ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 4 months, 4 weeks ago
Last updated 4 months, 3 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 3 months, 2 weeks ago
ዋዜማ ሬድዮ
በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን በጅማ ከተማ ቤታቸው ለኮሪደር ልማት የፈረሠባቸው ነዋሪዎች መንግሥት በተከራየላቸው የሆቴል አልጋዎች፣ በግለሰብ መኖሪያዎችና በቀበሌ ቤቶች ውስጥ እየተንገላቱ መኾኑን ለዋዜማ ተናግረዋል። በከተማዋ አውራ ጎዳናዎች ግራና ቀኝ ያሉ የንግድና የመኖሪያ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ለኮሪደር ልማቱ መፍረሳቸውን ምንጮች ተናግረዋል። ከፈረሱት ቤቶች መካከል፣ አብዛኞቹ ሕጋዊ ካርታ ያላቸውና ግብር ከፋይ እንደነበሩ የጠቀሱት ምንጮች፣ ለፈረሱት ቤቶች ባለቤቶች መንግሥት የገንዘብ ካሳም ይኹን ተለዋጭ ቦታ አልሠጣቸውም ብለዋል። በኮሪደር ልማቱ የፈረሱት ቤቶች 15 ሺሕ ገደማ እንደኾኑ ዋዜማ ተረድታለች።
ተምረው ተምረው
በቀለም ተነክረው፥
በደም የጻፉትን በእርሳስ ከደለዙት
የላመውን ቅመም በዕንባ ከበረዙት
እንጃ ስለ ነገ፥ ቀን ስለመንጋቱ
ባለመድኃኒቱን የግፍ ሞት ሲግቱ።
አገርም ቀወሰች ታሟል ሣር ቅጠሉ
ሰው በሰው ወዳድቆ ጣ'ዮቹ ቀጠሉ።
/ዮሐንስ ሞላ/
ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ መግለጫ
ጥር 27 ቀን 2017ዓ.ም
የአማራን ህዝብ ለዘላቂ የህልውና አደጋ የዳረገው፣ በፋኖ ብርቱ ክንድ እየፈራረሰ ያለው እና አማራን በመጨፍጨፍ ላይ የሚገኘው የብልፅግና ወራሪ ቡድን አማራን በገሐድ በጅምላ በመጨፍጨፍ የእብደት ፖለቲካዉን ለማሳካት ያደረገው ሙከራ በመክሸፍ ላይ ይገኛል።
በዚህ አገዛዙ የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፈ በሚገኝበት እና የአማራ ህዝብም ራሱን ለማዳን ከጨፍጫፊው ስርዓት ጋር ከባድ ጦርነት ውስጥ በገባበት ወቅት የብልፅግና ቡድን በጀግኖች የአማራ ፋኖዎች እና በጀግናው ህዝባችን ክንድ ያልጠበቀው የሐይል መፈራረስ እና ፖለቲካዊ መፈረካከስ ገጥሞታል።
ቡድኑ በገጠመዉ ከባድ የመከላከል ተጋድሎ ክፉኛ ተመቶ መበታተኑን በመካድ ድርጅታዊ መዋቅሩ ያለ ለማስመሰል ከሰሞኑ የጨረባ ምርጫ አድርጎ ዳግመኛ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለማላገጥ ሞክሯል።
በተለይ አማራ ክልል ላይ ራሱን በተጨባጭ መሬት ላይ ያጣው የብልፅግና ቡድን የክልሉ መዋቅር ላይ ያለ ለማስመሰል የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ከመክፈቱ ጎን ለጎን በባህርዳር ከተማ አዲስ ድራማ ሊሰራ ዝግጅቱን አጠናቋል ።
ይህ ጨፍጫፊ ቡድን ከየወረዳዎች የባንዳ ካድሬ ዘመዶችን በመመልመል በነፍስ ወከፍ ከ30 ሽህ ብር ጀምሮ የአበል ክፍያ በማዘጋጀት በምክክር እና በሰላም ስም ካድሬዎች እና ጨፍጫፊ ጀኔራሎች በተገኙበት ስብሰባ ለማድረግ መዘጋጀቱን አረጋግጠናል ።
ይህንን ስብሰባ ለማድረግ የተዘጋጁበት ዓላማም:-
1/ በታንክ ታጅበው ውለው የሚያድሩ ካድሬዎችን እና አበል ተከፋይ ዘመዶቻቸውን በአበል ስም ሆዳቸውን ለመሙላት፣
2/ በአማራ ህዝብ ላይ ግልፅ ጦርነት አውጆ በየ ዕለቱ የዘር ማጥፋት በሚፈፅምበት ህዝብ ላይ ርካሽ የፖለቲካ ንግድ ለመነገድ ፣
3/ በፋኖ ብርቱ ክንድ ያረፈበት በመሆኑ እና ፈራርሶ ከመጥፋቱ በፊት ጦርነት ይብቃ የሚል የኑዛዜ እና የአደባባይ ለፈፋ ለማድረግ በማሰብ፣
4/ ህዝቡ በአደባባይ ለመንግሥት ጥያቄ አቀረበ በሚል በህዝቡ ጥያቄ መሰረት ወደ ምክክር ኮሚሽን የህልዉና ተጋድሎዉን ለመቀልበስ እና የህዝብን ጥያቄ ማዳፈን፣
5/ ህዝቡ በአደባባይ ለመንግስት የሰላም ጥያቄ አቀረበ በማለት ራሱን መንግስት እንደሆነ አድርጎ ለተመልካች ማሳየት
መሆኑ ተረጋግጧል።
በመሆኑም :-
1/ የፖለቲካ ጥያቄህ በሐይል ተጨፍልቆ
በአብይ አህመድ ገዳይ ስርዓት ግልፅ ጦርነት ታውጆብህ በየ ደጅህ እየተገደልክ ያለኸው የአማራ ህዝብ ይህንን ስርዓት በመስዕዋትነትህ ለማስወገድ አጭር ጊዜ የቀረህ በመሆኑ በየአካባቢው ለሚደረገው የህልውና ተጋድሎ የበኩልህን አማራዊ ትግል ከማድረግ ባሻገር የጠላት የስናይፐር እና የፖለቲካ ጥቃት ሰለባ ከመሆን ራስህን እንድትከላከል እናሳስባለን ።
2/ የአማራን ህዝብ ጥያቄ ለመደፍጠጥ በታንክ ተደብቀው እና በወራሪ ሰራዊት ታጅበው የግል ጥቅማቸውን በሚያሳድዱ ካድሬዎች ተታላችሁ ከትውልድ አካባቢያችሁ ወደ ባህርዳር እና ሌሎች ከተሞች እንዳትንቀሳቀሱ ስንል በጥብቅ እናሳስባለን ።
3/ ይሉኝታቸውን ሽጠው በመናኛ ሳንቲም ተገዝተው የብልጽግናን ቡድናዊ ዓላማ የህዝብ ፍላጐት ለማስመሰል ከሚሯሯጡ ሆድ አደሮች ራሳችሁን እንድታርቁ ለማሳሰብ እንወዳለን ።
4/ በመጨረሻም የአማራን የፖለቲካ ጥያቄ በወታደራዊ ሐይል ለመጨፍለቅ በህዝባችን ላይ ጦርነት ያወጀው ብልጽግና የሐይል ብልጫ ሲወሰድበት በአንድ በኩል ያለ ርህራሔ ንፁሐንን እየገደለ፤ መሰረተ ልማት እያወደመ በሌላ በኩል ተመልሶ ወደ ፖለቲካዊ ማጭበርበር የገባ በመሆኑ በኃይል የጀመረውን መንገድ በኃይል ቀልብሰን ከኢትዮጵያ ሰማይ ስር እስከምናሰናብተው የድርጅታችንን ጥሪ በመቀበል ዛሬም እንደ ትናንቱ በፅናት ፤ በጀግንነት ወራሪውን እንድትፋለም ጥሪ እናቀርበዋለን ።
አዲስ ትውልድ!
አዲስ አስተሳሰብ!
አዲስ ተስፋ!
(የአማራ ፋኖ በጎጃም)
በ1ኛ ክ/ጦር ኮ/ል ታደሠ ሙሉነህ ብርጌድ 4ኛ ሻለቃ ነበልባሏ አለማየሁ ከቤ ጦር ዛሬጥዋት15_03_2017ዓ/ም በፈፀመችው ግዳጅ በደቡብሜጫ ገርጨጭ ከተማ ላይ በማህበረሠቡ መኖሪያ ቤት ውስጥ ደፍጦ የሚገኘውን አሸባሪው የአብይ ሀይል ላይ ሰርጎ በመግባት ከፍተኛ የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ አድርጓል። የነበልባሎቹን የአለማየሁከቤ ተዋጊ ተርቦችን ምት መቋቋም የተሣነው የአብይ ዝርክርክ ጦር አሉኝ የሚላቸውን ከባድ መሣሪያዎች በተራሮችና በንፁሃን አርሶአደሮች መንደር ላይ የዙ23እና ዲሽቃ የፈሪ ዱላውን እያዘነበው ይገኛል።
የኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ቃል አቀባይ ሀላፊ ፋኖ ሄኖክ አሸብር ከግንባር
ወሎ ቤተ-አምሃራ
የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ ጠላትን በደፈጣ ጥቃት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ማሳቀቅ ረፍት መንሳትና መፈናፈኛ ማሳጣት ብሎም ተሰላችቶና ተዳክሞ ሲገኝ በመደበኛ ዉጊያ መደምሰስና መማረኩ ተጠናክሮ ቀጥሏል::
አሳምነው ክፍለጦር 1ኛ ሻለቃ ቃሊም መስመር አፍሪኬር ላይ ዛሬ ህዳር 15/2017 ዓ.ም ንጋት በደፈጣ ጥቃት የተለመደዉን ክንዳቸዉን ያቀመሱት ሲሆን የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊትም ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ፈርጥጦ ወደ ሳንቃ ከተማ ገብቷል ሲል የአሳምነው ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ንጉስ አበራ ገልፇል::
ዙፋን ጠባቂ የጠላት ሰራዊት ቃሊም ላይ በጀግኖቹ የዋርካው ምሬ ወዳጆ ልጆች በተደጋጋሚ ስለተደመሰሰና ስለተማረከ አልዋጋም ብሎ ተስፋ ቆርጦ ወልድያ ከተማ ተቀምጦ ወደ ንፁሃን ህዝብ ጭምር ከባድ መሳርያ በማስወንጨፍ በርካታ ንፁሃን መጨፍጨፉና እንዲሁም ንብረት እንስሳቶችና የደረሰ ሰብል ማውደሙ የሚታወቅ ነው::
የህልዉና ተጋድሎው እስከ ድልና ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ድል ለፋኖ
ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ
ህዳር 15/2017 ዓ.ም
የአማራ ህዝብ እንኳን የሰው ልጅ ሊያርድ ቀርቶ ያሳደገውን በግ እና በሬ እንኳን ጨክኖ ቢላዋ ስለማያነሳበት ወደ ገበያ አውጥቶ ነው የሚሸጠው ።
ሰሞኑን እነተመስገን ጥሩነህ ስለዘመነ ካድሬዎቻቸውን በአዳራሽ ውስጥ ሲዋሹ የከረሙት ጉዳይ አፈር አልብሷቸዋል።
የፋኖን ትግል ከፍ የሚያደርግ ጉዳይ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ ተፈጽሟል።
መርካቶ ላይ የጫሩት እሳት ከገመቱት በላይ ቁጣ ቀስቅሷል ።
እናም እነዚህን አጀንዳዎች ለማፈን በተደጋጋሚ እንዳደረጉት ዛሬ ሰው አርደው በቪዲዮ ለቀዋል።
በርካታ የኦሮሞ አክቲቪስቶች ጉዳዩ የዐብይ እና ሽመልስ ስራ መሆኑን እየመሰከሩ ነው።
የሆነው ሁኖ ሰሞኑን ከጎንደር እና ጎጃም በየብስ ትራንስፖርት አዲስ አበባ ለመሄድ የተዘጋጃችሁ ሰዎች ጥንቃቄ አድርጉ።
ስለሆነም ሁሉንም አቅሞች በአንድ ቋት በመሰብሰብ በአንድ አሃድ ለመምራት መረባረብ ወደ ድል የሚወስድ መንገድ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።
"የኃይል የበላይነትን መያዝ ማለት ሁሉንም አቅሞች አቀናጅቶ በመምራት በዋናው ጠላት ላይ በማሳረፍ ከጠላት የበለጠ ጉልበት ያለው ኃይል መሆን ማለት ነው።"
ሕዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም
©?በዛብህ በላቸው
በማናቸውም ጊዜ እና ቦታ የሚደረጉ ትግሎች በአንድ ቀመር የሚመሩ ናቸው። የኃይል ብልጫን መያዝ የትግል ሁሉ ዋና ስትራቴጅ ነው። የትጥቅ ወይም የፖለቲካ ወይም የሁለቱም ቅይጥ ትግል መሆኑ በዚህ ቀመር ላይ የሚያመጣው ልዩነት የለም። በዚህ ድምዳሜ ላይ የረባ ልዩነት እንደሌለ በሳይንስም በታሪክም ተደጋግሞ የተረጋገጠ ነው። በዛሬው ጽሁፋችን የአማራ ህዝብ ትግል ያለበትን ይዞታ በተመለከተ አጭር ዳሰሳ የምናቀርብ ሲሆን በጽሁፋችን መቋጫ ደግሞ ትግሉ በአጭር ጊዜ ተፈላጊውን ውጤት እንዲያመጣ ምን መደረግ እንዳለበት እና ምን መደረግ እንደሌለበት እንጠቁማለን።
ትግሉ ፈርጀ-ብዙ እና ባለ ብዙ ግንባር ሲሆን የኃይል የበላይነትን መያዝ ማለት ሁሉንም አቅሞች አቀናጅቶ እና በአንድ አሃድ በመምራት በዋናው ጠላት ላይ በማሳረፍ ከጠላት የበለጠ ጉልበት ያለው ኃይል መሆን ማለት ነው። ከዚህ በቀር በተናጠላዊ የትግሉ ግንባሮች ላይ ብልጫ መውሰድ የኃይል የበላይነት መውሰድን አያመለክትም። ትግሉን በኃይል የበላይነት መምራት በአስተሳሰብና ህሊናዊ ሁኔታ፣ በፕሮፖጋንዳው፣ በውጊያ፣ በዲፕሎማሲ ወዘተ ድምር የኃይሎች አሰላለፍ የበለጠውን ኃይል ከጎን ማሰለፍን የሚገልጽ እንጅ በነጠላ ጉዳዮች ላይ የተሻለ ሆኖ መገኘትን የሚመለከት አይደለም [ትግሉ ጦርነትን እንጅ ውጊያን ድል ለማድረግ የሚካሄድ አይደለም]። ይህ የትግሉ ቀመር የሆነው የኃይል የበላይነት ውስብስብ በሆኑ የሁኔታ ትንተናዎች የሚጨመቅ እንጅ እንዲሁ ክስተቶቸን በመደርደር የሚሰላ አይደለም። በመሆኑም የአማራን ህዝብ ትግል የኃይል ሚዛን ለመገምገም በቅድሚያ የትግሉን ምክንያት መበየን አስፈላጊ ይሆናል። ባለፈው ጽሁፋችን ለመግለጽ እንደተሞከረው የትግሉ ምክንያት ሌሎች ጉዳዮችን ሁሉ የሚወስን በመሆኑ በዝርዝር፣ በጥራት እና በጥልቀት መተንተን የሚገባው ነው። በዚሁ አግባብ ተለይቶ የሚቀመጠው የትግሉ ርዕዮት የኃይሎችን ምንነት፣ አሰላለፍ እና የአማራ ፖለቲካ ኃይሎች በመካከላቸውና ከሌሎች ኃይሎች ጋር የሚኖራቸውን የግንኙነት ዓይነትና ደረጃ የሚወስን መሰረታዊ ጉዳይ ነው። በእነዚህ ጭብጦች ላይ ያለንን ዝርዝር ግምገማ እዚህ ማስጣት አስፈላጊም ጠቃሚም ባለመሆኑ የምንዘልለው ቢሆንም የአማራ ህዝብ ትግል በዚህ ረገድ ያልተሰሩ ጉዳዮች ያሉበት መሆኑን መጠቆም ግን ተገቢ ነው። በዚህ ረገድ ታሪካዊ ተጠያቂነቱን የሚወስደው በመሰረቱ የአማራ ምሁር ነው። የአማራ ምሁራን እንደ ሌሎች ብሄሮች አቻቸው በርሃ ወርደው ባይገኙ እንኳ በያሉበት ሆነው የአማራ ብሄርተኝነት የትግሉ ማስተንተኛ ርዕዮት የመሆኑን አግባብነትና አስፈላጊነት በማብራራትና የአጸፋ ሙግቶችን በመመከት አሰላለፉን የማጥራት ታሪካዊ ኃላፊነት ያለባቸው ቢሆንም ይህን አላደረጉም። ይህ ትችት የማይመለከታቸው ጥቂት ምሁራን ታሪክ በወርቅ የሚከትበውን ሚና በመጫወት ላይ ቢሆኑም የአማራ ህዝብ ካለው የዘርፉ እምቅ አቅም አንጻር ሲታይ አሁንም የትግሉ ዋና ጉድለት ሆኖ ይገኛል። በአማራ ህዝብ አመጽና ተቃውሞ ነባሩ የኢህአዴግ ስርዓትና መዋቅር ተገርስሶ <<ለውጥ>> በሚዋለድበት [ከ2010 ዓ/ም-2013 ዓ/ም] ጊዜ በንቁ አደረጃጀትና ተሳትፎ ሲገለጥ የነበረው የአማራ ምሁራን መማክርት የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል አውጆ በሚዋደቅበት በአሁኑ ጊዜ መክሰሙ መማክርቱን ከአማራ ህዝብ ትግል ጠላፊዎች ውስጥ የሚያስመድበው ያደርገዋል። ከዚሁ ጉዳይ ሳንወጣ ንዑስ ድምዳሜያችን ለመግለጽ ያህል ትግሉ ካልተጠቀመበት የአማራ ህዝብ እምቅ አቅም አንዱና ዋነኛው የአማራ ምሁራን ናቸው ማለታችን ነው።
ባለፈው ጽሁፋችን ከክልሉ ውጭ የሚኖረውን አማራ እንደ መያዣ አድርገው የሚያስፈራሩ እና እንደ ድክመት (ስስ ብልት) የሚቆጥሩ ሁሉ ሰነፎችና አድርባዮች መሆናቸውን ለመግለጥ ሞክረናል። የአማራ ህዝብ በሁሉም ክልሎች ሰፍሮ የሚገኝ መሆኑ የአማራ ፖለቲካን እድልና አቅም የሚያሳይ እንጅ ማስፈራሪያ ወይም መያዣ አይደለም። አገዛዙ በሚከተለው ወደር የማይገኝለት የጭካኔ ፖለቲካ እና ባወጀው ጸረ-አማራ ዘመቻ ምክንያት ከክልሉ ውጭ የሚኖረውን አማራ ብቻ ሳይሆን በክልሉ ውስጥም በየቀኑ ህጻናትን፣ አቅመ-ደካሞችን እና ሲቪሎችን እየጨፈጨፈ ያለ መሆኑ የህልውና ትግሉ ምን ያህል ተገቢና አስፈላጊ መሆኑን ከሚያሳይ በቀር ከክልሉ ውጭ ያለው አማራ የትግሉ ስስ ገጽ ስለመሆኑ የሚናገር አይደለም። በየትኛው አካባቢ ምን ያህል እና ምን ዓይነት አቅም አለ? እንዴትስ ለመጠቀም ይቻላል? የሚሉትን ጥያቄዎች ዝርዝር ምላሾች እዚህ ማስጣት አስፈላጊ ባለመሆኑ የምንዘልለው ቢሆንም በዚህ ረገድ ያለውን አቅም በአግባቡ ከማሰባሰብና ከመጠቀም አንጻር ያለው ውስንነት ግን የትግሉ አንዱ ጉድለት እንደሆነ መጠቆም ይገባናል።
የትግሉን ርዕዮት በበቂ ሁኔታ ከመተንተን እና አሰላለፉን ከማበጀት አንጻር በቂ ስራዎች ባለመከናወናቸው የተነሳ በፋኖ ኃይሎች መካከል ሳይቀር ወደ ግጭት ያመሩ / የሚያመሩ ልዩነቶች ተስተውለዋል። በመግቢያችን ላይ የጠቀስነው የኃይል የበላይነት የመያዝ የትግል ሁሉ ቀመር ከዋናው ጠላት በቀር ሌሎች ንዑስ ጠላቶች እንኳን ቢሆኑ ከፍ ሲል አጋር እንዲሆኑ ዝቅ ሲል ከጠላት ጋር ሳይሰለፉ በገለልተኛነት እንዲቆሙ የማድረግ ስልትን የሚያሳይም ነው። በአስተሳሰብም ይሁን በአካላዊ አሰላለፎች ስትራቴጅካዊ ወዳጅ መሆን የሚችሉ፣ የሚገባቸውና ያለባቸው ኃይሎች በጠላትነት ሲፈራረጁና ገመድ ሲጓተቱ የሚታዬው የትግሉን ምንነት፣ ኃይሎችና አሰላለፋቸውን ለክብደቱ በሚመጥን ጥራት ባለመተንተኑ ምክንያት ነው። በዚህ ንዑስ ጭብጥ የምናስቀምጠውም ድምዳሜ የትግሉ አካላዊ መገለጫ ተደርገው በሚወሰዱ የፋኖ አደረጃጀቶች መካከል ያለውን ኃይል ሁሉ ወደ አንድ አቅጣጫ ብቻ የሚፈስ ከማድረግ አንጻር ጉድለቶች ያሉበት ነው።
ከላይ ለማሳያነት የተዘረዘሩ እንጅ በኢኮኖሚ (ሎጅስቲክስ)፣ በፕሮፖጋንዳ፣ በዲፕሎማሲ ወዘተ አቅጣጫዎች የሚደረጉ ዝርዝር ግምገማዎችም ገዥ ከሆነው የትግሉ ቀመር አኳያ ጉድለት ያለባቸው ናቸው።
የጽሁፋችን ማዕከላዊ ጭብጥ የሚነግርልን ፖለቲካ ስናስስ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በሮሃ ቴሌቪዥን ቀርቦ ከመዓዛ መሃመድ ጋር ባደረገው ቆይታ ካለን አቅም ውስጥ 2% (ሁለት በመቶ) ብቻ ነው እየተጠቀምን ያለው ሲል አግኝተነዋል። ጥቅም ላይ የዋለው የአቅም መጠኑ በትክክል ስንት ነው? የሚለውን ጥያቄ ለአስተያየት ክፍት አድርገን በሁለት ጉዳዮች እርግጠኞች ሆነን ከይልቃል ጌትነት ጋር እንስማማለን። አንደኛ 2% አቅማችን ብቻ ነው የተጠቀምነው የሚለው ድምዳሜና አነጋገር በ10% አቅማችን ነው እየተዋጋን ያለነው እንደሚለው ያለ ፕሮፖጋንዳ አይደለም። ሁለተኛ የአማራ ህዝብ ካለው አቅም አንጻር አሁን ጥቅም ላይ የዋለው እጅግ አነስተኛውን ነው።
ለማጠቃለል ያህል የትግሉ ሂደት እንዴት ያለ ነው? ውጤቱስ ምን ይሆናል? የሚለውን ነጥብ በተመለከተ ልዩ ልዩ መልሶችና ግምቶች ወይም ማብራሪያዎች የሚቀርቡ ቢሆንም የማይለወጠው እውነት የኃይል የበላይነትን የመያዝ ስትራቴጅን መከተል ትግሉ ሊመራበት የሚገባው አቅጣጫ መሆን አለበት የሚለው ነው።
የአማራ ፋኖ በጎጃም የአምበሳ ጥርስ አውጥቶ ጠንካራ እንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመረበት ዕለት አንስቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ ዋና ዋና የሚባሉ ኮር አመራሮች ጀምበር ከባህር ዳር ሰማይ ስር ስታዘቀዝቅ አዳራቸው አዲስ አበባ ነው።
ጭራሽ ጁላ እና አበባው ታደሰ ባህር ዳር ለመቆየት ደህንነት ስለማይሰማቸው ተጣድፈው የሰአታት እድሜ ቆይተው ነው ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱት (ፈርጣጭ ሁላ አንድ ቀን መማረካቸው አይቀርም) ። ዛሬ የተደረገው ተጨባጩ ነገር የአብዮተኛው
ዘመነ ካሴ ወንድሞች ህዝብ ስትጨፈጭፍ የዋለችን የጦር ሄሊኮፕተር አየር ላይ እንዳለ ድባቅ መተው አስፋልት ላይ ቀላቅለዋታል ። ሄሊኮፕተሯ ውስጥ የነበሩ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ነፍሰ ገዳዮች የእጃቸውን አግኝተዋል ።
ኤርፖርቱ ላይ ወደ አዲስ አበባ ሊሄዱ እየተዘጋጁ ከነበሩ ሰዎች መካከል ድረስ ሳህሉ
አንዱ ነበር። ሄሊኮፕተሯ ተመትታ እንደወደቀች የእንግዳ መጠበቂያው ላይ የነበረው ድረስ ተሯሩጦ መኪናው ላይ ሂዶ ሲገባ የእጅ ቦርሳውን Reception ላይ ጥሎት ሩጦ ስለነበር የአየር መንገዱ የጸጥታ ሰራተኞች ናቸው ተከትለው ሂደው የሰጡት ?።
የአማራ ፋኖ በጎጃም ተዓምር መስራቱን ይቀጥላል ።
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ !!
Dk ሆይ ከእዚህ በፊት መርዓዊ ላይ ባንዳ ለምን ለምንብርክክ ሄደ ብለህ ታላቁ አባት የኔታ ይባቤ ላይ በማያገባቸው ጉዳይ ያዙኝ ልቀቁኝ ስትል ነበር ።
ኦሮሚያ ምድር የሽመልስ ጦር ትልልቅ ሰዎችን በሚዘገንን መልኩ እንዲህ እያሰቃዬ ነው።
እና ይኼንን የመቃወም ሀሳቡ አለህ ወይ ??
ያኔ መርዓዊ ላይ ሳምንት የዘመታችሁ ሌሎች የሞራል መምህራንስ ወዴት ናችሁ ?
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 4 months, 4 weeks ago
Last updated 4 months, 3 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 3 months, 2 weeks ago