Tofa al-inaya

Description
አሰላሙዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ይህ የማዲህ Tewfik Selahudin የቴሌግራም ቻናል ነው ::
https://t.me/tewfikalinaya
ለአስተያየት ወይም ለጥያቄ 👉https://t.me/Tofaalinaya
መሃባው ጮሌ ነው ሀድራ መገስገሻ ፤
መሃባው ታጅም ነው የስንቱ መንገሻ ፤
መሃባው መደድ ነው የአላህ መለገሻ ፤
🍀🍀🍀🍀🍀
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 month, 2 weeks ago
***🍂***የሌሊት ሶላት......

🍂የሌሊት ሶላት......

◈ የአማኝ ሐይባው ግርማ ሞገሱ ናት
    በመቃመል ማህሙድ ከሐቢብ ጋር ለመሆን የፈለገ በዚህች ሶላት ላይ አደራ‼️
   ◈ወቅቷ ከኢሻእ ሶላት እስከ ፈጅር ባለው ግዜ ነው።
   ◈ከቻልክ ከሌሊቱ ግማሽ በኋላ ስገድ በላጩ ሰዐት ነውና ካልቻልክ ደግሞ  ከኢሻእ በኋላ ሰግደህ ተኛ‼️ አሏህ ይውደድህና🥰
   ◈ በሀዲስ እንደመጣው ረሱል ከ11 ረከዐ በላይ አይጨምሩም ነበር
   ◈ ኢማም ጁነይድ አል ባግዳዲይ አሱፊይ 300 ረከዐዎችን ይሰግዱ ነበር ‼️በ1ሌሊት🥰

◈ ሰይደቲ ራቢዐ የእንስቶቹ ፈርጥ  ሪከርዱን ሳትሰብረው አትቀርም 1000 ረከዐዎችን በአንድ ሌሊት...🥰
     ለምንድነው ሺህ ረከዐ የምትሰግጂው ብለው ጠይቀዋት  ጥሩ መልስ ነበር የሰጠቻቸው:-
🍂 "በቂያም ቀን የኛ ውድ መልእክተኛ በአንቢያኦችም ላይ ሳይቀር እንዲኮሩብኝ ፡   'እቺ እንስትኮ ወንዶቻችሁ ያልሰሩትን ገድል የሰራች ናት ' ብለው እንዲመሰክሩልኝ ብዬ‼️"       
📚سنن الهدى

ለውብ የፍቅር ሌሊት 💚صلو على الحبيب

1 month, 2 weeks ago
ሸይኽ አማን ኬራጎ ምርጥ የሀድራ መንዙማ …

ሸይኽ አማን ኬራጎ ምርጥ የሀድራ መንዙማ ሰይዴ
https://youtube.com/watch?v=_CDHK9OY9jw&si=uA7gbTC6jwdFR4Rw

1 month, 2 weeks ago

subscribe eyaderegachu 👍 wendmochachnn enaberetata

የቃጥባሬ ሀድራ መንዙማውችን የምትፈልጉ ከሆነ ይህው subscrib በማድረግ ፋሚሊ ይሁኑ

1 month, 3 weeks ago
***❤*** ፍቅር ማለት.......

ፍቅር ማለት.......

🦋 የአንዱን ( የምትወደውን ) ሰው ስም በዱአህ ላይ እሱ ሳያውቅ መጥራት ነው።🥰

1 month, 3 weeks ago

🪭ካለው ተወለድ ወይም ካለው ተጠጋ

አንድ ሰው ወደ አላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በመምጣት ቂያማ መቼ ነው ይላቸዋል ?
እሳቸውም ምን አዘጋጅተህላታል ሲሉ ይጠይቁታል ?እሱም ብዙ ሰላት ብዙ ሰደቃ ብዙ ፆም አላዘጋቸውላትም ነገር ግን አሏህና መልክተኛውን እወዳለሁ አላቸው።እሳቸውም አንተ ከወደድከው ጋር ነህ አሉት።

🌙ይህ ነው እንግዲህ ካለው ተጠጋ ማለት

ዘ.ሐ

2 months ago

ጀነት መግባት ትፈልጋለህ? 

የንፁህ ቀልብ አስፈላጊነት 

እውቁ የነቢዩ ኻዲም አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረ.ዐ.) እንዲህ ይላል፡-

‹አንድ ቀን ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ዘንድ ተቀምጠን ሣለ ድንገት ‹አሁን ከጀነት የሆነ አንድ ሰው በዚህ በኩል ብቅ ይላል፡፡› አሉን፡፡

ወዲያውም ከመዲና ሰዎች የሆነ አንድ ሰው ከፂሙ ውሃ እየተንጠባጠበ ጫማዎቹን በግራ እጆቹ ይዞ ብቅ አለ፡፡ በነጋታውም የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ይህንኑ ቃል ደግመው ተናገሩ፡፡ በድጋሜ ይኸው ሰው ብቅ አለ፡፡ በሦስተኛውም ቀን እንዲህ አሉ፡፡ ይኸው ሰው በተመሣሣይ ሁኔታ ላይ ሆኖ ብቅ አለ፡፡

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ከቦታው በተነሱ ጊዜ የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ.) ሱናዎች አጥብቆ በመከተል የሚታወቀው ታላቁ ሶሐባ ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ.) ሰውየውን ተከተለው፡፡

ለሰውዬውም እንዲህ አለው ‹እኔ ሰሞኑን ከአባቴ ጋር በሆነ ጉዳይ ላይ አልተስማማንም፡፡ ለሦስት ቀንም ወደ ቤት ላልገባ ምያለሁ፡፡ እነኚህ ቀናት እስኪያልፉ ድረስ እባክህን አስጠጋኝ፡›፡
ሰውየውም ያለ አንዳች ማንገራገር‹እሺ› አለው፡፡

ዐብዱላህ (ረ.ዐ.) ሦስቱን ቀን ከሰውየው ጋር አብሮ እያደረ እዚያው ቆየ፡፡ ግና በሰውዬው ዒባዳ ላይ ልዩ እና ተጨማሪ ነገር ምንም አላስተዋለም፡፡ ለሌሊት ሰላት አንድም ቀን ሲነሣ አላየውም፡፡ ብቻ አልፎ አልፎ በውድቅት ለሊት ፍራሹ ላይ በሚገላበጥበት ጊዜ አላህን ከማውሣቱና ‹አላሁ አክበር!› ከማለቱ በስተቀር፡፡
የሚገርም ነው! ሰውዬው ሙሉውን ሌሊት ተኝቶ አድሮ ለሱብሂ ሰላት ይነሣል፡፡

ከዚህ ባለፈ መልካም ነገር ብቻ ይናገራል፡፡
ሶስቱን ቀን ያጠናቀቀው ዐብዱላህ ‹ታዲያ ምን ሠርቶ ነው ይህ ሰው የጀነት ሊሆን የቻለው!› በማለት የሰውየውን ሁኔታ ለማናናቅ ቃጣው፡፡ ሙሉ ውሣኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ግን እርሱ ቤት ያመጣውን ትክክለኛ ነገር ሊነግረው ወሠነ፡፡

ዐብዱላህ ሰውዬውን አናገረው፡ ‹አንተ የአላህ ባሪያ ሆይ! በኔና በአባቴ መካከል የተፈጠረ አንድም ችግር የለም፡፡ ነገር ግን የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ዘንድ ተቀምጠን ሣለ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ‹ከጀነት የሆነ አንድ ሰው በናንተ ላይ ብቅ ይላል› አሉንና ሦስቱንም ጊዜ ብቅ ያልከው አንተ ነበርክ፡፡

እኔም በምን ሥራ ይህን ክብር ልታገኝ እንደቻልክ ለማወቅ ፈለግኩና ተጠጋሁህ፡፡ ነገር ግን ይህ ነው የሚባል ትልቅ ሥራ ስትሠራ አላየሁህም፡፡ እባክህን የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.)
ለመሠከሩልህ ለዚህ ታላቅ ደረጃ ያደረሠህ ነገር ምንድነው?› አለው፡፡

ሰውየውም ‹በርግጥ ያየሀውን ነገር እንጂ ሌላ ነገር ምንም ተጨማሪ አልሠራም፡፡› አለው፡፡
ዐብዱላህ ዞር ብሎ በሄደ ጊዜም ሰውየው ጠራውና እንዲህ አለው ‹ጉዳዬ በርግጥ እንዳየሀው ነው፡፡ ነገር ግን አንድ ነገር አለ፡፡ በውስጤ ለአንድም ሙስሊም ጥላቻ ኖሮኝ አድሬ አላውቅም፡፡

አላህ በሰጠው መልካም ነገር ላይ አንድንም ሰው ተመቅኝቼ አላውቅም፡፡› ዐብዱላህም ‹አዎን ከዚህ ትልቅ ደረጃ ያደረሠችህ ይህች ነገር መሆን አለባት፡፡ እሷም በርግጥ በቀላሉ  የምትቻል ነገር አይደለችም፡፡› እያለ እየመሠከረ ወደኋው ተመልሶ  ሄደ።

2 months, 1 week ago
2 months, 1 week ago
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana