ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 weeks, 4 days ago
Last updated 1 week, 6 days ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month ago
ሰበር ዜና ጄነራሉ ለትንሽ አመለጠ ፋኖ ጎጃም ላይ አስደናቂ ታሪክ ሰራ
?????????????
https://youtu.be/7-nbPDwqU-0?si=osj0BrHwKFG7MA5a
https://youtu.be/7-nbPDwqU-0?si=osj0BrHwKFG7MA5a
ሰበር የዛሬው የፋኖ አስደናቂ ድል
??????????
https://youtu.be/kcfTJzNn7Gw?si=XG5_LEIcJRmyPfTQ
https://youtu.be/kcfTJzNn7Gw?si=XG5_LEIcJRmyPfTQ
ሰበር ፋኖ በኦሮሚያ ክልል የዛሬው የምስራቅ አማራ ፋኖ
????????????
https://youtu.be/KrnlKmZyVMQ?si=9QUm-LU2aKfngUqM
https://youtu.be/KrnlKmZyVMQ?si=9QUm-LU2aKfngUqM
ሰበር ዛሬ በፋኖ ከባዱን ምሽግ ተደረመሰ የአድስ አበባ መግቢያ ሁሉም በሮች ተዘጉ ከንቲባዋ ደንግጣለች
?????????????
https://youtu.be/1t2Bpyj6jgc?si=g1EdQ9DCjPOf1AEA
https://youtu.be/1t2Bpyj6jgc?si=g1EdQ9DCjPOf1AEA
YouTube
ሰበር ዛሬ ከባዱ ምሽግ ተሰበረ | የአድስ አበባ መግቢያ ሁሉም በሮች ተዘጉ ከንቲባዋ ደንግጣለች fano amhara fano
#fano #amharafano #ፋኖ
ሰበር የአድስ አበባ ተማሪዎች ምድር አንቀጥቅጥ ተቃዉሞ
?????????????
https://youtu.be/mxLD4aC8brU?si=T3Y85-KtLUZWRP4I
https://youtu.be/mxLD4aC8brU?si=T3Y85-KtLUZWRP4I
YouTube
ሰበር የዛሬው የአድስ አበባ ተማሪዎች ምድር አንቀጥቅጥ የተቃውሞ ሰልፍ የፋኖ ምርኮኞች ሰልፍ አደረጉ
ሰበር ዜና የጎጃም ፋኖ ዕዝ ጥሪ አደረግ የአገዛዙ ሰራዊት በአራት አቅጣጫ ጥቃት ከፍቷል
????????????
https://youtu.be/vEIf7_nNTVk?si=1VSP9XFB4cf7ftKs
https://youtu.be/vEIf7_nNTVk?si=1VSP9XFB4cf7ftKs
YouTube
ሰበር መረጃ የጓጃም ፋኖ ዕዝ ጥሪ አደረገ የአገዛዙ ሰራዊት በአራት አቅጣጫ ጥቃት ከፍቷል
3 ነጥቦች
✔ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ዛሬ ሚያዚያ 26/2015 አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ተሰምቷል።
✔በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ወታደራዊ ዘመቻ በርካታ ንፁሃን ሰለባ እየሆኑ እንደሚገኝ ከየአካባቢዎች የሚወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።
✔ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረገው የትራንስፖርት ጉዞ ሸዋሮቢትና አካባቢው በተፈጠረ ግጭት መንገዱ ዛሬም ዝግ መሆኑ ተሰምቷል።
አቶ ክርስቲያን ታደለ "ስልጣን በመልቀቅ የመፍትሄው አካል አይሆኑም ወይ? ብለው ለጠየቁት ጥያቄ ጠ/ሚንስተሩ የሰጡት ምላሽ?
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሰጡት ምላሽ፦
"ስልጣን ብትለቅ የተባለው በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው ፤ ግን ጥሩ የሚሆነው ስልጣን ብንለቅ ነበረ ምክንያቱም መንግስት ማለት አስፈፃሚ ብቻ ማለት አይደለም። ህግ አውጪ መንግስት ነው፣ ህግ ተርጓሚ መንግስት ነው ፣ አስፈፃሚ መንግስት ነው እኛ እዚህ ያለን ሰዎች የመንግስት ባለስልጣኖች ነን።
ይልቁኑንም የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ደግሞ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው የአንድ ሚኒስትር አለቃ ናቸው እና በጋራ ብንለቅ ቢሆን ምክንያቱም እርሶም እንደሚገነዘቡት የሁሉ ችግር ምንጭ እና ባለቤት እኔ ብቻ ልሆን አልችልም። ኃላፊነት ከወሰድንም በጋራ ቢሆን ጥሩ ይሆናል ብዬ አስባለሁ።
ነገር ግን ይሄን ጥያቄ እሳቸው ቢያነሱትም እሳቸው ላይም ይነሳ ነበር በውጭ ያሉ እንደሳቸው ፓርላማ አሸንፈው መግባት ያልቻሉ ሰዎች ለምንድነው እኚህ ሰውዬ የቋሚ ኮሚቴ ኃላፊነት ላይ የተቀመጡት አይለቁም እንዴ ? እያሉ ከዚህ ቀደም በሚዲያ እንደምትሰሙት ብዙ ይተቻሉ፤ እርሶ ምርጫ አሸንፈው ነው የገቡት እዚህ ተቀምጠው የህዝቡን ጥያቄ ማንሳትዎ ተገቢ ነው ብዬ ማስበው መቆጣጠሩም የሚያደርጉት ጥረትም።
ግን ከስልጣን ጋር ተያይዞ ያለውን ጉዳይ በአንድ ቀላል ምላሴ ለማስረዳት በደቡብ ህንድ ጦጣን የማጥመድ ቴክኒክ አለ ጦጣን እንደምታውቁት ቁንጥንጥ ናት፣ ቅብዝብዝ ናት ለአደን አትመችም እና በደቡብ ህንድ ያሉ አዳኞች ጦጣን ለማጥመድ የኮኮናት ፍሬ በጦጣ እጅ ልክ በቀጭኑ ይቀዱና ከውሥጥ ሩዝ ያስቀምጣሉ ሲቀዱት የጦጣ እጅ ቀጭን ስለሆነ በዚያ ልክ ይቀዱትና ውስጥ ግን ሰፋ አድርገው ሩዝ ያስቀምጣሉ፤ሊይዟት ስለማይችሉ ጦጣ ሩዝ አየሁ ብላ እጇን ሰዳ ካፈሰች በኃላ ልውጣ ስትል የተሰራው ለቀጭኑ ስለሆነ ከጨበጠች በኃላ አይለቃትም።
ይቺ ጦጣ የሰው ሩዝ ነው የያዝኩት የማይገባኝን ሩዝ ነው የያዝኩት ይዤው ከቆየሁ ልያዝ እችላለሁ በትኜው ልሂድ አትልም እንደጨበጠች ትታገላለች በዚህ ጊዜ ያን የኮከናት ፍሬ መውሰድ ስለማትችል አዳኙ መጥቶ ይይዛታል። ጦጣዋን ያደናት የያዛት ምንድነው ያላችሁ እንደሆነ ሃሳቧ ነው እንጂ ወጥመዱ አይደለም፤ እዛው በትና በትለቅ ትወጣለች በሀሳብ ግን ሩዝ አፍሼ ካልወጣሁ ስላለች ሀሳቧ አጥምዶ ያስቀራታል እዛው።
ዶሮ ብታልም ጥሬዋን እንደሚባለው ቁጭ ብለው የሚያልሙ ሰዎች አሉ ሁል ጊዜ በዚያ መንገድ ጥሩ አይሆንም።
ሁለተኛ ቢጨበጥ ጥሩ የሚሆነው ስልጣንን በሚመለከት በእኔ እና በተከበሩ አቶ ብናልፍ መካከል የሚደረግ ድርድር የለም። የስልጣን ባለቤት ህዝብ ነው፤ስልጣን ሰጪም ነፋጊም ህዝብ ነው፤እኔ ና አቶ ብናልፍ ማድረግ ያለብን የተሻለ ሃሳብ ይዘን ህዝባችን ጋር መቅረብ እና የኔን ሃሳብ ምረጥልኝ ብለን በሰጪው ነው የምንመረጠው እንጂ በምክር ቤት ውስጥ ስጠኝ ልቀቅልኝ በሚል አይሆንም።
ሰጪው ጋር ሃሳብ የተሻለ ይዞ መቅረብ ታስፈልጋል፤ ስለዚህ ስልጣን በኮሮጆ እንጂ በመናጀ አይያዝም እና ሶስት ዓመት ይቅራል ለምርጫ በውጭም አሉ ይሄ የኦሮሞ መንግሥት ይሄ የኦሮሞ መንግስት እያሉ የሚዘፍኑ ዘፋኞች አሉ እነሱን ጨምሮ ሰብሰብ ብሎ ሃሳብ አጠናክሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ ማቅረብ ነው እኛ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንደተባለድ የተገባውን ቃል ካልመለስን የኢትዮጵያ ህዝብ በእኛ አስተዳደር ካልረካ በምርጫ ከጣለን በተደጋጋሚ እንዳልነው በደስታ እናስረክባለን። ፓርቲዎች መዘጋጀት ያለባቸው ሃሳብ ይዘው መምጣት ነው፤ አሁን ሃሳብ የለም፤ ሰብሰብ ብሎ ሃሳብ ይዞ ያን ወደ ህዝብ አቅርቦ ለመመረጥ እና ለማሸነፍ የሚደረግ ጥረት ለሁላችን የሚጠቅመን ይሆናል" ብለዋል።
የፌደራሉ መንግስት ከአሸበሪዉ “ኦነግ ሸኔ” ጋር ለመደራደር 10 ጊዜ ሙከራ አድርጎ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ አስታዉቀዋል፡፡
ከሸኔ ጋር ለሚደረገዉ ድረድርም መንግስት ኮሚቴ አዋቅሮ ወደ ሥራ እንደገባ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ቀደም የተደረገዉ ድርድር ሙከራ ያልተሳካዉ የሸኔ ኃይል የተበታተነ በመሆኑ ነዉ ብለዋል፡፡
መንግስት ከሸኔ ጋር ያለዉን ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ፅኑ ፍላጎት እንዳለዉም ተነስቷል፡፡
በቅርቡ የኦሮሚያ ከልል ለሸኔ ያቀረበዉ የእንደራደር ጥያቄ የክልሉ ዉሳኔ ሳይሆን የፌደራሉ መንግስት ዉሳኔ እንደሆነም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በማብራሪያቸዉ አንስተዋል፡፡
በዛሬው እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ወቅታዊና ሀገራዊ ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በምላሻቸውም፦
ሰላምን በተመለከተ
ኢትዮጵያ ውስጥ ከዛሬ ስደስት ወር በፊት ከነበረው ዛሬ የተሻለ ሰላም አለ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቆም አንድ እርምጀ ወደፊት የወሰደ ነው፤ ወደ ተሟላ ሰላም ለመሄድ በርካታ ስራ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
ተኩስ ሲቆም ወዲያውኑ የሰላም ዓየር አይነፍስም፤ ድህረ ግጭት የሚያሳድረው ቁስል ቶሎ የሚሽር አይደለም፤ የጦርነት ነጋሪትን አብዝተው የሚጎስሙ ዜጎች በመኖራቸውም የሰላም ዓየር መኖሩን ለማስብ ያስቸግራል ብለዋል፡፤
ኢትዮጵያ ውስጥ የመጠላለፍ፣ የሴራ እና የጉልበት ፖለቲካ ሲንጸባረቅ ቆይቷል ያሉጥ ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ የሚያስፈልገን ግን የሚያስፈልገን የሰላም፣ የይቅርታ መንገድ ነው ሲሉ መልሰዋል።
ሰላምን ማምጣት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ በጽኑ እናምናለን ያሉት ተቅላይ ሚንስትሩ፣ይሁን እንጂ ሰላምን ለማምጣት እንደ ጦርነት ጀግንነት ይፈልጋል፤ ሰላም ከጦርነት ባልተናነሰ ከፍተኛ ጥረት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
