Tikvah Circle

Description
News from all #TIKVAH circles. All TIKVAH’s news in one place.

ዜና ከሁሉም #ቲክቫህ ክበቦች ። ሁሉም የቲክቫህ ዜናዎች በአንድ ቦታ ።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

2 months ago
የካፒታል ገበያ ጉባኤ ዛሬ ተጀመሯል።

የካፒታል ገበያ ጉባኤ ዛሬ ተጀመሯል።

ጉባኤው እስከ ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ይቆያል።

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከአፍሪካ ልማት ባንክ እና ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጀው።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ይህ ጉባኤ  " ዘላቂነት ያለው መንገድን ማበጀት " በሚል መሪ ቃል ነው መካሄድ የጀመረው።

ጉባኤው የገበያ ልማትን ለማፋጠንና ለአካባቢው ከፍተኛ የኢንቨስትመንት እድሎችን ለመክፈት ያስችላል ተብሏል።

ዛሬ በነበረው የጉባኤው የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ፣ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ አመራሮች ፣ ከአፍሪካ እና ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የተወጣጡ አመራሮች ተገኝተው ነበር።

በጉባኤው ቆይታ ከዓለምአቀፍ እና ከአፍሪካ በተወጣጡ የካፒታል ገበያ ባለሙያዎች የሚመሩ የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ።

ተሳታፊዎች በገበያ ሁኔታዎች፣ በቁጥጥር ማዕቀፎች፣ በኢንቨስትመንት እድሎች እና በቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ላይ ውይይቶችን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በጉባኤው ግልጽነትን እና የኢንቨስተሮችን ጥበቃ ለማጠናከር እንዲሁም ለኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ የቁጥጥር ማዕቀፍ ጠንካራ መሰረት ለመጣል ሲዘጋጅ ቆይቷል የተባለው የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ለህዝብ ሸያጭ ማቅረብ እና የግብይት መመሪያ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ለመጀመሪያ ጊዜ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮችን ለሽያጭ የሚያቀርቡ (IPO) አውጭዎች የዝግጅት ስትራቴጂ በተመለከተ፤ ተቋማዊ ባለሀብቶችን ማሰባሰብ እና እንደ ዘላቂ የፋይናንስ እና አረንጓዴ የካፒታል ገበያዎች ያሉ የኢትዮጵያን ልዩ ፍላጎቶች እና የልማት ግቦችን ማሳካት ላይ አውደ ጥናቶች ይደረጋሉ፡፡

@tikvahcircle

2 months ago
***💯*** የድምጽ ጥቅሎችን እየገዛን በ100% ጉርሻ …

💯 የድምጽ ጥቅሎችን እየገዛን በ100% ጉርሻ ደቂቃዎች እንንበሽበሽ!! ከሳፋሪኮም ጋር በአብሮነት አንድ ወደፊት⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
የቴሌግራም ቦታችንን በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን 24/7 ማግኘት ይቻላል!

2 months ago
Rosewood Furniture

Rosewood Furniture
ሮዝዉድ ፈርኒቸር

ዉበት! ጥንካሬ! አገልግሎት!

የተሟላ አገልግሎት የሚሰጥ ፈርኒቸር ለእርሶ በሚሆን መልኩ!

ደረጃዉን የጠበቀ ዲዛይን በማዘጋጀት የምንሰራልዎት ፈርኒቸር ምን እንደሚመስል በቅድሚያ ሙሉ እይታ እንዲኖርዎት እናደርጋለን!

What you see is what you will actually  get 👌

ይደውሉልን🤙📲   0905848586
Text us 💬   @Rosew0od

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ  👇

2 months, 1 week ago
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች …

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች ኦንላይን ምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 28 እስከ ህዳር 3/2017 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

በቅጣት ለመመዝገብ፦
ከህዳር 4-6/2017 ዓ.ም

Username እና Password ከሬጅስትራር ቢሮ በመውሰድ የኦንላይን ፖርታሉ ላይ መግባት ይችላሉ።

የኦንላይን ፖርታሉ የሚሠራው በዩኒቨርሲቲው ኔትወርክ ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

(የምዝገባ ሒደቱ እና የሚያስፈልጉ ሰነዶች ዝርዝር መረጃ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahcircle

2 months, 1 week ago
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች …

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የ2017 ትምህርት ዘመን ክፍያ ተመንን ይፋ አድርጓል።

በዩኒቨርሲቲው ሴኔት በፀደደቀ መመሪያ መሠረት አዲስ የማስተርስ እና የፒ.ኤች.ዲ. ፕግራሞች የክፍያ ተመን ከ2017 ዓ.ም የአንደኛ ሴሚስተር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

በዚህም የማስተርስ እና የፒ.ኤች.ዲ. ፕሮግራሞች የምዝገባ ክፍያ ለኢትዮጵያውያን ብቻ በሴሚስተር ብር 300 መሆኑ ታውቋል፡፡

(የዩኒቨርሲቲው የክፍያዎች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahcircle

2 months, 1 week ago
መመሳሰል ሰልችቷችኋል?

መመሳሰል ሰልችቷችኋል?
ጎልቶ አለመታየት ሰልችቷችኋል?
የተለመደውን አሰራር መከተል ሰልችቷችኋል?

ለስልጠናው አሁኑኑ ይመዝገቡ!
ለምርቶቻችሁ እና ለአገልግሎቶቻችሁ አዳዲስና ለየት ያሉ ሀሳቦችን ለማምጣት ይህንን ነፃ የኦንላይን ስልጠና ውሰዱ!

🗓 ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም
🕒 ከቀኑ 8:00 እስከ 11:00 ሰዓት

2 months, 2 weeks ago
5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ ነፃ …

5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቭ ነፃ ስልጠናን ለመከታተል ይመዝገቡ።

ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችልዎትን ስልጠና ይውሰዱ።

የስልጠና ዘርፎች፦

► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ

ስልጠናውን በስምንት ሳምንት ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይሰጣቸዋል።

ለመመዝገብ 👇

@tikvahcircle

2 months, 2 weeks ago
ጥራትን ከሚገርም ዋጋ ጋር ይዞ የመጣውን …

ጥራትን ከሚገርም ዋጋ ጋር ይዞ የመጣውን አዲሱን Kimem Itel Pro እናስተዋውቅዎ!  በአቅራቢያችን ወደ የሚገኝ የሳፋሪኮም ሱቅ ጎራ ብለን ዛሬውኑ እንግዛ!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያን በዚህ ሊንክ እናውርድ፦

የቴሌግራም ቦታችንን በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን 24/7 ማግኘት ይቻላል!

2 months, 2 weeks ago
Tikvah Circle
2 months, 3 weeks ago
" በፓለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት …

" በፓለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት ወደ ፀጥታ ሃይሉ እንዲጋባ የሚያደርግ ቅስቀሳና ነጭ ውሸት አልታገስም " - የትግራይ ክልል የፀጥታ እና የሰላም ቢሮ 

የትግራይ ክልል ፀጥታ እና ሰላም ቢሮ ባወጣው መግለጫ ፤ " የህዝብ እና የሰራዊት አንድነት በማላላት የአርስ በርስ ግጭት እንዲከሰት የሚሰሩት ግለሰቦች እና አካላት አንታገስም " ብሏል።

እንዲህ ያለው ተግባር ላይ ስለተሰማሩት ግለሰቦችና አካላት በግልጽ ስም ጠቅሶ ያለው ነገር የለም።

ቢሮው ፥ " በአገር ውስጥ እና በውጭ በመሆን በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች በመጠቀም በሬ ወለደ ውሸት በመንዛት በክልሉ የፀጥታ ሃይልና ህዝብ መካከል ያለው አንድነት እንዲላላ እየተሰራ እያየን በትእግስት ለማለፍ መርጠናል " ብሏል።

" ከአሁን በኋላ ህግ እንዲከበር በጥብቅ ይሰራል " ሲል አስታውቀዋል ።  

" በፀጥታ ሃይሉ ጉድለት አለ የሚል አካል ተጨባጭ አሳማኝ መረጃ በማቅረብ ህጋዊ በሆነ መልኩ ጥያቄ ማቅረብ ይቻላል " ያለው ቢሮው " ይሁን እንጂ ፓለቲካ አስታኮ የሚነዛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፅ ውሸት በግለሰብም ሆነ በየትኛውም አካል አያሰጠይቅም ማለት እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል " ሲል አስጠንቅቀዋል። 

" በፓለቲካ አመራሮች መካከል የተፈጠረውም ልዩነት ወደ ፀጥታ ሃይሉ እንዲጋባ የሚያደርግ ቅስቀሳና ነጭ ውሸት አልታገስም " ሲልም ገልጿል።

ቢሮው ፤ " የፀጥታ ሃይል የማንም የፓለቲካ ቡድን መሳሪያ አይደለም " ሲልም አክሏል።

የፀጥታ ኃይሉ በክልሉ ባለው የፓለቲካ መከፋፈል መካከል ገብቶ የአንዱ ደጋፊ የሌላው ተቃዋሚ እንዲሆን ታልሞ የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ መሆኑን የገለጸው ቢሮው " ይህ አይሳካም ፍፁም ተቀባይነት የለውም፤ ይህንን ተላልፎ የሚገኝ ግለስብና አካል በህግ እንዲጠየቅ በማድረግ የህግ ልእልና እንዲከበርና የህዝቡ ሰላምና ፀጥታ እንዲከበር እንሰራለን " ብሏል።

@tikvahcircle

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana