ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
Delighting your life is our job
__
የሆነ ቀን ሌሊት
ገላየ እንቅልፍ አጥቶ
ከሆነ ሕልሙ ጋር የትዝታ ጠረን
በልቡ ያሸታል ፣
ከወዲያ ጫፍ ደግሞ ፣ «ጥላሁን» ተከፍቷል ፣
.
ፍቅር ለብቻየ
የሚል እንጉርጉሮ
.
ከዚህ ዘፈን በታች
Pablo Neruda
''Every Day You play the light of the Universe '' !
እያለ ይወርዳል ፣
ከማን ጋር ልስማማ
ትዝታ አቅም ኑሮት ፣ ማንን ይጋርዳል ?
.
ዮሐንስ አድማሱን
በድሉ ዋቅጅራን
ቸርነት ወ/ገብሬልን
ወይ ደግሞ ኤፍሬምን
«ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር» ያለሽን ልቀፈው ፣
ከሁሉም ለመሸሽ
እንደምን ? እንደምን ? ፣ ይኼን ቀን ልለፈው ?
.
አሁን ለምሳሌ
የአምስት ግጥም ዕድሜ
ከሚለው መጽሐፍ ላይ
.
ከወዝ መጋራት ጋር
የሚመሽ አንድ ቀን
ይነጋል እያለ
የጻፈላት ግጥም ፣ መንጋቱን ሸረፈው ፣
ወቅትን እንደ ኩታ ፣ ዘቅዝቆ አነጠፈው ።
.
ታዲያ በዚህ መሃል
ናፍቆት ግፉን ትቶ ፣ ሲሄድ እያየሽው ፣
ፍቅር ለብቻየን ፣ ለምን ነበር ያልሽው ?
እንጃ ።
ብቻ ግን አንዳንዴ !
.
ሰትዮዋ እንዴት ናት ?
የሚል ግጥም ጽፎ
አቦል የፍቅር ወዝ ፣ መድፋት ስለሚቻል ፣
የኖሩት እያለ ፣ የሚመጣው ነገ እንዴት ይሰለቻል ?
ቢሆንስ
ቢሆንስ
.
አሁን በዚህ ሰዓት
ሴትዮዋ እንዴት ናት ?
.
በነገራችን ላይ
ከዚህ ሁሉ ኋላ
የጥላሁን ዘፈን
ሥራውን እርስቶ ፣
መዳፌ ላይ ያለ ፣ መጽሐፍ አንቺን ትቶ ፣
.
ፍቅር እዚህ ቦታ
ብለው የሰቀሉት ፣ ግጥም የለም ጠፍቷል ፣
ገጣሚው እንደ እግዜር ፣ ብቸኝነት ፈርቷል ።
.
በእርግጥ !
.
የሆነውን ሁሉ
አሁን የለም ብለው ፣ ሲገፉት እንዳሻው ፣
ከሁሉም መሸሽ ነው ፣ የሰው መጨረሻው ፣
_____
ሶሎሞን ሽፈራው
JOIN
@yourpoim
*እንቆቅልሽ ምንድነው?
═════ ❁ ═════
እንቆቅልህ በግዕዝ "አንቆቅሆ" ማለት ነው። ወደ አማርኛ ሲመለስ አንቆቅሆ እንቁላል ማለት ይሆናል፤ ስለዚህ እንቆቅልህ ማለት በስረ መሰረቱ እንደ እንቁላል ድፍን የሆነ ፍቺው ያልታወቀ መመርመርን የሚጠይቅ ፈተና ማለት ነው።
እንቆቅልህ የአዕምሮ ንቃትን ይጠይቃል፤ ተጠያቂው ወይም ተፈታኙ ሰው በተወሰነ ሰዓት የምሳሌውን ፍቺ ማግኘት አለበት፤ አለዚያ አገር መስጠት እና መሰደብ ይኖርበታል። ነገር ግን በተወሰነ ደቂቃ ውስጥ ትክክለኛ የሆነውን ፍቺ ያገኘ እንደሆነ አገር ከመስጠት እና ከመሰደብ ይድናል። የአዕምሮ ዝቅተኛነትም አይሰማውም።
እንቆቅልሽ ስዕላዊ ምርመራን ይፈልጋል። ጠያቂው የረቀቀ እና የበሰለ ምስጢር ያዘለ ምሳሌን ሲያቀርብ ተጠያቂው ከምሳሌው ጋር የሚነፃፀሩትን ነገሮች ሁሉ እያሰበ ትክክለኛ ከሆነ መልስ እስኪደርስ ማውጣት፣ ማውረድ እና መመርመር የሚያሻው ነው። ትርጉም የሚሆኑትን ነገሮች ሁሉ በዓይነ አእምሮ እየተመለከተ ከምሳሌው ጎን ለጎን እየኮለኮለ ማስተያየትና ማነፃፀር ይኖርበታል።
ተፈታኙ እንደ ኢላማ አነጣጥሮ ከእውነተኛው ትርጉም ሲደርስ የእንቆቅልሹ ትርጉም ይህ ነው ብሎ ይመልሳል። በትግል አቅምን በመገመት ጉልበትን መፈተን እንደሚቻል ሁሉ በእንቆቅልሽም የአእምሮን ንቃትና የአሳቡን ኃይል ማወቅ ይቻላል። ሰው ሁሉ አንድ ዓይነት አስተያየት የለውም፤ አንዱ ከሌላው በችሎታ ይበልጣል፤ አንዱ ደግሞ የተለየ ተሰጥኦ ኖሮት በአንደኛው ነገር ንቁ ሲሆን በሌላው ይደክማል።
ስለዚህ አንዳንድ ልጆች ብቻ እንቆቅልሽን ቶሎ ለማግኘትና ትክክለኛ ፍቺ ለመስጠት ይችላሉ። እንቆቅልሽ ጊዜን የሚጠይቅ የምርመራ ፈተና ነው። ይሁን እንጂ ጥያቄው በተወሰነ ደቂቃ ውስጥ መመለስ አለበት፤ የእንቆቅልሹ አቅራቢ "መሸብህ እንቆቅልሼ ተነዛብኽ፣ ዋለብህ አደረብህ አገር ስጠኝ?" እያለ ተጠያቂውን ይወተውተዋል፣ ያዋክበዋል። ተጠያቂው እንቆቅልሹን መፍታት፣ ከትርጉሙ መድረስ ያቃተው እንደሆነ አገር ይሰጠዋል፤ በዚህም ድል መሆኑን እና መሸነፉን ስለሚገልፅ የአእምሮ ዝቅተኛነት ይሰማዋል፤ የእንቆቅልሹ ባለቤት በበኩሉ ይደሰታል።
የአገሩን ስም እየጠየቀ "አነሰኝ፣ ጨምርልኝ" እያለ ያስገድደዋል፤ የሚመኘውን እና የሚፈልገውን ካገኘ በኋላ፣ "እዚህ ተቀምጬ ምን አጥቼ፤ ሁሉ በእጄ፣ ሁሉ በደጄ፤ እንዳልሰድብህ ወንድሜ፣ እንዳተውህ ጠላቴ" እያለ ይወቅሰዋል። በዚህ ጊዜ በጠያቂውና በተጠያቂው ፊት ላይ የበላይነትና የበታችነት ስሜት ማንበብ አዳጋች አይሆንም። የእንቆቅልሹ ባለቤት በጌታ ሁናቴ፤ "በሰንጋ በቅሎ ሆኜ አንተን አሽከሬን በገጣባ አህያ አስቀምጬ" እያለ የተሸናፊውን ዝቅተኛነት ያስረዳዋል።
ከዚህም አነጋገር ታላቅ ምስጢር እናገኛለን፤ ይኸውም በአእምሮ ያልጎለመሰ የማሰብ ኃይሉ ከተፈጥሮ ጓደኛው ያነሰ ሁሉ፣ ለወንድሙ አሽከር ሆኖ መኖሩን የሚያስገነዝብ ነው። ምንም እንኳን በቀድሞ ጊዜ ለጉልበት ሥራ ብቻ ከፍተኛ ግምት ቢሰጠው፤ አባቶቻችን የማስተዋል ንቃት፤ የመንፈስ ብርታትና የናላ ኃይል አስፈላጊ መሆኑን አልዘነጉትም።
ለምሳሌ፦
ጥያቄ፦ እንቆቅልህ? - ምን አውቅልህ?
ላዩ ሰርዶ ውስጡ ብርንዶ።
መልስ፦ ቀይ ሽንኩርት።
ጥያቄ፦ እንቆቅልህ? - ምን አውቅልህ?
ሲወለድ ይጠቁር፣ ሲያረጅ ይቀላ።
መልስ፦ በርበሬ።
ጥያቄ፦ እንቆቅልህ? - ምን አውቅልህ?
ወተቱ ጥቁር፣ ማለቢያው ነጭ።
መልስ፦ ቡና።
ጥያቄ፦ እንቆቅልህ? - ምን አውቅልህ?
እልም ካለ ዱር ገብቼ፣ የምቆርጠው አጥቼ።
መልስ፦ ጉም።
ጥያቄ፦ እንቆቅልህ? - ምን አውቅልህ?
ልብስም ጉርስም ትሆን።
መልስ፦ በግ።
━━━━━━━━━━━━
? የብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ
ወልደ መስቀል ስብስብ ሥራዎች
ምንጭ ?* ሰዋስው ? ? ? ? ?
[❖#ዓይነ_ጥላ_በወንዶች_ላይ
➥ሴት_ዛር_ወይም ዓይነ ጥላ
#የሴት_ዛር የዓይነ ጥላ](http://t.me/yourpoim)
`መንፈስ ያለችበት ወንድ ልክ እንደ ሴት ተመስላ ሌሊት እየመጣች ወንዱን ትገናኘዋለች
✅ዘሩን ታፈስበታለች
✅ብልቱ እንዲልፈሰፈስ ታደርጋለች
✅ብልቱን ወደ ውስጥ ትሰበስበዋለች
✅ብልትን በመጠን ታሳንሰዋለች
✅ብቻውን ሲተኛ ስሜቱ ይነሳል ከሴት ጋር ሲሆን አይነሳም ቢነሳም ዘሩ ተሎ ይፈሳል
✅ፆታዊ ግንኙነት በሚያደርግበት ጊዜ የዘር ተሎ መፍሰስ ታመጣለች
✅የመራቢያ ዘሩን በማቅጠን በማሳሳት ልጅ እንዳይወልድ ታደርገዋለች (መካንነት)
# ሰውነቱን ታደቀዋለች
⏩ሰውነቱን ታቀጭጨዋለች
⏩የሆድ መንፋት ታመጣለች
⏩የፍቅር አጋሩን እንዲጠላ ታደርገዋለች
⏩ትዳር እንዳይዝና ትዳር የያዘውም አስጠልቶት እንዲለያይ ታደርገዋለች
⏩ብቸኝነት
⏩ድብርርት
ጭንቀት
⏩እራስን ዝቅ አድርጎ መገመት
⏩ግለ ወሲብ እንዲፈጽም ታደርገዋለች
⏩የፀባይ መቀያየር ታመጣበታለች
??#ሴት ዛር (የዓነ ጥላ መንፈስ ) በብዙ ትመሰላለች
✔በቤተሰብ
✔በፍቅር አጋር
✔ቀን ባዩት ነገር በሚያውቁትና በማያውቁት
✔ባስ ሲልም በእንስሳት በመመሰል ወንድ ልጅን በህልመ ሌሊት እየመታች ስታሰቃይ ትኖራለች
?ልብ ይበሉ
➥ሴቶችን ደግሞ ሌሊት እየመጣች በመደበት ከባላቸው ጋር ሩካቤ እንዳይፈጽሙ
➥በባላቸው ዘንድ እንዲጠሉ ወይም እንዳይወደዱ
➥ለሩካቤ ስጋ ፍላጎት እንዳይኖራቸው ታደርጋለች
➥ከትዳር አጋር ጋር ሰላም እንዳይኖር ታደርጋለች
#ሴት ዛር ያለችበት ወንድ መንፈሷ የሕልመ ሌሊት ሰለባ ከማድረጓም ባሻገር
➡ስሜታዊ(ስነ ልቦናዊ) ጉዳት ታደርስበታለች
➡ሞራሉን ትጉዳዋለች
➡ብቻውን እዲኖር አድርጋ እራሷ ባል (ጓደኛ ታደርገውና) የስውር ሚስእስኪያልትኖራለች
?መፍትሔ
➱#አስተናግር ሥርና ፍሬ
➱#የጊዜዋ ሥር
➱#የአብላሊት ሥር
➱#የእጸ መናሔ ሥር
➱#እጽ ደብተራ ሥር
➱#የሴት ቀስት ሥር
?ጊዜዋ፣እጸ መናሔ፣አብላሊት እነዚህን እጽዋት ማክሰኞ ቀን በንፅህና ነቅሎ ቀጥቅጦ አድርቆ ወግጦ በወንፊት ነፍቶ እኩል እኩል አድርጎ ማገናኘት ከተገናኘ በኃላ ከእሩብ ኪሎ ማር ጋር አዋህዶ ለ9 ቀን በስኳር ማንኪያዋ ጧት በባዶ ሆድ መውሰድ።
?ለዓይነ ጥላ/ለሴት ዛር መንፈስ፦
#የሴት ቀስት ሥር በንጽህና ማክሰኞ ቀን ቆርጠው አድርቀው ሸርከት አድርጎ በመደቆስ ማታ ማታ ከከርቤ ዕጣን ጋር ለ9 ቀን ማታ ማታ እየታጠኑ መተኛት።
?ለዓይነ ጥላ/ለሴት ዛር መንፈስ
#የአስተናግሩንና የእጸ ደብተራ ሥራቸውዋ ሰብስቦ ቀጥቅጦ አድርቆ የአስተናግሩን ፍሬ በመጨመር ከ7-14 ቀን አንዳንድ የስኳር ማንኪያ ማታ ማታ እየታጠኑ መተኛት።
የሚከለክሎ ነገሮች #አልኮል #ተልባ #ፆታዊ ግንኙነት መድሐኒቱ እስኪያልቅ`
ምናልባት አጠገባችን የተሰወረ ነገር ቢኖርስ?
ስለ እጸ መሰውር ምን ያህል ያውቃሉ?
.
.
( ? Click here )
(The Cloaking Device)
.
.
Marvel የተሰኘው የፊልም አምራች ድርጅት በሰራቸው በርካታ ፊልሞች ላይ
የማይጠፋ አንድ ቴክኖሎጂ አለ! ይህ ቴክኖሎጂ ትንሽ ቆየት ብሎ የወጣውን
black panther እና እንደ marvel agents of shield የተሰኙት
ፊልሞች ላይ ያስተዋልነው Cloaking device የተሰኘው መሳሪያ ነው!
❤️ይህ መሳሪያ በተግባር ላይ እንደዋለ የሚያሳዩ መረጃዎች ያሉ ሲሆን በተለይ
የአሜሪካና የእንግሊዝ የጦር ሀይል ተጠቅሞበታል!
በተለይ የእንግሊዝ የጦር ሀይል በዚህ መሰወሪያ መሳሪያ በመጠቀም ታንክ
ሰውሮ ለውጊያ እንደተጠቀመ የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ።
በተጨማሪ Mercedes የተባለው የመኪና አምራች ድርጅት በዚህ መሰወሪያ መሳሪያ የተቀመረች መኪና አምርቶ ለሙከራ አብቅቶም ነበር
?ነጮቹ ይህን የቴክኖሎጂ ምርታቸውን
እና ጥናታቸውን እንደ Harry potter እና Hollow man በተሰኙ የሆሊውድ
ፊልሞች ላይ አሳይተውናል።
Black Panther ፊልም ላይ የተሰወረችው ከተማ ዋካንዳ እና ከሰው እይታ የሚሰወሩት ጀቶች ምስጢር ይህ ግዝፈት ያላቸውን ነገሮች ለመፈብረክ የተዘጋጀው የክሎኪንግ ዲቫይስ ቴክኖሎጂ ነው!
ሊሆን የሚችል ቴክኖሎጂ ነው...ለሙከራ ያህል እንጂ ሙሉ ለሙሉ ጥቅም ላይ አልዋለም፣ ዋነኛው ችግሩ ለስራው አስፈላጊ የሆነ ማቴሪያል ማምረቱ ላይ
ነው...ጽንሰ ሃሳቡ የተነደፈው በከፍተኛ ሙቀት ሠዐት ለምሣሌ አስፓልት ላይ
ከምናየው የብርሃን መጨበርበር ነው
?ተመራማሪዎችም የካርበን ቲዩቦች ውስጥ ከፍተኛ ሙቀት በማሣለፍ clocking effect መፍጠር
ችለዋል...ቢሆንም በማቴሪያሉ አቅም የተነሣ ያንያህል experment ተግባራዊ
ሊሆን እንደሚችል ከማሣየት የዘለለ ነገር አልተሠራም።
?ይህ ጥበብ በኛ ዘንድ የበርካታ ሺህ ዘመናት ታሪክ አለው!
በዚህ ጥበብ ልክ ብላክ ፓንተርስ ላይ እንደተመለከትነው አያቶቻችን በርካታ
ከተሞችን ከሰው እይታ ሰውረዋል! እነኚህ ከተሞች ልክ እንደ ዋካንዳ በርካታ
ሀብት ጥበብና ምስጢር ያዘሉ ናቸው! እነኚህን ከተሞች አያቶቻችን የሰወሩበት
መንገድ እና ቴክኖሎጂ ደግሞ መሰውር ይሰኛል!
?ይህን ጥበብ በመጠቀም አበው በርካታ ቅርሶችን ከዘራፊዎች ታድገዋል።
አሁንም እንደተሰወሩ የቀሩ ዋሻዎች ፣ ቅርሶች ፣ ፒራሚዶችና መንደሮች አሉ።
መሰወር የተሰኘው የመሰወሪያ መሳሪያ ሙሉ ለሙሉ ከእፅዋት ተቀምሞ
እንደሚዘጋጅ የዘርፉ ሊቃውንት ይናገራሉ! በተለምዶም እፀ- መሰውር እየተባሉ ይጠራሉ እፅዋቱ።
የኛ ሰው ይህን ጥበብ ጥንቆላ ብሎ ቢያንቋሽሸውም ምዕራቡ አለም የአዲሱ ዘመን አስደናቂ technology አድርጎታል።
ምን አልባት ይህ ጥበብ አገራችንን ከጠላት የምንከላከልበት ጥሩ አማራጭ ሊሆንም ይችላል።
የሚገርመው ገዳማውያን
አባቶች አሉ ፡ አብረዋቸው ከሚጓዙት ሰወች ተሰውረው ቀድመው ባሰቡት ቦታ የመድረስ ጥበብ ያላቸው አሉ።
?ከተማሪዎቻቸው (ከትውልዱ) በምግባር
የበቃ ተከታይ ስላልተገኘ ጥበባቸውን
አያወርሱም። ከዚህም በላይ ተማሪዎች
(የቆሎ) ፈሪሀ እግዚአብሔርን ከመማር
ይልቅ ጥበቡን በአቋራጭ ለመማር
የሚያደርገው መፍጨርጨር ስላላስደሰታቸው ትውልዱ ያለምግባር እግዚአብሔር በሰጠው ጥበብ የሰይጣን አጋዥ እንዳይሆን ጥበቡን ራሳቸው ጥንቆላ መተት መርገምት የሚል ካባ በመሸፈን ይጠብቃሉ።
ነገር ግን ይህ ጥበብ ከምድረገጽ ፈፅሞ ሳይጠፋ እንፈልገው ከወደቀበት እናንሳው።
አለም ላይ ተወልደን/ተፈጥረን ሳለን ሚስጢሯን ሳናውቅ ባሰመሩልን ኖረንላቸው መሞት ሞት ነው!!
ጤና ይስጥልኝ እንደት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች
❤ሰላም
❤ጤና
❤እድገት
❤ብልፅግና በያላችሁበት ተመኘሁ
\#የወባ_በሽታ ችግርና \#መፍትሔውን ላካፍላችሁ ወደድኩ
? የወባ በሽታ / malaria ምንድን ነዉ??
? በኢትዮጲያ ሀገራችን በዋናነት ሁለት አይንተ የወባ በሽታ አሉ ፡፡
➡ የወባ በሽታ ወቅትን ጠብቆ በተድጋጋሚ በስፋት የሚከሰት በሽታ ሲሆን በሴት ወባ ትንኝ ንክሻ ወቅት ከምራቅዋ ጋር ወደ ደም ዝውውራችን የሚገባ በአይን በማይታይ ጥቃቅን ፕሮቶዞአል ዝርያ ነው ፡፡
➡ የወባ በሽታ በኢትዮጲያ ብዙ
ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እና ሞት በማስከተል ቀዳሚ በሽታ ነው ።
? በኢትዮጲያ በዋናነት ሁለት አይነት የወባ በሽታ አሉ፦
1.#የጭንቅላት ወባ ፡- በአብዛኛው በኢትዮጲያ ቆላ ቦታዎች የሚከሰት ሲሆን ከፍትኛ ጉዳት እና ብዙ ሞት ያስከትላል
2.#ትንሽዋ ወባ ፡-በአብዛኛው በኢትዮጲያ ጋምቤላ አካባቢና በአነስተኛ መጠን በቆላ ቦታዎች የሚከሰት ሲሆን በተደጋጋሚ በመነሳት ታማሚውን በማሰቃየት ትታወቃለች ፡፡
? የወባ በሽታ ምልክቶች፡-
ፕሮቶዞአል ደም ዝውውራችን ውስጥ ከገባ በኋላ ለመራባት እና ለማድግ የቀይ ደም ህዋስን አካል በመብላት እና የቀይ ደም ህዋስን ቅርጽ በመቀየር ቶሎ እንዲሞቱ ያደርጋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የሰውንታችን ተፈጥሮአዊ መከላከል ሂደት ጋር በተያያዘ ብዙ ምልክቶችን
ይፈጠራል፦
✅እራስ ምታት
✅ድካም
✅የሆድ ህመም
✅የጡንቻ ህመም
✅ትኩሳት
✅ብርድ ብርድ ማለት አና ማንቀጥቀጥ
✅ማቅለሽለሽ አና ማስመልስ
✅ፈጣን የልብ ምት
✅ደም ማነስ ምልክት
✅ጣፊያ ማደግ
✅ደም ውሰጥ ስኳር ማንስ / የረሀብ ምልክት
✅ቶሎ ህክምና ካላገኘ በጣም መዝለፍለፍ
✅የሰውነት ሙቀት አተነፋፈስ ልብ ምት እና ደም ግፊት መዛባት
✅እራስን መሳት
✅ሽንት በደንብ አለመአጣራት እና ትንሽ ሽንት መውጣት
✅የደም መርጋት መፍሰስና ደም ማነስ
✅አሲድ በሰውነታችን ውሰጥ መከማቸት
?የወባ በሽታ መፍትሄ
የመቅመቆ ስር ነቅሎ አድርቆ አልሞ ሦሥት የሾርባ ማንኪያ መቅመቆ ትንሽ ማር ጨምሮ በአንድ ሌትር ውሀ አንተክትኮ አፍልቶ ግማሹ ሲቀር አንድ የውሀ ብርጭቆ ሞልቶ ጥዋት በባዶ ሆድ መጠጣት ነው መርዛማነት ሳይድ ኢፌክት የለውም የተወሰነ ያስቀምጣል ከሆድ ላይ ያለውን የወባ ስራይ ጠራርጎ ያወጣዋል ሙሉ በሙሉ ከወባ ይፈውሳል በረሀማ ቦታ በወባ ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ይደርስ ዘንድ ሽር በማድረግ አጋሯቸው።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana