Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

Description
ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 year, 5 months ago
Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
1 year, 5 months ago

#ሼር_ፖስት ባህርዳር ከተማ ጄኖሳይድ ተፈጽሟል።አባይ ድልድይ ሻሁር እየወሰዱ የነበሩ ሦስት ወጣቶችን ተኩሰው ገደሉ። አባይ ወንዝም እንደ እንጨት እያግተለተለ ወስዷቸዋል። አንድ ከመራዊ የመጣ አባት ቀበሌ 14 ላይ የ4 ዓመት ህፃን ልጁ ተገድሎ አባትዬው አቅፎ "ልጄን፥ ልጄን" እያለ እያለቀሰ ሲዞር ውሏል። አባይ ማዶ ሰማዕታት ፊት ለፊት አንዲት መጫትን በእንጨት አልጋ ይዘው የሚሄዱ ሰዎች በአደባባይ ተረሽነዋል። ተሸካሚዎች አራቱ፣ መጫቷንና ገና ከተወለደ አንድ ቀን የማይሞላውን ጨቅላ ተገድለዋል። እዛው አባይ ማዶ አየር ጤና አካባቢ ሁለት ወጣቶችን ድንጋይ አንሱ በማለት ደረታቸው በጥይት ተመትቶ ተገድለዋል። ቀበሌ 3 ሊስትሮ ይሰራ የነበረ ሙስሊም ሰውየ ለአራት ልጆቹ ደረቅ እንጀራ ፍለጋ ላስቲክ ይዞ እንደወጣ ገድለውታል።

የተባበሩት ስጦታ ሥጋ ቤት አካባቢ አንድ ሰውየ ይገደላል። ልጅ ያዘለች ሚስቱ እየጮኸች ስትሄድ እሷንም ገደሏት። ህፃን ልጃቸው እየሮጠ ሲመጣ እሱንም ደገሙት። አስክሬኑ ሲነሳ የታዘለው ህፃን እስትንፋሱ አለ። አልሞተም። በተመሳሳይ በተለምዶ ዲፖ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ አባት የህፃን ልጁን ይዞ ሲሄድ ህፃኑንና አባትዬውን ተኩሰው ገድለዋቸዋል።
ወጣቶች ለማንሳት እየሮጡ ሲሄዱ ተኩሰውባቸው ሬሳው ሳይነሳ ውሏል።

የሆራይዞን ትምህርት ቤት ባለቤት የሆነውን የ26 ዓመት ልጁን ልደታ ሰፈር ከቤት ገብተው እረሽነውታል። እዛው ልደታ ሰፈር የቤት ለቤት እረሸና ተፈጽሟል። አንድ ሰውየን ከውጭ አንበርክከው ከውስጥ ያለችውን ሚስቱን ደፍረዋታል። ቤት ለቤት በሚያደርጉት ፍተሻ ከአንገት ሀብል እየበጠሱ፣ ሞባይልና ላብቶፖ እየቀሙ ወስደዋል። ምንም የማያውቁ የቆሎ ተማሪዎች ተገድለዋል። ባጠቃላይ ከትጥቁ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸው ከ700 በላይ ንፁሐን ተጨፍጭፈዋል። ልደታ ማርያም ከ54 በላይ፣ አቡነ ሐራ ቤተክርስቲያን ከ46 በላይ፣ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከ36 በላይ ሰዎች ያሉበት የጅምላ መቃብር ተፈጽሟል።

እርምጃ ተወስዶባቸው በደም የተበከሉና ዝንጥልጥላቸው የወጣ አስክሬኖች በመስቀለኛ መንገዶች ላይ፣ በዋና አውራ ጎጃናዎች ላይ፣ እቤቶች አጠገብ ላይ ተጥለው የሬሳ ኤግዚቪሽን ታይቷል። የህዝቡን ስነልቦና ለመጉዳት ሬሳ ሳይነሳ ሦስትና አራት ቀን ቆይቷል። ባጠቃላይ
በባህርዳር የተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ እና እጅግ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት (grave violation of human rights) ለዐማራ ከልክ በላይ ያላቸውን ጥላቻ ያሳዩበት ነው። አሁንም ግድያው አልቆመም። ሰዎች እየተገደሉ የትም እየተጣሉ ናቸው። በየጥሻው፣ በየበቆሎው ተገድሎ የተጣለ ሬሳ እየተገኘ ነው። ባህርዳር የሚታየው ነጠላውን ዘቅዝቆ ለቅሶ ለመድረስ የሚመርመሰመስ ሰው ነው። አንድ ሰው በቀን ቢያንስ በእግሩ ከአራት እና ከአምስት በላይ ለቅሶ ቤት ይደርሳል። በየቦታው ሀዘን ነው። በየቦታው መከፋት ነው።

አሁንም ከሰኞ ጀምረን ቤት ለቤት ፍተሻ እናደርጋለን እያሉ ናቸው። አሁንም ንፁሐን ይገደላሉ። ንብረት ይዘረፋል። ሴቶች ይደፈራሉ። "በለው" ነው። "ተኩሰበት" ነው። አንድ ወታደር ርችት እንደመተኮስ ያህል ጥይት ተኩሶ ንፁሐንን ያጋድማል። ተጠያቂ የለም፤ ጠያቂም የለም።

እንዲህ ያሉ ግፎች እንዳይዘገቡ ኔትወርክ ተዝግቷል። ይህን የምንጽፈው በሞት ቀለበት ውስጥ ሆነን ነው። ከህዝባችን የሚበልጥ የለም በሚል ነው። መረጃውን በቲዊተር፣ በቴሌግራም፣ በፌስቡክና በምታገኙት አጋጣሚ እንድታሰራጩ እጠይቃለሁ።

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

1 year, 5 months ago
Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
1 year, 5 months ago

ባህርዳር ነበር የቀረቻቸው ባህርዳር ከተማን ዛሬ ሌሊት እንደ የመን ከተሞች ሲያፈራርሷት አድረዋል፤ አሁንም ከቱርክ እና ከምዕራባውያን ተገዝተው በመጡ ዘመናዊ መሳሪያዎች እየፈራረሰች ነው። ከትናንት ከሰዓት ጀምሮ ሙሉ አደሩን እስካሁን በተለይም ቀበሌ 14 የጦር አውድማ ሆኗል። በዐማራ ህዝብ ላይ ይፋዊ ጄኖሳይድ ታውጇል።
ንፁሐን እንደ ቅጠል እየረገፉ ናቸው። 14 እሸት ፓርክ አካባቢ ብቻ ከ50 በላይ የንፁሐን አስክሬን የሚያነሰው ጠፍቶ ወድቋል። እናት በሯ ላይ የተገደለውን ልጇን አልቅሳ መቅበር አቅቷ ቤት ውስጥ እስክሬን አስቀምጣ ብቻዋን ደረቷን እየደቃች ነው።

ይህ "ኦሮሙማ" የተሰኘ አይዲዮሎጂ የሚከተል ፀረ-ዐማራ፣ ፀረ-ኢትዮጵያዊ፣ ፀረ-ሃይማኖት፣ ፀረ ሰው የሆነ አገዛዝ ታሪካችንን በማጠልሸት በምናባዊ ልቦለድ እንደ አኖሌ እና ጨለንቆ ያለ የጥላቻ ሐውልት ሰርቶብናል። ያለስማችን ስም ሰጥቶናል። የራሱን ግፍ ደብቆ ግፈኛ አድርጎናል። ነጠ*ኛ፣ መጤና ሰፋሪ" እያለ ከክልሉ አፈናቅሎናል።

ዛሬም ይህ ኃይል በፅንፈኝነት ፈርጆ እያሳደደን ነው። ትናንት በወለጋ ገድሎን አልረካም። ከመተከል አሳዶን አላቆመም። "ከዚች ምድር እናጠፋችኋለን" (We Will Erase You From This Land) በሚል መመሪያ ክልሉ ላይ ወረራ ፈጽሟል። እቤታችን ድረስ መጥቶ መትረየስ ደግኖ እየጨፈጨፈን ነው። ሱሪ ለብሶ መንገድ ላይ የሚንቀሳቀሰውን ሁሉ እንደ ቀይ ሽብር በይፋ እረሽነው የሬሳ ኤግዚቪሽን እያሳዩ ናቸው።

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

1 year, 5 months ago
Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
1 year, 5 months ago

#ሼር_ፖስት! ይህን የምጽፍላችሁ በባሩድ ጭስ ውስጥ ነው። አሁን በዚህ ሰዓት ባህር ዳር በቅርብ ርቀት በምትገኘው "ጉብሪት" ላይ ሄሊኮፍተር አውርዳቸው የሄደችውን ወታደሮች ፋኖ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል። በተመሳሳይ በኮሎኔል ጌታው መኮነን የሚመራው አያሌው መኮነን የፋኖ ብርጌድ ከ30 በላይ የፌዴራል ፖሊሶችን ከባህርዳር 65 ኪ.ሜ. ቁንዝላ ከተማ አካባቢ ከነመሣሪያቸው ማርኳል። ፋኖ አያሌው ብርጌድ በድል እየገሠገሠ ይገኛል።

-ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ የኦህዴድ ብልፅግና ሠራዊት ባህርዳር ከተማን የጦር አውድማ አድርጓታል። ንፁሐን በየቦታው
ጨፍጭፏል። የተባበሩት አካባቢ መትረየስ ጠምደው ከተማውን እያረሱት ይገኛሉ። ከላይ ከደንባቄ ተራራ ቁልቁል ወደ ከተማዋ ከባባድ የመድፍ ቅምቡላ እየወደቀ ነው።

-ፋኖ የሚችለውን እያደረገ ነው። 50 ዓመት በሙሉ ሲሳደድ፣ ሲፈናቀል፣ በጨቋኝ-ተጨቋኝ ትርክስት ሲከሰስ የኖረውን የዐማራ ህዝብ ፈጽሞ ከመጥፋት ለማዳን ደሙን እያፈሰሰ፤ አጥንቱን እየከሰከሰ ነው። በከፍተኛ የአሸናፊነት ስሜት (Sense of invincibility) ወደፊት እየገሠገሠ ነው። እንደ ፊታውራሪ ገበየሁ ተክሌ "...ስሸሽ ከኋላዬ ከተመታሁ አሞራ ይብላኝ" እያለ መድፉን፣ መትረየሱን፣ ቦንቡን ጥሶት እያለፈ ነው።

"የዘሜ ታናሽ ተላይነህ ወንዱ
በልቡ አስተኛው በየመንገዱ" እያለ በመፎከር ላይ ነው።

-አሁን ባህርዳር ሁለት ችግር ብቻ ናቸው ፈተና የሆኑት። የመጀመሪያው ኦህዴድ ብልፅግና በኮማንድ ፖስቱ ያደራጃቸው የቀበሌ፣ የክፍለ ከተማ፣ የወረዳ፣ የዞንና የክልል ካድሬዎች መረጃ በመስጠት፣ በማሳበቅ ባንዳነታቸውን በሚገባ እያስመሰከሩ ነው። ለነዚህ ካድሬዎች የዐማራ መፈናቀል፣ መሞት፣ መሰደድ ጉዳያቸው አይደለም። ዛሬ ታማኝነታቸው አረጋግጠው ነገ የሥልጣን እድገት እናገኛለን ብለው በተስፋ የሚኖሩ ከንቱዎች ናቸው።

ሁለተኛው በአሁኑ ሰዓት ለከተማው ህዝብ ፈተና የሆኑት ስግብግብ ነጋዴዎች ናቸው። በእያንዳንዱ የምግብ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ዋጋ በመጨመር ከአገዛዙ ባልተናነሰ ሁኔታ ህዝቡን እያስመረሩ ስለሆነ ሊያርፉ ይገባል። ሲሆን ይህን ችግር በጋራ ለመሻገር ቢተባበሩ ጥሩ ነበር፤ አለበለዚያ ግን በምግብ አቅርቦቶች ላይ ከፍተኛ ዋጋ መጨመር አገዛዙን እንደማገዝ ይቆጠራል። ዛሬ ከጥዋቱ ጀምሮ በውሸት ውሃ ተበክሏል ብለው ያስቀመጡትን ምርታቸውን ሲሸጡ አርፍደዋል። ከዚህ በላይ ነውር፣ ለህዝብ ደንታቢስነትና ስግብግብነት የለም። መቆም አለበት።

