ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
Live stream finished (41 seconds)
Live stream started
Live stream finished (14 seconds)
Live stream started
ኢማም አሕመድ አል-ጋዚ
በሙዓዝ ሐቢብ
[[ ከሐዲዎች) ቢችሉ ከሃይማኖታችሁ እስከሚመልሳችሁ ድረስ የሚዋጉዋችሁ ከመሆን አይቦዝኑም፡፡]]
ሱረቱል በቀራ 217
- መካ ሳሉ ሶሓቦች ስድባቸውን እንኳ አይመልሱላቸውም ነበር።ይሰደባሉ፣ይዘለፋሉ፣ይታሰራሉ ይሰቃያሉ።ሆኖም የአፀፋ እርምጃም ሆነ ምላሽ አልሰጡም።ከሀዲያኑ ግን ሊተውዋቸው አልሹም። "አባትን ከልጅ፣ወንድምን ከእህት የሚለያዩ የአንድነት ፀሮች፣አማልክቶቻችንን የሚሳደቡ ውርጋጦች፣ባሪያዎቻችንን ያሳመፁ አመፀኞች!" እያሉ ሰዎችን ከነሱ ለማራቅ ቢጥሩም የሙእሚኖችን ቁጥር ከማሻቀብ ማገድ አልቻሉም።እናም ወደ ግድያ ተሻገሩ። ሱመያ፣ዐማርና መሰሎቻቸው "ለምን ሙስሊም ሆናችሁ?" በሚል ክስ ህይወታቸው በግፈኞች እጅ ተነጠቀ።
- ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም መዲና ላይ የፖለቲካ ስርዓታቸውን ሲዘረጉ በዙሪያው ያሉ አይሁዳንን የሚያቅፍ የሰላም ውልም አሰፈሩ።ግና ከሀዲያኑ የቁጣቸው እሳት የሚቀጣጠለው ሰላም በማጣታቸው ሳይሆን "ሙስሊም" የሚባል ፍጡር መመልከት ነውና ጧት ማታ የጥላቻ ሰይፋቸውን መርዝ መቀባት ያዙ።
እጅግ ሰላማዊት የሆነች ጥንፉፍ ሙስሊም ሴት አገር አማን ብላ ገበያ ወጣች።ይሁን እንጂ ሙስሊምን ለእይታ እንኳ የሚጠየፍ አንድ ከሀዲ ይህችን ምእምን በዝምታ ማለፍ አልቻለም።"ፊትሽን ገልጠሽ ካላሳየሽኝ" በማለት የጠብ እሳት ጫረ።ሙእሚኗ ጥቡቅ ናትና መቼም እንደማይሆን መለሰችለት።አይሁዲው ግን ከቶም ማረፍ አልቻለምና ልብሷን አስተሳስሮ ስትነሳ ኃፍረተ-ገላዋን በገበያ መሀል አሰጣው።ይህን ያየ እምቢኝ ባይ ክቡር ሙስሊም "ለእህቴ ክብር!" ብሎ ተነሳ። ገደለውም፤አይሁዳዊያኑም ሰፈሩበት።እነሆ ጦርነቱም ጀመረ!
- ነቢ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሓቦቻቸው ቅር እያላቸውም ስምምነቱን ተቀበሉ።ይህን የሰላም ዕድል ሊያጡት አልፈለጉም።እናም ሚዛናዊ ያልሆነው ውል ላይ ማህተማቸውን አሳረፉ።ይህ የሑደይቢያ ስምምነት ነው - ለአስር አመታት በሙስሊሙና በከሀዲያኑ መካከል እርቅ ይሆን ዘንድ የተፈፀመ ስምምነት።ከሀዲያኑ ግን የውሉ ቀለም ሳይደርቅ ከሀዲነታቸውን አስመሰከሩ።ውሉን ረግጠው ሰላማዊ ዜጎችን በማለዳ ጀንበር ፈጁ።ይሄኔ ነበር የሰላሙ ነቢይ ለሰላም ሰይፋቸውን የመዘዙት።ሰራዊታቸውን ክተት ብለው ወደ መካ ተመሙ።የከሀዲያኑን የክህደት ጎጆ ሊያፈራርሱ!
- ታላቅ የተሰኘው የሶቭየት ህብረት አመራር በስሩ የሚገኙ ሙስሊሞችን ኃይማኖት "ካላስቀየርኩ" ብሎ ተነሳ።በቀላሉ የሚበገሩ ሆነው ያለገኛቸውን ሙስሊሞች በዘመናዊ መሳሪያዎች ድብደባ ሀሳብ ለማስቀየር ወሰነ።ደበደበ፣ጨፈጨፈ፣ገደለ።ለፊርዓውን ሁሉ ሙሳ አለው ይባላልና የካውካሰስና የቺቺኒያ አንበሶች ተነሱ።እነ ሻሚል፣ኸጧብና ጀውሀር መሰል ሙጃሂዶች የራሺያን ሀይል ያብረከርኩት ጀመር።ትግሉም አየለ!
- ሙስሊሞች በጭቆና ጥላ ስርም ቢሆን "ቀን ያልፋል!" ብለው እየኖሩ ነው።አፄው ግን "ሀገሬ ላይ ሙስሊም የሚባል ፍጡር ማየት አልሻም" ብሎ ተነሳ።ምስኪኑን የወሎ ሙስሊም "ካልከፍርክ!" በማለት ዘመቻውን ጀመረ። "በዲኔስ አትሰበው!" እያሉ ሰይፋቸውን ከአፎቱ መዘው ተነሱ - ሙጃሂዱ ጦልሓ ጀዕፈር።ጦርነቱም ቀጠለ!
- "አትንኩን አንነካችሁም" እያሉ አለፍ ሲልም ለሰላም ሲሉ እየገበሩ ሀገራቸውን ለይተው ነበር የሚኖሩት።ግና አፄው ይህ አልጣመውም።ተዋጊወቹን አስከትሎ የሙስሊሙን መንደሮች አወደመ፣መሳጂዶችን አፈረሰ፣ቁርኣንንና ኪታባትን አቃጠለ።ይህን ድርጊትም ደጋገመ።ድል ዘውታሪ አይደለምና "በቃህ! " የሚሉ ወንዶች ተነሱ።ሐቀዲን፣ሰዕደዲን አሚር መሕፍዝና መሰሎቻቸው "እኛም ሰይፉን እንችልበታለን!" አሉት።ኢማም አሕመድ ተከተለ።አፄውን እያሳደደ አስፈረጠጠው።ፍልሚያውም በረታ!
- ዛሬም የተከሰተው ይኸው ነው።ፈጣሪያቸውን ለማመልክ መስጅድ ውስጥ የቆሙ፣ያጎነበሱ፣የተደፉ ሙስሊሞችን የትላንቱ ከሀዲዎች የልጅ ልጅ በበደል ጨፈጨፋቸው።'ዘመዶ'ቹም አጨበጨቡለት።
ልዩነቱ ለትላንቱ በደል ተበቃዮች ነበሩን።ዛሬ ግን ድርጊቱን ስታወግዝ እንኳ አፍህን የሚይዝህ ከጎንህ የቆመው ወንድምህ ነው - ወገንህ!
ግን ግን!
የባጢልና ሐቅ ፍልሚያ እስከ ቂያማ ይቀጥላል።ባጢል የረታ ሲመስለው ሐቅ ድባቅ ይመታዋል።ያ ቀንም ሩቅ አይደለም ኢንሻአሏህ!
ጊዜ ተገለባባጭ ናት! ህይወት ተዘዋዋሪ ናት! ጊዜው ይርዘም እንጂ ወሏሂ እንበቀላለን! ግራሙን በኪሎ፣ኪሎውን በቶን እንመልሳለን!
ግና እኛ እንደነሱ ወራዶች አይደለንምና መሳሪያ ያልታጠቀን ሰላማዊ ሰው አንነካም ! አዛውንትን አንገድልም! እንስቶችን አናስበረግግም !!!
እስከዚያው ግን ስማችን ብቻ ያስበረግጋችኋልና ተሸበሩ !!!
ሙስሊሞች በዘማቹ ኢማም አሕመድ መሪነት የአዋሽን ወንዝ ተሻግረው ለማጥቃት መሰናዳታቸውን የሰማው አፄ በፍርሀት ልቡ ራደ።በስሩ ያሉት ሰራዊቶች ጥቂት ሆነው ታዩት።መግቢያ መውጫው ቢጨንቀው ዳሞት ለሚገኘው ታላቅ የጦር መሪው ወሰን ሰገድ የድረስልኝ ጥሪ ላከበት።ወሰን ሰገድም የንጉሱን ጥሪ እንደሰማ ምላሹን ለገሰ።እንደደረሰም ሙስሊሞችን እንዴት መከላከል እንዳለባቸው ከጦር አበጋዞችና ቀሳውስቶች ጋር ተማከረ።"አንተው ነህ ያለኸን!" ቢሉት ጊዜ የልብ ልብ የተሰማው ወሰን ሰገድ "አሁን ያለፈው አልፏል።ካሁን በኋላ ወንድ ሁኑ፣ስለ ሀይማኖታችሁና ስለ ሀገራችሁ ስትሉ ተዋጉ!" ሲል በወኔ መከራቸው።
ሞራሉ ከፍ ያለው ወሰን ሰገድ በድንፋታ ለኢማም አሕመድ ጥሜቱንና ክህደቱን ከጠቀሰ በኋላ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ላከ።
" በመቀጠል:-
እኛ ክርስቲያኖች እናንተ ደግሞ ሙስሊሞች ናችሁ።በፊት ወደ ሀገራችሁ ሂደን አፈራርሰን እንቃጥልባችሁ ነበር።አሁን ግን አምላክ ድሉን ወደናንተ አድርጎታል።እስካሁን ያደረከው ይበቃሀልና ወደሀገርህ ተመለስ።ንጉሱ በሽምብራ ቆሬ፣አንፆኪያና ዙሬ(?) ማሸነፍህን ለራስህ እየነገርግ አትሸወድ!
ንጉሱ አሁን አይተኸውም ሆነ ሰምተኸው የማታውቀውን ብዛት ያለው ሰራዊት ሰብስቧል።
... አሁን የያዘከውን ምርኮ ይዘህ ወደሀገርህ ተመለስ።እምቢ ካልክ ግን ቀጠሯችን ቅዳሜ ነው።
እኔ ካሁን በፊት ታላቅ ወንድምህን ገራድ አቡንን ደጋግሜ አሸንፌዋለሁ።
እኔ እስካሁን እንዳገኘሀቸው ፓትሪያኮች እንዳልመስልህ! እኔ ወሰን ሰገድ ነኝ!!!"
እንዲህ በጉራና በዛቻ የተሞላው ደብዳቤ በወቅቱ ታሞ አልጋ ላይ ለነበረው ኢማም ይደርሰዋል።ኢማሙ ደብዳቤውን ይዞ የመጣውን መልዕክተኛ እንዲያ ታሞና ተዳክሞ መታየቱ ለከሀዲያኑ ወኔ እንደሚሰጣቸው ስላሰበ ህመሙን ተቋቁሞ ልብሱን ለባበሰና ተስተካክሎ ተቀመጠ።ሙስሊሞችም በተዋበ ሶፍ ተሰልፈው ፈረሶቻቸውንና የጦር መሳሪያቸውን አውጥተው፣ጋሻቸውን ወድረው ኢማሙን አጀቡት።የወሰን ሰገድ መልዕክተኛ ገባ።ደብዳቤውም ተነበበ።ኢማሙ ፍፁም አልፈራም አልደነገጠም።ይልቁኑም ኢማን በሞላው አንደበቱ "አለቃህን የትም ብትሄድ እንከተልሀለን በለው።ተመለሱ ላልከው የማይታሰብ ነው።ጦርነት ደግሞ ምኞታችን ቢሆንም እስካሁን ግን የሚፋለመን አላገኘንም በለው" አለ አሕመዴ በኩራት!
ቀጠለ "እስካሁን የያዘነውን ሀገርም አንለቅም።እንዲያውም ሙሉ ሐባሻን እንቆጣጠራለን - ኢንሻአሏህ! ነቢያችን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ((ምድር ተዘረጋችልኝና ምስራቋንም ምዕራቧንም ተመለከትኩ።የኡመቴ ንግስናም የተዘረጋልኝ ሁሉ ይደርሳል)) ብለው እንደነገሩን።እኛ ደግሞ በዚህ ንግግራቸው እርግጠኞች ነን - ኢንሻአሏሁ ተዓላ!
ተመለስና አሁን ያልኩህን ለአለቃህ ንገረው!"
መልዕክተኛው ለወሰን ሰገድ መልሱን አደረሰ።ይሄኔ ወሰን ሰገድ በፍርሀን ተንቀጠቀጠ።ቃላት አይደለም ጦር ቢደቀንበት፣ሰይፍ አንገቱ ላይ ቢዘረጋበት ጀግንነት አንጂ ፍርሀት የማይጨምርለት ሰው ጋር መፋጠጡን አወቀ።እናስ?
እናማ ዳግም መልዕክተኛውን ልኮ "እባክህን ያን ያልኩህ ቀሳውስቶቹ በል ስላሉኝ ነው።አንተን ለመዋጋት ደካማ ነኝ።መነኮሳቱ ባንተ እጅ እንደምወድቅ ነገረውኛልና እባክህን ስትይዘኝ እንድታዝንልኝ! " በማለት ልመናውን ቀብድ አስያዘ።
ኢማሜም ይህን ሲሰማ ከት ብሎ ሳቀና ለመልዕክተኛው "አይዞህ በእጃችን ስትገባ እናዝንልሀለን በለው" በማለት መለሰ።
ው።ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም" የምፈራላችሁ ድህነትን አይደለም።ግን ዱኒያ ከናንተ በፊት የነበሩት ዱኒያ እንደተዘረጋላቸው ለናንተም ተዘርግታ እነርሱን እንዳጠፋችው እናንተንም እንዳታጠፋችሁ ነው የምፈራላችሁ " ማለታቸው ተዘነጋ።
የዱንያ ፍቅር ከባድ ነው።የቱርኩ አሚርና የሀራቱ አሚር የምርኮ ድርሻቸውን ጠየቁ።በምርኮ ድርሻቸው ሁለቱ አልተስማሙም።ተጨቃጨቁ፤ከዚያም ሰይፍ ተማዘዙ።
አወ የታታር ወታደሮች ገና ሳያልቁ በምርኮ ገንዘብ ሰይፍ ተማዘዙ።ከሁለቱም ወገን ሰለባወች ወደቁ።ከተገደሉት ውስጥ የሰይፈዲን ወንድም ነበር።ሰይፈዲን በግራቅ በዚህ ተናዶ ወታደሩን ይዞ ለመሄድ ወሰነ።ጀላሉዲን ማድረግ የሚችለውን ሁሉ አድርጎ እንዲቀር ተማፀነው።እሺ ሊል ግን አልቻለም።ጀላሉዲን ስለ ጅሀድ እየጠቀሰ አላህን እንዲፈራ መከረው።ሰይፈዲን ግን አልሰማም።ሙስሊሞች ተለያዩ።
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
በሰይፈዲን ወታደር መቀነስ በሙስሊሞች ውስጥ ክፍተት ፈጠረ።የሰይፈዲን ወታደሮች ጦራዊ ቴክኒክ መቀነስ የሞራል ልሽቀት አስከሰተ። ቺንጊስ ካን ሁለት ጊዜ ያሸነፉትን ሙስሊሞች በራሱ ሊፋለም ሰራዊቱን ይዞ ወደ ገዝና ተንቀሳቀሰ። ሙስሊሞች ፍርሀት ፍርሀት አላቸው።ጀላሉዲን በቀረው ሰራዊቱ ታታሮችን መግጠም እንደማያዋጣ ስላሰበ ወታደሩን ይዞ ወደ
ደቡብ ሸሸ።ቺንጊስ ካን ግን የገባበት ገብቶ ለመፋለም
ቆርጧል።ጀላሉዲን ወታደሩን ይዞ እንዳባቱ ከከተማ ወደ ከተማ እየሸሸ ፓኪስታንን አቆራርጦ ህንድና ፓኪስታንን የሚለየው የኢንደስ ወንዝ ደረሰ።ጀላሉዲን ከህንድ አሚሮች ጋር የነበረው ግንኙነት የላላ ቢሆንም ከቺንጊስ ካን ግን ስለሚሻሉት ወደ ህንድ ለመሻገር ወሰነ።ነገር ግን ለመሻገሪያ የሚሆን ጀልባ የለም።ከሌላ ሀገር እንዲመጣለት አዘዘ።
ገና ጀልባወቹ ሳይደርሱ የቺንጊስ ካን ሰራዊት ደረሰባቸው።ከፊት ለፊታቸው የኢንደስ ወንዝ ከኋላቸው የቺንጊስ ካን ለአይን የሚያታክት ሰራዊት!
....ይቀጥላል
ክፍል አራት
ቺንግስ ካን በልጁ የሚመራ በመቶ ሺወች የሚቆጠር ሰራዊት ወደ መረው ላከ።የበለኽ ሙስሊሞችም አሉ።የመረው ሙስሊሞች ግን እንደ ሌሎች ሀገራት ከተማቸውን አስረክበው መታረድ አልፈለጉም።በሁለት መቶ ሺህ የሚገመት ሰራዊት አዘጋጅተው ጠበቋቸው።ፊት ለፊት ተፋጠጠጡ።ፍልሚያው ተጀመረ፤ሙስሊሞች በፅናት ተሟሙተው ተጋደሉ።ከሁለቱም ወገን ሰወች ወደቁ።ብዙም ሳይቆይ ግን የጦሩ ሚዛን ወደ ታታሮች አደላ።የሙጃሂዶቹን አብዛኛውን ሰራዊት ገደሉ።ቀሪወችን ማረኩ።ዳግም ከተማዋን ከበቡ።ለሶስት ቀናት ያክል ከተማዋን ሳይከፍቱ ቆዩ።በአራተኛው ቀን የታታሮች የጦር መሪ(የቺንግስ ካን ልጅ) ለመረው ከተማ አሚር "ራስህንና ህዝብህን አታስጨርስ፤እኛ ጋር ና እና አሚርነትህን እናፀናልሀለን፤ለቀንም እንሄዳለን" የሚል መልዕክት ላከ።የመረው አሚር የታታሮችን ቃል አመነ፤ወይም እንዳመነ ራሱን አሳመነ።በተባለው መሰረት ወጥቶ የቺንግስ ካን ልጅ ማረፊያ ዘንድ ሄደ።የታታሩ መሪ አከበረው፣በደማቁ ተቀበለው።ከዚያም "አጋዦችህንና የከተማውን ታላላቅ ሰወች አምጣቸውና ለስልጣን የሚገባ ካለ መርጠን እንሾመዋለን፤ከኛም ጋር ይሆናል" አለው።የመረው አሚር አሁንም ተታለለ።የመረውን ባለ ስልጣኖችና አጋዦቹን፣ታላላቅ ሰወችን አመጣ።የቺንግስ ካን ልጅ በእጁ ሲገቡ እንዲታሰሩ አዘዘ።ከዚያም ሁለት መዝገብ ሰጥቶ አንደኛው ላይ፦ የመረው ከተማ ባለ ሀብቶችና ከበርቴ ቱጃሮችን እንዲመዘግቡ፣ ሁለተኛው ላይ ደግሞ፦የባለ ሙያወችን ስም እንዲመዘግቡ አስገደዳቸው። ከዚያም የከተማዋ ሙሉ ነዋሪወች እንዲመጡ አዘዘ።ከሰባት መቶ ሺህ የሚልቁት የከተማው ነዋሪወች አንድም ሳይቀሩ መጡ።የቺንጊስ ካን ልጅ የወርቅ ወንበር ላይ ከተቀመጠ በኋላ የእባብ ልጅ እባብ እንዲሉ የሚከተሉትን ትዕዛዛት አስተላለፈ፦
_የመጀመሪያው ትዕዛዝ፦የከተማው አሚርና ባለ ስልጣናት እንዲገደሉ አዘዘ።ሁሉንም ተራ በተራ አረዷቸው።ሰወች እያዩ ያለቅሳሉ።
_ሁለተኛው ትዕዛዝ፦ባለ ሙያወችን ጠርተው ወደ ታታሮች ሀገር ወደ ሞንጎሊያ ተልከው በሙያቸው እንዲያገለግሉ
_ሶስተኛው ትዕዛዝ፦ባለሀብቶችና ነጋዴወችን በመጥራት ገንዘባቸው የት የት እንዳለ እስኪናገሩ እንዲቀጡ፤እንዲገረፉ።በዚህ መሀል በቅጣት ብዛት የሞቱ አሉ፡፡
_አራተኛው ትዕዛዝ፦ከተማው ውስጥ ገብተው ቤቶችን በሙሉ ፈትሸው ገንዘብና የገንዘብ ዘር ያለበት ነገር ሁሉ እንዲወረስ።ገንዘብ ፍለጋ ከተማዋን ሶስት ቀን ፈተሿት።የአሚሮችን ቀብር ቆፈረው ፈተሹ
_አምስተኛውና ዘግናኙ ለማመን የሚከብድ ትዕዛዝ፦የከተማዋ ነዋሪወች በሙሉ እንዲታረዱ አዘዘ።ሴቱን ወንዱንም ህፃናቱንም ሁሉንም እንደበግ አረዷቸው።ሰባት መቶ ሺህ ሰው በአንድ ቀን!
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
ታማኝ ምንጮች ባይጠቅሱት ወሏሂ ለማመን ይከብዳል።በምን ሰበብ እንደገደሏቸው ታውቃላችሁ?
ከተማዋን ልንከፍት ስንመጣ ተከላክላችኋል በማለት!
ሳታማሀኝ ብላኝ ነውኮ ነገሩ! በዚህ መልኩ መረውን ባዶ ከተማ አደረጓት።
የ #ነይሳቡር ወረራ
ታታሮች መረውን ካወደሙ በኋላ ወደ ነይሳቡር አመሩ።በከተማው ውስጥ በቂ የጦር ሀይል ቢኖርም የመረው አስደንጋጭ ዜና ልባቸውን በፍርሃት ስለ ሞላው ከአምስት ቀን ከበባ በኋላ ለታታር እጅ ሰጡ።ታታሮች የከተማዋን ነዋ ሪወች በሙሉ ወደ በረሃ አወጧቸው።የቺንግስ ካን ልጅ ወንዶቹ ሁሉም እንዲገደሉ አዘዘ።የመረው ነዋሪወችን ሲያርዱ በሰይፍ ተመተው የተረፉ ሰወች እንዳሉ ስለ ሰማ ያሁኖቹን ራሳቸውን ከሰውነታቸው እንዲበጥሱ አዘዘ።ሴቶችን ማረከ።ከተማዋን ለአስራ አምስት ቀናት ገንዘብ ፍለጋ አበራዩዋት።በዚህ መልኩ ነይሳቡርን ቅሪት አድርገው ለቀቋት።
#ሀራት ተረኛዋ የኹራሳን ከተማ ናት።በምዕራባዊ ሰሜን አፍጋኒስታን የምትገኝ ከተማ ስትሆን በጣም ሰፊና ብርቱ ከተማ ናት።ግና የታታርን ሀይል መቋቋም ሳትችል ቀርታ የመረውና የነይሳቡር እጣ ፋንታ ገጠማት።ወንዶቿ ተገደሉ፤ሴቶቿ ተማረኩ።"መሊክ ኻን" የተባለው ንጉሷ ግን ከተወሰኑ ወታደሮች ጋር ወደ ገዝና ከተማ ሸሽቶ ማምለጥ ቻለ።ኹራሳንን በሀራት አከተሙ።ቀጣይ እቅዳቸው ኸዋርዚምን መጠቅለል ነው።ኸዋርዚም የኸዋርዚም ሻህ ቤተሰቦች መናገሻ ስትሆን ከፍተኛ የህዝብ ክምችት አላት።በአሁን ሰዓን በኡዝቤኪስታንና በቱርክማኒስታን መካከልና በጀይሁን ወንዝ ፊት ለፊት ነች።ባላት ትልቅ ወሳኝነት ቺንግስ ካን ብዙውንና ታላቁን ሰራዊት ነበር የላከው።ይህ ሰራዊት ኸዋርዚምን ለአምስት ወር ከቦ ቢቆይም መክፈት ስላልቻለ ተጨማሪ ሀይል ተላከለት።ጥቃታቸውን አጠናክረው ምሽጉን ደርመሰው መግባት ቻሉ።አስፈሪ ፍልሚያ ተካሄደ።ከሁለቱም ጎን ብዙ ሰወች ቢገደሉም ድሉ ወደ ታታሮች አመዘነ።ሙስሊሞች እየሸሹ በየ ጉድጓዱ መደበቅ ጀመሩ።ታታሮች እጅግ ዘግናኝ እርምጃ ወሰዱ።ይኸውም የጀይሁንን ወንዝ ግድብ በማፈረስ ከተማዋን በጎርፍ አጥለቀለቋት።ቤቶች ተደረመሱ።ከኸዋርዚም ሰወች አንድም አልተረፈ።ከሰይፍ የዳነ በጎርፉ አለቀ።ኸዋርዚም ከከተማነት ወደ ባህርነት በአንድ ፀሀይ ተሸጋገረች።ከዚያ በፊት የሚያውቃት አሁን የት አካባቢ እንደነበረች ማወቅ አይችልም።በዚህ መልኩ ኸዋርዚምን ከካርታ ላይ ሰረዟት።
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
ታታሮች ቀጣይ እርምጃቸው የሆነው የታላቋን ኸዋርዚም ደቡባዊ ግዛት መዝመት ነው።ደቡብ ኸዋርዚም ታሪኩን ያሳለፍነው የሙሐመድ ኢብኑ ኸዋርዚም ሻህ ልጅ ጀላሉዲን ነው የሚያስተዳድረው።ጀላሉዲን የታታሮች ሙሉ ዜና ደርሶታል።የኹራሳንና የኸዋርዚም መውደቅ የአባቱ ሞት ደርሶታል።ቀሪው እሱ መሆኑ ኃላፊነቱን አክብዶበታል።እርሱም ይህን አስቦ የታታርን ጦር የሚመክት ሰራዊት እያሰባሰበ ነው።ጀላሉዲን መናገሻ ከተማው ገዝና(ከካቡል ሁለት መቶ ኪሜ አካባቢ ርቃ የምትገኝ በተራሮች የተከበበች አፍጋኒስታናዊ ከተማ
ነች) ከተማ ናት።
ጀላሉዲን ትልቅ ሰራዊት ማዘጋጀት ቻለ።በቅርቡ የሸሸው የሀራቱ አሚር መሊክ ኻን ከቀሪው ሰራዊቱ ጋር በመሆን ከጀላሉዲን ጎን ታታርን ለመፋለም ተዘጋጅቷል።ከቱርክ ሙስሊም መሪወች አንዱ የሆነው ሰይፈዲን በግራቅ ሰላሳ ሺህ ወታደር አስከትሎ ጀላሉዲንን ተቀላቀለ።ሰይፈዲን ጀግና፣በሳልና ብልህ መሪ ነው።ወታደሮቹም ጀግኖች ናቸው።ጀላሉዲን ሰራዊቱን አስከትሎ ከገዝና ከተማ ወጣ ብሎ በለቅ የተባለ በተራራ የታጠረ ቦታ ላይ ሰፍሮ ታታርን መጠበቅ ጀመረ።ታታሮች ደረሱ።
ፍልሚያው ተጀመረ፤ሙስሊሞች ተሟሙተው ተጋደሉ።ያላቸው ቀሪ ሀገር ይሄ ነው።የጀላሉዲን
አመራርና የሰይፈዲን በግራቅ ወታደሮች ጀግንነት የሙስሊሞችን መንፈስ አደሰ።ፍልሚያው ሶስት ቀን ዘለቀ።ታታሮች ያላሰቡት ጉድ ገጠማቸው።እንዲህ ፀንቶ የሚዋጋ ሀይል ይኖራል ብለው አልጠበቁም።ሙስሊሞች በፅናት ተፋለሙ።የአሏህ እርዳታ መጣ።ሙስሊሞች ድል አደረጉ።ታታሮች እግሬ አውጪኝ ብለው ወደ ቺንግስ ካን ፈረጠጡ።
አሏሁ አክበር!ወሊላሂል ሐምድ!!!
ታታሮች አይሸነፉም የሚለው ወሬ ከንቱ አደረጉት።ሽሽት የማያውቁት ታታሮች ለመጀመሪያ ጊዜ ተሸነፉ።
አሏሁ አክበር!!!
አወ! ሙስሊሞች በአንድ አሚር ስር በአንድነት ሲፋለሙ የአላህ እርዳታ መጣላቸው።
ጀላሉዲን በሙጃሂዶቹ ተማመኖ ቺንግስ ካንን ለዳግም ፍልሚያ ጋበዘው።ቺንግስ ካን አሁን ፍርሀት ተሰማው።በጣም ግዙፍ ሰራዊት በልጁ አሚርነት አድርጎ ላከ።
ከገዝናው ጦርነት የከበደ ፍልሚያ በካቡል ከተማ ተካሄደ።አሏሁ አክበር አሁንም ድሉ የሙስሊሞች ሆነ።በአስር ሺወች የሚቆጠሩ
ሙስሊም ምርኮኞችን ከታታሮች እጅ ማስጣል ቻሉ።በጣም ብዙ ገንዘብ ማረኩ።
ይህን ታላቅ ድል አጣጥመው ሳይጨርሱ ከካቡሉ ጦርነት መልስ አንድ አደጋ አንዣበበ።
የማረኩት ገንዘብ ፈተና ሆነባቸ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana