አብዱ ሰመድ || ᗩᗷᗞᑌᔑᗴᗰᗴᗞ

Description
{ إِنَّ ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّـٰلِحَـٰتِ سَیَجۡعَلُ لَهُمُ ٱلرَّحۡمَـٰنُ وُدࣰّا }

• • • እነዚያ ያመኑና በጎ ሥራዎችን የሠሩ አልረሕማን ለእነሱ ውዴታን ይሰጣቸዋል • • •
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 month, 3 weeks ago

አንዳንድ ሰው ላመነበት የፖለቲካ ርዕዮትም ይሁን አልያም "ህዝቤ" ለሚለውም አመለካከቱ ይሁን ብቻ በአካሄዱ ግን ምንም አይነት የአኼራ ግብ ሳይኖረው ለዱንያዊ ግብ የሚያደርገው መራር ትግልና ፅናት ይገርመኛል። የያኔዎቹ ትውልዶች የሚባሉት የዘመነ ሀይለስላሴና የደርግ ፖለቲካ ሰለባዎች እስከሞት ድረስ ላመኑበት መስመር የሚያደርጉት ትንቅንቅ አስደናቂ ነው። በተቃራኒው በዚህ መነጽር ውስጥ ለትግሉ የአኼራን እውነትነት የሚያምነው ህዝቡ ሙስሊምን ለተመለከተ ሰው ደግሞ ራሱን አብዝቶ እንዲፈትሽ የሚያደርግ ነው። አኼራ ያለብን እኛ ለዑማችን ሁለንተናዊ ለውጥ ስንል ዱንያን በመናቅ በሙሉ አቅማችን መትጋትና መልፋት ፈርድ የሚሆነው በኛ ላይ አልነበረም?

1 month, 3 weeks ago

ለማስታወሻ ያህል

ፍጡራንን አስመልክቶ የሚያደርጉት ነገር ኹሉ የተጻፈ ነው። የዝህችን ምድር ብርሀን ከማየታችን አስቀድሞ ስለእኛ በመዝገባችን ላይ ተጽፏል። ስለየትኛውም የሚገጥመን ነገር መጨነቅና መጠበብ ትርፉ ነፍስን መጉዳትና ማስጨነቅ እንጂ ሌላ ምንም የለውም። ረጅሙን መንገድ ቀጥል፣ የሚቻለውን ነገር ኹሉ በመፈጸም ላይ ታገል። ነገሮችህን ኹሉ ለእርሱ ብቻ ስጥ። ባሪያ ምን መብት አለው?! ዝም ብሎ አይደል የሚኖረው?!

ለአላህ የሚደረግ ባርነት (ዑቡዲያ) ደግሞ ትክክለኛውን ነጻነት ያወርሳል። ወዳጅ ከወዳጁ ጋር በሚገናኝበት ውድቅት ላይ ተነስቶ አስረዳኝ ብሎ መማጸን፣ ይህን የተወሳሰበ ዐለም ለመረዳት ያግዛል።

አላህ የልብ ንቃት ይለግሰን

1 month, 3 weeks ago

«ነገራቶችን በ‹ኩን ፈየኩን› የሚፈፅም ጌታ እስካለን ድረስ ‘ሁሉም ነገር በጊዜው መልካም’ ይሆናል»
ነጂብ መህፉዝ

ሰባሐል ኸይር

1 month, 4 weeks ago

ለሰዎች ቀልብ መሰበር ለሰዎች ሀዘን ውስጥ መግባት ለሰዎች ቁስል ሰበብ አትሁኑ ፣ በንግግራቸው በተግባራቸው አማኞችን የሚያስከፉና የማይሽር ጠባሳን የሚጥሉ ሰዎች آجلا أو عاحلا ዋጋቸውን ያገኛሉ ። በተለይ ያሀ ሰው ከአላህ ጋ ቅርበት ያለው ከሆነ መዘዙ የከፋ ነው የሚሆነው ። አንተ ያጠፋሀውን ጥፋት ከነጭራሹ ረስተሀው ሊሆን ይችላል ለዛሰው ግን በቀላሉ ማይሽር ቁስል ትተህ ነው ምታልፈው ። በዚሁ ስራህ ስትያዝ ራሱ ለምን እንደተያዝክ ሁሉ አታውቀውም ። የአማኞች ቀልብ የአላህ ውድ ንብረት ናትና እንጠንቀቃት ።

2 months ago

ታላቁ ሰሀቢይ ሰይዱና ዑስማን በድር ዘመቻ ላይ አልተሳተፉም ነበር ። ምክንያቱ ደግሞ የረሱለላህ ልጅ የሆነቺው ሩቅያህ በመታመሟና ዑስማንም እሷን የመንከባከብና የማስታመም ኃላፊነት ከረሱል በኩል ተጥሎበት ስለነበር ነው ። መዲና ውስጥ የሩቅያህን የማስታመም ኃላፊነት መውሰድ የሚችሉ ብዙ እንስቶች ነበሩ ። ነገር ግን ለሚስት ከቧላ በላይ ቅርብ ሰው የለምና እሷን ለማስታመም ሰይዱና ዑስማን በድርን ሚያህል ታሪካዊና ታላቅ ዘመቻ እንዲያልፈው ሆነ ። በዚህ ውስጥ ለቤት አባ ወራዎች ትልቅ ትምህርት አለ !

4 months, 2 weeks ago

በግንኙነት ዓለም ውስጥ ብዙ አይነት ሰዎች ያጋጥሙሀል ።
አንዳንዱ እንደ ፌክ ሽቶ ነው ለጌዜው ማዕዛው ቢማርክህም ግን ወዲያው ሽታው ብን ብሎ ይጠፋል - የማይዘልቁ ግንኙቶች በዚህ ይመሰላሉ ። እንደ በሽታ የሆነ ግንኙትም አለ ከዛ ሰው መለየትህ Reliefን የሚሰጥህ ፣ ሌላኛው ደግሞ በትውልድ ሀገር ይመሰላል ስትለያቸው ባይተዋርነት የሚሰማህ አይነት ግንኙነት ። ከዚህም የባሰ አለ እንደ ሩህና ጀሰድ አይነት ሆኖ እነሱን መነጠል እንደ ሞት የሆነ አይነት ወዳጅነት ። ሁሉንም ግንኙነቶች ጊዜና መከራ ይገልጣቸዋል።

4 months, 2 weeks ago

معالم فى الطريق

4 months, 2 weeks ago

ሰይዳ ዘይነብ አል-ገዛሊ ‹ሰይድ ቁጥብ ለምን የሞ'ት ፍር'ድ እንደተፈረደበት ለማወቅ መዓሊም'ን አንብቡ› ትለናለች ። ምክንያቱ ደግሞ መፅሀፉ ለእስርና ሞ'ት የሚዳርጉ ጠጣር ሀሳቦችን ያቀፈ በመሆኑ ነው ። እንደሚታወቀው ሙአሊፉም የህይወት ዋጋ ከፍሎበታል። ስለ ጃሂ'ሊ'ያውን ዓለም ፅልመትና ስለ ኢስላም ብርሀን ፣ ስለ ሃኪሚየቱል ዑልያ ፣ ስለ ተምሳሌታዊው የቁርዐን ትውልድ ፣ ስለ ኢስላማዊ ማህበረሰብ አመሰራረት ፣ በአላህ መንገድ ላይ የሚመጡ መከራዎችን መቋቋም ስለሚያስችለው ኢማናዊ ከፍታ እና መሰል ሀሳቦችን ያቀፈ ትልቅ መፅሀፍ ነው ። አይናችን ላይ ያጠላውን የጃሂሊ'ያ'ውን ስርዐት ለመግፈፍና ኢስላም የሰጠንን ነፃነት ለማጣጣም እንዲሁም በሁሉም እይታዎቻችን ከምዕራባዊያን ተፅዕኖ ተላቀን ወደ ዲናችን ለመመለስ ከከጀልን ይሄ አስደናቂና ዘመን አይሽሬ ኪታብ ብዙ ሚነግረን ነገር አለ ። እርግጥ ነው በዚህ መፅሀፍ ውስጥ የሰፈሩ ሀሳቦችን መሸከም የሚችል ትውልድ አፍርተናል ብዬ አላስብም ቢሆንም ግን የዛሬ ሀሳብ የነገ እውነታ ነውና መነበብ አለበት ብዬ አስባለው ።

መፅሀፉን የሚፈልግ በተከታዩ ሊንክ ያገኘዋል ?

4 months, 3 weeks ago

እስልምና ኪታብ ሱና ኢጅማዕና ቂያስ(ጀልይ) በሚባሉ ጠንካራ የመረጃ አይነቶች የተዋቀረ ዲን ነው ። ማንም ተነስቶ በህልሜ አየው ብሎ ወይም ከስሜቱ የመጣለትን በዲን ስም ማውራት አይችልም ። ኢስናድ የሚባል ነገር አለ ‹የሆነ ነገር ስታወራ› ከማን ይዘህ ነው ? ተብለህ ትጠየቃለህ ። ይሄ እስልምና ነው ለተራ እንቶፈንቶዎች ቦታ የለውም ።

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana