ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 3 недели назад
Last updated 2 недели, 2 дня назад
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 месяц назад
በዝግታ
First ቀስብዬ ገላዋን አሸዋት
ለስላሳ አካሉዋን በጆቼ ዳበስኳት
ከዛም ቀስ እያልኩኝ ገላዋን አራስኳት
በሰሜት ውስጥ ሆኜ በዝግታ ናጥኳት
በጣቶቼ ውስጧን በደንብ ጎረጎርኳት
.
.
.
.
.
.
በስተመጨረሻም ውዷ ብርጭቆዬን
በደንብ አለቅልቄ ውሀ ጠጣውባት::
ግን ምን አስባቹ ነበር? ሆ
✍ተገጠመ በኪያ
┈┈••◉❖◉●••┈
ዝም ብለሽ ስሚኝ?
❣️ :¨·......................:¨·.❣️
......... ✍️ፃፍኩልሽ? ........
አንድ ቀን እንደኔው የፍቅር ትርጉሙ
ሰው ወደሽ ካየሽው ስቃዩ ህመሙ
ላንቺ ብዙ እንደሆንኩ ያኔ ይገባሻል
ስነግርሽ ዝም ያልሽው ዛሬ ይቆጭሻል
አሁን ምን ያደርጋል ቢያዝኑ ቢቆጩ
ፍቅር አገርሽቶ በእንባ ቢራጩ
ያ የኔ ምስኪኑ እንግልቱ ልቤ
የፍቅርን ትርጉም ባየው ሰው ቀርቤ
እኔም ቆጨኝ ዛሬ ያኔ ያለቀስኩት
ሌላ ሌላ ስትይ አንቺን አንቺን ያልኩት
ዛሬ ግን
ልቤም ልብ ገዛ ሌላ ሰው ወደደ
አንቺን ለሰው ትቶ እሱ ከሰው ሄደ
በቃህ ሂድ ብለሽው ልቤ ሄዷል ቆርጦ
ይዟል አንቺን ትቶ የራሱን ሰው መርጦ
እኔስ የሰው ሆንኩኝ አንቺም ሰው ፈልጊ
ይመለሳል ብለሽ ተስፋ እንዳታደርጊ
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 105 ደረሰ!
ባለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ ከተደረገላቸው 659 ሰዎች መካከል 9 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ገለጸ። በዚህም በበሽታው የተያዙ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 105 ደርሷል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው መካከል 8 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 1 የኢኳቶሪያል ጊኒ ዜግነት ያለው ነው።
በጠቅላላው ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 105 መድረሱን ገልጸዋል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው ውስጥ ስድስቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ ሶስቱ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው ናቸው።
አራቱ (4) ከአዲስ አበባ ሲሆኑ ሶስቱ (3) ከጅቡቲ መጥተው በድሬዳዋ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን አንድ (1) የጅማ ከተማ ነዋሪ ነው።
አንድ ታማሚ ያገገመ ሲሆን አንድ ደግሞ በጽኑ ህሙማን ውስጥ ይገኛል። እንደ አገር 84 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ግለሰቦች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ ዶክተር ሊያ ገልጸዋል።
__
ዛሬ 1 ሰው ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ አገግሟል።
ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 16 ደረሱ።
ምንጭ፦ ኢዜአ
#coronaUpdate
በኢትዮጵያ ተጨማሪ አራት ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!
የታማሚዎች ሁኔታ ፦
ታማሚ 1: የ33 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከአሜሪካ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለች።
ታማሚ 2: የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከዱባይ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለች።
ታማሚ 3: የ29 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 4: የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት እየተጣራ ነው።
Via: Dr. Lia Tadesse
በኢትዮጵያ ተጨማሪ ዘጠኝ (9) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 442 ሰዎች መካከል ዘጠኙ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 65 ከፍ ብሏል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ዛሬ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ሁሉም ግለሰቦች የጉዞ ታሪክ አላቸው።
ከግለሰቦቹ መካከል ሰባቱ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ፤ አንድ ኤርትራዊ ቀሪዋ ደግሞ የህንድ ዜግነት ያላት ናት።
አራቱ ኢትዮጵያዊያን ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ መሆኑንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
ሁለቱ የቱርክ፤ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ደግሞ የእንግሊዝ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን፤ ሁሉም በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውን አውስተዋል።
የ20 ዓመቷ ህንዳዊት የአሜሪካ እንዲሁም የ40 ዓመቱ ኤርትራዊ ደግሞ የዱባይ ጉዞ ታሪክ ያላት ናቸው።
በጽኑ ህሙማን ክፍል ከሚገኙት ሁለት ግለሰቦች መካከል አንዱ የጤና መሻሻል በማሳየቱ ከክፍሉ መውጣቱንም ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።
እስካሁን ባለው ሂደትም በኢትዮጵያ ለሶስት ሺህ 232 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን ጠቁመው፤ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 57ቱ የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።
አራት ግለሰቦች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ ሁለቱ በበሽታው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። ሌላ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ወደ አገራቸው ተሸኝተዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ
#coronaUpdate በኢትዮጵያ አንድ የ9 ወር ህጻንን ጨምሮ ተጨማሪ ስምንት ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተያዙ!
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 264 ሰዎች ውስጥ 8 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።
በቫይረሱ ከተያዙት ሰዎች መካከል አንድ የዘጠኝ ወር ህጻን የተያዘ ሲሆን እናቱም ቫይረሱ ተገኝቶባታል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካካል አንዱ (1) ኤርትራዊ ሲሆን ቀሪዎቹ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።
ይህም በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 52 አድርሶታል ነው ያሉት።
ምንጭ፦ ኢዜአ
ከጤና ሚ/ር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ
................................
አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ መጋቢት 19 ፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ይታወሳል፡፡ ይሁንና ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡
በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን የጠቀሱት ሚኒስትሯ፤ ዛሬ መጋቢት 27 በቫይረሱ ተይዘው በህክምና ላይ የነበሩ የ60 ዓመት ሴት ህይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል። ግለሰቧ የፈረንሳይ አገር ጉዞ እንደነበራቸው እና በየካ ኮተቤ ገብተው ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውንም ጠቁመዋል።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 3 недели назад
Last updated 2 недели, 2 дня назад
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 месяц назад