ሰላም ከጦርነት ያልተናነሰ ትጋት እና ስራን ይፈልጋል፤በተለይም አወንታዊ ሰላም ብዙ ከእኛ ይቅር ከሰላም የምናተርፈው ይበልጣል ብሎ ማመንን ይጠይቃል ብለዋል በምላሻቸው።
ሚዲያን በተመለከተ
ሚዲያን ሰው መርጦ መስማት አለበት፤ ይህ ካልሆነ አላስፈላጊ ነገሮች ይተላለፋሉ፤ አድማጭ ሃላፊነት አለበት፤ ሚዲያ ስለሆነ ብቻ ማዳመጥ አስፈላጊ አይደለም።
የሚዲያ ነጻነት እስከምን ድረስ ነው? የሚዲያ ነጻነት ዜጎችን እስከ ማጫረስ መድረስ የለበትም፤ መገናኛ ብዙሃን መረጃዎችን በሚያስራጩበት ጊዜ ሃላፊነት ሊወስዱ እና ሊሰማቸው ይገባል ብለዋል፡፡
ሰላምና መረጋጋትን በተመለከተ
"ሰላምን በተመለከተ ከዛሬ ስድስት ወር የተሻለ ሁኔታ አለ።
ወደተሟላ ሰላም ለመሄድ በርካታ ሥራ መሥራት ያስፈልጋል።
ነገር ግን አንድ ርምጃ ወደፊት የወሰደ ሥራ ተሠርቷል። ጦርነት እንደቆመ ወዲያውኑ ሰላም አይሰፍንም ድኅረ ጦርነት አውድ ጫና አለ።
ባለፉት 50 እና 60 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ፖለቲካ የመተላለፍ፣ የሴራ እና የጉልበት ፖለቲካ ነበር።
ሰላም አስፈላጊ ነው ብለን በጽኑ እናምናለን። ሰላም እንደጦርነት ጀግንነት ይፈልጋል።
ከጦርነት ያልተናነሰ ሥራ ድካም ይጠይቃል። የረጋ ሰለማዊ ነገር እንዲሁ አይመጣም አዎንታዊ ሰላም በሀይል አይመጣም። ምንግዜም ሰላም ሲባል የአንድ ሰው ህይወት ማትረፍም ስለሆነ በዚህ ላይ መሥራት ይገባናል። " ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚንስትሩ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
• ከድህረ ጦርነቱ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ሰላምን ለማስፈን ጊዜ ይፈልጋል
• የተሟላ ሰላም ለማምጣት በትብብር መስራት ያስፈልጋል
• የሰላም አየር በተሟላ መልኩ ለማስፈን ጦርነት ጎሳሚዎች የሚፈጥሩት ችግር እንቅፋት ሆኗል
• በአሁኑ ጊዜ ገዳዩ ሰይፍ ሳይሆን የሰላም፣ የፍቅርና የይቅርታ ሰይፍ ነው የሚያስፈልገን
• ሰላምን ለማስፈን በይቅርባይነት እና በአዎንታዊነት ደግፈነው በጋራ እውን ለማድረግ በትብብር ልንሰራ ይገባል
• አዎንታዊ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የምክክር፣ የትብብር ተቀራርቦ የመስራት ጅምሮች አሉ፣ ተጠናክሮ ይቀጥላል
• የሰሜኑ ጦርነት በሠላማዊ መንገድ የተደረሰው ስምምነት ወጤታማ ነው
• የሰራ ፖለቲከኞች ሰላም እንዳይፈጠር ይሰራሉ፤ በጉልበት ፖለቲካ የሚያምኑ ሰላም እንዳይፈጠር ይሠራሉ
• ለሠለም ምክክረ ውይይት ለመግባባት ብዙ መድረኮች ተፈጥረዋል የሚሉ ነጥቦችን አነስተዋል፡፡
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 weeks, 4 days ago
Last updated 1 week, 6 days ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 month ago