ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 4 months, 1 week ago
Last updated 4 months ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 3 months ago
በአባታችን ሰፈር
“ያለጠረጠረ
……..ተመነጠረ “
ይባላል ሲነገር ።
፡
(ይኸው የሱ ልጆች
የቀንበር ወዳጆች
‘አሜን ፣ ይሁን’ ባዮች)
፡
ጠርጣሪም ቀን አንቆት
አየን ሲመነጠር ፤
አልጠበቅንም ነበር !
(ሚካኤል አ)
ልቤ እኮ ተራ ነው
የበረዶ ክምር
በድምፅሽ ይቀልጣል
ይሄ ሁሉ ግግር።
ብሽቅ ነው አንጀቴ
ቢመስል ጠንካራ
ተቆራርጦ ይወድቃል
ከመምጣትሽ ጋራ ።
ዉሸት ነዉ ካባዬ
ጥይቱም ፣ ዝናሩ
በሳቅሽ ቁጥር ነው
መሬት የሚዘሩ ።
ስስ የኔ ኩራት
ቀረርቶ ሽላዩ
እውሸለሸላለሁ
ጣቶችሽ ቢታዩ !
አላምንም ዙሪያዬን
ሰዎች ሲሉኝ ብርቱ
አንደበት ቃላቴ
ታዳሚን ሲረቱ …
አጀብ ቢባል አወይ
የግንባሬ ክርክር
ከፊቴ ለመቆም
ብዙ ሰው ቢያሰክር
ለመቅረብ ቢያስፈራ
የኔ ቦታ ፣ ሹመት
ሁሉ ባዶ ይሆናል
ከታየሽ በድንገት ።
እናም ማነው ሲሉ
በአንበሳና ነብር
ገፄን ሲመስሉ
ገርሞኝ የምስቀው
‘የብዙዎች ንጉስ …’
እንደዚህ ሳስብ ነው
፡
ይዘውሽ ቢመጡስ?
ባያቸውስ ኖሮ ?
(ሚካኤል አስጨናቂ)
እርግት ያለች ወተት
ስክን ያለች ቡና …
ይሄን ችኩል ዘመን
አልዋጀችምና …
ተንገበገብኩላት
ተሳተብኝ አቅሌ
ሆንኩላት ባተሌ ።
ጥልል እንደ ጠላ
ኩልል እንደ ጠበል
ከአንገቷ ስር ገነት
ገድ ጥሎኝ ብጠለል
አ..ን..ሰ…ፈ…ሰ…ፈ…ች….ኝ
አ…ር..ገ…ፈ...ገ…ፈ…ች…ኝ
ቃላት ሳ’ተነፍስ
ጥርሶቿን ሳትገልጥ
ቅቤ ሆነ ልቤ..
ገጽዋ ላይ ሲቀልጥ ፤
ያን ጊዜ ተቃናች !
ብታጣብኝ ኩራት
ስስ ጎኔ ቢገርማት
(ዓይኖቿ ፍም እሳት)
አንገቴን ሰበርኩኝ
ፈርቼው ይሄን ፍም
ቢሆንም …
ቢሆንም …
ለዓይኖቿ አፀፋ
መስጠት ሳልፈልግም
ለንቋሳው
……………………….. ተንጋለልሁ
ለዚ’ች ሞቃት ግርግም
:
ደረቷ ላይ ፍግም !
#የእንቢታሽ ሱሰኛ!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
አንቺን በማሰብ ውስጥ መደሰት ለምጄ
ፍቅርሽ ሱስ ሆኖብኝ ... ማንነቴን ክጄ
ባንቺ መወድስ ስም ክታብ አሰርቼ
ስምሽን አንግቼ …
እንደ አሞራ ዙሬሽ ፣ አንዣብቤ በላይ
አንቺን ሳይሽ ፣ ‘ዋይ ፣ ዋይ …’
አጃኢብ ነው መቼም!
ስትሄጅ ተራመድሁ... ስትቆሚ ቆሜ
ባንቺ ስፍር ልኬት.. .በጠርዝ ተመድሜ
ከዕድሜ ከዘመኔ ፣ ዓመታት ቆንጥሬ
ከእንቢታሽ ጋራ ፣ በእልህ ሰክሬ
ስንኞችን ጭሬ.. .
አንቺን በመጀንጀንጀን ፣ ልማድ ተጠፍሬ
በሚጣፍጥ ህመም ...
ብቻዬን በአርምሞ ፣ ስብሰለስል ኖሬ
ከሀሳቤ ማግስት ... በስንኜ ድርድር
ቃላት ድል ነስተውሽ ፣ በኃይላቸው በትር
እኔም በተራዬ ፣ መፈቀር ስጀምር
“ፍቅርህን ተቀበልሁ” ያልሽኝ ጊዜ ‘ለታ
ፍቅርሽ ጥሎኝ ጠፋ ፣ ትዝታሽ ተረታ።
(እንቢ በይኝ ዳግም
እልህን ላጣጥም ። )
ባዶ እስኪሆን ድረስ
(ሚካኤል አስጨናቂ)
እንባውን ይሰፍራል ፣ ኑሮ ያሻመደው
ጥርሶቹን ይገልጣል ፣ ምቾት የታደለው።
ሰፍረን እናውቃለን ፣ እንባን በኩባያ
ሀጫ ጥርስ ዘግነናል ፣ ስጥ ሆኖ ገበያ ።
ይሄን እናውቃለን ፣ ጥንትም ነበር ድሮ
የሷ ግን ገረመን ፣ ውል ሳትን ዘንድሮ ።
ትስቅ ነበር እኮ ፣ ሆዷን በእጇ ይዛ
ከጨዋታ መኃል ፣ አንዱን ሰበዝ መ’ዛ
አንድም አልሰማንም ፣ ሀዘን እንጉርጉሮ
አንገት አልደፋንም ፣ ቀኖቿ ተቆጥሮ
እንዲህ በሳቅ ውሀ ፣ ገፅዋ ተሸርሽሮ…
እስክናጣት ድረስ ፣ ያቺን መልካም እንስት
ከቶም አላየንም ፣ ቁዝሚያ ና ምልክት
ሳቅ እንዴት ይሆናል ?
የመታመም ቅኔ
………………. ዝግ ያለ ስንብት?
እህል'ና ውሃ
ደጋ እና በረሃ
ፀደይ እና ክረምት
ሲጋራ እና ቡና
ለምለም'ና ደረቅ የተፈጥሮ ውበት
ምን ቢፈራረቁ
ምን ቢለዋወጡ ለሰው መች ይመቻል
ሰው ከሰው ከራቀ
እንኳንስ መራመድ መቆም ይሰለቻል።
የደራ ከተማ ዘፈን ያደመቀው
ሸራፋ የሴት ሳቅ ሕይወት የዘለቀው
ቀጭን ውዝዋዜ ውበታም ዳንኪራ
አብሮት ከሚሰማ የሌት ዜማ ጋራ
ውበቱን ቢያጋራ
.
.
.
ሁለት ፍቅረኛሞች
በደረቀ ሌሊት
''ኮከብ ላውርድልሽ''
''ኮከብ አውርድልኝ'' እዬተባባሉ
በከንፈር በመዳፍ በጉንጭ እዬማሉ
ሃገር ቢያማልሉ
ሕይወት ቢያካልሉ
ከበተስኪያን ደጃፍ የእናቶች እልልታ
መንገድ ላይ የቀረ የቀጤማ ሽታ
የሶስት አመት ልጅ ሳቅ የህፃን ጨዋታ
ከበሮ ፀናፅል
እጣን ከርቤ ብርጉድ የካህን ውዳሴ
ወረብ እና መዝሙር ዜማ እና ቅዳሴ
ሃገሩን ቢሞላው ሃገሩን ቢያደምቀው
የሰማይ ገመገም
የ'ጧት ጠይም ፀሀይ በምስራቅ ቢፈልቀው
ላንድ ብቸኛ ሰው
እንባ ነው ትርጉሙ መከራ ነው ፍችው
ብቻውን ብቻውን ሕይወት ካለፈችው
ብቻውን ብቻውን ሕይወት ከተወችው ።
ለሰው እኮ ሰው ነው የመኖር ሰበቡ
ለሰው እኮ ሰው ነው የሕይወት አጀቡ
ሁነኛ ቀለቡ
የክት ቀን ልብሱ
የሃጃ ቀን ዳሱ
የተፈጥሮን ጣዕም በሰው ለመቅመሱ።
እንጂማ
ምን ሕይወት ቢሞላ
አቅደው ደክተው እንደሰሩት መንደር
የተፈጥሮ ሚዛን እኩል ቢደረደር
ሜዳው ሸንተረሩ
ጋራው ቦረቦሩ
ሁሌ አያስቦርቅም መልካው እና ፈፋው
ሁሌ አያስደስትም ጊዜው እና ስርፋው
አብሮነት ቁናውን በወጉ ካልሰፋው ።
#Amare Zewdu
አንተ እንሽላሊት
ብርቱ እኮ ነህ በርግጥ
ልፋትህ አለቅጥ …
ርምጃህ እሩጫህ
ድብብቆሽ ጥድፊያህ
ጉብዝና ተሰልቶ
ትጉ ነህ ቢሉህም………
ጅራትህ ሲቆረጥ ፣ እንጀራ የለህም።
እናስ አንተ ብኩን ….
ሸረሪት ሁን በቃ ፤
ጅራት ባጣስ ብለህ
በጉብዝናህ ንቃ ።
ተሸሸግ ፣ ተደበቅ
ግባ ወደ ጥጉ
አስላ ሆነህ ስጉ
አቅደህ ስለ ድር
መወጠን ብትጀምር …
ሸርተት ብለህ ትበላለህ
ጅራት እግርህ ቢያጥር ።
(ሚካኤል አ )
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 4 months, 1 week ago
Last updated 4 months ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 3 months ago