ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 week, 2 days ago
Last updated 4 days, 6 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 3 weeks, 1 day ago
✨የእግዚአብሔር ምህረት✨
👉ዳዊት አንዴ እግዚአብሔርን ከበደለ በኋላ እንደዚህ ሲል ፀለየ
“አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።”
—
መዝሙር 51፥1
👉እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን በቁጣው፣ በመቅሰፍቱና በሚያስፈራ ክብሩ ቢታወቅም ዳዊት ግን የእግዚአብሔርን ቸርነት ስፋት አሰበ፤ በምህረቱ ተማመነ። ቀጥሎ እንዲህ ይላል ዳዊት
“በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፤ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።”
— መዝሙር 51፥7
👉ሂሶጵ ለሀጥያት ማስተሰረያ የተሰዋውን የበግ ደም ለመርጨት የሚያገለግል ቅጠል ነው። ዳዊት በእርሱ ምትክ የሚፈስለትን የበግ ደም አሰበ ፤በእርግጥም እግዚአብሔር ዳዊትን ምሮታል የእንደገና እድልም ተሰጥቶታል።
📌 አዲስ ኪዳት እግዚአብሔር የምህረቱን ልክ አንድያ ልጁን ለመስቀል ሞት በመስጠት ገልጦአል። በተሻለው ኪዳንም
*ዕብራውያን 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ።
…
²⁸ እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል።*
📌 በክርስቶስ ኢየሱስ የሀጢአት ስርየትን ተቀብለናል ስለሆነም መሳትና መውደቅ በህይወታችን ቢኖር እንኳን በክርስቶስ ደም ታጥበን እንደገና ያለ ሀጥያት መቆም እንችላለን። ደሙም ሀጥያትን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን በፅድቅ ለሆነውም ኑሮ ጉልበት የሚሰጥም ጭምር ነው።
“ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 2፥24
ፀሎት : አዲስ ኪዳን✨
የእግዚአብሔር ምህረት
purity conference day 1
ፓስተር ይመስገን ሞላ
ርዕስ: የሰማይ ስርአት ለመጽሐፍ ቅዱሣዊ ግንኙነት
የህይወታችን ገንቢ እግዚአብሔር ነው። ነገር ግን ከፍጥረት የሠማይን ስርዓት የተቃወመው የሰው ልጅ ነው። ስው የመጣው ከእግዚአብሔር ነው መሆን ያለበትም ከእግዚአብሔር ጋር ነው። ሔዋን የወጣችው ከአዳም ነው መሆን ያለባትም ከአዳም ጋር ነው። our life goal is እግዚአብሔርን ማሣየት ነው። God's presence is distinct feature of us. በወጣትነታችን ማለትም በ በአስራዎቹ እና በሃያዎቹ የምንሰራው ስራ በአርባዎቹ እና በአምሣዎቹ ላይ ዋጋ ያስከፍለናል።
በፍቅር ግንኙነት ውስጥ የእግዚአብሔር ፈቃድ ምንድነው?
የጋብቻ ትክክለኛ ትርጉም ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። sex ከጋብቻ እንዲሁ ከልጅ ጋር ይያያዛል። sex ልጅ ከማሣደግ መነጠል የለበትም። ልጅ በጋብቻ መሃል የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። sex ማዕከል ያደረገ ግንኙነት መጽሐፍ ቅዱሣዊ አደለም። sexual purity ከቅድስና አንዱ part ነው። ትንቢተ ኤርሚያስ 6 :9 ትክክለኛውን የትውልድ መስመር ያሣየናል። በዚህም ክፍል ከ sex በፊት ጋብቻ እንደሚቀድም ና ከ ልጅ መውለድ እንደሆነ ያስተምረናል። ሰው ግን ትክክለኛ መረጃ ስለሌለው ጥፋተኛ ሆኗል። አዳም ና ሔዋን አንድ ስጋ የሆኑት ከተጋቡ በኃላ ነው። አሁን ላይ purity መጥፋት ዋናው ምክንያት Bible መሰረት ያደረገ ህይወት መጥፋት ነው ።
what is the purpose of sex according to bible?
አንደኛው ባል ና ሚስት አንድ እንዲሆኑ ነው ። ሌላኛው ዘራቸው እንዲበዛ እና የመጨረሻው መደሰቻ ነው። የዕለቱን ህይወት ዕለቱን መኖር ነገን ያድናል። ንፅህናችንን መጠበቅ የኛ ሀላፊነት ነው። false intimacy ከሚፈጥሩ መሃል አንዱ ራስን ማርካት ነው። እነዚህ ነገሮች በሙሉ ከእግዚአብሔር ሀሣብ ይለዩናል። ለእኛ የከበረ ነገር ስላለ ራሣችንን ማክበር አለብን። መንፈሣዊነታችን ለስጋችን መጠበቅ አስተዋጽኦ አለው።
የዛሬው ፕሮግራማችን ይሄን ይመስል ነበር አብራችሁን ስለነበራችሁ ከልብ እናመሰግናለን! ይሄንን ቻናል ለምታውቋቸው እህቶች share አድርጉ! መልካም በዓል ይሁንላችሁ እያልን እንሰናበተችኋለን እንወዳችዋለን? ተባረኩልን።
??መልካም አዲስ አመት??
የጨዋታው አሸናፊዎችን በውስጥ መስመር እንሸልማለን። የተሳትፋችሁ ሁሉ ጌታ እየሱስ ይባርካችሁ!!!
The winners; 1st @YonasAyele
2nd ; @Lael57
መልሱ ይህ ነበር;
1,አርዮስፋጎስ
2,5
3,በሉቃስ ወንጌል
4,31
5,ዮሐንስ እና ያዕቆብ
6,መዳንን
7,መንፈሱ ከእርሷ እንዲወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዘዘው
8,በአንጾኪያ
አሁንም አልረፈደም መልሳችሁን ላኩልን ?
1,በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የአቴና ሰዎች እና በዚያ ይኖሩ የነበሩ እንግዶች አዲስ ነገርን መናገርና መስማት ይወዱ ነበር እናም ይህንን ነገር የሚያካሂዱበት የተለየ አደባባይ አለ። ይህ አደባባይ ስሙ ምን ይባላል ?
ሀ,መላጥያ
ለ,አድራሚጢስ
ሐ,አርዮስፋጎስ
መ,አካይያ
2,መፅሐፍ ቅዱስ ላይ በአይሁድ ባህል መሠረት ዘር የሚቆጠረው በወንዱ በኩል ነው። ነገር ግን በማቴዎስ ወንጌል የክርስቶስ ዘር ቆጠራ ላይ የገቡ( የተጠቀሱ ) ሴቶች አሉ !! በክርስቶስ ዘር ተካተው የተቆጠሩ ሴቶች ስንት ናቸው ?
ሀ,3
ለ,5
ሐ,7
መ,ከ10 በላይ
ሠ,42
3,የጠፋው ልጅ ታሪክ በየትኛው የወንጌል መፅሐፍ ውስጥ ይገኛል ?
ሀ,በማርቆስ ወንጌል
ለ,በሉቃስ ወንጌል
ሐ,በዮሐንስ ወንጌል
መ,በማቴዎስ ወንጌል
4,እግዚአብሔር በሙሴ ተጠቅሞ እስራኤላውያንን ከግብፅ ምድር ካወጣቸው በኃላ... ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ሀገር ኢያሱ ከሙሴ ህዝቡን ተረክቦ ለማስገባት ስንት ነገስታትን ገደለ?
ሀ,100
ለ,1000
ሐ,77
መ,31
5,የነጎድጓድ ልጆች በመባል በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚታወቁት እነማን ናቸው ?
ሀ,ዮሐንስ እና ያዕቆብ
ለ,ጴጥሮስ እና ያዕቆብ
ሐ,ጴጥሮስ እና ጳውሎስ
መ,ጴጥሮስ እና ዮሐንስ
6,በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ልበሱ እንደሚል ከተዘረዘሩት ትጥቆች መካከል የራስ ቁር ምንን ይወክላል ?
ሀ,እምነትን
ለ,የእግዚአብሔር ቃልን
ሐ,መዳንን
መ,የሰላም ወንጌልን
ሠ,ጽድቅን
7,ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እና አብረውት ያሉት በፊልጵስዩስ በነበሩበት ወቅት ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ እና በሚያስተምሩበት ጊዜ ከእርሱ ጋር በመሆን እየተከተለች የመዳን መንገድ የሚነግሩአችሁ የልዑል አምላክ ባርያዎች እያለች ለነበረችው ገረድ ጳውሎስ ምን መለሰላት ?
ሀ,ይህን የገለጠልሽ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ነው አላት
ለ,ይህንን የተረዳሽውን እውነት ለሌሎች መስክሪላቸው አላት
ሐ,ለተሰበሰቡት ዘወር ብሎ እግዚአብሔርን እንድታምኑ የጌታ መንፈስ በእርሷ ተገልጦ ተናገረ አለ
መ,መንፈሱ ከእርሷ እንዲወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዘዘው
8,የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙራን በቤተክርስቲያን ታሪክ መሰረት ለመጀመርያ ጊዜ ክርስቲያን የተባሉት የት ነው ?
ሀ,በኤፌሶን
ለ,በእየሩሳሌም
ሐ,በአንጾኪያ
መ,በቤተልሔም
ሠ,በዮርዳኖስ
መልስ መላኪይ:@YididiyaTadesse
በመቀጠል አዝናኝና አስተማሪ የሆኑትን መፅሀፍቅዱሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድሮቻችንን የምንለቅበት ሰአት ላይ ነው። ሽልማት ስላለው ሁላችሁም ተሳተፉ!!! "ቀድመው በትክክል" ለመለሱ "ሁለት" ሰዎች የሞባይል ካርድ ሽልማት አለን።
መልሳችሁን የምትልኩት በዚህ ነው:
@YididiyaTadesse
?????????
መልካም አዲስ አመት
?????????
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 week, 2 days ago
Last updated 4 days, 6 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 3 weeks, 1 day ago