የድል ዜናዎች ተዘርዝረው አያልቁም። ባጭሩ ግን ሁሉም አስፈላጊውን ድጋፍ ያድርግ። ብልፅግና ያሰማራቸው ሌቦች የፋኖን ስም ለማጠልሸት ስለተሰማሩ ሁሉም አካባቢውን ነቅቶ ይጠብቅ። በየአካባቢው ይደራጅ። ይህን ፀረ-ዐማራ፣ ፀረ-ኢትዮጵያዊ፣ ፀረ-ሃይማኖት፣ ፀረ-ሥልጣኔ፣ ፀረ-ሰው አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ግብአተ መሬቱን ለመፈጸም ሁሉም ሚናውን መወጣት አለበት።

ድል ለዐማራ ህዝብ!
ድል ለኢትዮጵያ!

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

1 year, 5 months ago
Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
1 year, 5 months ago

#ሼር_ፖስት! "እኔም ፋኖ ነኝ" ኢንተርኔት በመዝጋት የህዝብን ድምጽ በማፈን የሚካሄድን የህዝብ ጭፍጨፋ በጽኑ እቃወማለሁ"

-"ይህ ጦርነት ተራ ጦርነት አይደለም። ልክ እንደ አይሁዳውያን ከምድረገጽ እንዲጠፋ የተፈረደበት ታላቁ ዐማራን በመሰረታት ሐገር አንገቱን ደፍቶ እንዳይኖር የሚደረግ የመጨረሻው ትግል ነው። ይህ ትግል ከቀያቸው አፈናቅለው ከቀየው ሊያፈናቅሉት የመጣን ኃይል የማክሸፍ ትግል ነው"

እንደዚህ ያሉ መልዕክቶችን በሜሴጅ ለ10 እና ለ15 ሰው ሼር በማድረግ እንድታስተላልፉ አደራ ለማለት እወዳለሁ።

-የትናንቱ አጠቃላይ ዝርዝር መረጃ።

-ባህርዳር ከትናንት ጀምሮ መንገዶች ሁሉ ዝግ ናቸው። ከሰዓት ቀበሌ 14 ልደታ ማርያም አካባቢ ከፍተኛ ተኩስ የነበረ ሲሆን፣ የኦህዴድ ብልፅግና ሠራዊት የቆሎ ተማሪዎችን ጨምሮ 6 ንፁሃንን ገድሏል። በተመሳሳይ ቀበሌ 13 በተለምዶ ገጠር መንገድ ላይ በፓትሮል ይንቀሳቀሱ የነበሩ የአገዛዙ ሠራዊቶች ወርደው ሁለት ወጣቶችን ተኩሰው አውራ ጎዳና ላይ ገድለዋል። ሥርዓተ ቀብራቸው እዛው 13 በዓታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

-ልደታ ማርያም ላይ በነበረው የተኩስ ልውውጥ ከ10 በላይ የአብይ አሕመድ ኮማንዶዎች ተማርከዋል።

-አገዛዙ መኮድን፣ ኤርፖርቱንና አሚኮን ለመከላከል በየቦታው ታንክ ጠምዷል። ለምሳሌ ገጠር መንገድ ላይ ታንክ ጠምዷል። መንገዱ ሁሉ ስለተዘጋጋበት ከጎርጎራ በጀልባ ወደ ባህርዳር ከተማ ኃይል እያስገባ ነው። ትናንት ምሽት በሁለት አውሮፕላኖችም አራግፏል። በተመሳሳይ ባህር ዳር ስታዲዬም ውስጥ የመሸገ የመከላከያ ኃይል አለ። ይህ በእንዲህ እያለ አሁንም የአማራ የብልፅግና ካድሬዎች ማታ ላይ ወጣቶችን በመጠቆም ሲያሳስሩ እንደነበር ታውቋል።

-ጎንደር ትናንት ከፍተኛ ችግር የነበረው ማረሚያ ቤቱ ላይ ነበር። ጠባቂ ፖሊሶች ከ20 በላይ ታራሚዎችን ተኩሰው ገድለዋል።

-አዲስአበባ የአማራ ተወላጆች ብቻ እየታሰሩ ይገኛሉ። ትምህርት ቤቶች ሞልተው አዲስአበባ እስታዲየም ታጉረዋል።

ድል ለዐማራ ህዝብ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut

1 year, 5 months ago
Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
1 year, 5 months ago
Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana