የእመቤታችን አንድምታ ወዳሴ ቅዳሴ

Description
በዚሕ ቻናል የእመቤታችን ዉዳሴዋ ንባቡና ትርጓሜዉ በአንድምታ ይቀረባል። ከኛ የሚጠበቀዉ መማር ብቻ ነዉ። አምላክ ከኛ ጋ ይሑን የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን።

ሐሳብ አስተያየት
👇👇👇👇👇👇
@woladite11
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

2 months, 2 weeks ago

ድንግል ሆይ

*ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች!!!

"ያዘነች ስትሆን በልጅሽ በወዳጅሽ ትንሣኤ የተጽናናችው፡፡

የተዋረደች ስትሆን በድንግልናሽ ቡቃያ መውጣት ከፍ ከፍ ያለችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች፡፡

በዕለተ ዓርብ ከልጅሽ ቀኝ በፈሰሰው ውሀ ተጠምቃ የውግታቱን ደም ተቀብታ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታመሰግንሻለች።

የልዑል እግዚአብሔር በግ የተባለ ልጅሽ ዐማኑኤልየተሞሸረባት መርዓዊ ሰማያዊ የተባለባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች"

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ❤️*

2 months, 2 weeks ago

ውድ  ቤተሰቦቼ እንደምን አላችሁልኝ በጣም ነው ሁለችሁንም የምወዳችሁ ፈጣሪ በመልካም ምግባር ያኑርልኝ 💖💖❤️❤️

2 months, 3 weeks ago

የቆየ ግሩፕ ባለቤቶች የማትጠቀሙት

ከ 2024 ውጭ ካላችሁ 2023 እና በታች

ካርድ እሞላለሁ በውስጥ አዋሩኝ

👇👇👇👇👇👇👇👇

@mogesinewokibrene

2 months, 3 weeks ago

ተወዳጆች

መኝታውን በወርቅ ያጌጠ ማድረግ ሲችል
በግርግም ውስጥ ማድረግን መረጠ
እናቱንም ከንግሥታት አንዲቱን ማድረግ ሲችል
አላደረገም ብሏል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ*❤️
ድንግል ማርያም እንዲህ ናት::
ታላላቅ ሀብታትን ሳትጠይቅ የተቀበለች ፣
ሳትለምን የተመረጠች ፣ ሳታገባ የፀነሰች ፣
ሳታምጥ የወለደች ፣ ድንግልናዋን ሳታጣ እናት የሆነች ፣
አንዳች ሳትሻ ሁሉን ያገኘች
የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ እርስዋ ናት፡፡*

2 months, 3 weeks ago

ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ

ደናግል ሆይ

የሰማያዊ ሕይወት አርኣያና አምሳል የሆነችው
የድንግል ማርያም ሕይወት ይኑራችሁ፡፡
እርስዋ ለክርስቶስ እናት ለመሆን
በምንም የምታንስ አልነበረችም'

2 months, 3 weeks ago

ቅዱስ አግናጥዮስ፣ መልእክት ኀበ ሰብአ ጥራልያን፣ ምዕ. 10
👉*የማምነውና ተስፋ የማደርገው በምትሐት ወይም በማስመሰል ሳይሆን ስለ እኔ በእውነት ሰው በሆነውና በሞተው በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

👉ሐሰት የሆነ ነገር ለእውነት አስጸያፊ ነውና፡፡ ስለሆነም የማምነው ድንግል ማርያም የፀነሰችውና የወለደችው እግዚአብሔር ቃል የተዋሐደውን ሥግው ቃልን ነው፡፡

👉 የእግዚአብሔር ቃልም የእኛን ባሕርይ ገንዘቡ አድርጎ በእውነት ከድንግል ማርያም ተወልዷል፡፡

👉ሰዎችን ሁሉ በማኅፀን የሚፈጥረውና የሚቀርጸው እርሱ ራሱ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ በድንግልና በማኀፀኗ ተፀንሶ ኖሯልና፡፡*

2 months, 4 weeks ago

ተወዳጆች

(ቅዱስ አግናጥዮስ፣ መልእክት ኀበ ፊልጵስዮስ፣ ምዕ. 4)

እንዳለው

“ሰይጣን በአንዳንዶች መስቀሉን ይክዱ ዘንድ በእነርሱ ላይ ሥራውን ይሠራል

የጌታችንን ሕማማቱንና ሞቱን እንዲያፍሩበትና ምትሐት ነው እንዲሉ በውስጣቸው ይሠራባቸዋል

ከድንግል መወለዱንና ሥጋ መልበሱን፣ እንዲሁም የእኛን ባሕርይ ርኩስ እንደ ሆነ አድርጎ ይነቅፋል፡፡

ከአይሁድ ጋር ደግሞ ሰዎች መስቀሉን እንዲክዱ ቤተ ክርስቲያንን ይዋጋታል፤ ከአሕዛብ ጋር ደግሞ ድንግል ማርያምን ይነቅፋሉ፣ ያክፋፋሉ፡ ክርስቶስ ከእርሷ ባሕርይዋን ገንዘቡ አድርጎ እንዳልተወለደ አድርገው ይናገራሉ፡፡

የክፋት ሁሉ መሪና ፍታውራሪ የሆነው ዲያብሎስ አሠራሩ ብዙ ዓይነት ነውና፣ እርሱ የሰዎች ፈታኝና አታላይ እንደ መሆኑ ሰዎችን በተለያዩ መንገዶች ከእውነት ይለያቸው ዘንድ ይፈትናቸዋል፡፡”

2 months, 4 weeks ago

ተወዳጆች

*ቅዱስ አትናቴዎስ

ሐዋርያዊ ይህን መሠረታዊ ጉዳይ በአርዮሳውያን ላይ በጻፈው ጥልቅና ሰፊ ትምህርቱ ላይ እንዲህ ሲል ያብራራዋል-

ቃል ፍጡር ቢሆን ኖሮ ይህ [የእኛ መዳን] ተፈጻሚ ሊሆን አይችልም ነበር፤ ፍጡር ቢሆን ኖሮ ዲያብሎስም ራሱ ፍጡር ስለሆነ ትግሉን ይቀጥልበት ነበር፤ ሰውም በሁለቱ መካከል ሆኖ ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋሐድበትና ከፍርሃት ነጻ የሚወጣበት መንገድ አጥቶ ሕይወቱ ሁል ጊዜ በአደጋ ውስጥና በጥፋት ላይ እንደ ሆነ ይቀጥል ነበር፡፡

ስለዚህም በእውነት የእኛ የሆነውን ሰውነትና ባሕርይ ነሣ (ገንዘብ አደረገ)፡ ይህም ባሕርያችንን እርሱ ፈጣሪውና አስገኚው እንደ መሆኑ በእርሱ በራሱ ያከብረው ዘንድ፣ በዚህም በእርሱ መሪነትና አርአያነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ያገባን ዘንድ ነው::' የሰው ባሕርይ (ትስብእት) የተዋሐደው ከፍጡር ጋር ቢሆን ኖሮ፣ ወይም ወልደ እግዚአብሔር እውነተኛ እግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ የእኛ ባሕርይ የጸጋ አምላክነትን አያገኝም ነበር፤ የእኛን ሥጋ የለበሰው የእርሱ (የእግዚአብሔር] እውነተኛና የባሕርይ ልጁ ባይሆን ኖሮ ሰው ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ከፍ ከፍ ሊልና ሊቀርብ አይችልም ነበር፡፡ (ትምህርት በእንተ አርዮሳውያን፣ ትምህርት 2፣ ቁ. 43)*

3 months ago

ከሴቶች ሁሉ ልዩ እንደሆነች በቅዱስ ገብርኤል እና በቅድስት ኤልሳቤጥ የተመሰከረላት እናታችን ንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም በሰው ልጅ ድኅነት ታሪክ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሥርዓተ አምልኮታችን ሁሉ ልዩ ቦታ እንዳላት የታወቀ ነው። እውነቱን ለመናገር ከሉተር መነሣት በኋላ ባሉ የክርስትና ዲኖሚኔሽኖች ካልሆነ በቀር ከጥንታውያን አብያተ ክርስቲያን መካከል እመቤታችን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላትን ልዩ ቦታ የማይቀበል ልዩ ምስጋና የማያመስግናት እና ልዩ አክብሮት የማይሰጣት የለም። ከዚህም የተነሣ ከዚያው ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ስለእመቤታችን ንጽሕት ድንግል ማርያም ብዙ ተብሏል፣ ተጽፏል፣ ተተርኳል። በተለይ ደግሞ መናፍቃን መነሣት ከጀመሩበት ከሦስተኛው እና ከዐራተኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የተነሡ ሊቃውንት ስለእመቤታችን ንጽሕት ድንግል ማርያም ብዙ አስተምረዋል፣ ብዙም ጽፈዋል። ሆኖም ጠላት ዲያብሎስም ኑፋቄን አሾልኮ ከአስገባበት ጊዜ ጀምሮ በእመቤታችን ላይ ብዙ አመለካከቶችን ለማምጣት ሳይሰለች እና ሳይደክም ሠርቷል። በአንጻሩ ደግሞ ሊቃውንትም ብዙ መልሶችን ሰጥተዋል፣ ቅዱሳንም ስለእመቤታችን ብዙ የምስጋና እና የተመስጦ ድርሰቶችን ደርሰዋል። ከዚህ የተነሣ አሁንም እመቤታችን ከሰው ሁሉ ከፍጥረትም ሁሉ የተለየች እንደመሆኗ ባለ ብዙ መልኮች በርካታ መጻሕፍት ተደርሰውላታል፣ ተጽፈውላታል።

እመቤታችን ልዩ መሆኗን ከሚያረጋግጡልን ነገሮች አንዱ ደግሞ ሰይጣንና መናፍቃን ሳያቋርጡ እንደሚዘልፏት ሊቃውንት እና ቅዱሳን ደግሞ ሳያቋርጡ የሚያመስግኗት መሆኗ ነው። ይህ መጽሐፍም የዚህ ተግባር እንዱ ማሳያ ነው ማለት ይቻላል። ከጥንት ዘመን ሰይጣን በመናፍቃን አድሮ ያናገራቸው ትችቶች አሁንም ድረስ እንደ አዲስ እየተነገሩ እየተጻፉ ቢቀጥሉም በአንጻሩ ደግሞ እንደ ጥንቱ መንፈስ ቅዱስ ያናገራቸው ሊቃውንት ትምህርቶች በልዩ ልዩ ሊቃውንት አሁንም ይመሠጠራሉ፣ ይሰበካሉ፣ እመቤታችንም ትመሰገናለች፣ እጂጉን ትከበራለች ። "አሐቲ ድንግል” የተባለው ይህ የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን መጽሐፍም ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው። መጽሐፉ የብዙ ሊቃውንትን ድርሰቶች ሰብሰቦ በአንድ ላይ በማቅረብ ቅድሚያውን ሊወስድ የሚችል መጽሐፍ እንደሆነ ይሰማኛል። በዚህም ቤተ ክርስቲያናችን ስለእመቤታችን ያላትን አስተምህሮ በሥርዓተ አምልኮዋ ውስጥ እመቤታችን ያላትን ቦታ እና ቅዱሳን ስለእርሷ እንዴትእንዳስተማሩ እና እንዴት እንዳመሰገኗት ማወቅ የሚፈልግ ሁሉ ይህ መጽሐፍ በእጂጉ ያስፈልገዋል።

ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ

7 months, 2 weeks ago

ድንግል ማርያም ሆይ❤️

?የአርያም እኅት ሁለተኛዋ ሰማይ ሆይ ሕዝቅኤል ካየው ሰረገላ አንቺ ትበልጫለሽ።

? ዳንኤል ካየው ኪሩቤልም ኮሚሽከሙት ዙፋን አንቺ ትበልጫለሽ።

? የጉስቁልናዬ ሽታ የሚከረፋ እንዳይሆንም ራሴን በሃይማኖት ዘይት አለዝቢው።

?በልጅሽ ፈውስም ዐይኖቼን ኳይ። በልጅሽ ደምም ከንፈሮቼን ቅቢ። በእርሱ ምልክትም ፊቴን ባርኪ። በወንጌሉ ልጓምነትም ጉንጮቼን /አፌን/ ለጉሚ።

? ትእዛዞቹን ለመስማትም የጆሮዬን መስኮቶች ክፈቺ። በመስቀሉ ቀንበርም አንገቴን ጥመጅው።

?የኃጢአቴን ሸክምም ከትከሻዬ አስወግጂ።

?በጀርባዬም የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ከምሪ። በሰውነቴም ማስተዋልን አሳድሪ። እጆቼንም በንጽሕና ውኃ እጠቢ።

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana