ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 3 недели назад
Last updated 2 недели, 2 дня назад
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 месяц назад
ሰዓት ጊዜን ያሳያል፣ ጊዜ ደግሞ የሰውን ማንነት!
መንደርተኝነትን ነፍሳችን አብዝታ ትፀየፋለች። የትግላችን አልፋና ኦሜጋም ከአማራነት ስንዝር ዝቅ ሊል እንደማይችል ብዕራችንን ስናነሳ ለእራሳችን የገባነው ቃልኪዳን ነበር።
የአማራ መገፋትና መሳደድ በጉራፈርዳ ጅማሮውን አድርጎ እያለ፣ በወለጋ "ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም" ያለችው ነፍስ ያላወቀች ህጻንን የትግል ቃልኪዳናችንን አድርገን ተነስተን፣ እኛ "ከመንደሬ ውጭ እንጃልህ" ወደሚል አቋም ልንከረበት ፈፅሞ አይቻለንም።
ይህንን እያልን ያለነው… ትናንት የአማራ ብሄርተኝነት እንዲያብብ ብዙ የሰሩ ወንድሞቻችንን ዛሬ በነበሩበት ቦታ ስላጣናቸው ብሎም የመንደርተኝነት ባንዲራ አንጋች ሆነው በማየታችን ነው። መንደርተኝነት ከብአዴናዊ አስተሳሰብም በእጅጉ ያነሰ የድንኮች መገለጫ ነው - ብአዴን በግልፅ "ከክልሉ ውጭ ያለ አማራ አይመለከተኝም" ይላል፤ መንደርተኝነት ደግሞ ከዚህም ያነሰና የከፋ ብአዴናዊነትና የአንካሶች መገለጫ ነው።
ይህን የሰንካሎች አስተሳሰብ ትናንት በአያሌው መንበርና ኃይለየሱስ አዳሙ ብቅ ብሎ እራሳቸውን ይዟቸው ከስሟል። ዛሬ ደግሞ የአያሌውን ቆብ ያጠለቁ፣ እሱን የበላ ቅጫም እኔንም ካልበላኝ ባዮች፣ የኃይለየሱስን ቡትቶ አስፍቼ ካለበስኩ የሚሉ መንደሬዎች ወደ አደባባይ ብቅ ብቅ ብለዋል።
በዚህ ሂደት ትናንት ያከበርናቸው አለፍ ሲልም ብዙ ነገሮችን አብረን የሰራን ወንድሞቻችን ሳይቀር እነሱም ቆቡን አጥልቀው፣ ቡትቶውን አገልድመው ስላየን በእጅጉ ህመም ሆኖብናል። ትናንት እነዛን ከጠላናቸውም በላይ የእነዚህ የጊዜ ጉዶች በእጅጉ ቀፈውናል። የጊዜ ጉዳይ ሆነና ዛሬ ነግቶባቸው ተጋልጠዋል፤ ነገ ደግሞ ይከስማሉ።
ሃሳብህ ተቀባይነት ያጣ ሲመስልህ "ከአያሌው ካልወለድኩ" በሚል መገልገል ከጀመርክ ድሮውንም ስህተቱ የማይገባህን ቦታ የሰጠንህ የእኛ ነበር። አይተናቸው አይተናቸው "እንዲህ ያደረጋቸው ጊዜያዊ እልህ ወይም ኢጎ ይሆናል" ከሚል አረዳድ ይልቅ ድብቅ ማንነታቸው ተጋለጠ ወደሚል ድምዳሜ ዛሬ ላይ ደርሰናል። በትግሉ ሜዳ ያሉ ወንድሞቻችን ወደ አንድነት እንዳይመጡ፣ መሃል ለመቆም እየሞከሩ ያሉ ደንቀራ ብዕረኞችና ምላሰኞችን ገሸሽ ማድረግ ከታጋዮችም ሆነ ከሰፊው ወገናችን ለነገ የማይባል የውስጥ ስራ ነው።
ለምንወደው ወገናችን ዛሬም የምንለው እንኳን እንደኛ እንቶ ፈንቶው ሲሞነጫጭር ለሚውል ብዕርተኛ ወይም ምላሰኛ ይቅርና ነፍጥ ያነሳ የትግል ሜዳን ጀግናንም ቢሆን… ግለሰቦች ላይ የተንጠለጠለ የትግል ግብ ሊኖረን አይገባም። ግለሰቦች እንደ አብኖች ሊንሸራተቱ ወይም ሊለዮን ይችላሉ ነገር ግን ትግሉን የትግሉ ቃልኪዳን ላይ ያመረኮዘ ኃይል እና ከትግሉ ዓላማ ላይ አይኑን የማይነቅል ትውልድ መሆን አለብን። የመንደሬን እንጉርጉሮ ስለሰማሁ ልበ-ተላላ የምሆን ከሆነ ገና አልገባኝም፤ ልክ አይደለሁም። ባህርዳር ዊክሊክስን የምታምኑት ለትግሉ ቃልኪዳን እስከታመነችና ትግሉን እስካገለገለች ድረስ ብቻ ነው፤ በአቋም ሸርተት ስንል አይናችሁን ለአፈር ማለት ከወገናችን የሚጠበቅ ነው። ለሌላውም ይህ እንደ አቋም ሊፈፀም የግድ ይላል።
የጨቅላው አቡሽ አህመድ ጉዳይና የአስተሳሰብ ደረጃ እያደር አዲስ ሆኖብናል። ይህ ማፍረስንና መናድን መለያው ያደረገ የወፍ ዘራሽ ልጅ፣ "እንጨት ለቅማ፣ ቤት መስራትን" ባለመች ምናባዊ ምስኪን ኮረዳ ቅናቱን በአደባባይ በፓርላማው ፊት ገልጿል።
ይህ ወፍ ዘራሽ የጠንቋይ ልጅ፣ ያች ትነግሳለህ ያለችው እናቱና ዝናሽ ታያቸው እንዲህ እያሉ እየተቀባበሉ በማዜም ፍላጎቱን እንደሚያረኩለት እምነታችን ነው……
ባለጊዜዎች ግቡ በተራ፣
ከተማ አውድሞ ፓርክ እስኪሰራ፣
ሺዎችን ገድሎ እናንተን ያኩራ¡
መምህር ዘመድኩን በቀለ "ዋን አማራ" የተባለን ፀረ-አማራ በታኝ ቡድንን ብዙ ዋጋ ካስከፈሉን በኋላም ቢሆን ማጋለጥ መጀመርክን ይበል ብለናል።
የዚህን ስብስብ አደገኝነትና በታኝ አካሄድ ሳይረዳ፣ በግልብ በአጋፋሪነት ለተሰደረው የማህበራዊ ሚዲያ ታዳሚ ይበልጥ እውነትን መግለጥ ከማንም በላይ አሁንም ከአንተ ይጠበቃል - ለምን? አንተን አምነው እነዚህን የጭቃ እሾሆችን ከእነ ግሳንግሳቸው የተቀበሉ ወገኖች በውል ሊነቁ የግድ ስለሚል።
ለካ የበለፀጉት የወረሙማ የዳልጋ 🐃ቶች "ዘመነን ገድለነዋል" እያሉ ይህንን የህልም እንጀራ እየቀረደዱት ሰንብተዋል አሉ። አይ ወረሙማ 🤣
አርበኛ ዘመነ ካሴ ዛሬ ዘለግ ያለ መግለጫን "ትግሉ ሚሊዮን እረኛዎችን (ዘመነዎችን) ፈጥሯል" ከሚል መልዕክት ጋር አስተላልፏል።
አሁንም እራሱን ሲያረካ የሰነበተው የወረሙማ የዳልጋ 🐃 መንጋ ከፈለገ የህልም እንጀራውን ይቀርድድ ሲፈልግ ደግሞ የዋርካ ስር ሳሩን ይጋጥ። እኛ ምን ጨነቀን 😁
(ለዳልጋው) የዚያች ልጅ ከሚል ሰላምታ ጋር 🫡
ሁለት መቶ ተራሮችን የፈጠረ የተራሮች ዘመቻ!
"ዘመቻ መቶ ተራሮች" ይፋ ሲደረግ የሩቅ ጠላቶችም የቅርብ የኮንዶም ትራፊዎችም ተሳልቀው ነበር። ነገር ግን ይህ ትውልድ ከምድር ፈልቆ እንደወጣ ገሞራ ተራራን ማንቀጥቀጥ ይቅርና ተራራን መናድ የሚችል፣ ሲያሻውም ተራራን በአረንጓዴ ለባሽ ምርኮኞች መሸፈን የሚችል ክንደ ነበልባል ትውልድ መሆኑን በዘመቻ መቶ ተራሮች አስመስክሯል።
አሁን ተራሮቹ 200 ደርሰዋል - ገሚሱ የዘመቻችን ስያሜ ሲሆን ገሚሱ ደግሞ የአራዊት ሰራዊቱ የአስክሬን ቁልል ነው። የአማራ ህዝብን ለማጥፋት ልጃችሁን መርቃችሁም ሆነ አልቅሳችሁ ለውትድርና የላካችሁ እናቶች፣ ልጃችሁ መንገድ ላይ ቀርቷል - አትጠብቁት። ቀሪዎቹም የተለየ እጣፈንታ የላቸውም።
በታሪክ መዛግብት ፊት በኩራት የሚያቆም ታሪክን እየጻፈ ያለው ይህ ትውልድ፣ ጥቂት ክላሽ ይዞ ተነስቶ፣ በሃገር ሃብት አሰሱንም ገሰሱንም የታጠቀውን የግለሰብ ወታደራዊ ተቋምና ሰራዊትን ብትንትኑ እያወጣው ነው። እንኳንም የእናንተ ሆን።
#የመውጫ_መልዕክት፦ አሁንም የድል ቀናችን የሚረዝመው በእኛ ድክመት እንጅ በጠላታችን ጥንካሬ አይደለም። የጎተተንን ድክመት ደግሞ በቅርብ የምናርመው ይሆናል።
የአዳዲስ ፋኖዎቻችንን ምርቃት ተከትሎ ወይም በሌላ ምክንያት እየታዮ ያሉ ወታደራዊ ሰልፎችና ትርዒቶችን ትግላችን ያለበትን ደረጃ ከማሳየቱም በላይ በጠላት ላይ የሚያሳድረው የስነልቦና ተፅዕኖ ይኖራል። ነገር ግን ላልተገመተ የጀትና የከባድ መሳሪያ አውዳሚ ጥቃትም ሲያጋልጥ ይችላል።
ገና ለገና ክረምት ነውና ድሮን መብረር አይችልም በሚል እየተፈጠረ ያለው መዘናጋት እጅጉን ያሳስበናል። ለእኛ እስካሁን ያሉት ወታደራዊ ትርዒቶች በቂ ይመስሉናል፤ ከአሁን በኋላ ደበቅ ብሎና ጥንቃቄ ታክሎበት ዝግጅትን ማጧጧፉ የተሻለ ነው ብለን በፅኑ እናምናለን፤ ምክራችንን እንለግሳለን።
ለምሳሌ ሰሞኑን ቋሪት ወረዳ ከጠላት ኃይል ሙሉበሙሉ ነጻ መሆኗን ተከትሎ፣ የሚሊሽያና የፖለቲካ አመራሩ ቤተሰቦች ሳይቀር ፍኖተሰላም ከተማ ካምፕ (የዞን አስተዳደሩ ህንጻ) ውስጥ ገብተዋል። ከዚህ ካምፕ አካባቢ የሚሰማው ነገር ደግሞ ለጀት ጥቃት የፋኖዎቻችንን መሰባሰብ እየጠበቁና መረጃ እየሰበሰቡ እንዳሉ ነው። እናም የትግላችን ጅማሮ ላይ (ከስልክ አጠቃቀምና ከአየር ጥቃት መከላከል አንጻር) ስናሳየው የነበረው ጥንቃቄ፣ አሁንም አብሮን ሊቀጥል ይገባል እንላለን። በማንኛውም ጊዜ ጥንቃቄ አይለየን!
ኮሎኔሉ አሸልቧል!
በምስራቅ ጎጃም ዞን ባሶ ሊበን ወረዳ፣ የጁቤ ከተማ የኮሎኔል ማዕረግ ያለው የአገዛዙ ወታደራዊ አዛዥ በካምፕ ውስጥ በውስጥ አርበኞች ተመርዞ መሸኘቱ ተረጋግጧል። ከቀናቶች በፊትም በሞጣ ከተማ አቅራቢያ በርካታ የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ተመርዞ የአስክሬን ቁልል መሆኑ የሚታወስ ነው።
ቻው ኮሎኔል!
ጥንቃቄ!
በማንነት በአመዛኙ ኦሮሞ የሆኑ የአገዛዙ ዲጅታል ሠራዊት አባላት ከሁለት ተቧድነው (ጎንደር እና ጎጃም ተባብለው) ፀያፍ ስድቦችንና ከፋፋይ ፁሑፎችንና ተግባራትን እንዲያስተጋቡ ከሰሞኑን ስልጠናና ስምሪት እንደተሰጣቸው ባህርዳር ዊክሊክስ የደረሳት መረጃ ያስረዳል። ከወዲሁ መንቃት ያስፈልጋል።
በእጅጉ ሊዳረስ የሚገባው የጥንቃቄ መልዕክት
የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት አዲሱ ዕቅድ… አባሎቹን በህዝብ ማመላለሻና በጭነት መኪኖች በመጫንና ከጭነት ጋር በመመሳሰል ኬላ ላይ ያሉ ፋኖዎቻችን ላይ ድንገተኛ ጥቃት ለመፈፀም ማቀዳቸውንና በአንዳንድ አካባቢዎችም እቅዱን እንደሞከረ ተሰምቷል።
ይህ የጥንቃቄ መልዕክት በደንብ ይዛመት።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 3 недели назад
Last updated 2 недели, 2 дня назад
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 1 месяц назад