ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
ህይወት ምርጫ አላት ይሉኛል ለኔ ግን
.
.
.
.
ዳሽ ሙላ ነው የሆነችብኝ???
@YazLekk For More
የእጅ ሰአት ልትገዛ ሂደህ 2500ብር ሲለህ
.
.
.
.
ምሳ ሰዓት ሲደርስ ይጋብዘኛል እንዴ???
@YazLekk For More
ከመጥፎ ሰዎች ጋር ጣፋጭ ነገር ከምትበላ
.
.
.
.
ከደጋግ ሰዎች ጋር ድንጋይ ብትሸከም ላንተ የተሻለ ነው!!???
@YazLekk For More
?♂?♀
ጠዋት ወደ ስራ ስሄድ መንገድ ላይ ማያት ቆንጅዬ ልጅ አለች፤ ብዙ ጊዜ ምንተላለፈው ፎቶ? ቤቱ ጋር ነው። በየቀኑ ስለምንተያይ ምንተዋወቅ ነው ሚመስለኝ፣ የሷም አስተያየት እንደምንተዋወቅ ነገር ነው። አንዳንዴ ፎቶ ቤቱ ጋር ካላየዋት “‘ምን አገኛት?’ ብዬ ስትዘገይ እኔ ሰጋለሁ”(uk this song a?) ምናልባት ቀድሚያት መጥቼ ይሆናል ብዬ አስባለሁ፥ ሳያት ደስ ይለኛል። ፎቶ ቤቱ ጋር ቀድሜ ከደረስኩ ስንትላለፍ ‘ቀደምኩሽ’ ዓይነት አስተያየት ዐያታለው፤ እሷም ስትቀድመኝ “አንተ ከርፋፋ ቀደምኩ እኮ” አይነት ዕይታ ታየኛለች። አልዋሻችሁም እሷን ቀድሜ ፎቶ ቤቱ ጋር ለመድረስ ቶሎ ቶሎ ምራመድበት ቀን አለ፥ መንገዱ ወደድኩት። ብዙ ሰዎች እኮ አሉ እንደዚህ በተደጋጋሚ ምተላለፋቸው ግን አንድም ቀን ቦታ ሰጥቻቸው አላውቅም። “እንዴት ብዬ ላወዳድርሽ ከዚ ሁሉ ኮሳሳ”…lol
አንድ ሰሞን ግን ጠፋች። መንገዱም እንደወትሮ በሰው ጋጋታ የታጀበ ቢሆንም ለኔ ጭር አለብኝ። አናግሪያት ማላውቃት ልጅ ናፈቀችኝ? ዐይኔም እሷን በማጣቱ ጭው? አለ። ሁሌ ማያት ብቻዋን ስለነበር ስለሷ ማንን እንደምጠይቅ ግራ ገባኝ። ሶስት ቀን ሳላያት?። ብዙ ጊዜ ምንተላለፍበት ቦታ ጋር ቆሜ ያልቀጠርኳትን ልጅ እጠብቃት ጀመር?♂ ልትመጣ ግን አልቻለችም። ውስጤ ብዙ ሃሳብ ? ይመላለስ ጀመር ‘አሟት ይሆን?’ ወይስ ‘አስቀይሚያት ይሆን? እንዴት አናግሪያት ማላውቃትን ልጅ አስቀይማለሁ? ማይመስሉ ትንታኔዎች ውስጥ ገባው፣ ምን ሆና ይሆን በሚል ሃሳብ እንሳፈፍ ጀመር። ከዐይን ቋንቋ ባለፈ ይዣት አለማናገሬ እየከነከነኝ ነው። አንድ ሳምንት አመት ሆኖብኝ አለፈ። “የምወዳትን ልጅ አድርግልኝ ጎረቤት” ያለው አሁን ደርሶ ተሰማኝ።
ዛሬ ጠዋት መንገዴን 'ዐያታለው' በሚል ተስፋ ጀምሪያለሁ። ልጅ እንደጠፋበት ሰው መንገደኛውን ጎንበስ ቀና እያልኩ ዕቃኝ ጀመር። ከሩቅ ዐየዋት ?። አባቱ ከጦር ሜዳ ወደቤት ሲመጣ ልጅ እንደሚሆነው ሆንኩ። እየቀረበችኝ ስትመጣ ደህና መሆኗን ሳይ ፊቴ ፈካ☺️። “አንቺ አይደብርሽም እንዴ?” አልኳት የመጀመሪያ ቃሌ ይሄ ነበር፣ እንደዛ ያልኳት ስለጠፋች እንደሆነ ገብቷት “ቀጣይ ሳምንት እንደማልመጣ ልነግርህ ፈልጌ ነበር ግን እንዴት ብዬ” አለች። ከድምጿ ውስጥ ናፍቆት ይሰማል። ሁለታችንም በየራሳችን ትዝብት ውስጥ ገብተን ዝም ዝም ተባባልን። ያገጣሚ ነገር ይሁን ወይም እግዜር ጋብዞን ባላውቅም የጥላሁን “ፈልጌ አስፈልጌ ያን ሰሞን ያጣዋት፥ አወይ አጋጣሚ ድንገት ዛሬ ዐየዋት” ሚለው ዘፈን ከሚያልፉት መኪናዎች ስንሰማ ተያይተን ሳቅን። ትንሽ ስለ እራሳችን አወራን ከዛም ስልክ ቁጥር ተለዋወጥንና ቀጠሮ ይዘን ተለያየን።
የዚ አይነት አጠር ያሉ እና በውብ ቃላት የተከሸኑ አጫጭር ልብ ወለዶችን ለማግኘት Like እና Share በማድረግ አበረታቱን። እናመሰግናለን
@YazLekk For More
ቺኮች የሚወዱትን ልጅ አጥተው ሌላ ከጠበሱ በኋላ
.
.
.
.
ያሰበልኝንን ሲሰጠኝ ያሰብኩት አስጠላኝ???
@YazLekk For More
ልጅ እያለሁ አኩርፌ አልበላም ያልኩትን ምግብ ሳስብ
.
.
.
.
ውስጤ በፀፀት ይቆስላል???
@YazLekk For More
ለራሳቸው ዝቅተኛ ግምት ያላቸው ሰዎች
.
.
.
.
ሌሎችን የመተቸት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው???
@YazLekk For More
ዋጋህን ከሚያሳንስ ከማንኛው ቦታ ራስህን አርቀ!???
@YazLekk For More
ቀበሌ ሄደህ ማትጉላላው እሁድ ቀን ብቻ ነው
.
.
.
.
ዝግ ስለሚሆን???
@YazLekk For More
ሁሌም የሴቶች ዶርም ድረስ መጥቶ ሸኝቶኝ ሲመለስ ባለማመን ያዩታል።
<<ሔለን ግን ሙድ እየያዝሽብን ነዋ! ያን ሁሉ ወንድ ያባረርሽው ይሔ ፉንጋ ጋር ለመሆን ነው?>> ትላለች አንደኛዋ።
<<እስኪ ተያት ምን ታውቂያለሽ? ራቁቱን ያዬችው እሷ!>> ብላ ሌላኛዋ ታሽካካለች።
እኔም አስከፋናት ብለው እንዳይደብራቸው እስቅላቸዋለሁ። ዋና ምክኒያቴን ከሚያውቁብኝ የጠረጠሩት እውነት እንደሆነ እንዲሰማቸው ባደርግ ይሻለኛል።
ለሰው ባይመስልም ፉንጋው የፀሎቴ መልስ ብቻ ሳይሆን ጨለማ ክፍል ውስጥ ያገኘሁት ሻማዬ ነው።
<<ሔሉዬ ሌላ ቅፅል ስም ጠፍቶ ነው 'ሻማዬ' የምትይኝ?>> ይለኛል።
<<ሻማዬ ካላልኩህ ችቦዬ ነው የምልህ...የቱ ይሻልሀል?>>
<<አይ ሻማው ይሁን በቃ!>> ይላል እየተቅለሰለሰ።
አንዲት ፀበል ለፀበል የምትመላለስ ታላቅ እህት አለችኝ። ሰዎች መንፈስ ይዟት ነው እያሉ ያወራሉ። እኔ ግን ባሏን ፈትታ ከመጣች ቡኃላ የዘመድ አዝማዱን ወሬ አትችለው ብላ እንዳበደች አውቃለሁ። ከዛ ጊዜ ጀምሮ ፀሎቴ አንድና አንድ ብቻ ነው። <<ጌታ ሆይ የምወደውን ሳይሆን የሚወደኝን ስጠኝ!>>
ለዛ ነው ሻማዬ የፀሎቴ መልስ ነው የምለው። የመጀመሪያ ቀን ሰውነቱ በላብ ተጠምቆ፣ እጁ እየተንቀጠቀጠ፣ መተንፈስ አቅቶት እየቃተተ ሲጠይቀኝ እንደማገባው ወስኜ ነበር። የግቢውን ወንዶች ሁሉ መልሼ እሱን የጠበስኩት እነሱ እንደሚሉት የተለዬ ነገር አግኝቼበት አይደለም። ሪስክ መውሰድ ስለማልችል ነው።
የፈሪ ሰው ጥቅም?...ቀድሞ አያጠቃም!
ግቢ ውስጥ በኔ ምክኒያት ያልደረሰበት ግፍ የለም። ለሁሉም ታዋቂ ካፕሎች ቅፅል ስም ሲሰጡ እኛን ማን ቢሉን ጥሩ ነው? "beauty and the beast" ሆሆ!
ተረባውን ችሎ አለፍ ሲል ደግሞ መምህራኖች ግሬድ ያበላሹበታል። ጉልበተኞች ዱላ የቀላቀለበት ማስፈራሪያ ያዘንቡበታል። ዘበኞች እንኳን ባቅማቸው ያዋክቡታል። ሁሉም እንደየስልጣኑ ይበድለዋል።
<<ሻማዬ ከዚህ በላይ እንድትጎዳ አልፈልግም>> ስለው
<<ቀላል ነው ብዬ አልዋሸሽም። ሽልማቴ አንቺ እንደሆንሽ ሳስበው ግን 'ኧረ ያንሰኛል ጨምራችሁ ምቱኝ' ልላቸው ሁላ ያምረኛል!>>
እያሳዘነ ያስቀኛል።
ገፍተው ገፍተው ለራሱ ያለውን አመለካከት እንዳወረዱበት የገባኝ የአመቱ መጨረሻ ላይ ነው። እሱ ተመራቂ ስለነበር ቀጣይ አመት እንደማንገናኝ ገብቶት እያለቀሰ መጣ።
<<አንተም ስራ ልታገኝ የምትችለው እዚሁ አዲሳባ ነው። እኔም እዚሁ ነው የምማረው! ምን የተለዬ ነገር ተፈጠረና ነው የምታለቅሰው?>>
<<አንድ ነገር ብቻ ቃል ግቢልኝ!>> አለ አሁንም እያለቀሰ!
<<እሺ ምንድን ነው?>>
<<እስክትመረቂ ድረስ የፈለግሽው ወንድ ጋር ሁኚ! ከዛ ቡኃላ ግን ተመልሰሽ ወደኔ ልትመጭ ቃል ግቢልኝ!>>
ምንም አላልኩትም። በቆመበት ጥዬው ሔድኩ። ምን ባደርገው ነው ሊተማመንብኝ የሚችለው? እኔስ በዚህ ደረጃ ከሚወደኝ ወንድ ውጭ ሌላ ምን እፈልጋለሁ? ከሶስት ቀን ቡኃላ የሻማዬን ልብ ያረጋል ብዬ ያሰብኩትን ትልቅ ውሳኔ ወሰንኩ።
ሲያዬው አዲስ እንደተወለደ ህፃን ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ። ለነገሩ እኔም ከዛ ያነሰ ግብረመልስ አልጠበኩም። ይሔንን ፊት ለዘላለም እንዳይጠፋ አድርጌ ጀርባዬ ላይ ተነቅሼለት ለቅሶ ሊበዛብኝ ነው?
የሚያስቀው እንራራቃለን ብዬ ፊቱን ተነቅሼለት ሌክቸረር ሁኖ እዛው ግቢ ቀረ። የሚያሳዝነው ደግሞ ተማሪዎች በገቡ በመጀመሪያው ሳምንት ሁሉም ስለታቱዬ አወቁ።
የፈሪ ትልቁ ችግር.....ምርኮኛ አያያዝ አይችልም!
<<ለማን ተናግረህ ነው?>> ብዬ ሳፈጥበት...አብሮት ሌክቸረር ለሆነ ሰቃይ ጓደኛው ብቻ መናገሩን ነግሮ ይቅርታ ጠየቀኝ። እኔም ከተያዙ ቡኃላ መንፈራገጥ ጥቅም የለውም ብዬ ተውኩት።
የግቢው አየር ባንድ ጊዜ ተገለበጠ። ሻማዬ የግቢው ቁጥር አንድ ተፈላጊ ወንድ ሆኖ ቁጭ አለ። እኔ ደግሞ ስወጣ ስገባ የተረባ መለማመጃ ሆንኩ። አንዴ ወጣቶች ተወራርደው አስገድደው ልብሴን ገልጠው፣ ታቱዬን ካዩብኝ ቡኃላ ከሀዘን የወጣሁበት ቀን ትዝ አይለኝም።
ሻማዬ ሊጠብቀኝ ቀርቶ ቶሎ ቶሎ ሊያገኘኝ ራሱ ጥረት አያደርግም። እኔ ነኝ የምደውልለት። እንዲያውም አልናገርም ብዬ እንጂ አልፎ አልፎ የግቢው ታዋቂ ሴቶች ከቢሮው ሲወጡ አያለሁ። በአንድ ወቅት ሊነካኝ ከብዶት ሲንቀጠቀጥ የነበረ ሰው፤ ዛሬ መዳፉ ላይ ሲያገኘኝ ጨብጦ ሊያፈርጠኝ ሲዳዳ ባዬው...ለመረዳት ከበደኝ።
የሆነ ቀን ጉዳዩን ጨራርሰን እንደተቀመጥን <<ሰሞኑን መድሀኒት ስትጠቀሚ አላይሽም! ሌክቸረር ሆነ ብለሽ ልታረግዥብኝ ነውዴ?>> አለኝ። በዚች ንግግሩ ታሪኬን ቀዬረው።
ትምህርቴን አቋርጨ አዲስ ህይወት ጀመርኩ። ስሜንም ቀየርኩ። ታቱዬን ሙሉ ጥቁር አድርጌ "ብላክ ሆል" ነው እያልኩ መንገር ጀመርኩ። ሰላም ያለው ህይወት ለመኖር የነበረኝ አንድ አማራጭ ነበር። ሁሉንም ሰው ከህይወቴ አስወጥቼ ልጄን ማሳደግ። የዚያኔ እንደዛ ባለኝ ሰዓት ፀባዩ ሲስተካከል እነግረዋለሁ እያልኩ ያረፈድኩባት ፅንስ ነበረችኝ።
አሁን አሁን ሳስበው ታሪኬ ረጅም ይመስላል እንጂ አጭር ነው። ይቺው ናት ውጣ ውረዴ! ልጄን እስካሳድግ ድረስ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው ከቤተሰቦቼ ጋር የተገናኘሁት። እነሱም እምብዛም ሊያዩኝ አይፈልጉም። መላቀቅ ነው! ይቅሩብኝ ከነምላሳቸው! ምላስ ሽሽት ነው ነው ኑሮዬ!
አልፎ አልፎ ስር እንዳይሰድ አድርጌ የወሲብ ግኑኝነት እጀምራለሁ። እነሱም ስለኔ ትንሽ ማወቅ ሲጀምሩ ጥያቸው ዲዲዲዲዲዲ! በዚህ ርዕስ ላይ ከማወራ ይሻለኛል።
ልጄ በኔ መልክ ባባቷ ጭንቅላት በመውጣቷ ያገኛት ሁሉ ይወዳታል። እኔም በሷ እየተፅናናሁ እኖራለሁ። በቃ።
ይሔን ሁሉ ቁጭ ብዬ የማስበው ዛሬ <<አባቴ ማነው?>> ብላ ጠይቃኝ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ሩጨ የማላመልጣት ሰው ገጠመችኝ። የመመለስ ግዴታ እንዳለብኝ አውቃለሁ። ግን እንዴት ነው የአ'ምሮ በሽተኛ ሳላደርጋት ስለአባቷ ልነግራት የምችለው? ተረት ላድርገው ይሆን? እምብዛም የማይንቁት...እምብዛም የማያደንቁት የ'ንደኔ አይነቷ ኖርማል ሰው ህይወት እንዴት ነው የሚተረተው?
<<ተረት ተረት>>
<<የመሰረት>>
<<በድድሮሮሮሮ ጊዜ አንዲት ሔለን የምትባል ከብርጭቆዋ ጋር ጨለማ ክፍል ውስጥ የምትኖር ልዕልት ነበረች>>
<<እእእሽ>>
<<ሁሌም ሌቦች ብርጭቆዬን ይሰርቁብኛል ብላ ስለምትሰጋ ጨለማው ያስፈራት ነበር። ከዛ አንድ ቀን ምን ብታገኝ ጥሩ ነው?>>
<<ምን?>>
<<ሻማ! በጣም ደስ አላት። ሻማዋን አብርታ እያዬች ደስ አላት። ይቺ ሻማ እስካለች አልሰጋም ስትል አሰበች። ሻማዋ ግን እጠፋለሁ ብላ ትሰጋ ነበር። ንፋስ በመጣ ቁጥር ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል። ልዕልቷም ሻማዋን ከንፋስ ለማስጣል ብላ አንድ የሞኝ ውሳኔ ወሰነች!>>
<<ምን አደረገች?>>
<<በብርጭቆዋ ሸፈነቻት።>>
<<ከዛስ?>>
<<ከዛማ ሌባ ይገባል ብላ በር በሩን እያዬች ከኋላዋ ቃቃቃቃቃቃ የሚል ድምፅ ተሰማት። ደንግጣ ስትዞር የምትሳሳላት ብርጭቋዋ ናት። ንፋስ መቋቋም አቅቷት ልትጠፋ የነበረችው ሻማ በሙቀቷ ብርጭቆዋን ሰንጥቃባታለች። ልዕልቲቱ አዘነች። ውሀ አጣጯ ቢመጣም ውሀ መጠጫ እንደሌላት እያሰበች አለቀሰች! አለቀሰች!..>> እያለ የሚቀጥል ተረት!
ታሪኩን ከወደዳችሁትና እንደዚ አይነት አጫጭር ታሪኮችን እንድንፅፍላችሁ ከፈለጋችሁ በLike ግለፁልን።?*?*?**
@YazLekk For More
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana