ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
“በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።”
— መዝሙር 65፥11
ለሁላችሁም በዓሉ የሰላም የፍቅር ይሁንላችሁ እንዲሁም ቅዱስ ቃሉ እንደሚነግረን👇 አዲሱን ዓመት ስንቀበል በአዲስ መንፈስ ይሁን ጌታም አዲስ ልብ ይሰጠናል እንዲሁም አዲሱን ዓመት ስንቀበል ኢየሱስን መልበስ ይገባናል።
“አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።”
— ሕዝቅኤል 36፥26
በሉ እንደባህላችን ክርስቲያናዊ ምርቃን ልመርቃችሁ😁
በአዲሱ ዓመት ክርስቲያናዊ ፍሬ አፍሩ።
በአዲሱ ዓመት የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር የባህሪይ አባቱ የእግዚአብሔር አብ ፍቅር እንዲሁም የባህሪይ ሕይወቱ የእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ፍቅር ይብዛላችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁን የምትወዱበት ዓመት ይሁንላችሁ በእርግጥ አምላኩን የማይወድ ክርስቲያን የለም ነገርግን የቃሉ ባለቤት ክርስቶስ ኢየሱስ እንደነገረን እሱን መውደድ ፍቃዱን መፈፀም ነው ስለዚህ አዲሱ ዓመት የሥላሴን ፍቃድ የምትፈፅሙበት ይሁንላችሁ።
“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤”
— ዮሐንስ 14፥15-16
በአዲሱ ዓመት የጌታን ስጋና ደም ለመቀበል ያብቃችሁ።
ጌታ በአዲሱ ዓመት ኃጢያትን ለመስራት የደነደነ ልብ ፅድቅን ለመስራት የበረታ የጠነከረ ልብ ያድላችሁ።
በአዲሱ ዓመት ጌታ ጸሎት ወዳድነትን፣ጥበብን፣ማስተዋልን፣ ትዕግስትን ያድላችሁ እንዲሁም ሰዉንሁሉ የሚወድ ልብ ይስጣችሁ።
አዲሱን ዓመት በማንበብ በክርስቲያናዊ ስራ እንድታሳልፉ ጌታ ይርዳችሁ።
#ማሳሰቢያ
በዓሉን ስታከብሩ ክርስቲያናዊ በሆነ መንገድ አክብሩ መስከር መጨፈር ክርስቲያናዊ ትውፊት አይደለም።
"ጌታሆይ ሰላምን ስጠን እንዲሁም ከጠላታችን እጅ አድነን...ጌታሆይ በርህራሄህ ወንዞችና ምንጮችን ዛፉንና ፍራፍሬውን ባርክ ዓውደ አመቱን ባርክልን" (Doxology for the coptic new year) የአስክንድርያ ቤተክርስቲያን ምእመናንም ነገ አዲስ ዓመትን ያከብራሉ በዓሉን ሲጠሩትም በዓለ ናይሩዝ (The feast of nayrouz) ብለው ነው😊ለነገሩ በግብፅ ያለችውን ቤተክርስቲያን ለአብነት አነሳሁ እንጂ መስከረም ፩ (1) የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም አዲስ ዓመቷን የምታከብርበት ነው በዓሉንም (church new year) ብለው ያከብሩታል ለሁላችንም መልካም በዓል
"እኛምኮ እንቃወማለን አንደግፍም" ውሸት! አባባሉንማ እኔም እለዋለሁ ውስጣዊ ስሜቴ ጾታዊ ጥቃትን ሊደግፍ አይችልም ግን ምን አድርጌ አውቃለሁ? እስኪ በኢትዮጵያ ላሉ ሴቶች ሰብአዊ ነጻነት ምን አድርገህ ታውቃለህ? መቃወም ማለትኮ ውስጣዊ ስሜትህ ያን ጾታዊ ጥቃት መቃወሙ አይደለም። ያ ጥቃት እንዲቆም መስራት ነው ምን እየሰራን ነው? እንዲሁ ቁጭ ብለን የሚሰሩ ልጆች ላይ አስተያየት እንስጥ? ያ ነው መቃወም ብላችሁ የምታስቡት? የእናንተ መቃወም 0.01 እንኳን ለመፍትሄው አጋዥ ካልሆነ መቃወም አይደለም። በመንፈሳዊነት እንኳን እንሂድ እስኪ ስንቶቻችን ነው ጾታዊ ጥቃት ስለሚደርስባቸው እህቶች ጸልየን የምናውቀው? ስንቶቻችን ነን ስለተጠቃች ሴት ልጅና እግዚአብሔር መንፈሷን እንዲያጠነክር በጸሎት ያሰብናት? ስንቶቻችን ነን በክርስቲያናዊ ኅብረቶች መሀል አስተምረን የምናውቀው? ስንቶቻችን ነን መንፈሳዊ ንቅናቄን በጾታ ጥቃት ዙሪያ እንዲፈጠር አድርገን አይደለም አስበን የምናውቀው? ስንቶቻችን በዚህ ጉዳይ ጽፈናል? ስንቶቻችን በዚህ ጉዳይ ሰብከናል? ስንቶቻችን ጓደኞቻችንን አስተምረናል?
እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም አንድ ነገር እንደምንል "እያየሁ ሴት ልጅ ብትጠቃ ዝም ብዬ አላይም" For real? እያየህ ካልሆነስ? አንተ ፊት ካልሆነስ? ባንተ ዙሪያ ያሉት እህቶች ካልሆኑስ? በቃ? ዝም ነው የምንለው? ምንም አናረግም? ይሄኮ አጠገባችን ያለውን ጾታዊ ጥቃት ለማቆም እንጂ generally የሴቶች ጥቃት እንዲቆም አንዲት ፐርሰንት እንኳን ዋጋ አይኖረውም። አጠገባችን ያለችውን እሰየው ጠበቅናት። ግን ያቺ እህታችን የሆነ ቦታ፣ እኛ የሌለንበት፣ እኛ ልናድናት የማንችልበት፣ እኛ ልንደርስላት የማንችልበት ቦታ ላይስ ጥቃቷ እንዲቆም ምን እናድርግ? አይተኸዋል መቃወም ማለት ያ እንዲቆም መስራት ነው። አንተ እቃወማለሁ ያልከው አጠገብህ ጥቃት ቢፈጠር ነው ፌሚኒስቶች ግን ስራቸው በየትኛውም ስፍራ ስለምትጠቃ ሴት መቃወም ነው። ስለዚህ ከቻልን እናግዛቸው ካልቻልን አፋችንን እንዝጋ አረማመድና አነጋገራቸው ላይ አስተያየት አንስጥ።
ሴት ልጅ በሴትነቷ ምክንያት የሚገጥማትን ጾታዊ ጥቃት እንዲቆም መታገል የሁላችንም ጤነኛ ሰዎች ሰብአዊም ክርስቲያናዊም ኃላፊነት ነው። እኛ ያልተወጣነውን ኃላፊነት ግን የሚወጡ እህቶችን ቁጭ ብሎ መቃወም ለእኔ ጤነኝነት አይደለም እግዚአብሔርም ፈጽሞ አይወደውም።
ፍትህ ለህጻን ሄቨን። አሁንም ድምጻችንን እናሰማ
ወንድማችሁ አቡ ነኝ ሰላም ቆዩ
@APOSTOLICsuccession
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana