ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
ብርሸለቆ የገባ ምድረ ባንዳ ban ተደርጓል😁
ሞቅ ሞቅ አድርጉት ግዙፉን የሀገሪቱን ማስልጠኛ ተቋም እኮ ነው የተቆጣጠር ነው💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪
ሰከላ‼️
በአሁኑ ሰዓት መከላከያ እየተንቀሳቀሰ ስለሆነ ጥንቃቄ አድርጉ።
አሁን አምቢሲ አካባቢ እየደረሱ ነው።
ተጨማሪ መረጃ ያላችሁ በውስጥ አድርሱን።
ሰበር ዜና!
በዳውንት ወረዳ ገበያ ገብይተው ሲመለሱ በነበሩ ንፁኋኖች ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ከ50 በላይ የሚሆኑት መገደላቸው ታወቀ!
በሰሜን ወሎ ዞን ዳውንት ወረዳ ትናንት ህዳር 19/2017 ዓ/ም ገበያ ገብይተው በተሽከርካሪ ተሳፍረው ሲመለሱ በነበሩ ንፁኋን ወገኖች ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ከ50 በላይ የሚሆኑት ሕይወታቸው ማለፉን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
የድሮን ጥቃቱ የተፈፀመው በወረዳው ሰጎራ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ሲሆን፣ ህይወታቸው ካለፈ ንፁኋኖች በተጨማሪ በርካቶች ቆለው ወደ ህክምና ጣቢያ መወሰዳቸውን ነው የመረብ ሚዲያ የወሎ ወኪል የአይን እማኞችን በማነጋገር ለማረጋገጥ የቻለው።
ጥቃቱ የተፈፀመው ለደላንታ ወረዳ አዋሳኝ በሆነችው ልዩ ስሟ ሾጋ ተብላ በምትጠራ ቀበሌ ሀሙሲት ገበያ ገብይተው በተሽከርካሪ ተሳፍረው ሲመለሱ የነበሩ ገበያተኞች ላይ ነው ብለዋል ጣቢያችን ያነጋገራቸው ከጥቃቱ የተረፉ የአይን እማኞች።
በጥቃቱ ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች መካከል የሸቀጣሸቀጥ ነጋዴዎች፣ ገበያ ለመገብየት የመጡ እናቶችን ጨምሮ አርሶ አደሮችና መምህራን እንደሚገኙበት የተገለፀ ሲሆን ከ50 በላይ የሚሆኑት ወዲያውኑ ነው ህይወታቸው ያለፈው ተብሏል።
ህዳር 20/2016 ዓ/ም በደላንታ ወረዳ ወገል ጤና ከተማ ላይ በተፈፀመ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የወላድ እናቶች አምቡላንስ አሽከርካሪን ጨምሮ ሌሎች አምስት የሚደርሱ የጤና ባለሙያዎች መገደላቸው ይታወሳል።
በጥቃቱ ህይወታቸው ካለፈ ንፁኋኖች በተጨማሪ ተሽከርካሪ አምቡላንሱ እና በተሽከርካሪው ላይ ተጭኖ የነበረ መድሃኒት ሙሉ በሙሉ መውደሙ የሚታወቅ ሲሆን፡ በተመሣሣይ በዓመቱ ከዚኸው ቀጠና በቅርብ ርቀት በንፁኋኖች ላይ ከፍተኛ እልቂት ያደረሰ ጥቃት ነው የተፈፀመው።
አስቼኳይ መረጃ‼****
አመሻሹን ጨለማን ተገን በማድረግ ብዛት ያለው የአገዛዙ ጥምር ጦር ከአድስ ቅዳም ከተማ ወደ ፋግታ አቅጣጫ መንቀሳቀሱን የአይን እማኞች አረጋግጠውልናል። ፋግታዎች የኤፍሬም አጥናፉ ፍሬዎች ጥንቃቄ አይለያቹህ ስንል እናሳስባለን‼
ከአዲስ ቅዳም ብዛት ያለው ኃይል ወደ ፋግታ አቅጣጫ ተንቀሳቅሷል‼️**
1:00 ጀምሮ
20/3/17 ዓ.ም**
መረጃ‼️
ከባህርዳር የተነሳ አራዊት ሠራዊት በጥዋቱ 12:43amወደ ጎንደር 👉 አቅጣጫ ወጧል 1ዙ 23 ሌሎች በካሱኔ የተጫኑ ናቸው በ 5መኪና ፍጥነት አላቸው እስኪ share አድርጉት እንደ ተለመደው በስልክም አድርሱ‼️
#የአማራ ድምፅ ሚዲያ
*🔥#የአገዛዙ_የመጨረሻ_ጣረሞት‼️*
በመቅደላ ወረዳ በትናንትናው ዕለት በድሮን ሲደበድብ ከዋለበት ቀበሌ ሁለት ሞርታር፣ አራት ድሽቃ እና ከስድስት መቶ በላይ ጥምር ጦር ይዞ ከላይ #በድሮን ሽፋን በመሥጠት በጅሳ 018 ቀበሌ ዶሽትን ጨምሮ በግለሠብ ቤት በመግባት የአዝመራ ማከማቻ ጎተራዎችን በሰደፍ በመምታት የእህል አይነትን እንደህጻን ልጅ ሲበትንና ሲደፋ ውሏል።
ይህም ሳይበቃው ምጣድ፣ ብረትድስት በእየ ቤቱ እየገባ ከጥቅም ውጭ አድርጓል።በዶሽት ቀበሌ የፋኖ ቤት ነው በሚል #በእሳት_አቃጥለዋል‼️
ከእዚህ ቀድም ከፋኖ ጋር ሁነው ሲዋጉ የነበሩ አሁን ግን በእርቅ ስም የገቡ ሁለት ሰዎችን #አሠቃቂ ድብደባና ግፍ አድሮሶባቸዋል። ሌሎቻችሁም ከእዚህ ድርጊት ትምርት እንድትወስዱ እያሣሠብን
በዛሬው ዕለት ጀግናው የ018 ቀበሌ ህዝብ ለጀግናው የመቅደላ ፋኖ ላደረከው ተግባር ከልባችን እያመሠገን በቀጣይ ለምናደርገው ሁሉን አቀፍ ማጥቃት የተለመደውን ድጋፍ እንድታደርጉልን እና በተባበረ ክንድ ጠላቶቻችንን እንቀብራለን ሲሉ የአማራ ፋኖ በወሎ አምሃራ ሳይንት መቅደላ ክ/ጦር ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ቃል አቀባይ ፋኖ ሰይድ ከንስር አማራ ጋር በነበራቸው ቆይታ ጥሪ አቅርበዎል‼️
የደረሠውን ውድመትበ ፎቶና ቪዲዮ እንደደረሰን ይዘን እንመለሳለን‼️
©ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ**
*🔥#ወሎ_ቤተ_አምሐራ‼️*
የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ ጠላትን በደፈጣ ጥቃት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ማሳቀቅ ረፍት መንሳቱና መፈናፈኛ ማሳጣቱ ብሎም በደፈጣ ተዳክሞ ሲገኝ በመደበኛ ዉጊያ መደምሰስና መማረኩ ተጠናክሮ ቀጥሏል::
ዞብል አምባ ክፍለጦር ካለው ሰራዊት 1ኛ ሻለቃ እና በፋኖ አሻግሬ ሙሉ (ቦምበኛው) የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ ልዩ ዘመቻ ዛሬ ህዳር 13/2017 ዓ.ም በጋራ በወሰዱት የደፈጣ ጥቃት ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::
ጥቃቱ ከቆቦ ከተማ በምዕራብ ተኩለሽ መስመር ከ4-5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተፈፀመ ሲሆን በደፈጣ ጥቃት የተጀመረው ዉጊያ ወደ መደበኛ አድጎ ጠላት በርካታ ሙትና ቁስለኛዉን ይዞ ወደ ቆቦ ከተማ ፈርጥጧል:: የደፈጣ ጥቃቶቹ ከከተሞች በቅርብ ርቀት ተጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን ጠላትም በበርካታ ጥቃቶች ተሰላችቶ ወደ ፋኖ እየኮበለለ ይገኛል::
ራያ ቆቦ ተኩለሽ የገባው ጠላትም መሉ ለሙሉ ከበባ ዉስጥ ገብቶ ረሽንና ተጨማሪ የሰው ሃይል እንዳይደርሰው ሆኖ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው ሲል የዞብል አምባ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ሃብተማርያም መንበሩ ገልፇል::
በቀጣይም የህልዉና ተጋድሎው እስከ ድልና ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የዞብል አምባ ክፍለጦር አመራሮች እና የልዩ ዘመቻ አዛዡ ፋኖ አሻግሬ ሙሉ (ቦምበኛው) ገልፀዋል::
©የአማራ ፋኖ በወሎ**
በድጋሚ ሁሉም እንዲያውቀው !
አብይ አህመድ መራሹ አገዛዝ የታወጀና ያልታወጀ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመተግበር በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን የዘር ፍጅት እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ንፁሃን አማራዎችን የሚገድሉ፣ የሚያግቱና የሚዘርፉ ቡድኖች በባህር ዳር፣ በጎንደርና በደሴ ተደራጅተው እየሰሩ እንደሆነ ከውስጥ አዋቂ ምንጮች መረጃ ደርሶናል።
የጎንደርና የደሴን የገዳይና አስገዳይ እንዲሁም የአፋኝና ዘራፊ ቡድን ወደፊት የምንመጣበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በባህር ዳር ከተማ ያለውን የንፁሃን አማራዎች ገዳይ አስገዳይ ቡድን እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡
1.1 አቶ ደሳለኝ ጣሰው--------የአማራ ክልል የሰላምና ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ
1.2 ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን------የአማራ ክልል ፓሊስ ፖሊስ ኮሚሽነር
1.3 ረ/ኮ/ር ዋኘው -----የአድማ ብተና ም/ል አዛዥ ከላይ በሥም የተሰጠቀሱት የአማራ ክልል የሰላምና የፀጥታ አመራሮች የክልሉን መንግሥት መዋቅርና አቅም ሙሉ በሙሉ በመጠቀም ማንም የማያውቀው ስውር አደረጃጀት በመፍጠር በበላይነት የሚመሩ ናቸው፡፡
ይህን ስውር ገዳይና አፋኝ እንዲሁም ዘራፊ ቡድን በአብዛኛው ያደራጁት ከክልሉ የፀጥታ መዋቅር ውስጥ ማንም ሳያውቀው ወታደራዊ ብቃት አላቸው የሚሏቸውንና በጥቅም ሰንሰለት የያዟቸውን አባላት ከተለያዩ የፀጥታ ዘርፎች በመመልመል ነው፡፡
እነዚህ አመራሮች ባደራጁት የስውር ቡድን አማካኝነት በየቀኑ ማን መገደል፣ መታፈንና መዘረፍ እንዳለበት መረጃ ይቀበላሉ፤ በተገኘው መረጃ መሰረት ደግሞ ለገዳዩ የቡድኑ ክንፍ ማን መቼ መገደል እንዳለበት፤ ማን ምን ያህል ገንዘብ ከፍሎ መቼ ከእገታ ይውጣ፤ ማን በምርመራ ሥም በቀል ይፈፀምበት….ወዘተ እያሉ ስምሪት ይሰጣሉ፡፡
በአጠቃላይ እነዚህ በአማራ ክልል ራሳቸውን አድራጊና ፈጣሪ ያደረጉ አመራሮች የብልፅግናው አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰድ በስውር በአደራጁት ቡድን የነቁ አማራዎችን እያስገደሉ፣ እያሳፈኑና እያዘረፉ ከፍተኛ የሆነ ሐብትና ንብረት እያካበቱ ያሉ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ለእነሱ ስውር አደረጃጀት አይመችም የሚሉትን በየደረጃው ያለውን የክልሉን አመራር በሐሰት መረጃ ወደ ተለያዩ ማጎሪያ ጣቢያዎች እንዲጋዝ እያደረጉ ይገኛል፡፡
እነሱም፡- 4 ፓትሮል መኪናዎች፣ 2 ዲሽቃዎች፣ 2 ብሬን፣ 2 እስናይፐር፣ ቀሪዎች በቁጥራቸው ልክ ክላሽና ሙሉ ትጥቅ፣ የእነዚህ ስውር ገዳይና አፋኝ አባላት ጥቅማጥቅም እንደማነኛውም የአድማ ብተና አባላት ቋሚ ደምወዝ ያገኛሉ፡፡ ሌላው በልዩ የፀጥታ ሥራ ላይ ናቸው እየተባለ ከወር እስከ ወር ከክልሉ የሰላምና ደህንነት ቢሮ አበል ይከፈላቸዋል፡፡ ባለሐብቶችንና ነጋዴዎችን በማ*ገት ከሚሰበሰበው ገንዘብና የዓይነት ሐብት ኮሚሽን ይከፈላቸዋል፡፡
ይህ 31 አባላት ያሉት የገዳይና አፋኝ ቡድን በእነደሳለኝ ጣሰውና በእነ ኮ/ር ደስዬ ደጀን በስውር ከተቋቋመ ጀምሮ በባህር ዳርና አካባቢው ከፈፀማቸው ተግባራት መካከል የሚከተሉት ዋና ዋናዎች ናቸው፡፡ ከባህር ዳር ከተማ 13 ወጣቶችን አፍኖ በመውሰድ ገድሎ መንገድ ላይ ጥሏቸዋል፡፡
ከ50 በላይ ባለሐብቶችን በማፈን እንደመክፈል አቅማቸው ከ50 ሽህ እስከ 4 ሚሊዮን ብር ተቀብላል። ገንዘቡን የተቀበሉት አብዛኞችን አፍኖ ወስዶ በማሰር ሲሆን አንዳንዶችን ደግሞ በቤታቸው እንዳሉ ይህን ያህል ብር አምጡ ካልሆነ ትታሰሩና ትገደ*ላላችሁ ብሎ በማንገራገር ነው። በርካታ የመንግሥት ተሸከርካሪዎችን የአማራ ፋኖ ወሰዳቸው በሚል ሽፋን የውስጥ እቃዎቻቸውን በመፍታት አዲስ አበባ እየሄዱ እንዲሸጡ አድርጓል፡፡
የተለያዩ ባለሐብቶችን ተሸከርካሪዎች መንግሥት ለግዳጅ ፈልጎታል በሚል ሰበብና በእገታ በመያዝ እንዲሁ በቁማቸው እያረዱ ሸጠዋል፡፡ አገዛዙ ከአሰራቸው ውጭ በዚህ አፋኝ ቡድን ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ የባህር ዳር ነዋሪዎች በተለያዩ ቦታዎችና በግለሰብ ቤቶች ታፍነው ይገኛሉ፡፡ 4 የስውር ቡድኑን አባላት ረሽኗል፡፡ ስውር ቡድኑ ሲቋቋም አባላቱ 35 የነበሩ ሲሆን 4ቱን መረጃ አውጥታችኋል በሚል በእስር ሲያማቅቋቸው ቆይተው ረሽነዋቸዋል፡፡
ከእነዚህ መረሸን በኋላ እነ ደሳለኝ ጣሰው፣ ኮሚሽነር ደስዬ ደጀንና ረ/ኮ/ር ዋኘው ቀሪዎቹን 31 አባላት ሰብስበው በሚሰጣችሁ ተልዕኮ ዙሪያ መረጃ የምታወጡ ከሆነ እጣ ፈንታችሁ እንደ እነሱ መረሸን ነው ብለዋቸዋል፡፡ የተረሸ*ኑትን የስውሩ ቡድን አባላት ማንነትና የትውልድ አካባቢ ወደ ፊት የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
ከላይ እንደተባለው ይህ መረጃ በባህር ዳር ከተማና አካባቢው የተቋቋመውን ስውር ቡድን የሚመለከት ሲሆን በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ተግባራት እንደሚፈጽም የመረጃ ምንጫችን አረጋግጧል፡፡ የዚህ ስውር ቡድን ዋና ዓላማ የፖለቲካ ንቃት ያላቸውን አማራዎችንና የቡድኑ መሪዎች የማይፈልጓቸውን አማራዎች መግ*ደልና አጋጣሚውን በመጠቀም ሐብትና ንብረት ማካበት ነው፡፡
በመሆኑም የፌደራልም ሆነ የክልሉ መንግሥት በየራሳቸው መንግሥታዊ መዋቅሩን በመጠቀም እንዲህ የማፍያ ቡድኖችን በማደራጀት ስለሚሰሩ ይህን መረጃ ወስደው በማጣራት ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳሉ ተብሎ አይታሰብም፡፡ ይህ መረጃ የሚጠቅመው ለአማራ ክልል የከተማ ነዋሪ ሲሆን ሕዝቡም በሕግ ማስከበር ሥም እየገደለው፣ እያገተው፣ ሐብትና ንብረቱን እየዘረፈው ያለውን ስውር ቡድን በሚገባ አውቆ የሚችለውን ሁሉ እንዲያደርግ ከአፋኙ ቡደን አባላት መካከል የደረሰንን መረጃ ለማሳወቅ ነው።
(nkuamhara)
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana