Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Description
➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡

@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!
We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month ago

The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 month, 1 week ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 3 weeks, 4 days ago

4 days, 11 hours ago

...........ሳቅሽ.......

ሳቅሽ  ለመተብተብ ብቻ ሚቃጣው
የሸረሪት ድር ነው  ሸማ የማይወጣው
ሳቅሽ
የተንኮል ፈገግታ  የተንኮል ወትብትብ
የዘመን ማዘሎ  ማይቆረጥ ማተብ
ሳቅሽ
የማያልቅ ፈትል  የማይጠፋ እሳት
የሳቅሽ ሚስጥር ነው እሳትን ማስነሳት

By kerim

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

4 days, 17 hours ago

❤️❤️‍🔥💔የልቤን ብታዪ❤️❤️‍🔥💔

አይኔ እንደ ቆራጥ አንቺን ባያይሽም
     ሞልቶት ትንሽ ኩራት

አፌም ጀነን ብሎ አሻፈረኝ ቢልም
      ስምሽን ለመጥራት

ጆሮዬም ቢያስመስል ከቶ እንደማይሰማ
      አንቺን የሚል ወሬ

በሄድሽበት መሄድ ሁሌ መከተሉን
       ባይሞክረው እግሬ

በይ ልንገርሽ ዛሬ
ሞኝ ልብ እንዳለኝ ማያውቅ ማስመሰል

ጠዋትና ማታ ስራው አድርጎታል
         አንቺን ማሰላሰል።

*📝*📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝

በግጥም እናውጋ(** @gitim101)

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

5 days, 14 hours ago

ቀጣዩ ‘ስቴፕ”
(በእውቀቱ ስዩም)

እንደ ቀነኒሳ አይነት ልእለ-ሰብ ሰዎችን ስታይ የእድሜ መገስገስ አያስፈራህም፤ እድሜ ሆይ መውጊያህ ወዴት አለ? ብለህ ትፎክራለህ ፤

“ ቀነኒሳ አንበሳ “ ይላል ጀግና አሞጋሹ ጀግና ቴዲ አፍሮ፤ አንበሳ በምን እድሉ ነው ቀነኒሳን የሚስተካከለው ? አንድን አንበሳ በሀያ አመቱ በአጸደ ስጋ አታገኘውም፤ ካገኘኸው ጭርጭስ ብሎ፥ ጎብጦ ቁርበቱን እየላሰ ተኝቷል፤ ቀነኒሳ ግን በአርባ ሁለት አመቱ ማራቶን ያሸንፋል፤

ዋናው ጥያቄ- ለእድሜ ትገብራለህ ወይስ እድሜን ታስገብራለህ?” የሚል ነው፤

ርግጥ ነው እኔ በዚህ እድሜየ እንኳን ማራቶን ልሮጥ ውድድሩን በቲቪ ጨርሶ ለማየት ራሱ አቅምና ትግስት የለኝም፤ አንዳንድ ቀን፥ ከባለንጀሮቼ ጋር ኳስ ለማየት እቀመጣለሁ፤ በተቀመጥኩበት ሶፋ ላይ አራት ዙር ግልገል እንቅልፍ (ናፕ ) እተኛለሁ፤

በቀደም ከስንት ጊዜ በሁዋላ ጂም ሄድኩ፤ አሰልጣኙ ተቀብሎ ገና የስነልቦና ምክር እንኳ ሳይሰጠኝ “ ሀያ ጊዜ ቁጭ ብድግ ስራ “ አለኝ ፤” ቁጭ ማለቱ ላይ ችግር የለብኝም ብሮ ! ብድግ ማለቱ ላይ ግን እገዛህን እሻለሁ “ ብየው ፥ ትንሽ ወልመጥ ወልመጥ አልሁ ፤

ቀጠለና አስር ፑሽ አፕ አዘዘልኝ፤ አምስቱን ወገቡን እንደተመታ እባብ እየተቅመደምድሁ ሰራሁ፤ በተረፈች፥ ጉልበቴ ምንጣፉን እየሳምኩ ተነሳሁ፤ በመጨረሻ ሳልፈልግ ፥በርከክ ብየ ለወጫጫ ተራራ ሰገድሁ፤

ማጠቃለያው ላይ፥ አምስት ኪሎ ድምቤል አሸከመኝ፤

ከዚያ መስታውት ፊት ቆሜ ፥ ከክርኔ በላይ ያለውን ክንዴን ክፍል እየዳበስኩ ገመገምኩት፤
ብዙም ሳይቆይ አሰልጣኙ ከተፍ አለና፥

“አሁን አሟሙቀሀል፤ ቀጣዩ ስቴፕ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ” ሲል ጠየቀኝ፥

“ ቀጣዩ “ ስቴፕ”ማ ንቅሳት እሚሰሩ ሰዎችን ማፈላለግ ነው ዠለስ“

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

2 months, 1 week ago

እኖር ብዬ ብታረድም ፣
ለመኖር ስል ብሰደድም
እኖር ብዬ ብጨነቅም ፣ እኖር ብዬ ብዋረድም
ዘጠኜ ሞቴን ብሞተው…
አንዴ እንደመኖር አይከብድም!
መኖር ከመሞት አይልቅም
ሞት እንደሕይወት አይጨንቅም፡፡
.
የሞተ ‹‹እሞታለሁ›› ሲል…
በጭራሽ አያውቅም ፈርቶ፡፡
ያልኖረ አያውቅም ሞቶ።
.
መኖር እንጂ የሚያስፈራኝ
መኖር እንጂ የሚያስገፋኝ
መኖር እንጂ የሚያስከፋኝ
መኖር እንጂ የገደለኝ
መኖር እንጂ የበደለኝ
ሞት አያምም ካቆሰለኝ
ምት አያምም ከገደለኝ!

[በላይ በቀለ ወያ]

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

2 months, 1 week ago

***ቆሞ ቀር አትበሉኝ

አትበሉኝ ሰው ያጣ፡ ከሰው የተጣላ
ብቸኝነት መራጭ፡ መጣመር የጠላ
ተነጥሎ ያለ፡ መምህረ ነጠላ
ቆሞ ቀር አትበሉኝ፡
ከእህል ባለፈ ፍቅርን ላታበሉኝ።

አዎ ብቻዬን ነኝ፡ የራቅኩኝ ከመንጋ
ብቻየን በአካሌ፡ ብቻዬን በስጋ
በልቤ ከሷጋ፡
በመንፈስ ከሷጋ፡
ካፈር ባልተሰራው፡ እስትንፋስ በሆነው፡
በተሸፋፈነው፡
ህግ በማይገዛው፡
ከሷ ጋር ነኝ እዛው !

አካል ስጋ አፈር፡ተለዋጭ ሁነቶች፡
ግዜ ገዝ ኡደቶች፡
ጥገኛ ፍጥረቶች፡
ትስስር ይሻሉ፡
እውነታ ይሸሻሉ፡
ይደጋገፋሉ ፡
ከዚያም ይጠፋሉ።

መንፈስ ግን፡ ልብ ግን ምሁራነ ፍቅር፡
ገደብ የሌላቸው፡ ዘመን የሌላቸው የአምላክ መዋቅር፡
ፍፁምነትና እውነቱ ያላቸው፡
አንዴ ከወደዱ ሁሌም እዛው ናቸው።

እኔ ሰው ሳላርቅ፡እኔ ሰውን ሳልጥል
አትበሉኝ ንጥል
በልቤ ካለችው፡ ከምወዳት ጋራ ኑሮዬን ልቀጥል
                  በኃይሉ
🖊️***

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

2 months, 1 week ago

ርዕስ ፦ እምዬ እናት አለም

እምዬ እናት አለም ፥ ታግሶኛል ላንቺ ብሎ
በፀሎትሽ ፥ ቁጣው ቀሎ
የእርሱን ፍቅር ፥ ለኔ ያለው
ባንቺ ልብ ውስጥ ፥ አየዋለሁ
.
.
.
ጉያሽን አልጠግበው ፥ እምዬ እናት አለም
እንደ ልጅነቴ....... ፥ እቀፊኝ ዘላለም

የዋህ ለሰው አዛኝ ፥ ለሁሉም ጥሩነሽ
እንኳን ለወለድሽው ፥ ለባዳም ዘመድ ነሽ

እምዬ እናት አለም
ለአንድ ቀን ዓይንሽን ፥ ካላየው ይከፋኛል
ብዙ ካንቺ ሥርቅ ፥ እንዴት ያስችለኛል ?

አቤል ታደለ (ይድረስ ለእናቴ ጥሩነሽ )

ያንቺን ጠረን ፥ ያንቺን ጉርሻ
የትም ሆኜ ፥ ማስታወሻ
ናፍቆትሽን ፥ መተንፈሻ
ግጥሜ ናት ፥ ......አንቺን ስሻ

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

2 months, 1 week ago

#ጉዴ_ፈላ

ከብዙ ጊዜያት በኀላ

50 አመቴ ሲሞላ

እድሜዬ ገፍቶ

ፀጉሬ ሸብቶ

ካየዉህ አመታት አልፈዉ

ያኔም እንዳሁኑ
ስላንተ ቢሆንስ ምፅፈዉ....?

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

2 months, 1 week ago

---አቤቱ---

ድካም ባዛለው ገላ
ሰባቱንም ቀን ናፍቀናል፤
እኛ ሰንበት ባይኖረንም
ባንተው ሰንበት አርፈናል፤
ከድፍረት አይጣፍብን
እግዚኦ ማረን ብለናል፤
ወዮልን ወዮታ አለብን
ከንቱ መዋቲን ገላ
ከማይሞተው ጋር ቆጥረናል፤
የአንተን እረፍት እኛ ቀምተን
እረፍታችንን አጥተናል።
...
By አበባው መላኩ

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

2 months, 1 week ago

ነጋልን ደሞ

በዚህ ጭጋግ መኃል ፣ ጥቅጥቅ ያለ መውደቅ ከቦኝ ፣ ኋላ መቅረት እየደለቀ ፣ የቅርብ ግቤን አርቄ ሰቅዬ ....

መንጋቱን ስጠራጠር ፣ መፍዘዜ ቋሚ ሲመስለኝ ፣ ልብሴ ማርጀቱን ሲያቃጥር ፣ ቃል ሲሰብረኝ ፣ ሆድ ባሻነት ማንነቴ ለመሆን ሲታገለኝ

ቃል ሳይወጣሽ ያንቺ ፈገግታ ብቻ ነው ይነጋል የሚለኝ !!
©Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

2 months, 2 weeks ago

[🎧🎵የማንን ሙዚቃ ማዳመጥ ይፈልጋሉ👇

👤 Mikaya Behailu

👤 Minyeshu Kifle

👤 Muluken Melesse

👤 Neway Debebe

👤 Nati Haile

👤 Nhatty Man

👤 Sami Dan

👤 Sayat Demissie

👤 Seleshe Demissie

👤 Shewandagne Hailu

👤 Tamrat Desta

👤 Teddy Afro

👤Aster Awoke

👤Abnet Agonafr

👤Geremew Asefa

🌐 All Ethiopian Music🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶](https://t.me/addlist/Brme6a7XIcU1MjI8)

We recommend to visit

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 1 month ago

The first Telecom operator in Ethiopia https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 1 month, 1 week ago

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 Film ቻናላችን በሰላም መጣቹ

አዳዲስ እና የድሮ እንግሊዘኛ/አማርኛ/ህንድ/ቱርክ ፊልሞችን እና ከ1000 በላይ ተከታታይ ፊልሞችን የምታገኙበት ቻናል ነው

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc

ሃሳብ አስታየት ካሎት - @Abushecbot

Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 3 weeks, 4 days ago