ የኾነው ሰውና መለኮት በአንድነት እንዲመለኩ ነው፤ ኹለቱ ባሕርያት የክብር መለያየት ሳይኖርባቸው በመጠባበቅ አሉና" (H Alfeyev, The Spiritual World of Isaac the Syrian, Cistercian Publications, Michigan, 2000, pp. 54-5)
ይህ ፍጹም ንስጥሮሳዊ አስተምህሮ ነው ቅዱስ ቄርሎስ በAnathema 8 ላይ "ማንም ሰው በቃል የተነሣው ሰው ፤ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በአንድነት ይመለካል የሚል ቢኖር የተወገዘ ይኹን" ሲል ያወግዛል። Father Tadros Malatyም በዚህ ሃሳብ ይስማማሉ እንዲህ በማለት "ይስሐቅ መስቀል የእግዚአብሔር ማደርያ ለኾነው ሰው ምሳሌው ነው ያላል፤ መስቀል "መለኮት ባደረበት ሰው" ስም የተሠራ ነው በማለት የክርስቶስን ሰውነት የመለኮቱ ማደርያ ልብስ ያደርገዋል።(Part II / 11-24) ይህ ጽሑፍ የሚያሳየው የይስሐቅ ነገረ ክርስቶስ ንስጥሮሳዊ እንደኾነ ነው" ( Fr. Tadros Malaty, A PANORAMIC VIEW OF PATRISTICS)
ይህን ስጽፍ ማር ይስሐቅ ቅዱስ አይደለም ለማለት አለመኾኑን ልብ ይበሉልኝ። ምክንያቱም ቅዱሳን ኹል ጊዜ ፍጹም ትምህርት የላቸውም ሰው እንደመኾናቸው አንድ አንድ አስተምህሮ ሊስቱ ይችላሉ፤ ማር ይስሐቅም የነበረበት ቤተክርስቲያን ከሌላው ዓለም ተገላ የዓለም አቀፍ ጉባኤ እንኳን መሳተፍ ያልቻለች ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለኾነ ባልተሳተፈበት ጉባኤ አተስተምህሮ ልንወቅሰው አንችልም።
ለሕይወት እንጠይቅ
"የዘለዓለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ?"ይህን ጥያቄ ጌታን የጠየቀው አንድ ሃብታም ወጣት ነው። ይህ ወጣት የጥያቄውን መልስ ባይተገብረውም የጠየቀው ጥያቄ ግን በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ነው። እኛ የሰው ልጆች የተፈጠርነው ለሕይወት ነው ለሕይወት ተፈጥረን ሳለ ግን በዙሪአችን ባሉ distraction ተስበን ዋና ዓላማችንን ችላ እያልን ነው። ክርስቶስ የሞተው በእርሱ ለዘለዓለም እንድንኖር ነው ፣ የክርስቶስ ተከታዮች ክርስቲያን የኾነውም ከክርስቶስ ጋር ለዘለዓለም ለመኖር ነው። አብዛኞቻን ግን ክርስቲያን የኾነው በክርስቶስ ለመኖር ሳይኾን ነፍስ ካወቅን ጀምሮ እራሳችንን በክርስትና ውስጥ ስላገኘነው ነው። ስለዚህም የምንጠይቃቸው ጥያቄዎችም ለሕይወት የሚኾኑ አይደሉም። "በሚካኤል ቀን ልብስ ይታጠባል?" ፣ "አሳማ ይበላል?" ፣ " በሰንበት ቡና ይወቀጣል?"፣ " የሙስሊም ሥጋ የበላ ሰው ቄደር ይጠመቃል?" እያልን ለድኅነት እንኳን ረብ የሌላቸው ጥያቄዎች ላይ ጊዜ እናጠፋለን።
እንዲሁም ልክ ለመንጻት ሥርዓት ብቻ እንደሚጨነቁ ፈሪሳውያን ሰውን በየእያንዳንዱ ነገሮች እያሳቀቅን ከክርስቶስ እናርቃለን እንደው በጌታ "በበዓል ቀን ወፍጮ ፈጨህ ፣ ሥራ ሠራህ"፣ "የአርሴማን ጸበል ተጠምቃ ቡና ጠጣች" ፣ " በማርያም ቀን ልብስ አጠብክ" ፣ " በወር አበባ ላይ ኾና ጸበል ጠጣች" እያሉ ክርስቲያኑን ማሳቀቅ ተገቢ ነው? ይህ በክርስትና ውስጥ የተደበቀ ፈሪሳዊነት ነው! ክርስቶስ አሁን ቢመጣ ኖሮ "ሰንበት ለሰው ተሠራች እንጂ ሰው ለሰንበት አልተሠራም" ብሎ ፈሪሳውያንን እንደ ወቀሰ አንደኛ ተወቃሾች እኛ ነበርን።
ክርስቲያን የኾነው በክርስቶስ የዘለዓለምን ሕይወት እናገኝ ዘንድ ነው ስለዚህ የኹል ጊዜ ጥያቄያችን "ወደ ክርስቶስ እንዴት ልቅረብ?" ፣ "የዘለዓለም ሕይወትን እንዴት ላግኝ?" ይኹን ለሕይወት እንጠይቅ፤ ፈሪሳዊነት ከመካከላችን ይውጣ!
"ኦ ወልድ ዋሕድ፣ እግዚአብሔር የወደድከን ቃል ሆይ፣ ከፍቅሩ የተነሣ ከዘለዓለም ሞት ሊበዠን ወደደ።
በመቤዠቱ መንገድ ላይም ሞት ስለነበር ከፍቅሩ የተነሣ በዚሁ መንገድ ሊያልፍበት ወደደ። ስለዚህም የኃጢአታችንን ቅጣት ይሸከም ዘንድ መስቀል ላይ ወጣ።
የበደልነው እኛ ነን፤ መከራን የተቀበለ እርሱ ነው።
በኃጢአት ምክንያት ለመለኮታዊ ፍትሕ ባለ ዕዳ የኾነው እኛ ነን፤ ስለእኛ ዕዳውን የከፈለው ግን እርሱ ነው።
ስለ እኛ ከደስታ ይልቅ መከራን፣ ከዕረፍት ይልቅ ድካምን፣ከክብር ይልቅ መናቅን፣ ኪሩቤል ከሚሸከሙት ዙፋንም ይልቅ መስቀልን መረጠ።
ከኃጢአት እስራት ነጻ ያወጣን ዘንድ በገመድ ለመታሰር እራሱን አሳልፎ ሰጠ። እኛን ከፍ ያደርገን ዘንድ እርሱ ዝቅ አለ። ያጠግበን ዘንድ እርሱ ተራበ፤ ጥማችንንም ይቆርጥ ዘንድ ተጠማ።
የእርሱን የጽድቅ ልብስ ያለብሰንም ዘንድ እርቃኑን መስቀል ላይ ዋለ። ወደ እርሱ ገብተን የጸጋው ዙፋን ላይም እንቀመጥ ዘንድ ጎኑን በጦር ይወጋ ዘንድ ከፈተ።
በእውነት ሞተ፤ በመቃብርም ተቀበረ፤ እንዲሁም ከኃጢአት ሞት አስነሥቶ የዘለዓለም ሕይወትን ይሰጠን ዘንድ ተነሣ።
ኦ አምላኬ ራስህን የወጉት እሾኾች የእኔ ኃጢአቶች ናቸው፤ በዚህ ዓለም ከንቱ ደስታ ተደስቼ ልብህን ያሳዘንኩት እኔ ነኝ።
ኦ አምላኬ ፣ መድኃኒቴ ይህ የምትሔድበት ወደ ሞት የሚያደርሰው መንገድ ምንድነው?
ይህ በትከሻህ የተሸከምከው ምንድነው? ይህ ስለእኔ የተሸከምከው የውርደት መስቀል ነው።
ኦ ቤዛዬ ሆይ ይህ ምንድነው? ለእዚህ ፈቃደኛ እንድትኾን ያደረገህ ምንድነው?
ታላቁ ይጠላልን? ክቡሩ መከራን ይቀበላልን? ልዑሉ ይዋረዳልን? ኦ የፍቅርህ ታላቅነት።
አዎ ስለ እኔ ይህን ኹሉ መከራ እንትታገስ ያደረህ የፍቅርህ ታላቅነት ነው።
ኦ አምላኬ አመሰግንሃለሁ፤ መላእክቶችህ ከፍጥረታትህ ኹሉ ጋር ስለእኔ ምስጋናን ያቀርቡልሃል ፤ እኔ ለፍቅርህ የሚመጥን ምስጋናን ማቅረብ አይቻለኝምና! ከዚህ የሚበልጥ ፍቅርን አይተን እናውቃለን?
ኦ ነፍሴ ሆይ በሩህሩሁ ቤዛዬ ላይ ይህን ኹሉ መከራ ስላደረሰው ኃጢአትሽ እዘኚ ። ቁስሎቹን በፊትሽ ሳዪ የጠላት ቁጣ ሲነሳብሽም በእርሱ ተስፋ አድርጊ።
ኦ አዳኜ ሆይ መከራህን ሀብቴ ፣ የእሾህ አክሊልህን ክብሬ፣ ኃዘንህን ደስታዬ፣ ምሬትህን ማጣፈጫዬ፣ ደምህን ሕይወቴ ፣ ፍቅርህንም ኩራቴና ማመስገኛዬ አደርግ ዘንድ እርዳኝ።
ኦ ስለ ኃጢታችን የቆስልህ ፣ በቁስልህም የተፈወስን ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማሕየዊ በኾነው መለኮታዊ ፍቅህ አቁስለኝ። ኦ ትቤዠኝና ሕይወትን ትሰጠኝ ዘንድ ስለ እኔ ሞትን የተቀበልከው ሆይ በመስቀልህ ደም ከኃጢአቴ አንጻኝ፣ በፍቅርህም አጽናናኝ።
ኦ እውነተኛ የወይን ግንድ የእኔ ውድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እንደ ደረቀ ተክል አካል ካየኸኝ በጸጋህ ዘይት አለስልሰኝ ሕያው እንደኾነ ቅርንጫፍም በአንተ አጽናኝ። " (Coptic Fraction to the Only Begotten Son )
ኦ ወልድ ዋሕድ መድኃኔዓለም ሆይ ሥራህ ድንቅ ነው ❤️
ክርስቶስ ጽጌ ጸአዳ ወቀይሕ
ነጭና ቀይ አበባ ክርስቶስ
“ውዴ ነጭና ቀይ ነው፥ ከእልፍ የተመረጠ ነው።”
— መኃልየ. 5፥10
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 2 weeks ago