Amhara Revolution

Description
ሀሳብ አስተያት መስጫ
👇👇
@Revolu1
@hyab5
✅የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው።
የአማራ ሕዝብን
✅ ፖለቲካዊ
✅ ማህበራዊ
✅ ኢኮኖሚያዊ
ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል።
✅ FANO ✅

🙅🙅🙅
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 1 week ago

4 weeks, 1 day ago
**የቅድመ ጥንቃቄ መረጃ - ለሁሉም ቀጠና …

የቅድመ ጥንቃቄ መረጃ - ለሁሉም ቀጠና ፋኖዎቻችን

ሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚገኙበትን ትክክለኛ መገናኛ ቦታ የሚያሳይ የ X እና Y ኮርዲኔት መረጃ ሁሌም በየ ዓመቱ እየተሰበሰበ ወደ ማዕከላዊ የመረጃ ቋት እንደሚላክ ለማወቅ ተችሏል።

ይህ መረጃ የሚሰበሰበውና የሚደራጀው በትምህርት ሚኒስቴር ስር ባሉ የተዋረድ መዋቅርና ትምህርት ቤቶች ሲሆን ይህ መረጃ "ፋኖዎች በትምህርት ቤቶች ካምፕ ሊያደርጉ ይችላሉ" በሚል በአገዛዙ ለድሮን ጥቃት እየተጠቀመበት ወይም ወደፊትም ሊጠቀምበት እንደሚችል ተጠቁሟል።

ምንም እንኳን ፋኖዎቻችን የትምህርት ተቋማትን እንደ ወታደራዊ ካምፕ የሚጠቀሙ ባይሆንም፣ ነገር ግን እዚህ ጋር ማስተላለፍ የፈለግነው ጥብቅ መልዕክት በአንድ አካባቢ አገዛዙ የድሮን ጥቃት መፈፀም ካቀደ ትምህርት ቤቶች ቀዳሚ የአገዛዙ ዒላማዎች መሆናቸውን ነው።

4 weeks, 1 day ago
የግል አስተያየት ነው። እናንተም በቀናዒነት ሓሳባችሁን …

የግል አስተያየት ነው። እናንተም በቀናዒነት ሓሳባችሁን ማጋራት ትችላላችሁ።

ጠላት እና ከጠላት ጋር አብሮ የወገነ ያው ሁሉም ጠላት ነው። እንዴውም የውስጥ ባንዳ፣ የወዳጅ ጠላት እጅግ ከባድ ነው። በመሆኑም አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ግድ ይላል።

ከላይ በምስሉ የምትመለከቷቸው አርሶ አደር አባት በስለላ ተጠርጥረው በአፋጎ ፩ኛ ክ/ጦር ባህርዳር ብርጌድ የተረሸኑ የሶስት ልጆች አባት አርሶ አደር ሽማግሌ ናቸው። ታድያ እንደዚ ያለ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ የአፋጎ ድርጅት እንደ ድርጅት ህጎችን ቢያወጣ እና ቢያፀድቅ እላለሁ እንደ Criminal law እና Civil code አይነት ጊዜያዊ ማስታገሻ ቢቀርፁ ጥሩ ይመስለኛል። ይህን ያጠፋ እንዲህ ዓይነት ይጠብቀዋል ቢባል ጥሩ ነው። "ይሰቀላል፣ መሬቱ ይወረሳል፣ መሬቱ አይታረስም፣ ይታሰራል ወይም የገንዘብ መቀጮ ይጣልበታል..." የሚሉ ነገሮች የድርጅቱ የህግ እና አስተዳደር ክፍሉ ቢሰራበት እና ቢያጤንበት እላለሁ። ከዚያ ውጭ ከሆነ ግን የዛሬ ሁለት ዓመት ላይ አባቴን ክስ ስላሸነፈው፣ እኔ ሰውየውን ባለኝ አሁናዊ power ላጥቃው የሚል ነገር ሊያስከትል ይችላል። በብልጽግናው መንግሥት ያለው ኢ-ፍትሃዊነት እና ሌሎች ጉዳዮች በፋኖዎችም እንዳይደገም በማለት ለወገን የቀረበ ወገናዊ ትችት ነው።

ሌላው እነኚህ ሽማግሌ አባት መቼም ድርጊታቸውም፣ ሆዳቸው ከሚማረኩት የዐብይ ወትደር እና የጦር ኮሎኔል አይበልጥምና እውነት ቢሆን እንኳ

  1. የተጠረጠሩበት ስለላ የተባለው ከመረሸን ይልቅ አስሮ፣ መርምሮ ማቆየት አይቻልም ወይ?

  2. ይህንንስ ከሰው ሰውኛ አንፃር እንዴት ታዩታላችሁ?

  3. የቅርብ ጠላትን ከማብዛትስ አንፃር እንዴት ትመለከቱታላችሁ?

የግል አስተያየት ነው። እናንተም ሓሳባችሁን ከስሜት በፀዳ መልኩ፣ ምክንያታዊ ሆናችሁ መግለጽ ትችላላችሁ።

4 weeks, 1 day ago

አጫጭር መረጃዎች

  1. አገዛዙ ሰሞኑን የድሮን ጥቃቶችን ለመፈፀም የእቅድ ዝግጅት ላይ እንዳለ የባህርዳር ዊክሊክስ ምንጮች መረጃ ያስረዳል። #ምክር ለወገን ኃይሎች፦ በማንኛውም ጊዜ በማንኛውም ቦታ የድሮን ጥቃትን ታሳቢ ያደረገ እንቅስቃሴ አይለያችሁ።

  2. የካቲት 05/2017 ዓም ሮቡዕ በምስራቅ ጎጃም አንዳንድ ቦታዎች የመንግስት ሰራተኞች ስብሰባ እንዲደረግ ተወስኖ እንቅስቃሴዎች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። ስብሰባው ዓላማ ያደረገው የመደበኛ የፖሊስ ሰራዊቱና የመንግስት ሰራተኛውን ከፋኖ መነጠል የሚል ነው።

  3. በሰሜን ሸዋ ያሉ የሃይማኖት አባቶችን በትናንትናው ዕለት ማለትም የካቲት 03/2017 ዓም ፋሽስታዊው አገዛዝ በአዲስ አበባ ሰብሰቧዋቸው እንደነበር ተነግሯል። #ጥቆማ በስብሰባው ተሳትፎ ከነበራቸው ሰዎች ተጨማሪ መረጃዎችንና ማጣራቶችን በአደረጃጀቶቻችን ለመሰብሰብ ይሰራ።

  4. አገዛዙ ወደ ጎጃም የላከው ኃይል መሽቶ በነጋ ቁጥር እየሟሸሸና እየቀለጠ መሆኑን ተረድቷል። እናም በቀጣይ ሁርሶ ወታደራዊ ካምፕን ተስፋ ማድረጉን ለማወቅ ተችሏል። እዛ አካባቢ ተጨማሪ መረጃዎችን እንፈልጋለን።
    Bw

3 months, 1 week ago

የሺ ደመላሽ - ፋኖ | Yeshi Demelash - FANO (Official Music) https://youtube.com/watch?v=UH9k37Z2I2E&si=1w9VyhKhvh19K_cy

3 months, 1 week ago

ሰበር ዜና!

በዳውንት ወረዳ ገበያ ገብይተው ሲመለሱ በነበሩ  ንፁኋኖች ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ከ50 በላይ የሚሆኑት መገደላቸው ታወቀ!

በሰሜን ወሎ ዞን ዳውንት ወረዳ ትናንት ህዳር 19/2017 ዓ/ም ገበያ ገብይተው በተሽከርካሪ ተሳፍረው ሲመለሱ በነበሩ ንፁኋን ወገኖች ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ከ50 በላይ የሚሆኑት ሕይወታቸው ማለፉን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

የድሮን ጥቃቱ የተፈፀመው በወረዳው ሰጎራ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ሲሆን፣ ህይወታቸው ካለፈ ንፁኋኖች በተጨማሪ በርካቶች ቆለው ወደ ህክምና ጣቢያ መወሰዳቸውን ነው የመረብ ሚዲያ የወሎ ወኪል የአይን እማኞችን በማነጋገር ለማረጋገጥ የቻለው።

ጥቃቱ የተፈፀመው ለደላንታ ወረዳ አዋሳኝ በሆነችው ልዩ ስሟ ሾጋ ተብላ በምትጠራ ቀበሌ ሀሙሲት ገበያ ገብይተው በተሽከርካሪ ተሳፍረው ሲመለሱ የነበሩ ገበያተኞች ላይ ነው ብለዋል ጣቢያችን ያነጋገራቸው ከጥቃቱ የተረፉ የአይን እማኞች።

በጥቃቱ ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች መካከል  የሸቀጣሸቀጥ ነጋዴዎች፣ ገበያ ለመገብየት የመጡ እናቶችን ጨምሮ አርሶ አደሮችና መምህራን እንደሚገኙበት የተገለፀ ሲሆን ከ50 በላይ የሚሆኑት ወዲያውኑ ነው ህይወታቸው ያለፈው ተብሏል።

ህዳር 20/2016 ዓ/ም በደላንታ ወረዳ ወገል ጤና ከተማ ላይ በተፈፀመ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የወላድ እናቶች አምቡላንስ አሽከርካሪን ጨምሮ ሌሎች አምስት የሚደርሱ የጤና ባለሙያዎች መገደላቸው ይታወሳል።

በጥቃቱ ህይወታቸው ካለፈ ንፁኋኖች በተጨማሪ ተሽከርካሪ አምቡላንሱ እና በተሽከርካሪው ላይ ተጭኖ የነበረ መድሃኒት ሙሉ በሙሉ መውደሙ የሚታወቅ ሲሆን፡ በተመሣሣይ በዓመቱ ከዚኸው ቀጠና በቅርብ ርቀት በንፁኋኖች ላይ ከፍተኛ እልቂት ያደረሰ ጥቃት ነው የተፈፀመው።

3 months, 1 week ago

?#ደንበጫ_የጠላት_መቅጫ‼️
~~~~~፲፩ኛው ቀን የተጋድሎ ውሎ
~~~~~በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ሁለት ሳምንት አለፈው ያለማቋረጥ ውጊያ ማድረግ ከጀመረ!!
ይህም ሆኖ ግን ጠላት እንደ ቅጠል እየረገፈ ነው።
አስራ አንድ ቀን ሙሉ የእጅ በእጅ ውጊያ ሲያደርግ የነበረው የኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ ትናንት ምሽት እስከ አንድ ሰዓት ድረስ ሲፋለሙት አምሽተው ጠላት በየጫካው ከተበተነ በኃላ ለአይን ሲነሳ ፋኖ ከምሽጉ ወጥቶ ቦታውን ሲይዝ ጠላት እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈረጠጠ።

ዙ23 ካልመጣና ሽፋን ካልተሰጠን ተከበናል አድኑን ያለው የወንበዴው ቡድን ከየጨረቃ ተነስቶ አንድ ዙ 23 አስከትሎ የተመታበትን ኃይሉን ሊያወጣ ቢመጣም ያሰበው አልተሳካለትም!!!

ዙ-23 የተበተነን ጦር ማስለቀቅ አይችልም።ይህንም በተግባር ደንበጫ ላይ አይተናል።

አንድ ጀግና ከእነ ጓዶቹ ጋር በጨለማ ተስቦ ዙ 23ቱን ዶግ አመድ አርጎ ሹፌርና ረዳቱንም እስከወዲያኛው አሰናበታቸው።

ጠላት ተደናግጦ ዙ-23 ሲቃጠል እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደ መጣበት ፈረጠጠ።ቀኑን ሙሉ ሲመታ የዋለው ኃይልም ከተበታተነበት ተለቃቅሞ የያዘውን ሸንሸል ተተኳሽ ሁሉ በየቦታው እየጣለ ራሱን ለማዳን ፈረጠጠ።
እጅግ ብዛት ያለው ተተኳሽና የቡድን መሳሪያ ከአነ ሸንሸሉ ተተኳሹን ጥሎ ፈረጠጠ።
ተመቶ የተቃጠለው ዙ 23 ከጥቅም ውጭ ሆኖ እየጎተተ ይዞት ተመልሷል።

#በሺ አለቃ ይርሳው ደምስ የሚመራው የደንበጫ ፋኖ ግን #ምድራዊ_ድሮን በመባል ቢጠራ ያንስበታል ይሆን? እረ አያንስበትም አስራ አንድ ቀን ሁሉ ባደረገው ውጊያ  ኮለኔሎችን፤ሻለቃዎችን፣
ሻምበሎችን፣ኮማንደሮችን ሁሉ ደምስሷል።

በርካታ ተተኳሾችንም ለመማረክ ችሏል።
ታሪክ በእጃቸው መስራት ልማዳቸው የሆኑት የኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድ ዛሬ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው እይዘዋለሁ ያለውን ቦታም ሳያየው አብዛኛውን ደምስሰው የተረፈውን መልሰው  ልከውታል።

በየመንገዱ እየፈረጠጠ ሳለ የቆሰለበትን እየረሸነ ይጓዝ ነበር።ሬሳውንም የሚያነሳበት መኪና ስላልነበረው በየቦታው  ወድቆ ቀርቷል።
ድል በድል የሆነው የኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድን አስራ አንድ ቀን ተዋግቶ ዛሬም ሌላ ስራ ላይ ነው።

ይሔ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር ግን ምን አይነት ብርጌዶችን ነው በውስጡ የሰበሰበው አለኝ አንድ ወዳጄ በውስጥ መስመር መጥቶ?

አይ ወንድሜ ታቃለህ ያኔ መስከረም 21/01/2016 ዓም ከተመሰረቱት ክፍለ ጦሮች ከተመሰረተበት ቀን አንስቶ ያለምንም ማመንታት ራሱን በብዙ ነገር ሲያደራጅ የነበረ ክፍለ ጦር በኃላም ጥር ሶስት ጠቅላላ ጉባኤ በማድረግ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የውስጥ አደረጃጀቶችን ያለማንም ጣልቃ ገብነት በመርህ የሚሰራ ጦር ለመገንባት ቃል ገብቶ ወደ ስራ ከገቡት ጠንካራ ክፍለ ጦር አንዱ ነው።

በዚህ ደግሞ ከፊት ያሉት መሪዎች እንደ ወርቅ በእሳት የተፈተኑ የረዥም ጊዜ የትግል ልምድ ያላቸው ጀግና መሪዎች ያሉበት ዳሩ ግን በጀግንነታቸው ልክ ስራቸውን ለአዓለም ያልታወቀላቸው በስራ ብቻ የሚታወቁ #ዝምኛ ገዳይ የሚባሉ አናብስቶች የበዙበት ስለሆነ በስሩ ያሉ ብርጌዶችንም እንዲሁ መንፈሰ ጠንካራ ናቸው ስለው በደስታ ወደቀ።
ገና ታሪክ በክንዳችን እና በፈጣሪ እረዳትነት እንሰራለን።ይሔ ክፍለ ጦር ታምረኛ ነው።የአራት ኪሎው ባንዳ አጥብቆ ከሚፈራቸው ክፍለ ጦሮች ግንባር ቀደሙ ነው ማለት እችላለሁ።

ደብረ ማርቆስ ላይ ወሽቆ የሚገኘው የካድሬ ስብስብ ሲተኛም ሲነሳም ሲበላም ሲራመድም በአዕምሮው የሚመጣበት የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር ነው።
በዚህ ክፍለ ጦር ውስጥ ስድስት ብርጌዶች አሉ።ሁሉም ግን እጅን በአፍ የሚያስጭን ታሪክ በየቀኑ ይሰራሉ።ፈክረው ገብተው ያሰቡትን ጀብድ የሚፈፅሙ የድንቅ ብርጌዶች ስብስብ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለ ጦር።

ኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌድን አለማድነቅ ማለት የአማራን ትግል እንዳለመደገፍ ይቆጠራል።
ኢንጅነር ክበር ተመስጌን ብርጌዶችን አመስግኑልኝ!!!

አዲስ አብዮት፣አዲስ ድል ፣አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ

በወንበዴዎች ወንበር የማይናውዝ አዲስ ትውልድ በክንዳችን እና በአንደበታችን እንፈጥራለን።

©የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ መ/ር ታደገ ይሁኔ(ሸርብ)

3 months, 2 weeks ago

ሟቹ ከተናገረው “የእናንተው ነኝ” ንግግር እና  ከገዳዮቹን ስድብ የቱ ነው እውነታው?
~~
ማቹ ወጣት ሲናገር እንደተሰማው “እኔም የእናንተው ነኝ” ሲላቸው ተሰምቷል፤ “የእናንተው ነኝ” ሲላቸው አንድም “እኔም እንደ እናንተው ኦሮሞ ነኝ” እያላቸው ነው አልያም “እኔም እንደ እናንተ አማራ ነኝ” እያላቸው ነው። ከዚህ ውጪ አይሆንም።

ስለዚህ “እኔም እንደ እናንተ አማራ ነኝ” የሚል ከሆነ ተጎጂው አማራ ነው፤ ምንም እንኳን ጉዳዩ አሰቃቂ ቢሆንም ግን “ኦሮሞ ነው” እያሉ መብሰክሰኩ እና ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ማያያዙ ራስን ማታለል ነው የሚሆነው።

ልጁ “እኔም እንደ እናንተው ኦርሞ ነኝ” ከሆነ ያለው ገዳዮቹ ኦሮሞዎች ናቸው ማለት ነው። ይህም ምናልባትም አስገድዶ እያፈሰ ያለው ብልፅግና የተሻለ አማራጭ አድርጎ ያሰበው በዚህ መልክ ቅስቀሳ ማድረግን ሊሆን ይችላል። ይህ ከሆነ ደግሞ አራጁ እራሱ የኦሮሞ ብልፅግና ነው ማለት ነው።

ስለሆነም የኦሮሞ ህዝብም ሆነ ሌላው ማህበረሰብ የብልፅግና ካድሬዎችና እና አማራ ጠሎች የሚሉትን ጭፍን የእውር ድንብር ጉዞ አቁሞ እውነታውን ሊመረምር፣ ይልቁንም ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል እየታረደ ላለው ወገኑ ድምፅ ሊሆን፣ ለፖለቲካ ሲባል ንፁሃንን እያረደ ያለውን አራጅ መንግስት ሊያወግዝ ይገባል።

ይሄው ነው።

የጨፍጫፊው አብይ አህመድ አገዛዝ ስንቱን ጀግና በሰበብ አስባቡ የገደለና ያስገደለ አገዛዝ መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ሆኖ ሳለ በዚህና መሰል ድራማዎች መታለልም፣ ሰለባ መሆንም መቆም አለበት።

ማቹ ወጣት ኦሮሞ እንደሆነ በራሱ ቪዲዮም በቤተሰቡ ንግግርም ተገልጿል። ስለዚህ “እኔም የእናንተው ነኝ” ሲል እሱም ኦሮሞ ገዳዮቹም ኦሮሞ መሆናቸውን እየገለፀ ነው። እንግዲህ ኦሮሞው ነው ልጁን ለፖለቲካ ሲባል “ጋ*ላ” እያለ እየሰደበ ያረደው። ያሳዝናል፤ ለፖለቲካ ሲባል በንፁህ ወገን ላይ በዚህ ልክ መጨከን በጣም የሚያሳዝን ነው።

ይህ አገዛዝ የጃዋርን ፖለቲካ ለመግደል ሃጫሉ ሁንዴሳን፣ የአብን እና የባልደራስን ትግል ለማኮላሸት እነ ዶ/ር አምባቸውን የበላ ጭራቅ አገዛዝ መሆኑን እናውቃለን። እየሆነ ያለውም ይሄው ነው።
ንቃ!

ድል ይህን ጭራቅ አገዛዝ ለሚታገለው ፋኖ!

አለባቸው ግርማ

ህዳር 13/2017 ዓ.ም
  አሻራ ሚዲያ

ወቅታዊ መረጃ እና ጥቆማ መስጠት ለፈለጋችሁ???

@Revolu1
@Revolu1

3 months, 2 weeks ago

#Share **Many Amharas were slaughtered in Addis Ababa, pretending that Hachalu Hundesa killed by the government.

If you have an Oromo who says they will repeat the ethnic killings that happened then, think of your relatives.

Prosperity's government kills itself for its own benefit and is crying and crying. A lot goes into making the war ethnic. But we believe that the intelligent Oromo people understood this game and actively passed it with their Amara brothers.**

ሀጫሉ ሁንዴሳን መንግሥት ገድሎ ዐማራ የገደለው በማስመሰል ብዙ አማራዎች አዲስ አበባ ላይ ታርደዋል።

ያኔ የተፈፀመውን አይነት ብሄር ተኮር ግድያ አሁንም እደግመዋለሁ የምትል ኦሮሞ ካለህ ዘመዶችህን አስባቸው።

ብልጽግና ለራሱ ጥቅም ሲል ራሱ ገድሎ ራሱ አልቅሶ እያስለቀሰ ነው። ጦርነቱን የብሄር ለማድረግ ብዙ ይለፋል። ግን አስተዋዩ የኦሮሞ ህዝብ ይህን ጨዋታ ተረድቶ ከወንድሞቹ አማራ ጋር ሆኖ በንቃት ያልፈዋል የሚል ግምት አለን።

Ammaaraan baay’een addis Ababa keessatti, Hacaaluu Hundeessaa mootummaarratti ajjeese jechuun sobaa fi gowwoomsaan ajjeefamaniiru.

Namni Oromoo tokko yommuu ajjeechaa gosaatti deebi’anii raawwatu jedhanii dubbatan, maatii keessan yaadadhaa.

Mootummaan badhaadhinaa faayidaa ofiif jecha of ajjeesa; akkasumas, iyyaa fi boo’aa jira. Warri baay’een akka waraanni gosaatti jijjiiramu taasisa. Garuu Oromoonni baratanii fi beekan dargaggoonni ammaa tapha kana sirritti hubatanii obboloota isaanii Amhaara waliin wal ta’anii darbuun isaanii ni amanama.

ወቅታዊ መረጃ እና ጥቆማ መስጠት ለፈለጋችሁ???

@Revolu1
@Revolu1

3 months, 2 weeks ago

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በትምህርትም ሆነ በስራ ያላችሁ አማራዎች በያላችሁበት ቦታ እየተደረጉ ስለሚገኙ ነገሮች መረጃዎችን  በዚህ አድራሻ አድርሱን!??

@Revolu1
@Revolu1

3 months, 3 weeks ago

አንድነት ኃይል ነው።
ልዩነት የህዝቡን ሰቆቃ ከማርዘም ውጭ አይጠቅምም።

የውርደት ሁሉ ውርደት፤ የሞት ሁሉ ሞት ወገንህን ለገንዘብ እና ለስልጣን ብለህ በወገንህ ላይ ቁማር ስታስይዝ ነው።

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 1 week ago