ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
የችሎት ዘገባ ‼️****
የታሪክ ልሂቁ እና ጋዜጠኛው ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ በፋሽስታዊ አገዛዙ የ6 ዓመት ከ3ወር ጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ተጣለባቸው።
የአምሓራ ጥላቻ የዘር ፍጅትን በተቋም ደረጃ አዋልዶ የዘር ጭፍጨፋ እየተፈፀመባት ባለች ሀገር የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና ግጭት መቀስቀስ ወንጀል በሚል የፋሽስቱ አገዛዝ በፈበረከው ድራማ የተከሰሱትን አቶ ታዲዮስ ታንቱ ያለ በደላቸው በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ።
የኦህዴድ አገዛዝ በቀል በትር ሆኖ እያገለገለ የሚገኘው ስመ የፍትህ ስርዓተ ተቋሙ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የህገ-መንግስትና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አቶ ታዲዮስ ታንቱን በተከሰሱበትና ጥፋተኝነት በተባሉባቸው 3 የፈጠራ ክሶች ነው የጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት የጣለባቸው።
አቶ ታዲዮስ ታንቱ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት እና የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በፍትህ ሚኒስቴር በተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በኩል ተደራራቢ አራት ክሶች ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።
ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው አንደኛው ክስ ላይ እንዳመላክተው በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/(1)ሀ እና አንቀጽ 257/ሀ ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ግንቦት 11 ቀን እና በመጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም እና በተለያዩ የዩቲዩብ ቻናሎች ህዝባዊ አመጽ መቀስቀስ ወንጀል የሚል ነው።
በ2ኛ ክስ በተመለከተ ደግሞ የጥላቻ ንግግርንና ሀሰተኛ መረጃን ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁ 1185/2012 አንቀጽ 4 እና 7/4 በመተላለፍ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም በአንድ የዩቲዩብ ቻናል ሀሰተኛ መረጃ አሰራጭተዋል የሚል ክስ በዐቃቤ ሕግ ክስ ቀርቦባቸው ነበር።
በ3ኛ ክስ ደግሞ የወንጀል ህግ ከንቀጽ 32 /1ሀ ና አንቀጽ 337 በመተላለፍ የመከላከያ ሰራዊትን እቅስቃሴን ለማሰናከልና የመከላከል አደጋ እንዲደርስ ለማድረግ በማሰብ ሀሰተኛ ወሬ በመንዛት ቅስቀሳ ማድረግ ወንጀል የተከሰሱ ሲሆን በ4ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ቁ 958/2008 አንቀጽ 14 በመተላለፍ ህዝባዊ አመጽ እንዲፈጠር ቀስቃሽ መልዕክት በድምጽና በተቀሳቃሽ ምስል ተሰራጭቷል የሚል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።
ፍርድ ቤቱም የ6 ልጆች አባት መሆናቸውንና የ70 ዓመት አዛውንት መሆናቸውን ከግምት ውስጥ አስገባሁ በማለት ሁለት የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በዕርከን 24 መሰረት በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።
ሆኖም፣ አገዛዙ የሰጠውን የስልክ ትዕዛዝ ከመፈፀም ውጭ ክርክር የማያዳምጠው የችሎቱ ስዩማን በአቃቢ ህግ የቀረበለትን ክስ እንጅ፣ ጠበቃ እና ተበዳይ ያቀረቡትን ነፃ የመውጣት መብት አቤቱታ በመግፋት የኦህዴድ ብልፅግናን ትዕዛዝ ፈፅሟል።
ታዲዮስ ታንቱ በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ
ጋዜጠኛ ወግደረስ በጎጃም ፋኖ ቁጥጥር ስር ዋል። ለመላው የዐማራ ፋኖ ከሕዝብ ከተሰበሰበው ዶላር ላይ በእስክንድር ነጋ እየተከፈለው በጎጃም የእስክንድር የምናብ ሠራዊት እና ለሀብታሙ አያሌው ቅዠት ኢትዮ 360 በጎጃም ምድር ቋሚ ዘጋቢ በመሆን ሲያገለግል የነበረውን ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናውን የዐማራ ፋኖ በጎጃም በቁጥጥር ስር አውሎታል። ወግደረስን በቁጥጥር ስር ያዋለችው ደግሞ ፋኒት ትግስት ጫኔ ትባላለች። ዛሬ ጠዋት 1:15 አካባቢ ፈለገ ብርሃን አልጋ ቤት ውስጥ እያለ ነው ከእናት ድርጅቷ ከጎጃም ፋኖ አመራሮች በተሰጣት ትእዛዝ መሰረት ፋኒት ቲጂ ፋኖዎቿን አስከትላ ቀጨም ያደረገችው። አሁን የሀብታሙ አያሌውና የእስክንድር የመረጃ ምንጭ ከስሩ ከሰመ ማለት ነው።
ሰበር ሰበር ሰበር ‼️
የ73ኛ ክፍለ ጦር አመራር ከነ ሻምበል አመራሮቹ ተማረከ::
የአማራ ፋኖ በጎጃም የጎጃም አገው ምድር ክፍለ ጦር በሠከላ ከተማ የአገዛዙን አጎብዳጅ የ73ኛ ክፍለ ጦር አመራርን ጨምሮ በርካታ የሻለቃ እና የሻምበል አመራሮችን ከነ መገናኛ ሬዲዮናቸው ማረከ።
የአማራ ፋኖ በጎጃም የጎጃም አገውምድር ክፍለ ጦር ከትናንት ማለትም ከሀምሌ 19/2016 ዓ.ም ጀምሮ በስሩ ባሉ ብርጌዶች አማካኝነት ታላቅ ተጋድሎ እና ድል መቀናጀቱ ይታወቃል። የክፍለጦሩ ህዝብ ግንኙነት ለኢትዮ 251 ሚዲያ እንደገለጠው ዛሬ ማለትም ከሀምሌ 20/2016 ዓ.ም በጥዋት ጀምሮ ሰከላ ከተማን ለመቆጣጠር ፋኖ ባደረገው ታጋድሎ ከ5ኛ ክፍለ ጦር ጋር በመቀናጀት ባደረጉት ዘመቻ "ሰምበቶ እንዳጣፎ" የተባለ የ73ኛ ክፍለ ጦር አመራርን (ሻምበል አዛዥ) ጨምሮ በርካታ የሻለቃ እና የሻምበል አመራሮችን ከነ መገናኛ ሬዲዮናቸው ማርኳል። የአማራ ፋኖ በጎጃም የጎጃም አገውምድር ክፍለ ጦር ከ5ኛ ክፍለ ጦር ጋር በመቀናጀት የሠሩት ከፍተኛ ድል አመራሮችን ጨምሮ ከ40 በላይ የጠላት ጦር እእጁን ሲሠጥ ለአይን በሚያታክት መልኩ የጠላት ጦር ተረፍርፎ ወደ ሠማይ ተሸኝቷል።
የአገዛዙ ጦር አማራን በኢኮኖሚ ፣ በስነ ልቦና እና ህዝብን በማሳጣት ከሚያደቀውም በላይ በማይደራደርባቸው ጉዳዮች መምጣት ከጀመረ ሠነባብቷል። ቤተ እምነቶች ውስጥ በመግባት አጥራቸውን ምሽግ በማድረግ የማይደራደርባቸው መሆኑን በመረዳት ለማጢቂያነት ይጠቀምባቸዋል። ለዚህም ማሳያ በትናንትናውና በዛሬው ዕለት የአማራ ፋኖ በጎጃም የጎጃም አገውምድር ክፍለ ጦር ወደ ሰከላ በማቅናት ጠላትን ሲያርበደብድ ወደ አንቢሲ ጊዮርጊስ ገብቶ ቢቆይም በታላቅ ተጋድሎ ፋኖ አስወጥቶታል። በሀገር ቅርስ በሆነው ታላቁ የጊዮን አባይ ምንጭ መነሻ በሆነው የታላቁ የጊዮን በአል በሚከበርበት አባይ ዘራብሩክ ቤተክርስቲያን በመግባት ምሽግ ቆፍሮ እንዲሁም አጥሩን እንደ ምሽግ በመጠቀም የሀገርን ሀብት ለማውደም ቢነሳም ፋኖ በመረጋጋት እና በስልት ከቤተክርስቲያን እንዲወጣ በማድረግ ቀጥቅጦ አባሮ ሙትና ቁስለኛ እንዲሆን አድርጎታል።
የአማራ ፋኖ በጎጃም የጎጃም አገው ምድር ክፍለጦር(3ተኛ ክፍለጦር) ህዝብ ግንኙነት የጋዜጠኛ ጋሻዬ ንጉሴ ነው::
የአገዛዙ ጥምር ጦር ከፍተኛ ሽንፈትን አስተናገደ
በወሎ ግንባር በራያ ቀጠና የአገዛዙ ሰራዊት በትላንትናው እለት ከፍተኛ ሽንፈትን አስተናግዷል!
የፋኖን ትግል ከሀይማኖት ጋር በማያያዝ የወርቄና ገደመዩ አካባቢን ሙስሊም ማህበረሰብን ለፖለቲካ ፍጆታው መጠቀሚ ያደረገው የገዥው መንግስት ስርአትን ሴራ በማክሸፍና ከማህበረሰቡ ጋር የውይይት መድረኮችን በመፍጠር ማህበረሰቡ እስካሁን የሄደበት መስመር ስህተት እንደሆነ አምኖ እና ተገንዝቦ የፋኖን ሀሳብ በመደገፍ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
ይህንን የሰማው የገዥው መንግስ ጥምር ጦር ብረት ለበስ ታንክ እና ዙ 23 በመታጠቅ ፋኖን ለማፈን በተለያዩ አቅጣጫዎች የተሰማራ ቢሆንም በዲቢ ገደመዩ ቀበሌ የአማራ ፋኖ በወሎ የምስራቅ አማራ ፋኖ ዞብል አምባ ክ/ጦ እና የድቢና የወርቄ ባለሽርጡ ብርጌድ በጥምረት ባደርጉት ከፍተኛ ፍልሚያ ጥምር ጦሩን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ከ20 በላይ ነብስ ወከፍ መሳሪያ ገቢ መደረጉንም የዞብል አምባ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ሀብተማሪያምና የባለሽርጡ አመራሮች መረጃውን አድርሰውናል
-በአራዱምና በአቧሬ ቀበሌ ማህበረሰቡን ሲያሸብሩና ሲረብሹ የነበሩ የአገዛዙ አሽከር የነበሩ ሚሊሻዎቸም እና በሮቢት መንጀሎ የተሰማራውን የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት የካላኮርማ ክፍለ ጦር ሲቀጠቀጥ ማምሸቱን ከቦታው የደረሰን መረጃ ይገልጿል!
እስክንድር ቆስላለች የሚባል ነገር አለ
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ አለም አቀፍና ቀጣናዊ ትስስር ሃላፊ ፋኖ ዳዊት ቀፀላ መልዕክት
ጋሽ አሰግድ ዛሬ ላይ በጠላት እጅ ቢወድቅም** ሺሺሺሺዎች አሰግድ አለንና ልባችሁ አይታወክ ሁላችንም በያለንበት ጸንተን እንቁም!!
የትግሉ ባለቤት አማራ የተባለ ህዝብ ነው የምናደርገው የነፃነት ጉዞ ውጣ ውረድ ያለበት ብርሃንና ጨለማም የሚፈራረቅበት ብዙ ሥቃይና መንገላታት የማይታጠበት ነው እንደሁኔታው የራስ ጥላም ሳይቀር ይሸሻል በየትኛውም አጋጣሚ ቢሆን ሞገድ በማይሰብረው ጽኑ ዓላማ ከጫፍ መድረስን ግብ ያደረገ እልፍ ሰራዊት አለን እናም ልባችሁ አይታወክ። መጣ ሄደ በሚል ጉዳይ ላይ የሚባክን ጊዜ የለንም አንበሳው መሬት ላይ ታሪክ መስራቱን እንደቀጠለ ነው ይልቅስ በደራሽ አጀንዳ አትራኮቱ እያለፋችሁ ሂዱ ድላችንን አጣጥሙ ትግላችንን በልኩ ደግፉ በዚህ ግርግር ውስጥም የቆመ ስራ የለም በርካታ ድሎች ተመዝግበዋል።
ይህ ጉዞ መራራ ነው ነብስ የሚገበርበት ነው እንጂ የቅንጦት አይደለም በውስጥ ባንዳ አሳልፎ መስጠትም መማረክም የትግል አጋጣሚዎች ናቸው። ይህ ነውረኛ የሆነ የአገዛዝ ስርዐት ከእስከዛሬው ትግላችን በላይ ዛሬ አንድ ነገር አብራርቶልናል። በተለያዩ የዜና አውታሮቹና በዲጅታል ሰራዊቱ በኩል ካለበት የድል ናፍቆት የተነሳ በሰበር ያራገበው እጅ የመስጠት ዘገባ ለረጅም ጊዜ ያጣውን ደስታ እየካሰበት ቢሆንም ለእኛ ግን ክንዳችን በርግጥም ኃያል እንደሆነ አቅማችንም ጠንካራ ጉልበታችንም የተፈራ ስማችንም የሚያስጨንቅ እንደሆነ የተረዳንበት በጎ አጋጣሚ ነው።
የአማራ ትግል ከዚህም ከፍ ሲል ብዙ ጀግኖችን የሰዋ ነው ይሄው የአማራ ትግል በጀግኖች የደም መስዋዕትነት እልፎች እየተወለዱ ዛሬ መላው የአማራ ምድር በጀግኖች ተሞልቷል እናም አትሸበሩ አይዟችሁ እጅ በአፍ የሚያስጭን ተጋድሎ ውስጥ ያለው ብዙ ነው። ከፊት ካለው ኃያል ስም በላይ እጆቻቸው ኢላማ የማይስቱ ጽኑ ተፋላሚዎች አሉ መሬት ላይ ባሉት ተአምር አድራጊዎች ትገረማላችሁ የሰነፎች ወሬ አይጥለፋችሁ ዝም ብላችሁ እለፉ። ተስፋ የሚያስቆርጥ የትግል ጉዞ የለንም መራራ ዋጋ የሚጠይቅ የድል ጉዞ ላይ ነን ፍፃሜያችን የሚሆነው የፍትህ አደባባይ ላይ ነው። የመላእክት ዓለም በሁከት ተሞልቶ ነበር ነገር ግን በያለንበት ፀንተን እንቁም የሚል የሚያረጋጋ ድምጽ ነበር እኛም
በአላማጣ ከተማ የሪፐብሊካን ጥበቃ ኃይል አመራሮች በቀጥታ ከዐቢይ አሕመድ ትዕዛዝ እየተቀበሉ እንደሚሰሩ በራሳቸው አንደበት አሳውቀዋል።
የሪፐብሊካን ጋርድ የአንደኛው ክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አህመድ ኢሚ ይባላል።
የራያ አላማጣ አካባቢ ኮማንድ ፖስት አዛዥ ነው። ትውልዱ የጅማ ኦሮሞ ነው።
የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ብርጋዲየር ጄኔራል በላይ አየለ ይባላል።
የራያ አላማጣ አካባቢ ኮማንድ ፖስት ምክትል አዛዥ ነው። ትውልዱ አማራ ነው።
በነገራችን ላይ ልክ በወያኔ ዘመን እንደነበረው አንድ መቶ አለቃ ትግሬ ኮሎኔል የሆነው አማራ ወይም ኦሮሞውን ማዘዝ ይችል እንደነበረው፤ በዘመነ ኦሕዴድም የኮሎኔል ወታደራዊ ማዕረግ ያለው የኦሮሞ ተወላጅ የጀኔራል ማዕረግ ያለውን አማራ ወደላይ ያዘዋል።
አላማጣ ላይ ያለው የብልጽግና ሰራዊት የኃይል ስምሪት፦
ይህ ነው፦
የሪፐብሊካን ጋርድ የአንደኛው ክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አህመድ ኢሚ ይባላል።
የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ብርጋዲየር ጄኔራል በላይ አየለ ይባላል።
ኮሎኔሉ የጀኔራሉ አለቃ ነው። ያው የወያኔ ዘመን አሰራር ነው ተገልብጦ የመጣው።
የሆነው ሆኖ በአላማጣ የራያ አማራ ወጣቶችን ታርጌት ያደረገ አፈና እየተካሄደ ነው።
ኮሎኔል አህመድ ኢሚ፣ አላማጣ ሕዝቡን ሰብስቦ የማንነት ጥያቄ በምታነሱ፣ ከኋላ ሆናችሁ በምትቀሰቅሱ ላይ እርምጃ እንወስዳለን፤ በአደባባይ መቀጣጫ (በአደባባይ መረሸን ማለት) ነው የምናደርጋችሁ በሚል የዛቻ ንግግር ማድረጉ የመረጃ ምንጮች ለኢትዮ 251 ያደረሱን መረጃ ያመለክታል።
የራያ አላማጣ አከባቢ ኮማንድ ፖስት አዛዥ የሆነው ኮሎኔል አህመድ የአላማጣ ከተማ ወጣቶችን እና የሀገር ሽማግሌዎችን ሰብስቦ በዚህ ቀጠና ጉዳይ፣ ቀጥታ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠኝን ትዕዛዝ ብቻ ነው የማስፈፅመው፤ ከዚህ ውጭ ማንም አያዘኝም፤ ሁሉም ነገር በኮማንድ ፖስቱ ስር ይቀጥላል ከዚህ እንወጣለን ብትሉ በአደባባይ ነው እርምጃ የምንወስድባችሁ በሚል የዛቻ ንግግር ማድረጉን በስብሰባው የተሳተፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ለሚዲያችን ያደረሱት መረጃ ያመለክታል።
ኮሎኔል አህመድ፣ ይሄንን የተናገረው የወያኔ ታጣቂዎች ከነ ትጥቃቸው በተፈናቃይ ስም መግባታቸውን ተከትሎ ከራያ አላማጣ አማራ ሕዝብ ተከታታይ ተቃውሞዎች መነሳቱን ተከትሎ ነው ።
የራያ የማንነት ጥያቄን የሚያነሳው ፋኖ ነው እናንተም ይሄን ጥያቄ የምታነሱ ከሆነ ፋኖ ናችሁ ስለዚህ እርምጃ ይወሰድባችኋል ሲል ሕዝቡን ሰብስቦ ሊያስፈራራ የሞከረው ኮሎኔል አህመድ ትዕዛዝ ሚቀበለው ከዐቢይ አሕመድ ብቻ እንደሆነ በዚያው መድረክ ገልፆል።
ኮሎኔሉ ለዚህ እንዲያግዘን ደግሞ የሕወሓት ታጣቂዎች ከነ ትጥቃቸው ወደ ከተማዋ መግባታቸው ጥሩ ነው ሲል ቃል በቃል መናገሩን የስብሰባው ታዳሚዎች ለሚያዲያችን ያደረሱት መረጃ ያረጋግጣል።
በስብሰባው የተሳተፉት የከተማዋ ወጣቶችና የሃገር ሽማግሌዎች፡ የወያኔ ታጣቂዎች ሊወጡልን ይገባል፤ ሲቪል ተፈናቃይ የተባሉ ትግሬዎች ወደአማራ ግዛት ከመግባታቸው አስቀድሞ መጀመሪያ ስም ዝርዝራቸው ይላክልንና እውነተኛ ተፈናቃይ መሆናቸውንና አለመሆናቸውን በኮሚቴ ደረጃ ተዋቅሮ ይታይ የሚል ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም፣ ኮሎኔሉ በወታደራዊ እብሪት ተሞልቶ "አይመለከታችሁም። ማንም ይምጣ ማን ሁሉንም ትቀበላላችሁ" የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
ኮሎኔሉ አክሎም "እኔን የአማራ ክልል መንግስት ሊያዘኝ አይችልም፡ የኔ ኃላፊነት ቀጥታ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠኝን ተልዕኮ ማስፈፀም ብቻ ነው።ከዚህ ውጭ እንሆናለን ካላችሁ በአደባባይ ነው እርምጃ የምወስድባችሁ" ሲል ቃል በቃል ተናግሯል።
በስብሰባው ላይ ኮሎኔል አሕመድ
ደጋግሞ የተጠቀመው ቃል "በአደባባይ እርምጃ እንወስድባችኋለን"
በማለት ደጋግሞ ተናግሯል። ይህ ማለት ቀይ ሽብር እንደማለት ነው። የዘፈቀደ የጅምላ ፍጅት በዓለማቀፍ ሕጎች መሠረት ከጦር ወንጀሎች አንዱ ነው።
የስብሰባው ታዳሚዎች ያለስምምነት በዝምታ ስብሰባውን ጨርሰው ወጥተዋል።
በፎቶው ላይ የምትመለከቷቸው
ከግራ ወደቀኝ
1) ኮማንደር አብርሃም [በስተግራ] በአላማጣ ከተማ የፌዴራል ፖሊስ ኮማንዶ ልዩ ግዳጅ ኮማንደር የሆነ የኦሮሞ ተወላጅ
2) ኮሎኔል አህመድ ኢሚ [መሀል ላይ ያለው] የሪፐብሊካን ጋርድ የልዩ ግዳጅ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል አህመድ ኢሚ፤ (የኦሮሞ ተወላጅ)
3) ብርጋዲየር ጄኔራል በላይ አየለ [በስተቀኝ] የሪፐብሊካን ጋርድ የልዩ ግዳጅ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ (በሆዱ የወደቀ አማራ)
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana